Telegram Web Link
ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቶተንሀም ተሸንፏል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለቀያዮቹ ሴጣኖች የማሸነፊያ ግቦችን ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ጋርናቾ እና ክርስቴንሰን በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

ሩድ ቫን ኔስትሮይ ቡድኑን ለመጨረሻ ጊዜ የመራ ሲሆን በመራባቸው አራት ጨዋታዎች አልተሸነፈም በሶስቱ ማሸነፍ ችሏል።

አሌሀንድሮ ጋርናቾ በዚህ አመት በሁሉም ውድድሮች ከየትኛውም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች በበለጠ 1️⃣1️⃣ ግቦችን አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሀም በኢፕስዊች ታውን 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

ኒውካስል ዩናይትድ በበኩሉ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ረተዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር አመቱ በሊጉ #አራተኛ ድሉን ሲያሳካ ቶተንሀም #አምስተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

3️⃣ ኖቲንግሀም ፎረስት :- 19 ነጥብ
8⃣ ኒውካስል ዩናይትድ : - 18 ነጥብ

🔟 ቶተንሀም : - 16 ነጥብ
1⃣3⃣ ማንችስተር ዩናይትድ : - 15 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

እሁድ - ኢፕስዊች ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ቅዳሜ - ማንችስተር ሲቲ ከ ቶተንሀም

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
"ፈታኝ ጨዋታ ይሆናል" ኢንዞ ማሬስካ

የምእራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የዛሬው የለንደን ደርቢ ጨዋታ ፈታኝ እንደሚሆን ተናግረዋል።

"ጨዋታው ፈታኝ እንደሚሆን ገልፅ ነው" ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ "እንደዚህ አይነት ጨዋታዎች ራሳችንን ለመፈተሽ ይረዱናል" ብለዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሪስ ጄምስ ለዛሬው ጨዋታ ብቁ መሆኑን ገልፀው "እሱ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ያልተካተተው የጨዋታ መደራረብ እንዳያጋጥመው አስበን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀምሯል

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
9'

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
20'

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
28'

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
41 '

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የእረፍት ሰአት !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አስራ አንደኛ ሳምንር መርሐ ግብር ቼልሲ ከአርሰናል ጋር እያደረጉ የሚገኙት ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ እረፍት አምርቷል።

🟨 እነማን ቢጫ ካርድ ተመለከቱ ?

በቼልሲ በኩል ማዱኬ ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ኮል ዊል እንዲሁም በአርሰናል በኩል ቤን ዋይት ቢጫ ካርድ ተመልክተዋል።

⚽️ የመጀመርያው አጋማሽ የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመርያው አጋማሽ አርሰናል 52%-48% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮማ አሰልጣኙን በይፋ አሰናበተ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ሮማ የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ከሀላፊነት ማሰናበቱን በይፋ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ዳንኤል ዲ ሮሲን ተክተው ለአንድ አመት ሮማን የተረከቡት አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ከ 5️⃣3️⃣ ቀናት በኋላ ተሰናብተዋል።

ሮማ አሰልጣኙን ለማሰናበት የወሰነው ዛሬ በሜዳው በቦሎኛ ከደረሰበት የ 3ለ2 ሽንፈት በኋላ ነው።

ሮማ ካለፉት አምስት የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች በአራቱ ሽንፈት አስተናግደዋል።

አሰልጣኝ ኢቫን ጁሪች ሮማን በሁሉም ውድድሮች በስምንት ጨዋታዎች ሲመሩ ማሳካት የቻሉት አስር ነጥቦችን ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጥሩ ቀን አሳልፈናል “ ብሩኖ ፈርናንዴዝ

ፖርቹጋላዊው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቡድናቸው ውጤት ማስመዝገቡን መቀጠል እንዳለበት ከዛሬው ድል በኋላ ተናግሯል።

" ዛሬ ጥሩ ቀን ነበር ያሳለፍነው " ያለው ፈርናንዴዝ " ባለፉት አራት ጨዋታዎች አልተሸነፍንም ውጤቶችን እያስመዘገብን መቀጠል ይኖርብናል።" ሲል አሳስቧል።

አሰልጣኝ ሩድ ቫን ኔስትሮይን " ድንቅ ሰው ነው " ሲል የገለፀው ተጨዋቹ " እሱ ክለቡን ይወዳል በነበረው አጭር ጊዜ ጥሩ ውጤቶችን አስመዝግቧል።" ብሏል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለማንችስተር ዩናይትድ ባደረጋቸው የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች 100 የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

ፈርናንዴዝ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 100 የግብ ተሳትፎ በማድረግ ከሮናልዶ በመቀጠል ሁለተኛው ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
53 '

ቼልሲ 0-0 አርሰናል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
60 '

ቼልሲ 0-1 አርሰናል

ማርቲኔሊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
70 '

ቼልሲ 1-1 አርሰናል

ኔቶ              ማርቲኔሊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
78'

ቼልሲ 1-1 አርሰናል

ኔቶ              ማርቲኔሊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
85 '

ቼልሲ 1-1 አርሰናል

ኔቶ              ማርቲኔሊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
90 '

ቼልሲ 1-1 አርሰናል

ኔቶ              ማርቲኔሊ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አስራ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ከአርሰናል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የመድፈኞቹን ግብ ጋብሬል ማርቲኔሊ ሲያስቆጥር ፔድሮ ኔቶ ሰማያዊዎቹን አቻ ማድረግ ችሏል።

መድፈኞቹ ያለፉትን አራት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በሁለቱ ተሸንፈው በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።

3️⃣ ቼልሲ :- 19 ነጥብ ( +8 )
4️⃣ አርሰናል :- 19 ነጥብ ( +6 )

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

ቅዳሜ ሌስተር ሲቲ ከ ቼልሲ

ቅዳሜ አርሰናል ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

*ቀጣይ ጨዋታዎች ከሀገራት ጨዋታ በኋላ የሚደረጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የኢንተር እና ናፖሊን  ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:45 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
2024/11/15 17:22:42
Back to Top
HTML Embed Code: