Telegram Web Link
" ካራባኦ ካፑን መድገም እንፈልጋለን " አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው በዚህ አመት ለሁሉም ዋንጫዎች መፎካከር እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

" ሊቨርፑል ባለፈው አመት ካራባኦ ዋንጫ አሸንፏል በዚህ አመትም ዋንጫውን መድገም እንፈልጋለን " ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም በዚህ አመት ለሁሉም ዋንጫዎች መፎካከር እንደሚፈልጉ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ " ራሽፎርድ የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በቀጣይ ለአዲስ ፈተና ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው የተጠየቀው ማርከስ ራሽፎርድ " ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብዬ አስባለሁ " በማለት ተናግሯል። “ ማንችስተር ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ከእኔ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ መጥፎ ነገር አይሰማም ሁልጊዜም በዩናይትድነቴ…
" እኔ ራሽፎርድን ብሆን አሰልጣኙን አናግር ነበር " አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድ ለመገናኛ ብዙሃን የሰጠው ቃለምልልስ ስህተት እንደነበር ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ሲናገሩም “ እኔ ራሽፎርድን ብሆን ኖሮ ሚዲያ ላይ ወጥቼ ቃለምልልስ ከመስጠት ይልቅ አሰልጣኙን አነጋግረው ነበር " ሲሉ ገልፀዋል።

ጋርናቾን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኙ “ እሱ በጥሩ ሁኔታ ልምምዱን ሰርቷል በእኔ የተናደደ ይመስል ነበር ነገርግን የተጠበቀ ነው አሁን ለቶተንሀም ጨዋታ ዝግጁ ነው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራትክሊፍ በዩናይትድ ያላቸውን ድርሻ አሳደጉ !

እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በማንችስተር ዩናይትድ ያላቸውን የአክሲዮን ድርሻ ማሳደጋቸው ተገልጿል።

በቅርቡ የክለቡን አነስተኛ ድርሻ የገዙት ቢሊየነሩ አሁን ላይ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ ተጨማሪ 100 ሚልዮን ዩሮ ፈሰስ ማድረጋቸው ተነግሯል።

ይህንንም ሰር ጂም ራትክሊፍ በማንችስተር ዩናይትድ ያላቸው የአክስዮን ድርሻ 28.94 % መድረሱ ተዘግቧል።

ባለሀብቱ እስካሁን 237 ሚልዮን ፓውንድ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ ፈሰስ ማድረጋቸውን ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን አዲስ ባለቤት ማግኘቱ ይፋ ሆነ !

የአሜሪካው ተቋም ፍሬድኪን ግሩፕ የመርሲሳይዱን ክለብ ኤቨርተን በባለቤትነት መቆጣጠሩ በይፋ ተገልጿል።

ፍሬድኪን ግሩፕ ኤቨርተንን ለመቆጣጠር ከወራት በፊት ከስምምነት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ህጋዊ ሂደቱን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ከእንግሊዝ ትልቅ ክለቦች አንዱን ወደ እኛ በመቀላቀላችን ኩራት ይሰማናል ፤ ኤቨርተንን በባለቤትነት በመረከባችን ኩራት ይሰማናል “ ሲሉ ፍሬድኪን ተናግረዋል።

አሜሪካዊው ፍሬድኪን በተጨማሪ የጣልያኑ ክለብ ሮማ ባለቤት እና ፕሬዝዳንት መሆናቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዊልፍሬድ ሲንጎ ዶናሩማን ይቅርታ ጠይቋል !

አይቮሪኮስታዊው የሞናኮ የፊት መስመር ተጨዋች ዊልፍሬድ ሲንጎ ትላንት ምሽት ዶናሩማ ላይ ለሰራው ጥፋት ይቅርታ ጠይቋል።

ትላንት ምሽት ፒኤስጂ ሞናኮን ባሸነፈበት ጨዋታ ዊልፍሬድ ሲንጎ የፒኤስጂው ግብ ጠባቂ ዶናሩማ ፊቱ ላይ ጉዳት አድርሶበት ነበር።

" ጥፋቱን የሰራሁት አስቤበት አልነበረም ዶናሩማን ይቅርታ እጠይቃለሁ ፤ በፍጥነት እንድታገግም እመኛለሁ “ ሲል ዊልፍሬድ ሲንጎ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ያገኘነው ሶስት ነጥብ ብቻ ነው " አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ሲቲ ላይ ያሳኩት ከሶስት ነጥብ የዘለለ አይደለም ሲሉ ለደጋፊው ተናግረዋል።

የዩናይትድ ደጋፊዎች ከማንችስተር ሲቲ ጨዋታ በኋላ ስላሳዩት ደስታ የተጠየቁት ሩበን አሞሪም " ያገኘነው ሶስት ነጥብ ብቻ እንደሆነ መናገር እፈልጋለሁ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ ከዚህ በፊት በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ደጋፊዎች ስማቸውን እየጠሩ ማዜማቸው እንዳላስደሰታቸው ገልፀው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ይለያያል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከተከላካዩ ኬራን ቴርኒ ጋር እንደሚለያዩ ተገልጿል። መድፈኞቹ ስኮትላንዳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች በውሉ ውስጥ ያለውን ለአንድ አመት የመቀጠል አማራጭ ላለመጠቀም መወሰናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። የ 27ዓመቱ የግራ መስመር ተጨዋች ኬራን ቴርኒ በአርሰናል ያለው ውል በአመቱ መጨረሻ ክረምት ላይ ይጠናቀቃል።…
ሴልቲክ ኬራን ቴርኒን ማስፈረም ይፈልጋል !

የስኮትላንዱ ክለብ ሴልቲክ የቀድሞ አምበሉን ኬራን ቴርኒ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በድጋሜ ማስፈረም እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ስኮትላንዳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኬራን ቴርኒ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከአርሰናል ጋር ያለው ውል ሲጠናቀቅ ክለቡን እንደሚለቅ ይታወቃል።

የስኮትላንዱ ሻምፒዮን ሴልቲክ አሁን ላይ በጥር የ 27ዓመቱን የግራ መስመር ተጨዋች ኬራን ቴርኒ ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ስታዲየም እያፈላለጉ መሆኑ ተገለጸ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በቀጣይ መጋቢት ወር ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የካምፕ ኑ ስታዲየም እድሳት መዘግየቱን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ይህንንም ተከትሎ ባርሴሎና በቀጣይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የሚጫወትበትን ስታዲየም በማፈላለግ ላይ መሆኑን ማርካ ዘግቧል።

ባርሴሎና በአሁን ሰዓት እየተጠቀመበት የሚገኘው የ ሞንትጁይች ስታዲየም በሌላ ዝግጅት ምክንያት ለሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዝግጁ እንደማይሆን ተገልጿል።

ባርሴሎና በቀጣይ ለመጠቀም ከያዛቸው ስታዲየም ስሞች መካከል የቫሌንሽያው ሜስታላ ስታዲየም እና የአትሌቲኮ ማድሪዱ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-SPORT
ዎልቭስ አሰልጣኝ ሊሾም ነው ! አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔልን ያሰናበተው ዎልቭስ በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በመስራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ዎልቭስ አሁን ላይ የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሻባቡን አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ በሀላፊነት ለመሾም በንግግር ላይ እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል። ዎልቭስ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ በአል ሻባብ ቤት ያላቸውን ኮንትራት ማፍረሻ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸው…
ዎልቭስ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

በቅርቡ አሰልጣኝ ጋሪ ኦኔልን ያሰናበተው ዎልቭስ በምትኩ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ዎልቭስ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሻባብ በመውሰድ በሀላፊነት ሾመዋል።

የ 56ዓመቱ አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራ ዎልቭስን ለአንድ አመት እና ስድስት ወራት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዩናይትድ የጠባቂዎችን ጉርሻ ቀንሷል !

ማንችስተር ዩናይትድ የስታዲየም ደህንነት ጠባቂዎችን “ Steward " አበል እና ተጨማሪ ክፍያዎች መቀነሱ ተገልጿል።

የስታዲየም ደህንነት ጠባቂዎቹ በየአስር ጨዋታው 100 ፓውንድ ጉርሻ ይቀበሉ እንደነበር ሲገለፅ አሁን ላይ በመቀነሱ መበሳጨታቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ የተለያዩ አላስፈላጊ ያላቸውን ወጪዎች በመቀነስ የክለቡን የፋይናንስ ሁኔታ በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስተካከል እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።

ከእንግሊዛዊው ቢሊየነር መምጣት በኋላ በርካታ የክለቡ “ Steward " ተማረው እየለቀቁ መሆኑን ተናግረዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የፖል ፖግባ ወንድም የእስር ፍርድ ተላለፈበት !

የፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፖል ፖግባ ወንድም ማትያስ ፖግባ የሶስት አመታት እስራት ፍርድ እንደተላለፈበት ተገልጿል።

ከሁለት አመታት በፊት ፖል ፖግባ ዝርፊያ እና የተለያዩ ማስፈራሪያዎች በቡድን ከተደራጁ ሰዎች እንደደረሰበት ተናግሮ ነበር።

በቡድን ከተደራጁ ሰዎች መካከል ወንድሙ አንዱ እንደነበረ ተገልጾ የነበረ ሲሆን ፖል ፖግባ በወቅቱ 13 ሚልዮን ዩሮ እንደጠየቁት አሳውቆ ነበር።

አሁን ላይ በድርጊቱ የተሳተፈው የፖል ፖግባ ወንድም በድርጊቱ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ተከትሎ የሶስት አመት እስር እንደተፈረደበት ተነግሯል።

በወቅቱ ጓደኞቹ ፖግባን ወደ ቤታቸው በመጥራት እውቅናን ካገኘ በኋላ በገንዘብ እየረዳቸው እንዳልሆነ ገልፀው ገንዘብ ስጠን ማለታቸውንም ተናግሮ ነበር።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
” የምንፎካከረው ከራሳችን ጋር ነው “ ማዱኬ

የሰማያዊዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኖኒ ማዱኬ ቡድናቸው በየቀኑ ለመሻሻል ከራሱ ጋር ፉክክር ላይ መሆኑን ተናግሯል።

ከሊቨርፑል ፣ አርሰናል እና ሲቲ ጋር ለመፎካከር ስለመብቃታቸው የተጠየቀው ማዱኬ “ በየቀኑ ለመሻሻል እና የተሻልን ለመሆን ከራሳችን ጋር  እየተፎካከርን ነው “ ብሏል።

ኖኒ ማዱኬ አክሎም " ቼልሲ የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ ይችል እንደሆነ አላውቅም የወደፊቱን መተንበይ አልችልም " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ቼልሲ ከ ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )

5:00 ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዝግጁ የሆኑ ተጨዋቾችን መርጫለሁ " አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ለምሽቱ ጨዋታ ዝግጁ የሆኑ ተጫዋቾችን መምረጣቸውን ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ማርከስ ራሽፎርድን ለሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ በቡድኑ ስብስብ ውስጥ ሳያካትቱት ቀርተዋል።

ተጫዋቹን ስላልመረጡበት ምክንያት የተጠየቁት ሩበን አሞሪም “ ከባድ ጨዋታ ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ ተጨዋቾችን መርጫለሁ " ሲሉ መልሰዋል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ በበኩሉ ጥሩ ልምምድ መስራቱን የገለፁት አሰልጣኙ ለጨዋታው ዝግጁ ነው አማራጭ ተጨዋች ይሆናል ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17 '

ቶተንሀም 1-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )

ሶላንኬ

ቼልሲ 0-0 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
26 '

ቶተንሀም 1-0 ማንችስተር ዩናይትድ ( ካራባኦ ካፕ )

ሶላንኬ

ቼልሲ 1-0 ሻምሮክ ሮቨርስ ( ኮንፈረንስ ሊግ )

ጉዩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/01 07:03:52
Back to Top
HTML Embed Code: