Telegram Web Link
#TeamEthiopia 🇪🇹

በትላንትናው ዕለት በ10,000 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ውድድር የብር ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት በሪሁ አረጋዊ ሜዳሊያውን ተረክቧል።

ፎቶ :- Getty Image

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦሲሜን ለወዳጅነት ጨዋታ ጥሪ አልቀረበለትም !

ናፖሊ ከስፔኑ ክለብ ጂሮና ጋር እያደረገ ለሚገኘው የወዳጅነት ጨዋታ ለናይጄሪያዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ጥሪ አለማቅረቡ ተገልጿል።

ናፖሊዎች ቪክቶር ኦሲሜን በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን በሚለቅበት ሁኔታዎች ላይ በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

አዲሱ የናፖሊ ዋና አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ሮሜሎ ሉካኩን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ሲገለፅ ቪክቶር ኦሲሜን በበኩሉ ስሙ ከቼልሲ እና ፒኤስጂ ጋር እየተያያዘ ይገኛል።

ጂሮና በአሁን ሰዓት ከናፖሊ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን የወዳጅነት በዶኒ ቫን ዴቢክ ግብ 1ለ0 እየመሩ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024 አሜሪካዊቷ ፈጣን የ 100ሜትር ሯጭ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች። የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ተሳትፎን እያደረገች የምትገኘው የአለም ሻምፒዮና ሻ ካሪ ማጣርያውን 10.94 በማግባት ማሸነፏ ይታወቃል። የጃማይካ ተፎካካሪዋ ሼሪካ ጃክሰን በውድድሩ አለመኖር ሻ ካሪ በቀላሉ እንድታሸንፍ ከፍተኛ ግምትን አሰጥቷታል። ሆኖም…
#Paris2024

ጃማይካዊቷ ታሪካዊ የ 100ሜትር ሯጭ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ከፓሪስ ኦሎምፒክ 100ሜትር ሩጫ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ውጪ ሆናለች።

አምስተኛ እና የመጨረሻ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በማድረግ ላይ የምትገኘው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በአምስት ተከታታይ ኦሎምፒክ ሜዳልያ በማግኘት ባለታሪክ መሆን ትችል ነበር።

አትሌቷ በምን ምክንያት ከግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር ውጪ እንደሆነች በይፋ የተገለፀ ነገር የለም።

የ 37ዓመቷ አትሌት ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በ100ሜትር ሩጫ ሁለት የወርቅ ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

በተጨማሪም ሌላኛዋ ጃማይካዊት ሼሪካ ጃክሰን በፍፃሜ ውድድሩ የማትሳተፍ ይሆናል።

ይህንንም ተከትሎ አሜሪካዊቷ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ዛሬ ምሽት በሚደረገው የፍፃሜ ውድድር የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝታለች።

የ 100ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ዛሬ ምሽት 4:15 ሲል ይጀምራል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከእኛ ጋር የሚስማማ አጥቂ ያስፈልገናል " አንሄ ፖስቴኮግሉ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ከቡድናቸው አጨዋወት ጋር የሚስማማ አጥቂ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

" ከአጨዋወታችን ጋር የሚስማማ በአካልም በስነልቦናውም ጠንካራ የሆነ አጥቂ ያስፈልገናል ፤ ከክለቡ ጋርም በዚህ ጉዳይ እየተነጋገርንበት ነው " ሲሉ አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት ቶተንሀም የበርንማውዙን የፊት መስመር አጥቂ ዶሚኒክ ሶላንኬን ለማስፈረም እንቅስቃሴ መጀመራቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024 ጃማይካዊቷ ታሪካዊ የ 100ሜትር ሯጭ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ከፓሪስ ኦሎምፒክ 100ሜትር ሩጫ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ውጪ ሆናለች። አምስተኛ እና የመጨረሻ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በማድረግ ላይ የምትገኘው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በአምስት ተከታታይ ኦሎምፒክ ሜዳልያ በማግኘት ባለታሪክ መሆን ትችል ነበር። አትሌቷ በምን ምክንያት ከግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር ውጪ እንደሆነች በይፋ…
ጁሊያን አልፍሬድ ደማቅ ታሪክ ፃፈች !

ሴንት ሉሺያዊቷ አትሌት ጁሊያን አልፍሬድ የ 100ሜትር ሴቶች ሩጫ ፍፄሜ ውድድር በበላይነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችላለች።

የፍፃሜ ውድድሩን አትሌት ጁሊያን አልፍሬድ 10.72 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የወቅቱ የአለም ፈጣኗ ሴት መሆኗን አረጋግጣለች።

አትሌት ጁሊያን አልፍሬድ ለሀገሯ ሴንት ሉሺያ በታሪክ የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳልያ በማሳካት ደማቅ ታሪክ መፃፍ ችላለች።

በውድድሩ ለወርቅ ሜዳልያ የተጠበቀችው አሜሪካዊቷ ሻ ካሪ ሪቻርድሰን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳልያ ስታሸንፍ ሌላኛዋ አሜሪካዊት ጄፈርሰን የነሐስ ሜዳልያ ባለቤት ሆናለች።

የጃማይካ ያለፉት አራት ኦሎምፒክ ውድድሮች የ 100ሜትር ሴቶች የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊነት ሪከርድ ተገቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ኮንፈረንስ ሊግ ከምንም ይሻላል “ ማሎ ጉስቶ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ማሎ ጉስቶ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ በወጣቶች ለትገነባው ቡድናቸው ጥሩ ልምድ መቅሰሚያ እንደሚሆነው ተናግሯል።

“ ኮንፈረንስ ሊግ ከምንም ይሻላል “ የሚለው ማሎ ጉስቶ እኛ ገና ወጣት ቡድን ነው ያለን የአውሮፓ መድረክን ለመላመድ ጥሩ እድልን ይፈጥርልናል ብሏል።

“ በዚህ አመት የሆነ ዋንጫ ማሸነፍ አለብን “ ሲል ስለቀጣዩ እቅዳቸው የተናገረው ተጨዋቹ ኮንፈረንስ ሊግ ፣ ፕርሚየር ሊግ ወይም የሀገር ውስጥ ውድድር ሊሆን ይችላል ማሸነፍ ግን ይኖርብናል ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል አሸንፏል !

የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል በአሜሪካ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የቅድመ ውድድር ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ 3ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

በጨዋታው የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ካርቫልሆ ፣ ጆንስ እና ሲሚካስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ አስተያየት የሰጡት አርኔ ስሎት "እኛ በምንፈልገው መንገድ ጥሩ ተጫውተናል ፤ እኔ ምርጥ ጎሎች እና እንቅስቃሴ ከቡድኔ ተመልክቻለሁ" ብለዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ በበኩላቸው "እኛ እድሎች መፍጠር ችለናል ሆኖም አልተጠቀምንበትም ሊቨርፑሎች በሚገባ ያገኙትን እድል ተጠቅመዋል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ሊቨርፑል በቀጣይ ከ ሲቪያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርግ ማንችስተር ዩናይትድ ቀጣይ ሳምንት በኮሚኒቲ ሺልድ ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ድል አድርጓል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በቅድመ ውድድር ዝግጅት የወዳጅነት ጨዋታ ከሪያል ማድሪድ ጋር አድርጎ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው የባርሴሎናን የማሸነፊያ ሁለት ግቦች ፓኦ ቪክቶር ሲያስቆጠር ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ኒኮ ፓዝ አስቆጥሯል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ ሀሳባቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ "ሪያል ማድሪድን አሸንፈናል ነገር ግን 90 ደቂቃ ተጭነን መጫወት አልቻልንም ይህ ችግር ነው" ብለዋል።

ካርሎ አንቾሎቲ በበኩላቸው "ይህ ብዙ አስፈላጊ ጨዋታ አልነበረም ለወጣቶች እድል የምንሰጥበት ነበር ፤ ምባፔ እና ቤሊንግሀም በሱፐር ካፕ ፍፃሜ ላይ ቋሚ ሆነው ይጀምራሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
PSV - Feyenoord
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው #የማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 1,500 ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 3000 መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

-
ቀን 5:05 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ( አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ አለማየሁ )

- ምሽት 3:45 :- 800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ( አትሌት ወርቅነሽ መሰለ  እና ፅጌ ድጉማ )

- ምሽት 4:10 :- 1,500ሜ ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ ( አትሌት ሳሙኤል ተፈራ እና ኤርሚያስ ግርማ)

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Paris2024

የህንድ መንግሥት በፓሪስ ኦሎምፒክ እየተሳተፉ ለሚገኙ የሀገሪቱ አትሌቶች አርባ የአየር መቆጣጠሪያ " AC " ገዝቶ መላኩ ተገልጿል።

የፓሪስ ኦሎምፒክ አዘጋጆች በአትሌቶች መንደር ውስጥ ለሚገኙ አትሌቶች ባቀረቡት የማረፊያ ክፍል ውስጥ የአየር መቆጣጠሪያ ባለማቅረባቸው ቅሬታ ሲቀርብ እንደነበር ይታወሳል።

የህንድ ስፖርት ሚኒስቴር በበኩሉ ፈረንሳይ ከሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ እና ኦሎምፒክ ኮሚቴ ጋር በመነጋገር የአየር መቆጣጠሪያውን በራሱ ወጪ ገዝቶ መላኩ ተገልጿል።

የሀገሪቱ ስፖርት ሚኒስቴር ይሄንን ያደረገው አትሌቶቹ በፓሪስ በሚኖራቸው ቆይታ ጥሩ እረፍት እንዲያደርጉ እና ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እንዲያግዛቸው መሆኑ ተነግሯል።

በፓሪስ የሚገኙ አትሌቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ተጋርተው እንደሚገኙ እንዲሁም ለሊቱን በሙቀት ምክንያት በር ከፍተው እንደሚተኙ ሲገለፁ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹 የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው #የማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ። በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 1,500 ወንዶች ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 3000 መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ? - ቀን 5:05 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል…
#Paris2024

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ውድድር ዘጠነኛ ቀኑ ላይ ሲገኝ ዛሬ ሀያ የወርቅ ሜዳልያዎችን ለአሸናፊዎች የሚያሰጡ የፍፃሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

የኦሎምፒክ ሜዳልያ ሰንጠረዡን ቻይና በአስራ ስድስት የወርቅ ሜዳልያዎች በበላይነት እየመራች ትገኛለች።

አስራ አራት የወርቅ ሜዳልያ ያላት አሜሪካ በበኩሏ በአጠቃላይ ስልሳ አንድ ሜዳልያ ቀዳሚ መሆን ችላለች።

በኦሎምፒኩ በዛሬው ዕለት ከሚጠበቁ የፍፃሜ ውድድሮች መካከል የወንዶች ነጠላ ሜዳ ቴኒስ ፍፃሜ ውድድር ዋነኛው ነው።

ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት በሮላንድ ጋሮስ በሚደረገው ተጠባቂ የቴኒስ ፍፃሜ ኖቫክ ጆኮቪች ከካርሎስ አልካራዝ ለወርቅ ሜዳልያ ይፋለማሉ።

በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የሚካሄደው የ 100 ሜትር ወንዶች ፍፃሜ ሩጫ የዕለቱ ተጠባቂ ውድድር ነው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቻይና :- ( 16 ወርቅ ፣ 12 ብር እና 9 ነሐስ ሜዳልያ )

2️⃣ አሜሪካ :- ( 14 ወርቅ ፣ 24 ብር እና 23 ነሐስ ሜዳልያ )

3️⃣ ፈረንሳይ :- ( 12 ወርቅ ፣ 14 ብር እና 15 ነሐስ ሜዳልያ )

4️⃣ አውስትራሊያ :- ( 12 ወርቅ ፣ 8 ብር እና 7 ነሐስ ሜዳልያ )

5️⃣ ብሪታኒያ :- ( 10 ወርቅ ፣ 10 ብር እና 13 ነሐስ ሜዳልያ )

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ሜዳልያ ሰንጠረዡ በአንድ የብር ሜዳልያ ከአለም አርባ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ሳውዝሀምፕተን ለ 21ዓመቱ አማካይ ፋቢዮ ካርቫልሆ ያቀረበውን 15 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

ያለፈውን የውድድር ዘመን በውሰት በሁል ሲቲ ያሳለፈው ፋቢዮ ካርቫልሆ አሁን ላይ ወደ ቡድኑ በመመለስ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በአሜሪካ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ሊቨርፑል ፋቢዮ ካርቫልሆ በውሰት መስጠት እንደማይፈልጉ ሲገለፅ በቋሚነት ከሸጡት ግን ሳውዝሀምፕተን ካቀረበው የተሻለ ሒሳብ እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ፋቢዮ ካርቫልሆ በበኩሉ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ቋሚ ተሰላፊ የመሆን ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት ሎሚ ሙለታ በማጣሪያ ውድድሩ 9:10.73 በሆነ ሰዓት በመግባት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሲምቦ አለማየሁ እና ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ አልፈዋል።

በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈለችው አትሌት ሲምቦ አለማየሁ 9:15.42 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ ማለፍ ችላለች።

በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን ያደረገችው ሎሚ ሙለታ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ለፍፃሜ መድረሷ ይታወቃል።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Paris2024 ጃማይካዊቷ ታሪካዊ የ 100ሜትር ሯጭ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ከፓሪስ ኦሎምፒክ 100ሜትር ሩጫ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ውጪ ሆናለች። አምስተኛ እና የመጨረሻ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን በማድረግ ላይ የምትገኘው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በአምስት ተከታታይ ኦሎምፒክ ሜዳልያ በማግኘት ባለታሪክ መሆን ትችል ነበር። አትሌቷ በምን ምክንያት ከግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ውድድር ውጪ እንደሆነች በይፋ…
“ ውድድሩ ስላመለጠኝ በጣም አዝኛለሁ “ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ

ከ 100ሜትር ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ውጪ የነበረችው ጃማይካዊቷ ታሪካዊ ሯጭ ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ በውድድሩ ባለመካፈሏ ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማት ገልፃለች።

በውድድሩ ስትጠበቅ የነበረችው አትሌቷ ትላንት በተደረገው የ 100ሜ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ላይ ሳትሳተፍ መቅረቷ አይዘነጋም።

ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ከውድድሩ ውጪ የነበረችው ወደ ውድድሩ መግቢያ ሰዓት አርፍዳ ነው ቢባልም የጃማይካ ሀላፊዎች በጉዳት ምክንያት መሆኑን አሳውቀዋል።

“ ባለመሳተፌ የተሰማኝን ሀዘን የምገልፅበት ቃል የለኝም “ ስትል በማህበራዊ ትስስር ገጿ የገለፀችው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ደጋፊዎቼም እንደሚጋሩኝ አውቃለሁ ከጅምሩ በተደረገልኝ ድጋፍ እኮራለሁ " ብላለች።

የመጨረሻ ኦሎምፒክ ውድድሯን ያደረገችው ሼሊ አን ፍሬዘር ፕራይስ ትላንት ሜዳልያ ብታሳካ በአምስት ተከታታይ ኦሎምፒክ ሜዳልያ በማግኘት አዲስ ታሪክ ትፅፍ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 15:17:59
Back to Top
HTML Embed Code: