Telegram Web Link
ይገምቱ ይሸለሙ

የበርንማውዝ እና ቼልሲን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 4:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
ባየር ሙኒክ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ የሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ከሆልስቲን ኬል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን 3x ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ኦሊሴ እና ሬምበርግ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በጀርመን ቡንደስሊጋ አምስተኛ ሀትሪኩን መስራት ችሏል።

ቀደም ብሎ በተደረገ የቡንደስሊጋው ጨዋታ ባየር ሌቨርኩሰን ከሆፌንሄም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ኛ ባየር ሙኒክ :- 9 ነጥብ
1️⃣8️⃣ኛ ሆልስቴን ኬል :- ምንም ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶን ቪላ ከኤቨርተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ግቦች ኦሊ ዋትኪንስ 2x እና ዱራን ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኤቨርተን ማክኔል እና ካልቨርት ሌዊን አስቆጥረዋል።

ኤቨርተን በሁለት የግብ ልዩነት ሲመራ ቢቆይም ግቦች ተቆጥረውበት ሽንፈት አስተናግዷል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ያደረጋቸውን አራት የሊግ ጨዋታዎች ተሸንፏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3ኛ. አስቶን ቪላ :- 9 ነጥብ
20ኛ. ኤቨርተን :- ምንም ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ቅዳሜ - አስቶን ቪላ ከ ዎልቭስ

ቅዳሜ - ሌስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ዩናይትድ እና ሳውዝሀምፕተን ጨዋታ :-

1ኛ. Eb
2ኛ. @G27az
3ኛ. @YeabT99

የሊቨርፑል እና ኖቲንግሀም ፎረስት :-

1ኛ. @abuuuuuuu15
2ኛ. @Asgedase
3ኛ. Abush

የማንችስተር ሲቲ እና ብሬንትፎርድ

1ኛ. @maybe_1year
2ኛ. Eb
3ኛ. @The_endxyz

@tikvahethsport
እረፍት

በርንማውዝ 0-0 ቼልሲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

በርንማውዝ 0-1 ቼልሲ

ንኩንኩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ድል አድርገዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ አራተኛ ሳምንት መርሐግብር ቼልሲ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የቼልሲን የማሸነፊያ ግብ ፈረንሳዊው አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ በቼልሲ የመጀመሪያ ጨዋታው ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በጨዋታው አንቶኒ ቴለር አስራ አራት የማስጠንቀቂያ ካርዶችን ሲመዙ ይህም የሊጉ ሪከርድ ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

7ኛ. ቼልሲ :- 7 ነጥብ
11ኛ. በርንማውዝ :- 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

ቅዳሜ - ዌስትሀም ዩናይትድ ከ ቼልሲ

ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ በርንማውዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሎስ ብላንኮዎቹ ድል አድርገዋል !

በስፔን ላሊጋ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የአምናው የሊጉ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁኒየር እና ኪሊያን ምባፔ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 11 ነጥብ
16ኛ. ሪያል ሶሴዳድ :- 4 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ሪያል ማድሪድ ከ እስፓኞል

ማክሰኞ - ማዮርካ ከ ሪያል ሶሴዳድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ቲክቫህ ስፖርት ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የመውሊድ በዓል ይመኛል!

እንኳን አደረሳችሁ!

@Tikvahethsport
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

10:00 ቶተንሀም ከ አርሰናል

11:15 ጂሮና ከ ባርሴሎና

12:30 ዎልቭስ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

1:00 ካግሊያሪ ከ ናፖሊ

3:45 ሞንዛ ከ ኢንተር ሚላን

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የአርሰናል እና ባርሴሎና ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሁለት ሽልማቶቻችን 8:30 ፣ 9:45 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርስ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሜሲ ከጉዳት መልስ ግቦች አስቆጥሯል !

በጉዳት ምክንያት ከሶስት ወራት በላይ ከሜዳ ርቆ የቆየው አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ግቦች አስቆጥሯል።

ኢንተር ሚያሚ ከፊላደልፊያ ጋር ያደረገውን የሊግ ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ሊዮኔል ሜሲ ሁለት ግቦች ከመረብ ማሳረፍ ሲችል አንድ አመቻችቶ አቀብሏል።

ሊዮኔል ሚሴ በአሜሪካ ሊግ በአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች አስራ አምስት ግቦች እና አስራ አምስት ለግብ የሆኑ ኳሶች ያመቻቸ ፈጣኑ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ 840ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ኢንተር ሚያሚ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድርን በስልሳ ሁለት ነጥቦች በመምራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቪንሰስ ታላቅ ተጨዋች ነው “ ምባፔ

ፈረንሳዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ቪንሰስ ጁኒየር ታላቅ ተጨዋች መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ቪንሰስ ትላንት ምሽት እንዲመታ ስለ ለቀቀለት የፍፁም ቅጣት ምት የተናገረው ኪሊያን ምባፔ “ ቪንሰስ ምርጥ ተጨዋች ነው እሱ ለሪያል ማድሪድ ብዙ ነገር አድርጓል ፣ ከእሱ ጋር በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ።“ ብሏል።

ኪሊያን ምባፔ አክሎም ዋናው ነገር የፍፁም ቅጣት ምት መቺው ሳይሆን ያገኘናቸው ሁሉም መቆጠራቸው ነው በማለት ተናግሯል።

ሪያል ማድሪድ በዚህ አመት አራት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ሲያገኝ ቪንሰስ ጁኒየር ሁለቱን ለኪሊያን ምባፔ ሰጥቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ህመም አጋጥሞታል !

ፖርቹጋላዊው የአል ነስር የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የኢንፌክሽን ህመም እንዳጋጠመው ክለቡ አሳውቋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በህመሙ ምክንያት እረፍት ማድረግ እንደሚያስፈልገው የክለቡ የህክምና ቡድን መምከሩ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሮናልዶ አል ነስር ወደ ኢራቅ ተጉዞ ከአል ሾርታ ጋር የሚያደርገው የእስያ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የአርሰናል እና ቶተንሀምን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 10:00 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ቶተንሀም ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ግዴታ ማሸነፍ ያለብን ጨዋታ ነው “ ኡዶጊ

ጣልያናዊው የቶተንሀም የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዴስትኒ ኦዶጊ የሰሜን ለንደን ደርቢ ትልቅ ጨዋታ መሆኑን ገልጿል።

“ ትልቅ ጨዋታ እና ትልቅ ደርቢ ነው “ ሲል የገለፀው ዴስትኒ ኦዶጊ ለደጋፊዎቹ ግዴታ ልናሸንፈው የሚገባን ጨዋታ ነው ሁሉም በጥሩ እንደሚሄድ ተስፋ አደርጋለሁ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የቶተንሀም ደጋፊዎች ዛሬ ካላሸነፋችሁ ክለብ ቀይሩ “ ፖል ሜርሰን

የቀድሞ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ፖል ሜርሰን ለቶተንሀም ዛሬ አርሰናልን ለማሸነፍ ትክክለኛው ጊዜ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

“ የቶተንሀም ደጋፊዎች ከሆናችሁ እና በዛሬው ጨዋታ  አርሰናልን ማሸነፍ ካልቻላችሁ ሌላ ክለብ መቀየር አለባችሁ “ ሲል ፖል ሜርሰን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 13:29:37
Back to Top
HTML Embed Code: