Telegram Web Link
ቼልሲ እና ሲቲ አራተኛውን ዙር ተቀላቅለዋል !

በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ቼልሲ ባሮውን 5ለ0 እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ዋትፎርድን 2ለ1 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ክርስቶፈር ንኩንኩ 3x ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ፋርማን በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለማንችስተር ሲቲ የማሸነፊያ ግቦችን ጄርሚ ዶኩ እና ማቲውስ ኑኔስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለዋትፎርድ ቶማስ ኢንስ አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሎስ ብላንኮዎቹ ድል አድርገዋል !

በስፔን ላሊጋ የሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከዲፖርቲቮ አላቬስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ሉካስ ቫስኩዌስ ፣ ሮድሪጎ እና ኪሊያን ምባፔ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ዲፖርቲቮ አላቬስን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ኪኬ ጋርሽያ እና ካርሎስ ፕሮቴሶኒ አስቆጥረዋል።

ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዘመኑ አምስተኛ የላሊጋ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 17 ነጥብ
8️⃣ኛ. ዲፖርቲቮ አላቬስ :- 10 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ

ቅዳሜ ሄታፌ ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
“ አቡበከር ናስር አሁን ከእኛ ጋር አይደለም “ ማንቆባ ማንጊቲ

ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ በውሰት ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እንደሚቀላቀል ተገልጿል።

የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ ትላንት ምሽት በሰጡት አስተያየት “ አቡበከር ናስር በዚህ ሰዓት ከእኛ ጋር አይደለም “ ብለዋል።

“ አቡበክር በአሁኑ ሰዓት ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ ውስጥ ያለ ይመስለኛል ማወቅ አለባችሁ “ ሲሉ አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ያለፈውን አመት በጉዳት ከክለቡ ስብስብ ውጪ የነበረው አቡበከር ናስር በአዲሱ የሰንዳውንስ አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ የቅድመ ውድድር ስብስብ ውስጥ ተካቶ ግብ ማስቆጠሩም ይታወሳል።

አሰልጣኙ የአቡበከር ናስርን ቀጣይ ማረፊያ በይፋ ቢገልፁም ዝውውሩን ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እስካሁን ይፋ አላደረገውም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቫራን ጫማውን ለመስቀል ማሰቡ ተገለጸ !

በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን ጫማውን ለመስቀል ማሰቡ ተገልጿል።

ራፋኤል ቫራን ከወራት በፊት የጣልያኑን ክለብ ኮሞ ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ክለቡን መልቀቁ ይታወቃል።

የ 31ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በቅርቡ ቀጣይ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቫራን ጫማውን ለመስቀል ማሰቡ ተገለጸ ! በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን ጫማውን ለመስቀል ማሰቡ ተገልጿል። ራፋኤል ቫራን ከወራት በፊት የጣልያኑን ክለብ ኮሞ ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም በጉዳት ምክንያት ክለቡን መልቀቁ ይታወቃል። የ 31ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በቅርቡ ቀጣይ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ተነግሯል። …
ራፋኤል ቫራን በይፋ ጫማውን ሰቀለ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በ 31ዓመቱ ከእግርኳስ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በቅርቡ የጣልያኑን ክለብ ኮሞ ተቀላቅሎ በጉዳት ምክንያት ክለቡን ለቅቆ ነበር።

ራፋኤል ቫራን በእግርኳስ ህይወቱ 573 ጨዋታዎች ሲያደርግ 26 ግቦች አስቆጥሮ ስምንት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ቫራን በእግርኳስ ህይወቱ ምን አሳካ ?

4️⃣ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የአለም ክለቦች ዋንጫ

3️⃣ ላሊጋ ፣ ሱፐር ኮፓ

2️⃣ ሱፐር ካፕ

1️⃣ አለም ዋንጫ ፣ ኤፌ ካፕ ፣ ኮፓ ዴላሬ ፣ ሊግ ካፕ ፣ ኔሽንስ ሊግ ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ስለ ሲቲ ሁሉም መረጃ አለኝ “ ሚኬል አርቴታ

የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች ስለ ቡድናቸው የአጨዋወት ዘይቤ የሰጡት አስተያየት አግባብ አይደለም ስለ እነሱም አውቃለሁ ብለዋል።

“ እኔ ማንችስተር ሲቲ ውስጥ አራት አመታት አሳልፌያለሁ ከእነሱ በፊት እዛ ነበርኩ ስለዚህ እመኑኝ ስለ እነሱ ሁሉም መረጃ አለኝ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ገልፀዋል።

“ ኢትሀድ ላይ ባደረግነው ነገር እኮራለሁ በሁሉም መንገድ መላመድ እንደምንችል አሳይተናል በውጤቱ ግን ደስተኛ አይደለሁም ማሸነፍ ፈልገን ነበር።“ አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
Photo
ሮድሪ ከባድ ጉዳት አጋጥሞታል !

ስፔናዊው አማካይ ሮድሪ በሳምንቱ መጨረሻ ከአርሰናል በነበረው ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት የ “ ACL “ ጉዳት መሆኑን ማንችስተር ሲቲ በይፋ አረጋግጧል።

ተጨዋቹ በቀኝ ጉልበቱ ላይ ጉዳቱ እንዳጋጠመው የገለፀው ክለቡ ለተሻለ የህክምና ምርመራ ስፔን እንደሚገኝም አስታውቋል።

ሮድሪ በቀጣይ ለምን ያህል ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ለማወቅ የህክምና ምርመራዎች መቀጠላቸውን ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ሮድሪ ያጋጠመው ጉዳት ለበርካታ ወራት ከሜዳ የሚያርቅ መሆኑ በመዘገብ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ጉዳት አጋጠመው !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በትላንት ምሽቱ የላሊጋ መርሐግብር ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኪሊያን ምባፔ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ እስከ ሶስት ሳምንታት ጊዜ እንደሚወስድበት ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ የፊታችን እሁድ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር የሚያደርገው የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ዛሬ ምሽት በግብ ጠባቂነት ማንን ያሰልፋል ?

አርሰናል ግብ ጠባቂው ዴቪድ ራያ መጠነኛ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ለጥንቃቄ ዛሬ ምሽት ከቦልተን ጋር በሚያደርጉት የሊግ ካፕ ጨዋታ እንደሚያሳርፉት ተገልጿል።

በጨዋታው መድፈኞቹ የ 16ዓመቱን የአካዳሚያቸው ግብ ጠባቂ ጃክ ፖርተር በቋሚነት ለማሰለፍ ማሰባቸው ተገልጿል።

የክለቡ ቁጥር ሁለት ግብ ጠባቂ ኔቶ ከበርንማውዝ ጋር በሊግ ካፕ መጫወቱን ተከትሎ ለአርሰናል መሰለፍ እንደማይችል ተነግሯል።

በተጨማሪም በቅርቡ ከአያክስ ያስፈረሙት ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ጉዳት እንዳጋጠመው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ካሴሚሮ በቴንሀግ የታክቲክ እውቀት ተደንቆ ነበር “ ስቲቭ ማክላረን

የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የቀድሞ ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት ስቲቭ ማክላረን ካሴሚሮ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የታክቲክ እውቀት ተደንቆ እንደነበር ገልጸዋል።

“ ካሴሚሮ ሁሉንም ነገሮች ሪያል ማድሪድ ውስጥ አይቻለሁ ብሎ ስለሚያስብ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በነበራቸው የጨዋታ ታክቲክ እና አጠቃላይ ስራ ተደንቆ ነበር።“ ሲሉ ስቲቭ ማክ ክላረን ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ ታክቲሺያን መሆናቸውን ገልፀው ሌሎች ሜዳ ላይ ሊታዩዋቸው የማይችሉ ነገሮችን መመልከት ይችላሉ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮድሪ ባሎን ዶር ይገባዋል “ ሎታር ማቲያስ

የቀድሞ ጀርመናዊ ተጨዋች ሎታር ማቲያስ የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት ለስፔናዊው ተጨዋች ሮድሪ እንደሚገባው ገልጿል።

“ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከቪንሰስ ጁኒየር በበለጠ ሮድሪ የባሎን ዶር ሽልማት ይገባዋል “ ሲል ሎታር ማቲያስ አስተያየቱን ሰጥቷል።

እንደ ቀድሞ ተጨዋቹ ሎታር ማቲያስ ገለፃ “ በእኔ የዚህ አመት ምርጥ ተጨዋቾች ደረጃ ቪንሰስ ጁኒየርን ሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጠዋለሁ “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

ሐሙስ ⏩️ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ አርባምንጭ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሼዝኒ ጓንቱን መስቀሉን አሳወቀ ! ፖላንዳዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በ 34ዓመቱ ጓንቱን መስቀሉን በይፋ አስታውቋል። ሼዝኒ በቅርቡ ሰባት የውድድር አመታት ካሳለፈበት የጣልያን ሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየቱ አይዘነጋም። ሼዝኒ በእግርኳስ ህይወቱ ምን አሳካ ? 3️⃣ የጣልያን ሴርያ ፣ የጣልያን ዋንጫ 2️⃣ ኤፌ ካፕ ፣ የጣሊያን ሱፐር ካፕ…
ሼዝኒ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ተስማማ !

ፖላንዳዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በቅርቡ ጓንቱን መስቀሉን ይፋ ቢያደርግም ተመልሶ ለባርሴሎና ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

የቴር ስቴገንን መጎዳት ተከትሎ ባርሴሎና በምትኩ ሼዝኒን ለአንድ አመት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

“ አሁን ላይ ወደ እግርኳስ ተመልሼ ባርሴሎናን ለመቀላቀል በንግግር ላይ ነኝ “ ሲል ሼዝኒ ተናግሯል።

“ ባርሴሎና አለማችን ላይ ካሉ ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው “ ያለው ሼዝኒ “ በእግርኳስ ህይወቴ ይህንን የመሰለ እድል አልቀበልም ብል ንቀት ይሆናል “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቤንታኩር በእንግሊዝ ኤፍኤ ክስ ቀረበበት ! ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታኩር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ በቡድን አጋሩ ላይ ያልተገባ ነገር ተናግሯል በሚል ክስ እንደተከፈተበት ተገልጿል። ሮድሪጎ ቤንታኩር ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ የሰን ሁንግ ሚን ማልያ ማገኘት ከተቻለ ሲጠየቅ “ ምናልባት የአጎቱን ልጅ ምክንያቱም ሁሉም ይመሳሰላሉ “ ሲል መልሶ ነበር።…
“ ቤንታንኩር እያለቀሰ ይቅርታ ጠይቆኛል “ ሰን

ዩራጓዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ለሰጠው አስተያየት የቡድን አጋሩ ሰን ሁንግ ሚንን ይቅርታ ጠይቋል።

ሮድሪጎ ቤንታንኩር በቅርቡ ከዩራጓይ መገናኛ ብዙሀን ጋር በነበረው ቆይታ " ሰን ሁንግ ሚን እና የአጎቱ ልጆች ሁሉም አንድ አይነት ናቸው " ብሎ ተናግሮ ነበር።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው ሰን " የእንግሊዝ ኤፍኤ ጉዳዩን እያየው ስለሆነ ብዙ አልናገርም ነገርግን ቤንታንኩርን በጣም ነው የምወደው “ ሲል ተደምጧል።

በቀጥታ ይቅርታ ጠይቋል ለእኔም ጉዳዩ ምን እንደሆነ ሳላውቅ ቀድሞ ረጅም መልዕክት ፅፎልኝ ነበር ፣ ወደ ቡድኑ ከተመለሰም በኋላም እያለቀሰ ይቅርታ ብሎኛል ሲል ሰን ተናግሯል።

በኮንትራት ዙሪያ እስካሁን ከክለቡ ጋር ለንግግር አለመቀመጡን የጠቆመው ሰን “ አሁን ላይ ሙሉ ትኩረቴ ውድድር አመቱ ላይ እና ክለቡ የሚገባውን ነገር ማሳካት ላይ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ወልቂጤ ከተማ ስድስት ነጥቦች ይቀነሱበታል ! የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ የስድስት ነጥብ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ( ክለብ ላይሰንሲግ ) ባለሟሟላታቸውን እና በውድድሩ ያልተመዘገበ ቡድን ወደ ሜዳ መግባት #አለመቻሉን ተከትሎ ጨዋታው ሳይደረግ ቀርቷል። በአሁን ሰዓት ከ መቻል ጋር መርሐ…
ወልቂጤ ከተማ በተከታታይ ጨዋታ ሳይገኝ ቀርቷል !

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለአዲሱ የውድድር ዘመን የሚጠበቅበትን ህጋዊ መስፈርት አለሟሟላቱን ተከትሎ በተከታታይ መርሐግብር ጨዋታውን ሳያደርግ ቀርቷል።

ዛሬ ምሽት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር የወጣለት ወልቂጤ ከተማ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላቱ ጨዋታው በፎርፌ ለንግድ ባንክ ተሰጥቷል።

ወልቂጤ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተመሳሳይ ተገቢውን የምዝገባ ሂደት ባለሟሟላታቸው የመጀመሪያ ሳምንት መርሐግብር በፎርፌ እንደተሰጠባቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የውድድር ደንብ መሰረት አንድ ክለብ በተከታታይ ጨዋታዎች ሜዳ ላይ የማይገኝ ከሆነ ከውድድሩ እንዲሰረዝ ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውን የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከጊኒ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ይሆናል። የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል። ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሁለቱንም ጨዋታ በ ኮትዲቯር ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት ፌዴሬሽኖች በንግግር…
ዋልያዎቹ በኮትዲቯር እንደሚጫወቱ ይፋ ሆነ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ይፋ ሆኗል።

የሁለቱ ሀገራት እግርኳስ ፌዴሬሽኖች ጨዋታዎቹን ኮትዲቯር ላይ ለማድረግ በንግግር ላይ እንደሚገኙ መዘገቡ አይዘነጋም።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ሶስተኛ ጨዋታ ጊኒ ባስመዘገበችው 20,000 ተመልካችን በሚይዘው ያሙሶኩሮ ቻርለስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር " በሜዳው " የሚያደርገው የምድብ አራተኛ ጨዋታ ደግሞ አቢጃን በሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።

የደርሶ መልስ መርሐ ግብሩ ጥቅምት 1 እና ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም የሚደረጉ ይሆናል።

ዋልያዎቹ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው በምድባቸው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 09:33:01
Back to Top
HTML Embed Code: