Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
Apple M3 Pro 16 inch

🔹14 inches
512GB / 18GB
275,00 ETB

🔸16 inches
512GB / 18GB
349,000 ETB

🔹16 Inches
512GB / 32GB
379,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
“ እኛ ላይ አሁን አትፍረዱብን “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንግ ቡድናቸው ላይ ለመፍረድ የውድድር ዘመኑ መጨረሻ እንዲጠበቅ ጠይቀዋል።

“ በዚህ ሰዓት ሆናችሁ አትፍረዱብን በውድድር አመቱ መጨረሻ ፍረዱብን እንሻሻላለን “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም “ እቅዳችን በሂደት ላይ ነው መጠበቅ አለባችሁ “ ሲሉ አሳስበዋል።

ማርከስ ራሽፎርድ ከእረፍት በኋላ ተቀይሮ የወጣው ጉዳት አጋጥሞት ሳይሆን በታክቲካል ምክንያት መሆኑን ኤሪክ ቴንሀግ ጠቁመዋል።

ለክለቡ የአቻነት ግብ በመጨረሻ ደቂቃ ያስቆጠረው ሀሪ ማጓየር በበኩሉ “ ቡድኑ ውስጥ የአስተሳሰብ ችግር አለ እሱ መቀየር አለበት “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የተሻለ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች አሉ “ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ቡድናቸው ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጉን ገልፀዋል።

“ ጨዋታው ከባድ ነበር ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል ጥቃቅን ስህተቶች ማስቀረት አለብን የተሻለ ማድረግ የምንችላቸው ብዙ ነገሮች አሉ።“ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።

ቼልሲ በሁሉም ውድድሮች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ አስራ ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል።

የቼልሲ ቀጣይ የሊግ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

ሰማያዊዎቹ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር :-

- ኖቲንግሀም ፎረስት

- ሊቨርፑል

- ኒውካስል ዩናይትድ

- ማንችስተር ዩናይትድ

- አርሰናልን በተከታታይ የሚያገኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤልጅየም ስብስቧን አሳውቃለች !

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ለሚያደርጋቸው የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

በስብስቡ ውስጥ የማንችስተር ሲቲው አማካይ ኬቨን ዴብሮይን በጉዳት ምክንያት ሳይካተት ቀርቷል።

በተጨማሪም የናፖሊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ በስብስቡ ያልተካተተ ሌላኛው ተጨዋች ነው።

ቤልጅየም በቀጣይ ከጣልያን እና ፈረንሳይ ጋር ተጠባቂ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

( ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።)

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሪክ ቴንሀግ ጫና ውስጥ አይደሉም !

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በጫና ውስጥ እንደማይገኙ የክለቡ አመራሮችን ከሚያውቁ ቅርብ ምንጮች ማረጋገጡን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የክለቡ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በአሁን ሰዓት ሁኔታዎች ካላስገደዱ አሰልጣኝ የመቀየር ፍላጎት እንደሌላቸው ተገልጿል።

የክለቡን ውጤት ማጣት ተከትሎ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከክለቡ ደጋፊዎች ተቃውሞዎች እየቀረበባቸው እንደሚገኝ ይታወቃል።

አሰልጣኙ ከቀናት በፊት “ የመሰናበት ስጋት የለብኝም የሚያሳስበኝ ጉዳይ አይደለም “ ሲሉ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ተጫዋቾቻችን የሊጉ መሪ መሆን ለምደዋል “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ነገ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ምን አሉ ?

- " ክሪስታል ፓላስ ከዩናይትድ እና ቼልሲ ጋር በነበረው ጨዋታ ባገኘው ውጤት ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ አሳይቷል።

- እሮብ ተጫውተን ቅዳሜ ምሳ ሰዓት መጫወት ለእኛ አስቸጋሪ ነው ነገርግን ይህ የትልቅ ክለብ አንዱ አካል ነው።

- እኛ ሊቨርፑሎች ነን እዚህ ያሉ ተጨዋቾች የፕርሚየር ሊጉ መሪ መሆንን የለመዱ ናቸው።

- ፌዴሪኮ ኬሳ ባለፉት ቀናት ልምምድ አልሰራም ዛሬ ልምምድ ይሰራል ለነገው ጨዋታ ከደረሰ መጠበቅ እና መመልከት እንችላለን።“ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚽️አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተኛ ሳምንት ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች!

👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

👉 የዲኤስቲቪን ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
💡PEDAL BIKES💡

new bike shop in addis ababa.

📍 Bole, bora ground floor.
📍 ኣድራሻ ቦሌ ቦራ ግራዉንድ ፍሎር
ቻናላችን ይቀላቀሉ✔️ ኣዳዲስ እቃዎች እየገቡ ነዉ👇👇
https://www.tg-me.com/pedalbikes11
  ሳይክኰን መንዳት ይጀምሩ!

ከተማ ውስጥ በሳይክል ይጓዙ!

የተለያዩ ሳይክሎች እና የሳይክል መለዋወጫ እቃዎች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎️ስልክ 0911271458 ወይም 0924435348
✉️Inbox @pedalbikes
ቶተንሀም የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከብራይተን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።

በጉዳት ላይ የሚገኘው ደቡብ ኮሪያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሰን ሁንግ ሚን በጉዳት ምክንያት ከጨዋታዉ ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል።

ሰን ሁንግ ሚን በተጨማሪም ከደቡብ ኮርያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ስብስብ ውጪ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሻምፒየንስ ሊግ መሳተፍ እንፈልጋለን “ ካይሴዶ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞይሰስ ካይሴዶ ቡድናቸው እያደረገ በሚገኘው ነገር ደስተኛ መሆናቸውን ገልጿል።

ከቅድመ ውድድር ዝግጅት ጀምረን ጠንካራ ስራ ሰርተናል በማለት የገለፀው ሞይሰስ ካይሴዶ “ በአጀማመራችን በጣም ደስተኞች ነን “ ብሏል።

ሞይሰስ ካይሴዶ አያይዞም ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር መሳተፍ አላማው መሆኑን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሲቲን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ነው የምወደው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ለቡድናቸው እስከመጨረሻው ሰዓት እንደሚከላከሉ ገልጸዋል።

“ እኔ የማንችስተር ሲቲ አካል ነኝ “ ያሉት ጋርዲዮላ አጠቃላይ ክለቡን አምነዋለሁ ለዚህ ክለብ እስከመጨረሻው ሰዓት እከላከላለሁ በማለት ተናግረዋል።

“ ማንችስተር ሲቲን  ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እወደዋለሁ ፍቅሬን የማሳየው ጨዋታዎችን በማሸነፍ እና የቻልኩትን ሁሉ በማድረግ ነው።“ ጋርዲዮላ

“ ኬቨን ዴብሮይን ለቀጣይ ጨዋታ አይደርስም ዝግጁ አይደለም ለእኛም ሆነ ለቤልጂየም መጫወት አይችልም።“ ሲሉ ጋርዲዮላ አክለው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከሲቲ እና አርሰናል ጋር መፎካከር አንችልም “ ኢንዞ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቡድናቸው በዚህ ሰዓት ከማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጋር መፎካከር ይችላል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

“ ከማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ጋር መፎካከር እንችላለን ብዬ አላስብም “ ያሉት ኢንዞ ማሬስካ “ አሁን ዝግጁ አይደለም “ ሲሉ በሂደት ላዬ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ማንችስተር ሲቲ ለዘጠኝ አመት አርሰናል ለአምስት አመት በአንድ አሰልጣኝ መስራታቸውን ያነሱት ኢንዞ ማሬስካ “ እኛ ሶስት ወራችን ነው አላማችን እነሱን መቅረብ ነው “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቶማስ ፓርቲ ምርጡን አቋም እያሳየ ነው “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ነገ ከሳውዝሀምፕተን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ምን አሉ ?

- “ ማርቲን ኦዴጋርድ መቼ እንደሚመለስ በግልጽ ገደብ ማስቀመጥ ከባድ ነው ነገርግን በቅርቡ ወደ ሜዳ ለመመለስ የተቻለውን ጥረት እያደረገ ነው።

- ጁሪየን ቲምበር ፣ ቤን ዋይት እና ቶሚያሱ ወደ ሜዳ መመለሳቸውን ዛሬ ከሚኖረን ልምምድ በኋላ የምንወስን ይሆናል።

- ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ አስቸጋሪ የጨዋታ መርሐ ግብር ነው ያለን ነገርግን ሁኔታውን እንላመደዋለን።

- ቶማስ ፓርቲ አርሰናልን ከተቀላቀለ ወዲህ ምርጥ የሚባለውን ብቃት በዚህ አመት እያሳየ ይገኛል አስፈላጊ ተጨዋቻችን ነው።" ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ስለ መሰናበት አላስብም “ ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አሁን ላይ ስለወደፊት ቆይታቸው እያሰቡ እንደማይገኙ ገልጸዋል።

“ ስለ መሰናበት እያሰብኩ አይደለም “ ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ ምክንያቱም ጉዳዩ ይሄ አይደለም ሁላችንም አንድ ላይ ነን በማለት ተናግረዋል።

“ አመቱን በስኬት ማጠናቀቅ ከፈለግን መሻሻል አለብን ዋንጫ ማሸነፍ የምንችለው ባለፉት አመታት እንዳደረግነው ስንሻሻል ብቻ ነው በዚህ ላይ እንሰራለን።“ ቴንሀግ

አሰልጣኙ አያይዘውም በእሁዱ የአስቶን ቪላ ጨዋታ ኮቢ ማይኖ መድረስ አለመድረሱን አይተው እንደሚወስኑ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በትናንትናው ዕለት ተጠናቋል። ሳፋሪኮም ኢትዮጵያም የዚህ ዝግጅት የክብር የወርቅ ስፖንሰር በመሆናችን ታላቅ ኩራት ይሰማናል።

የኦሮሚያን ባህል ፣ ታሪክ እና ተፈጥሮአዊ ውበት ለማድነቅ ባለፉት ሶስት ቀናት በስካይላይት ሆቴል በነበረን ቆይታ ላይ የተለያዩ ኤግዚቢሽኖችን፣ የፋሽን ትርኢቶችን እና የፓናል ውይይቶችን ለታደማችሁ ጎብኚዎች ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ!

ከዳር እስከ ዳር በሚገኘው በሳፋሪኮም ኔትወርክ እንገናኝ! አስተማማኙን ኔትወርክ አሁኑኑ እንቀላቀል! ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ!

#MPESASafaricom #SafaricomEthiopia #1Wedefit #Furtheraheadtogether#OromiaTourismWeek #visitOromia #Oromia
2024/10/05 05:30:49
Back to Top
HTML Embed Code: