Telegram Web Link
Bagga Ayaanaa Ireechaa Negaan Isiin Gahee!

📌 Saraara Bilbilan Gabaaba keenyatiin waanaaw Jechaa dhaan Bilbilaa;

- Ingilifaan
- Amariffaan
- Afan Oromotiin

Instagram | Facebook | TikTok

🏅Waanaaw, garaa Fulduuraa...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
“ ዋንጫ የምንበላበት አመት ነው “ ቡካዮ ሳካ የመድፈኞቹ ኮከብ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ስኬታማ የሚሆኑበት እመት ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል። “ ራሳችን ላይ ጫና መፍጠር አልፈልግም ግን ዋንጫ የምንመላበት አመት ዘንድሮ ነው ብዬ አስባለሁ “ ቡካዮ ሳካ ስለ ክለቡ የአጫወወት ዘይቤ ሲጠይቀም “ ለእኛ ዋናው ነገር ውጤት ነው ፣ የምንፈልገው ማሸነፍ ነው “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።…
“ በዚህ አመት ዋንጫ የምናሸንፍ ይመስለኛል “ ጋብሬል

ብራዚላዊው የመድፈኞቹ ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ቡካዩ ሳካ በቅርቡ " አመቱ አርሰናል ዋንጫ የሚበላበት ይሆናል " ባለው አስተያየት እንደሚስማማ ተናግሯል።

“ በሳካ ሀሳብ እስማማለሁ የሚሆን ይመስለኛል “ ያለው ጋብሬል ማግሀሌስ " ባለፉት ሁለት አመታት ብዙ ነገሮችን አረጋግጠናል ዋንጫ ማሸነፍ እንፈልጋለን “ በማለት ገልጿል።

ቡካዩ ሳካ በቅርቡ “ ራሳችን ላይ ጫና መፍጠር አልፈልግም ግን ዋንጫ የምንመላበት አመት ዘንድሮ ነው ብዬ አስባለሁ “ ሲል ተናግሮ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቴንሀግ ጥሩ አሰልጣኝ ነው “ ሰር ጂም ራትክሊፍ

የማንችስተር ዩናይትድ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ ስለ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥያቄ ቀርቦላቸው አስተያየት መስጠት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ላይ እምነት አላቸው እንደሆነ የተጠየቁት ሰር ጂም ራትክሊፍ “ ይህንን ጥያቄ መመለስ አልፈልግም “ ሲሉ መልሰዋል።

" ኤሪክ ቴንሀግን እወደዋለሁ በጣም ጥሩ አሰልጣኝ ነው ብዬ አስባለሁ ፣ የትኛውም ውሳኔ የእኔ አይደለም ክለቡን የሚመራው አስተዳደር ውሳኔ ነው።" ሰር ጂም ራትክሊፍ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል ። በዚህም መሰረት :- ኪሊያን ምባፔ ላሚን ያማል ኢናኪ ዊሊያምስ ሎ ሴልሶ ካርሎስ ቪሴንቴ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ስፔናዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ላሚን ያማል በወሩ ውስጥ ሶስት ግቦችን ሲያስቆጥር አንድ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖል ፖግባ ወደ እግርኳስ ሊመለስ ነው  !

አበረታች ንጥረ ነገር ተጠቅሟል በሚል ከእግርኳስ ለአራት አመታት የታገደው ፖል ፖግባ ቅጣቱ ሊቀነስለት መሆኑ ተገልጿል።

አለምአቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት የፖል ፖግባን የአራት አመታት አግድ ቅጣት ወደ አስራ ስምንት ወራት መቀነሱን ዴይሊ ሜል ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ፖል ፖግባ ከሚቀጥለው ጥር ጀምሮ ከጁቬንቱስ ጋር ልምምድ መጀመር እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቼልሲን የምንገጥመው ማሸነፍ እንደምንችል በማመን ነው “ ኢላንጋ

የኖቲንግሀም ፎረስቱ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ኢላንጋ ቡድናቸው እሁድ ቼልሲን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል።

“ በድፍረት እና ቼልሲን ማሸነፍ እንደምንችል በማመን ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም እንሄዳለን “ ሲል አንቶኒ ኢላንጋ ተናግሯል።

“ ይህንን ማድረግ የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን “ የሚለው ኢላንጋ ቼልሲን እናከብራለን ጥሩ ጅማሮ አድርገዋል ነገርግን ያለንን ሁሉ አውጥተን እንጫወታለን ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለዩናይትድ ከሙኒክ በበለጠ እንዘጋጃለን “ ኤምሬ

የአስቶን ቪላው ዋና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ቡድናቸው ለባየር ሙኒክ ካደረገው ዝግጅት በበለጠ ለማንችስተር ዩናይትድ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል።

“ ለማንችስተር ዩናይትድ ክብር አለኝ “ ያሉት አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ “ ለዩናይትድ ጨዋታ ለባየር ሙኒክ ካደረግነው የበለጠ ጠንካራ ዝግጅት እናደርጋለን “ ብለዋል።

“ ዩናይትድ አሸናፊ ክለብ ነው ልምድ ያለው አሰልጣኝ እና ተጨዋቾች አሏቸው አሁንም ዋንጫ እያሸነፉ ነው ባለፈው አመት ሲቲን አሸንፈው ኤፌ ካፕ በልተዋል።“ ኡናይ ኤምሬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ ስራ አስፈፃሚ ስብስባ ሊቀመጥ ነው !

የማንችስተር ዩናይትድ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከአስቶን ቪላ ጨዋታ በኋላ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ለንደን ውስጥ ስብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተገልጿል።

በስብሰባው ላይ የክለቡን አመራሮች ጨምሮ እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ አንዲሁም ጆኢል ግሌዘር እንደሚገኙ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የማንችስተር ዩናይትድ ወቅታዊ አቋም እና የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቆይታ የስብሰባው አጀንዳ መሆን አለመሆኑ እንዳልተረጋገጠ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ መሪነቱን አጠናክሯል !

በጣሊያን ሴርያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ናፖሊ ከኮሞ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የናፖሊን የማሸነፊያ ግቦች ማክ ቶሚናይ ፣ ሮሜሎ ሉካኩ እና ዴቪድ ኔሬስ ማስቆጠር ሲችሉ ለኮሞ ስትሬፌዛ ከመረብ አሳርፏል።

ስኮትላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስኮት ማክ ቶሚናይ የመጀመሪያ የጣልያን ሴርያ ግቡን አስቆጥሯል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ ናፖሊ :- 16 ነጥብ
1️⃣0️⃣ኛ ኮሞ :- 8 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ኢምፖሊ ከ ናፖሊ

ቅዳሜ ኮሞ ከ ፓርማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Apple M3 Pro 16 inch

🔹14 inches
512GB / 18GB
275,00 ETB

🔸16 inches
512GB / 18GB
349,000 ETB

🔹16 Inches
512GB / 32GB
379,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

8:30 ክሪስታል ፓላስ ከ ሊቨርፑል

10:30 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ሆልስቴን ኬል

10:30 ዩኒየን በርሊን ከ ዶርትመንድ

11:00 አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን

11:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ፉልሀም

11:00 ዌስትሀም ከ ኢፕስዊች ታውን

1:30 ኤቨርተን ከ ኒውካስል ዩናይትድ

3:45 ኢንተር ሚላን ከ ቶሪኖ

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ቪያሪያል

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የሊቨርፑል ፣ አርሰናል ፣ ማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሽልማቶቻችን 7:00 ፣ 9:30 ፣ 10:00 ፣ 3:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሲቲ ደጋፊዎች ለጋርዲዮላ መልዕክት ያስተላልፋሉ !

የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች በዛሬው የፉልሀም ጨዋታ በኢትሀድ ስታዲየም ለአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ መልዕክት ለማስተላለፍ ማሰባቸው ተገልጿል።

ደጋፊዎቹ “ ፔፕ ጋርዲዮላ እንድትቆይ እንፈልጋለን አትልቀቅ “ የሚል ፅሁፍ በማዘጋጀት አሰልጣኙን ለመጠየቅ ማቀዳቸው ተነግሯል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው “ ፅሁፍ ያዘጋጁበትን ቢል እኔ እከፍላለሁ በጣም አመሰግናለሁ ይህንን ክለብ ከልቤ እወደዋለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

ደጋፊዎቹ ፔፕ ጋርዲዮላ እንዳይለቅ የሚጠይቀውን ፅሁፍ ለማዘጋጀት 1,000 ዶላር ማሰባሰባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ ለሊጉ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም !

ማንችስተር ሲቲ የሚቀጥለው የውድድር አመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች እንዲራዘሙለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም።

ማንችስተር ሲቲ ለውድድሩ ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ ለማግኘት ጥያቄውን ማቅረቡን የገለፁት ፔፕ ጋርዲዮላ “ ነገርግን ውድቅ ተደርጎብናል “ ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣዩ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ምክንያት ለሊጉ ጨዋታዎች ለመዘጋጀት በቂ ጊዜ አይኖረንም በሚል ቅሬታዎች ሲቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

የ 2025 አለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ከተጠናቀቀ ሶስት ሳምንት በኋላ አዲሱ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሚጀምር ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 07:29:08
Back to Top
HTML Embed Code: