Telegram Web Link
" አላማችን ፕርሚየር ሊጉን ማሸነፍ ነው " ሉካስ ቤርግቫል

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ቤርግቫል ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር ዘመን የመጀመሪያ አላማው ፕርሚየር ሊጉን ማሸነፍ እንደሆነ ተናግሯል።

" በቀጣይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር መሳተፍ እንፈልጋለን " የሚለው ሉካስ ቤርግቫል የመጀመሪያው አላማችን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ ነው " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በቂ ዝግጅት ባናደርግም ነጥብ ላለመጣል እንጥራለን “ ፔፕ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በእረፍት ምክንያት ሙሉ ተጨዋቾቻቸውን ባለማግኘታቸው በቂ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እንዳላደረጉ ገልጸዋል።

" እኛ እንደ ሌሎቹ በቂ ዝግጅት ለማድረግ ጊዜ አላገኘንም " ያሉት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " በቂ ዝግጅት ባናደርግም በሊጉ ብዙ ነጥብ ላለመጣል እና ጥሩ ፉክክር ለማድረግ እንሞክራለን " ብለዋል።

" በኮሚኒቲ ሺልድ ከዩናይትድን ላለብን ብቻ ሳይሆን ፤ በሊጉ ከቼልሲ እና ከኢፕስዊች ታውን ጋር ለምናደርገው ጨዋታ በተመሳሳይ ዘግይተን ብንዘጋጅም ጥሩ ለመፎካከር እና ለማሸነፍ እንሞክራለን " ጋርዲዮላ

ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም " ወሳኝ ተጨዋቾቻችን የሉም ምክንያቱም እረፍት ማድረግ አለባቸው ፣ ሁሉም ሲመለሱ ጥሩ ቡድን ይኖረናል ፣ ባለፈው አመት ያደረግነውን ማሳካት እንችላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በፓሪሱ የ2024 ኦሎምፒክ ውድድር አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ በቅርጫት ኳስ ውድድር የምድብ ጨዋታ ጠንካራዋን አውስትራሊያ መርታት ችለዋል።

የናይጄሪያ ሴት ቅርጫት ኳስ ቡድን የአለም ቁጥር ሶስት ደረጃ ባለቤቷን አውስትራሊያ 75-62 በማሸነፍ ወሳኝ ድል አሳክቷል።

በፓሪሱ ኦሎምፒክ ውድድር የናይጄሪያ ሴት ቅርጫት ኳስ ቡድን ሁለተኛ የኦሎምፒክ ውድድር ተሳትፎውን እያደረገ ይገኛል።

የናይጄሪያ ሴት ቅርጫት ኳስ ቡድን በሀያ አመታት ውስጥ የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ድሉ ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኖቫክ ጆኮቪች ራፋኤል ናዳልን አሸነፈ !

ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ኖቫክ ጆኮቪች ስፔናዊውን ራፋኤል ናዳል በኦሎምፒክ የነጠላ ሜዳ ቴኒስ ጨዋታ በመርታት ሶስተኛውን ዙር ተቀላቅሏል።

ኖቫክ ጆኮቪች የአስራ አራት ጊዜ የፈረንሳይ ኦፕን ሻምፒዮኑን ራፋኤል ናዳል በሁለተኛው ዙር 6-1 እና 6-4 ማሸነፍ ችሏል።

የሀያ አራት ግራንድ ስላም የነጠላ ዋንጫ አሸናፊው ኖቫክ ጆኮቪች የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያውን ለማሸነፍ ይፋለማል።

ራፋኤል ናዳል በሮላንድ ጋሮስ ካደረጋቸው 117 ጨዋታዎች አምስተኛ ሽንፈቱን ሲያስተናግድ በሶስቱ የተሸነፈው በኖቫክ ጆኮቪች ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔊 ከዋናው ማዘዝ በጣም ቀላል ነው!

📲 በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
“ ሲቲ አምስተኛ ዋንጫውን እንዲያሸንፍ መርዳት እፈልጋለሁ “ ግቫርዲዮል

የማንችስተር ሲቲው የመስመር ተጨዋች ጆስኮ ግቫርዲዮል በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ቡድኑ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ መርዳት እንደሚፈልግ ተናግሯል።

“ በሚቀጥለው የውድድር አመት ማንችስተር ሲቲ ተከታታይ አምስተኛ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን እንዲያሸንፍ ለመርዳት ዝግጁ ነኝ።" ሲል ጆስኮ ግቫርዲዮል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የጁሊያን አልቫሬዝ የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ? አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ማንችስተር ሲቲን መልቀቅ እንደሚፈልግ ተገልጿል። ጁሊያን አልቫሬዝ እንዲሁም ቤተሰቡ የማንችስተር ከተማ አየር ንብረት እንዳልተስማማቸው እና ሞቃታማ የአየር ንብረት እንደሚመርጡ ተነግሯል። በተጨማሪም የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ የተሻለ የጨዋታ ሰዓታ ማግኘት እንደሚፈልግ ተዘግቧል።…
አልቫሬዝ የሲቲ ቆይታው ያልተረጋገጠ መሆኑን ገለጸ !

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ የማንችስተር ሲቲ የወደፊት ቆይታው ያልተረጋገጠ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ባለፈው አመት ብዙ የጨዋታ ጊዜ ማግኘቱን የገለፀው ጁሊያን አልቫሬዝ " ነገርግን በትልቅ ጨዋታዎች መጫወት እፈልጋለሁ ስለወደፊቱ ቆይታዬ ማሰቤን አላቆምኩም “ ብሏል።

“ የኦሎምፒክ ውድድር ሲጠናቀቅ የራሴን ጊዜ ወስጄ ወደፊት ስለምፈልገው ነገር አስባለሁ በቀጣይ ምን እንደሚፈጠር እንመለከታለን። “ ጁሊያን አልቫሬዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ከቦሎኛ ማስፈረማቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ በአርሰናል ቤት የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ በክለቡ የሰላሳ ሶስት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ይፋ ሆኗል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ የራሱን ክለብ ሊገዛ መሆኑ ተገለጸ ! ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በቀጣይ የራሱን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማቀዱ ተገልጿል። ኪሊያን ምባፔ እና ቤተሰቡ በቀጣይ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ኮን እግርኳስ ክለብ ለመግዛት ማሰባቸው ተነግሯል። ምባፔ በልጅነቱ ተጫውቶበት እንደነበር የተገለፀው ክለቡ በአሁን ሰዓት በፈረንሳይ ሊግ ሁለት ሲወዳደር ባለፈው…
ምባፔ የእግርኳስ ክለብ ባለቤት ሊሆን ተቃርቧል !

ፈረንሳዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በእድሜ ትንሹ የእግርኳስ ክለብ ባለቤት የሆነ ተጨዋች ለመሆን መቃረቡ ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ በፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ኮን እግርኳስ ክለብ በ20 ሚልዮን ዩሮ ለመግዛት መስማማቱ ተነግሯል።

ምባፔ የክለቡን ከፍተኛ ድርሻ እንደሚገዛ ሲገለፅ በተጨማሪም የክለቡን የተወሰነ እዳ እንደሚከፍል ታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል በይፋ ተጨዋች አስፈረመ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል። መድፈኞቹ ተጫዋቹን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ከቦሎኛ ማስፈረማቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በአርሰናል ቤት የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ በክለቡ የሰላሳ ሶስት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ይፋ ሆኗል። @tikvahethsport    …
“ መጫወት እንጂ ብዙ ማውራት አልወድም “ ካላፊዮሪ

አርሰናልን በይፋ የተቀላቀለው ጣልያናዊው ተከላካይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በመጨረሻም መድፈኞቹን በመቀላቀሉ ልዩ ስሜት እንደተሰማው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

“ ብዙ ውጣውረዶች ነበሩ በመጨረሻም እዚህ ነኝ ልዩ ስሜት እየተሰማኝ ነው “ ሲል ስሜቱን የገለፀው ተጨዋቹ ቡድኑን ተቀላቅዬ አስከምጫወት ጓጉቻለሁ ብሏል።

የአርሰናል እቅድ ለእኔ ትክክለኛው መሆኑን አምናለሁ የሚለው ሪካርዶ ካላፊዮሪ የትልቅ ነገር መጀመሪያ ነው ለአርሰናል በመጫወት ዋንጫ ለማሸነፍ ተዘጋጅቻለሁ ሲል ተደምጧል።

ስለ አጨዋወት ዘይቤው ሀሳብ እንዲሰጥ በጋዜጠኞች የተጠየቀው ሪካርዶ ካላፊዮሪ " ብዙ መናገር አልፈልግም መጫወት እንጂ ማውራት አልወድም ፣ ምን ማድረግ እንደምችል ሜዳ ላይ ይጠብቁ ያዩታል “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጂዮርጂዮ ቼሊኒ የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል !

ጣልያናዊው የቀድሞ ታሪካዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጂዮርጂዮ ቼሊኒ የቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ትምህርቱን ተከታትሎ የማስተርስ ዲግሪውን መያዙ ተገልጿል።

በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ለሎስ አንጀለስ ሲጫወት የነበረው ጂዮርጂዮ ቼሊኒ በቅርቡ በ39ዓመቱ ጫማውን መስቀሉ አይዘነጋም።

ጂዮርጂዮ ቼሊኒ በአሁን ሰዓት በአሜሪካው ክለብ ሎስ አንጀለስ አሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ተቀላቅሎ የክለቡ “ Player Development Coach “ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Sparta Prague - Shamrock Rovers
TNS - Ferencvaros
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር አራተኛ ቀን ውሎ ዛሬም ሲቀጥል አስራ ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ይበረከታሉ።

በሶስተኛው ቀን ውሎ ጃፓን የወርቅ ሜዳልያ ቁጥሯን ወደ ስድስት ከፍ በማድረግ የሜዳልያ ሰንጠረዡን መምራቷን ቀጥላለች።

በሜዳልያ ብዛት አሜሪካ አጠቃላይ ሃያ ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ስትሆን አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ አስራ ስድስት ሜዳልያዎች በማግኘት ትከተላለች።

ዛሬ ከሚደረጉት የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድሮች መካከል የሴቶች ራግቢ ውድድር ግማሽ ፍፃሜ እና ፍፃሜ ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት በዋና ፣ በሴቶች ዳይቪንግ ፣ በቴብል ቲኒስ ፣ ሴቶች ራግቢ፣ ሹቲንግ፣ ሰርፊንግ እና የሴቶች ጂምናስቲክ ለሜዳልያ ከሚደረጉት ውድድሮች መካከል ዋነኞቹ  ናቸው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጃፓን :-🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥉🥉🥉🥉

2️⃣ፈረንሳይ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉🥉

3️⃣ ቻይና :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉

4️⃣  አውስትራሊያ :- 🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈

5️⃣ ደቡብ ኮርያ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥉

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮነር ጋላገር ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ?

የስፔኑ ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮነር ጋላገር ለማስፈረም ከቼልሲ ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከተጨዋቹ ዝውውር እስከ 40 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ መጠየቃቸው ተነግሯል።

በአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የሚመሩት አትሌቲኮ ማድሪች ኮነር ጋላገር ለማስፈረም ቅድሚያ ሰጥተው በመስራት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ሰማያዊዎቹ በቅርቡ ከአስቶን ቪላ ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረውን ኮነር ጋላገርን ከእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውጪ ላለ ክለብ መሸጥ እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ቤን ቺል ዌልን መሸጥ ይፈልጋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለእንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ቤን ቺል ዌል ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ከቀረበ መሸጥ እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ቤን ቺል ዌል ከአዲሱ አሰልጣኛቸው ኢንዞ ማሬስካ የአጨዋወት ዘይቤ ጋር ላይጣጣም ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ተነግሯል።

ቼልሲ የግራ መስመሩን ለማጠናከር የሊቼውን የ 19ዓመት ተጨዋች ፓትሪክ ዶርጉ በመመልከት ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

በተጨማሪም ቼልሲዎች አሬማንዶ ብሮሀ ፣ ዴቪድ ፎፋና እና ሴሳር ካሳዴይን ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ካገኙ እንደሚሸጧቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ እና ናፖሊ በንግግር ላይ ናቸው !

የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር በድርድር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በተቃራኒው ቼልሲዎች በበኩላቸው ናይጄሪያዊውን አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ከናፖሊ ለማስፈረም በድርድር ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ቼልሲዎች ቪክቶር ኦሲሜንን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የረጅም ጊዜ ውሰት ውል እንደሚያስፈርሙት ሲገለፅ ናፖሊ በበኩሉ ሮሜሎ ሉካኩን በቋሚነት እንደሚያስፈርሙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 01:27:14
Back to Top
HTML Embed Code: