Telegram Web Link
ቲቧ ኩርቱዋ ጉዳት አጋጥሞታል !

ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቷ በምሽቱ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ገልፀዋል።

ግብ ጠባቂው ስላጋጠመው ጉዳት መጠን ለማወቅ በዛሬው እለት የህክምና ምርመራዎች እንደሚደረጉለት አሰልጣኙ አያይዘው ተናግረዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የፊታችን እሮብ ከሊል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ የተጨዋቾቹን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ነገ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የኦስማን ዴምቤሌን ግልጋሎት እንደማያገኝ አርኤምሲ አስነብቧል።

ተጨዋቹ ጉዳት እንዳላጋጠመው ሲገለፅ ይሁን እንጂ ውሳኔው የአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ መሆኑ ተዘግቧል።

በተጨማሪም ፒኤስጂ በነገው ጨዋታ :-

- የዶናሩማ

- ማርኮ አሴንሲዮ

- ቪቲኒሀ

- ኑኖ ሜንዴዝን ግልጋሎት ላያገኙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ፒኤስጂ ነገ ምሽት 4:00 በኤምሬትስ ስታዲየም ከአርሰናል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቷን ግሪዝማን ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ፈረንሳዊው የአትሌቲኮ ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቷን ግሪዝማን በ 33ዓመቱ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

“ በበርካታ ትዝታዎች የተሞላውን አስደሳች የህይወት ክፍል በዚሁ እዘጋዋለሁ ሁሉንም ሰው በጣም አመሰግናለሁ “ ሲል አንቷን ግሪዝማን ተናግሯል።

ግሪዝማን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን 137 ጨዋታዎች ሲያደርግ 44 ግቦችን አስቆጥሮ 38 ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል።

አንቷን ግሪዝማን ከፈረንሳይ ጋር ምን አሳካ ?

1️⃣ የአለም ዋንጫ

1️⃣ ዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ

1️⃣ የአውሮፓ ዋንጫ ወርቅ ጫማ አሸናፊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፒኤስጂ የተጨዋቾቹን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል ! የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ነገ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የኦስማን ዴምቤሌን ግልጋሎት እንደማያገኝ አርኤምሲ አስነብቧል። ተጨዋቹ ጉዳት እንዳላጋጠመው ሲገለፅ ይሁን እንጂ ውሳኔው የአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ መሆኑ ተዘግቧል። በተጨማሪም ፒኤስጂ በነገው ጨዋታ :- - የዶናሩማ - ማርኮ አሴንሲዮ - ቪቲኒሀ …
ኦስማን ዴምቤሌ ለምን ከስብስብ ተቀነሰ ?

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦስማን ዴምቤሌ ኦስማን ዴምቤሌ ከነገው የአርሰናል ጨዋታ ውጪ አድርገዋል።

አሰልጣኙ ተጫዋቹን ከስብስባቸው የቀነሱት ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ መሆኑን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ፒኤስጂ ከቀናት በፊት ሬንስን ባሸነፈበት ጨዋታ ኦስማን ዴምቤሌ ከአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቲቧ ኩርቱዋ ጉዳት አጋጥሞታል ! ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቷ በምሽቱ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ገልፀዋል። ግብ ጠባቂው ስላጋጠመው ጉዳት መጠን ለማወቅ በዛሬው እለት የህክምና ምርመራዎች እንደሚደረጉለት አሰልጣኙ አያይዘው ተናግረዋል። ሎስ ብላንኮዎቹ የፊታችን እሮብ ከሊል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።…
ቲቧ ኩርቱዋ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቱዋ በተደረገለት ምርመራ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ክለቡ አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ቲቧ ኩርቱዋ ለሚቀጥሉት ሁለት ወይም ሶስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በቀጣይ ከሊል እና ቪያሪያል በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች አንድሬ ሉኒን እንደሚጠቀሙ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፒኤስጂ በጣም ጠንካራ ነው “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የነገ ምሽት ተጋጣሚያቸው ፒኤስጂ ጠንካራ መሆኑን ገልፀዋል።

“ ፒኤሴጂ በጣም ጠንካራ ነው ጨዋታውን ተቆጣጥረው ይጫወታሉ ግልፅ የሆነ ፍላጎት ነው ያላቸው ኳስ ሲቀሙ በፍጥነት ለማግኘት ይሞክራሉ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

በነገው ጨዋታ የኋላ መስመር ተጨዋቾቹ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እና ቤን ዋይት መሰለፋቸውን ተገምግመው እንደሚወስኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ካፍ ከሱፐር ስፖርት ጋር ስምምነት ፈፅሟል !

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) ከሱፐር ስፖርት ጋር የቴሌቪዥን መብት ስርጭት ስምምነት መፈፀሙን ይፋ አድርጓል።

ስምምነቱ ካፍ የሚያዘጋጃቸውን የአፍሪካ ወንዶች እና ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እና የአፍሪካ ሱፐር ካፕ ውድድሮችን የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል።

በዘንድሮው የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የምትወከል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ቴንሀግን ቢያሰናብት ስንት ያወጣል ?

በቅርቡ ውላቸውን ያራዘሙት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን ጅማሮ ማድረጋቸውን ተከትሎ በድጋሜ ጫና ውስጥ መግባታቸው እየተነገረ ይገኛል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሁን ሰዓት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ቢያሰናብቷቸው 17.5 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ተነግሯል።

ክለቡ አሰልጣኙን ውላቸውን ሳያራዝሙ በፊት ባለፈው ክረምት ቢያሰናብት 10 ሚልዮን ፓውንድ ካሳ መክፈል ይጠበቅበት እንደነበር ተዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሁን ሰዓት አሰልጣኙን ለማሰናበት አለማሰቡ ሲገለፅ በቀጣይ የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የኤሪክ ቴንሀግን እጣፈንታ እንደሚወስኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፊሊፔ ሉዊስ በሀላፊነት ተሾመ !

ብራዚላዊው የቀድሞ የአትሌቲኮ ማድሪድ የመስመር ተጨዋች ፊሊፔ ሉዊስ የብራዚሉ ክለብ ፍላሚንጎ ጊዜያዊ አሰልጣኝ በመሆን መሾሙ ተገልጿል።

ፍላሚንጎ በዛሬው ዕለት አሰልጣኛቸው የነበረውን የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴ በይፋ አሰናብተዋል።

የ 39ዓመቱ ፊሊፔ ሉዊስ አሰልጣኙን ተከቶ በጊዜያዊነት ቡድኑን እንደሚመራ ተገልጿል።

ፊሊፔ ሉዊስ ከዚህ በፊት የፍላሚንጎን ከ 20ዓመት በታች ቡድን በማሰልጠን ላይ ይገኝ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለንደን የምንሄደው ለማሸነፍ ነው “ ጇ ኔቬስ

ፖርቹጋላዊው የፒኤስጂ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ኔቬስ ቡድናቸው በነገው የአርሰናል ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

“ አቻ ለመውጣት ወደ ለንደን አንጓዝም “ ያለው ጇ ኔቬስ “  ወደዛ የምንሄደው አርሰናልን ለማሸነፍ ነው ይህ የእኛ ስነልቦና ነው እኛ ፒኤስጂዎች ነን “ በማለት ተናግሯል።

የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 በኤምሬትስ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አዲስ ፈራሚ ሚኬል ሜሪኖ ካጋጠመው የትከሻ ጉዳት በማገገም ልምምድ መስራቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሪካርድ ካላፊዮሪ እና ቶሚያሱ መድፈኞቹ ከፒኤስጂ ጨዋታ በፊት ባደረጉት የመጨረሻ ልምምድ መሳተፍ ችለዋል።

ቤን ዋይት በበኩሉ በዛሬ የክለቡ መደበኛ የቡድን ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ብርሀኑ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ⏩️  መቐለ 70 እንደርታ ከ መቻል

እሁድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ ቅጣት ተጣለበት !

የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ የጨዋታ እግድ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ሳሙኤል ኤቶ የተጣለበት እግድ በቅርቡ በተካሄደው የ 20ዓመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ ውድድር ላይ ያልተገባ ባህሪ አሳይቷል በሚል መሆኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሳሙኤል ኤቶ ለስድስት ወራት የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን እንዳይታደም መታገዱ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሀገሪቱ ክለቦች በሚያደርጓቸው ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ላይ እንዳይታደም መታገዱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦስማን ዴምቤሌ ለምን ከስብስብ ተቀነሰ ? የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦስማን ዴምቤሌ ኦስማን ዴምቤሌ ከነገው የአርሰናል ጨዋታ ውጪ አድርገዋል። አሰልጣኙ ተጫዋቹን ከስብስባቸው የቀነሱት ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ መሆኑን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ፒኤስጂ ከቀናት በፊት ሬንስን ባሸነፈበት ጨዋታ ኦስማን ዴምቤሌ ከአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ጋር…
“ ለቡድኔ የሚበጀውን ስለምፈልግ ነው ያስቀረሁት “ ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ኦስማን ዴምቤሌን ከቡድኑ ስብስብ የቀነሱት ለቡድኑ ጥሩውን በመፈለግ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተጨዋቹ ጋር አለመግባባት አለመኖሩን ያስረዱት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ “ ችግሩ በቡድኑ ያለውን ግዴታ ያለመወጣት ነው “ ብለዋል።

“ በእኔና በደምበሌ መካከል ምንም ፀብ አልበረም ለቡድኔ የሚበጀውን ስለምፈልግ ነው ያስቀረሁት “ ሉዊስ ኤንሪኬ

አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ አያይዘውም ውሳኔያቸውን የክለቡ ሀላፊዎች መደገፋቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፒኤስጂን መግጠም የሚፈልግ ቡድን የለም “ ሀኪሚ

የፒኤስጂው የመስመር ተጨዋች አሽራፍ ሀኪሚ “ እኛን መግጠም የሚፈልግ ቡድን የለም “ ሲል በቡድኑ ጠንካሬ እምነት እንዳለው ገልጿል።

“ በጣም እርግጠኛ ነኝ እኛን መጋፈጥ የሚፈልግ የአውሮፓ ክለብ የለም “ የሚለው አሽራፍ ሀኪሚ በተጨዋቾች መካከል ጠንካራ ግንኙነት አለ ጥሩው ጎናችን ይህ ነው ብሏል።

“ አርሰናል ለመጫወት አስቸጋሪ የሆነ ቡድን ነው ፤ በአዲሱ አቀራረብ ለእኛ በጣም አስፈላጊው ጨዋታ ነው።" አሽራፍ ሀኪሚ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለጨዋታው ዝግጁ መሆን አለብን “ ዴክላን ራይስ

የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ቡድናቸው ለነገው የፒኤስጂ ጨዋታ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

“ ፔኤስጂ ጥሩ ቡድን ነው “ ሲል የገለፀው ዴክላን ራይስ ለጨዋታው ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል በማለት ተናግሯል።

“ ከዚህ በፊት ከፔኤስጂ ጋር ተጫውተን አናውቅም ስለዚህ ለጨዋታው ጎጉተናል ዝግጅታችን ጥሩ ነው" ሲል ዴክላን ራይስ ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዴብሮይን መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

የማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ኬቨን ዴብሮይን በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

ተጨዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ የሚመለሰው ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ መሆኑን ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኬቨን ዴብሮይን ማንችስተር ሲቲ ነገ በሻምፒየንስ ሊጉ ከስሎቫን ብራቲስላቫ እንዲሁም በሊጉ ከፉልሀም የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በ 2017 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን

ማክሰኞ ⏩️ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ባሕር ዳር ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ነስር ድል አድርጓል !

በእስያ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል ነስር ከኳታሩ ክለብ አል ራያን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ሳዲዮ ማኔ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 904ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለሀገሩ እና ክለቡ ስምንት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 22:26:02
Back to Top
HTML Embed Code: