Telegram Web Link
ሪያል ማድሪድ እና ሙኒክ ሽንፈት አስተናገዱ !

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ እና ባየር ሙኒክ ያልተጠበቀ ሽንፈት ሲገጥማቸው ሊቨርፑል አሸንፏል።

የአምናው የሻምፒየንስ ሊጉ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ከሊል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ሊቨርፑል ከቦሎኛ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመሐመድ ሳላህ እና ማክ አሊስተር ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

በቪላ ፓርክ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረጉት አስቶን ቪላዎች 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ አትሌቲኮ ማድሪድን 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት መርታት ችለዋል።

ሳላህ አንፊልድ ላይ በአምስት ተከታታይ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የሊቨርፑል ተጨዋች መሆን ችሏል።

ግብፃዊ ተጨዋች መሐመድ ሳላህ 45ኛ የሻምፒየንስ ሊግ ግቡን በማስቆጠር ዲዲዬር ድሮግባን በልጦ የአፍሪካ ከፍተኛ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

ሪያል ማድሪድ በሁሉም ውድድሮች ከሰላሳ ሰባት ጨዋታዎች ያለ መሸነፍ ጉዙ በኋላ የመጀመሪያ ሽንፈት አስተናግደዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመጀመሪያ ዘጠኝ ጨዋታዎች ስምንቱን ማሸነፍ የቻሉ የመጀመሪያው የሊቨርፑል አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ባየር ሙኒክን ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር ሆነው በማሸነፍ ከጆዜ ሞሪንሆ ታሪክ ጋር ተስተካክለዋል።

የዛሬ ምሽት ውጤቶች ከላይ በምስሉ ተያይዘዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCL

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙሮች ተደርገው ሲጠናቀቁ ቦርስያ ዶርትመንድ በመሪነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የሴርያው ታላቁ ክለብ ኤሲ ሚላን በሁለቱ የምድብ ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።

በመጀመሪያው ሁለት መርሐ ግብሮች :-

👉 ዶርትመንድ
👉 ብረስት
👉ቤንፊካ
👉ሌቨርኩሰን
👉 ሊቨርፑል
👉 አስቶን ቪላ እና
👉 ጁቬንቱስ ድል በማድረግ ስድስት ነጥቦችን መሰብሰብ ችለዋል።

የመጀመሪያ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱት :-

1️⃣5️⃣ኛ ባየር ሙኒክ
1️⃣6️⃣ኛ ባርሴሎና ( በመጀመሪያው ዙር) እና
1️⃣7️⃣ኛ ሪያል ማድሪድ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

የከፍተኛ ግብ አግቢነትን :-

👉 ሀሪ ኬን :- አራት ጎል
👉ካሪም አዲዬሚ ፣ ሴርሁ ጉራሲ እና ቤንጃሚን ሴስኮ በሶስት ጎሎች ተከታዩን ደረጃዎች ይዘዋል።

👉 ሙሉ የወቅታዊ ደረጃ ሰንጠረዥ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጆሮዬን ህመም ተሰምቶኛል “

የአስቶን ቪላ ግብ ጠባቂ ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ በምሽቱ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች ባሳዩት ድጋፍ መደነቁን ገልጿል።

“ የደጋፊዎቹ የድጋፍ ድምፅ የተለየ ነበር “ የሚለው ማርቲኔዝ “ በአንዳንድ አጋጣሚ በድጋፍ ድምፃቸው ምክንያት ጆሮዬን ህመም ተሰምቶኛል “ብሏል።

“ በአስቶን ቪላ ክለብ ቆይታዬ እንዲህ ያለ የድጋፍ ድምፅ ሰምቼ አላውቅም ፣ በዚህ ክለብ የቆየሁት ለዚህ ነው። እወዳችኋለው!” ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ

የሙኒክን የምሽት ድል ተከትሎ ማርቲኔዝ “ ምርጥ ስምንት ውስጥ መቀላቀል እንፈልጋለን ፣ ይህ ግልፅ መልዕክት ነው “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Apple M3 Pro 16 inch

🔹14 inches
512GB / 18GB
275,00 ETB

🔸16 inches
512GB / 18GB
349,000 ETB

🔹16 Inches
512GB / 32GB
379,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
💡PEDAL BIKES💡

new bike shop in addis ababa.

📍 Bole, bora ground floor.
📍 ኣድራሻ ቦሌ ቦራ ግራዉንድ ፍሎር
ቻናላችን ይቀላቀሉ✔️ ኣዳዲስ እቃዎች እየገቡ ነዉ👇👇
https://www.tg-me.com/pedalbikes11
  ሳይክኰን መንዳት ይጀምሩ!

ከተማ ውስጥ በሳይክል ይጓዙ!

የተለያዩ ሳይክሎች እና የሳይክል መለዋወጫ እቃዎች እኛ ጋር ያገኛሉ
☎️ስልክ 0911271458 ወይም 0924435348
✉️Inbox @pedalbikes
“ ሽንፈት ለኛ ጥሩ ነው “ ካርሎ አንቾሎቲ

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ትላንት ምሽት ሽንፈት ያስተናገዱት ሎስ ብላንኮዎቹ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ተጋጣሚያቸው ድሉ እንደሚገባው ገልጸዋል።

“ ሽንፈት ለኛ ጥሩ ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ “ እንደ ማንቂያ ደውል ነው “ ሲሉ ገልፀውታል።

ተጋጣሚያቸው ሊል ጥሩ እንደነበሩ የገለፁት አንቾሎቲ “ ማሸነፍ ይገባቸዋል “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል !

የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር የ “ Supporter's Sheild “ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፏል።

ኢንተር ሚያሚ ትላንት ሌሊት ከ ኮለምበስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በሊዮኔል ሜሲ ሁለት ግቦች እና ሉዊስ ሱዋሬዝ ጎል 3ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

ሊዮኔል ሜሲ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለኢንተር ሚያሚ ባደረጋቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ሰባት ጎሎች አስቆጥሮ አስራ አምስት አመቻችቶ አቀብሏል።

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ 46ኛ ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።

ኢንተር ሚያሚ የ “ Supporter's Sheild “ ዋንጫ ማሳካቱን ተከትሎ በቀጣዩ የ 2025 አለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በቀጣይ የሚቀጥሉ ሲሆን ኢንተር ሚያሚ ከሀያ ቀናት በኋላ በሜዳው ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ መራር ሽንፈት ነው “ ኮምፓኒ

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ከሰባት አመታት በኋላ የተሸነፉት ሙኒኮች አሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ “ መራር ሸንፈት “ ሲል ገልፆታል።

“ ሽንፈቱ መራር ነው “ ያለው ኮምፓኒ “ ሻምፒየንስ ሊጉ በምሽቱ ጨዋታ አይወሰንም ፣ በቀጣይ ወደ አሸናፊነት መመመለስ ይኖርብናል “ ብሏል።

ተጋጣሚያቸውን አስቶን ቪላ “ እንኳን ደስ አላችሁ “ ሲል የተናገረው ኮምፓኒ “ ከምሽቱ ሽንፈት እንማራለን “ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በአቋማችን ደስተኛ ነኝ ማለት አልችልም “

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በምሽቱ የቡድናቸው እንቅስቃሴ ደስተኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

“ ጥሩ ውጤት ነው “ ሲሉ የገለፁት አሰልጣኙ “ ነገርግን ባሳየነው እንቅስቃሴ ደስተኛ አይደለሁም “ በማለት ተናግረዋል።

“ አመታችንን በዚህ መልኩ መጀመር በጣም ጥሩ ነው የበለጠ አስቸጋሪ የሆኑ ጨዋታዎች ከፊታችን እየመጡ ነው “ ሲሉ አርኔ ስሎት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ላለመባረር ማሸነፍ ነው ያለብህ “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አሰልጣኞች ላለመሰናበት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው ያለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

“ ብዙ አሰልጣኞች ስለ እቅድ ሲያወሩ እሰማለሁ “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ “ ነገርግን እሱ አይሰራም ጨዋታዎችን ማሸነፍ አለብህ ወይም ትሰናበታለህ “ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰርጂዮ ራሞስ ወደ ግብፅ ሊግ ?

የግብፁ ክለብ ዛማሊክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሂሻም ናስር ዛማሊክ ስፔናዊውን ተከላካይ ሰርጂዮ ራሞስ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

ሰርጂዮ ራሞስ ለንግግር ፍቃደኛ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው “ ሄደቱ አሁንም ክፍት ነው ነገርግን ከባለሀብቶች የገንዘብ ድጋፍ ይጠይቃል “ ብለዋል።

የራሞስ ዛማሊክ ዝውውር ከሮናልዶ አል ነስር ዝውውር ጋር ተመሳሳይ ነው ያሉት ሂሻም ናስር “ ብዙዎች የሚናገሩት ስለ ክፍያው ነው ነገርግን በምላሹ የሚገኘው ጥቅም ከፍ ያለ ነው “ ብለዋል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሰርጂዮ ራሞስ በቅርቡ ከሲቪያ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሩድ ቫን ኔስትሮይ ዩናይትድን ሊረከብ ይችላል !

ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን የሚያሰናብቱ ከሆነ ሩድ ቫን ኔስትሮይን በሀላፊነት ሊሾሙ ይችላሉ የሚል እምነት እንዳለ ዘ አትሌቲክ ገልጿል።

የቀድሞ የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋች ሩድ ቫን ኔስትሮይ ከክለቡ ተጨዋቾች እና ሀላፊዎች ጋር ያለው ጥሩ ግኑኝነት ለሀላፊነት ሊያበቃው እንደሚችል ተገልጿል።

የክለቡ ሀላፊዎች በአሁን ሰዓት ኤሪክ ቴንሀግ በልምምድ ቦታዎች በሚያደርጓቸው ነገሮች እና ባላቸው ታክቲካል ደረጃ ለመረጋጋት ማሰባቸው ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ደካማ እንቅስቃሴ እና ውጤት የሚያስመዘግብ ከሆነ ሀሳቸውን እንደሚቀይሩ ተገልጿል።

የማንችስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ እሁድ ማንችስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ ለመታደም ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ኤምሬ አርሰናል ቢቆይ ስኬታማ ይሆን ነበር “ ቴሪ ሄንሪ

ፈረንሳዊው የቀድሞ የመድፈኞቹ ታሪካዊ ተጨዋች ቴሪ ሄንሪ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በአርሰናል ጊዜ ቢሰጣቸው ስኬታማ ይሆኑ እንደነበር ተናግሯል።

“ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ አርሰናል ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ቢቆዩ ስኬታማ ይሆኑ ነበር “ ሲል ቴሪ ሄንሪ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ቴሪ ሄንሪ በንግግሩም አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬን “ የታክቲክ ሊቅ “ ሲል ለአሰልጣኙ ያለውን አድናቆት ገልፆላቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 07:27:57
Back to Top
HTML Embed Code: