Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ቤንታኩር በእንግሊዝ ኤፍኤ ክስ ቀረበበት ! ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታኩር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል ክስ እንደተከፈተበት ተገልጿል። ሮድሪጎ ቤንታኩር ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ የሰን ሁንግ ሚን ማልያ ማገኘት ከተቻለ ሲጠየቅ “ ምናልባት የአጎቱን ልጅ ምክንያቱም ሁሉም ይመሳሰላሉ “ ሲል መልሶ ነበር።…
“ ቤንታንኩር እያለቀሰ ይቅርታ ጠይቆኛል “ ሰን

ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ለሰጠው አስተያየት የቡድን አጋሩ ሰን ሁንግ ሚንን ይቅርታ ጠይቋል።

ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ " ሰን ሁንግ ሚን እና የአጎቱ ልጆች ሁሉም አንድ አይነት ናቸው " ብሎ ተናግሮ ነበር።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው ሰን " የእንግሊዝ ኤፍኤ ጉዳዩን እያየው ስለሆነ ብዙ አልናገርም ነገርግን ቤንታንኩርን በጣም ነው የምወደው “ ሲል ተደምጧል።

በቀጥታ ይቅርታ ጠይቋል ለእኔም ጉዳዩ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ቀድሞ ረጅም መልዕክት ፅፎልኝ ነበር ፣ ወደ ቡድኑ ከተመለሰም በኋላም እያለቀሰ ይቅርታ ብሎኛል ሲል ሰን ተናግሯል።

በኮንትራት ዙሪያ እስካሁን ከክለቡ ጋር ለንግግር አለመቀመጡን የጠቆመው ሰን “ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቴ ውድድር አመቱ ላይ እና ክለቡ የሚገባውን ነገር ማሳካት ላይ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ወልቂጤ ከተማ ስድስት ነጥቦች ይቀነሱበታል ! የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ የስድስት ነጥብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ( ክለብ ላይሰንሲግ ) ባለሟሟላታቸውን እና በውድድሩ ያልተመዘገበ ቡድን ወደ ሜዳ መግባት #አለመቻሉን ተከትሎ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል። በአሁን ሰዓት ከ መቻል ጋር መርሐ…
ወልቂጤ ከተማ በተከታታይ ጨዋታ ሳይገኝ ቀርቷል !

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ በተከታታይ መርሐግብር ጨዋታውን ሳያደርግ ቀርቷል።

ዛሬ ምሽት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር የወጣለት ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላቱ ጨዋታው በፎርፌ ለንግድ ባንክ ተሰጥቷል።

ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላታቸው የመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር በፎርፌ እንደተሰጠባቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ መሰረት አንድ ክለብ በተከታታይ ጨዋታዎች ሜዳ ላይ የማይገኝ ከሆነ ከውድድሩ እንዲሰረዝ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውን የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከጊኒ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ይሆናል። የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል። ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሁለቱንም ጨዋታ በ ኮትዲቯር ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት ፌዴሬሽኖች በንግግር…
ዋልያዎቹ በኮትዲቯር እንደሚጫወቱ ይፋ ሆነ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ይፋ ሆኗል።

የሁለቱ ሀገራት እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ጨዋታዎቹን ኮትዲቯር ላይ ለማድረግ በንግግር ላይ እንደሚገኙ መዘገቡ አይዘነጋም።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ሶስተኛ ጨዋታ ጊኒ ባስመዘገበችው 20,000 ተመልካችን በሚይዘው ያሙሶኩሮ ቻርለስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር " በሜዳው " የሚያደርገው የምድብ አራተኛ ጨዋታ ደግሞ አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።

የደርሶ መልስ መርሐ ግብሩ ጥቅምት 1 እና ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም የሚደረጉ ይሆናል።

ዋልያዎቹ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው በምድባቸው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

3:45 አርሰናል ከ ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

Bolton XI: Southwood; Toal, Collins, Santos; Dacres-Cogley, Sheehan, Arfield, Williams, McAtee; Forino-Joseph, Dempsey.

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 ሊቨርፑል ከ ዌስትሀም

4:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ትዌንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
18 '

አርሰናል 1-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

ራይስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
35 ' አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
ንዋኔሪ

22 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 ትዌንቴ

ሊቨርፑል 0-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
29 'ሊቨርፑል 1-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

45 ' አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
        ንዋኔሪ

29 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0-0 ትዌንቴ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
35 ' ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ትዌንቴ

ኤሪክሰን

35 'ሊቨርፑል 1-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ

እረፍት | አርሰናል 2-0 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ
        ንዋኔሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
58 ' አርሰናል 3-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ ኮሊንስ
        ንዋኔሪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 '

ሊቨርፑል 2-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )

ማንችስተር ዩናይትድ 1-0 ትዌንቴ

ኤሪክሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
65 ' አርሰናል 4-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ             ኮሊንስ
        ንዋኔሪ
ስተርሊንግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TikvahGoal

የጨዋታዎቹን አጫጭር ቪዲዮች እና ጎሎች በጎል ቻናላችን መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 ' አርሰናል 5-1 ቦልተን ( ካራባኦ ካፕ )

        ራይስ             ኮሊንስ
        ንዋኔሪ
         ስተርሊንግ
ሀቨርትዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
68 ' ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

ኤሪክሰን ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 '

ሊቨርፑል 3-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )
ሳላህ

ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

        ኤሪክሰን            ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከቦልተን ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙሩ ተቀላቅሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግብ ንዋኔሪ 2x ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ራሂም ስተርሊንግ እና ካይ ሀቨርትዝ ማስቆጠር ችለዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ ለአርሰናል በቋሚነት ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ አንድ ግብ አስቆጥሮ አንድ አመቻችቶ አቀብሏል።

አርሰናል የካራባኦ ካፕ አራተኛ ዙር ተጋጣሚውን ከደቂቃዎች በኋላ በሚወጣ እጣ የሚያውቅ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 '

ሊቨርፑል 4-1 ዌስትሀም ( ካራባኦ ካፕ )

ጆታ             ኳንሳህ ( በራስ ላይ )
ሳላህ
ጋክፖ

ማንችስተር ዩናይትድ 1-1 ትዌንቴ

        ኤሪክሰን            ላመርስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 13:30:51
Back to Top
HTML Embed Code: