Telegram Web Link
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ተለያይቷል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂያቸው ቺዶ ኦቢ ማርቲን በክለቡ ውሉን እንደማያራዝምና ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ አሳውቀዋል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቺዶ ኦቢ ማርቲን በማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሌሎች ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

ባለፈው አመት በአርሰናል አካዳሚ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ተጨዋቹ በቀጣይ በነፃ ዝውውር የሚቀላቀለውን ክለብ እንደሚያሳውቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩኤፋ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አደረገ ! የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ከቀናት በፊት በማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ሮድሪ እየተመሩ ያሰሙትን ዝማሬ እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጿል። ዩኤፋ ምርመራውን የከፈተው ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማድሪድ ውስጥ በምታክብርበት ወቅት ተጨዋቾቹ " ጂብላርታር ስፔን ነው " እያሉ እንግሊዞች ላይ ቀልደዋል በሚል መሆኑ ተነግሯል። በሰዓቱ ሮድሪ…
ሮድሪ እና ሞራታ ክስ ቀረበባቸው !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች የሆኑት ሮድሪ እና አልቫሮ ሞራታ ላይ ክስ ማቅረቡን አስታውቋል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ከዩኤፋ ክስ የቀረበባቸው ባለፈው ሳምንት ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን በምታከብርበት ወቅት ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ዩኤፋ አሁን ላይ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ተጨዋቾች ላይ ካቀረበው ክስ ውስጥ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለሌላ ስፖርታዊ ያልሆነ አላማ በማዋል የሚል ይገኝበታል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዲሲፕሊን ኮሚቴ በቀጣይ በተጨዋቾቹ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተያይዞ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማድሪድ ውስጥ በምታክብርበት ወቅት " ጂብላርታር ስፔን ነው " እያሉ በመዘመራቸው ምክንያት ቅሬታዎች ሲቀርቡባቸው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዴቪድ ዴህያ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለታል ! ባለፈው አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ የሚገኘው ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ አሁን ላይ የዝውውር ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተገልጿል። ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ ከቀያይ ሴጣኖቹ ጋር የተለያየው ዴቪድ ዴህያ ከሳውዲ አረቢያ እና አሜሪካ በርካታ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተነግሯል። በተጨማሪም ዴቪድ ዴህያ ከጣልያን ሴርያ…
ዴቪድ ዴህያ በኤሪክ ቴንሀግ መናደዱ ተገለጸ !

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ ማንችስተር ዩናይትድን ለመልቀቁ ምክንያት ናቸው ባላቸው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና የቀድሞ የክለቡ ሀላፊ ጆን ሙርታፍ መናደዱ ተገልጿል።

ዴቪድ ዴህያ ሁለቱ ግለሰቦች በክለቡ ከሌሉ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ቢመለስ ደስተኛ እንደሚሆን ለእሱ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች መናገሩም ተጠቁሟል።

ዴህያ በቀጣይ አዲስ ክለብ መቀላቀል ቢፈልግም ከማንችስተር ዩናይትድ ውጪ ለእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብ ተሰልፎ መጫወት እንደማይፈልግ መግለፁ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ከፍተኛ ገቢ ማግኘቱን አሳወቀ !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ በተጠናቀቀው የ2023/24 የውድድር ዘመን ከአንድ ቢሊዮን ዩሮ በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድረጓል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የተጨዋቾች የዝውውር ገቢን ሳይጨምር ባለፈው አመት 1.073 ቢሊዮን ዩሮ ትርፍ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

የዘንድሮው ገቢያቸው ካለፈው አመት ገቢ በሀያ ሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን ያሳወቁት ሎስ ብላንኮዎቹ አንድ ቢልዮን ገቢ ያገኘ በታሪክ የመጀመሪያው እግርኳስ ክለብ መሆንም ችለዋል።

የላሊጋ እና ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ ባለፈው አመት ከቴሌቪዥን መብት እንዲሁም በስታዲየሙ ከተዘጋጁ ፕሮግራሞች ከፍተኛ ጊቢ ማግኘቱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞሪንሆ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በድል አጠናቀዋል !

የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ በፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ እየተመራ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጥሎ ማለፍ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከስዊዘርላንዱ ሉጋኖ ክለብ ጋር ያደረገው ፌነርባቼ 4ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

በጨዋታው የቀድሞ የሮማ ታሪካዊ ተጨዋች ኤዲን ዤኮ ለፌነርባቼ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ መስራት ችሏል።

የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በፌነርባቼ ሜዳ የሚደረግ ሲሆን በድምር ውጤት አሸናፊው በቀጣይ ዙር ከሊል ጋር ይገናኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
🔸MacBook Air, M1
256GB/ 8GB
137 CYcle Count
79,000 birr

🔹MacBook Pro, M1
512GB/ 8GB
407 CYcle Count
69,000 birr

Contact Us
0953964175 @heymobile
0925927457

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Uzbekistan Ol. - Spain Ol.
France Ol. - USA Ol
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" በኤደርሰን ቆይታ እርግጠኛ አይደለሁም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን የክለቡ የወደፊት ቆይታ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ለቅድመ ውድድር ዝግጅት አሜሪካ የገባው ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ሌሊት ከሴልቲክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን አድርጎ 4ለ3 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " ኤደርሰን በማንችስተር ሲቲ መቆየት አለመቆየቱ ላይ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ከውሳኔ መድረስ አለበት " ብለዋል።

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ኤደርሰንን ለማስፈረም በጥረት ላይ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን ለመሸጥ ከ50 ሚልዮን ፓውንድ በላይ እንደሚፈልግ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ ያለሁት ለዋንጫ ለመፎካከር ነው " ኢንዞ ማሬስካ

አዲሱ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ክለቡን የተረከቡት እንደሌሎቹ ሁሉ ለዋንጫ ለመፎካከር መሆኑን ገልጸዋል።

" እዚህ ያለሁት ዋንጫ ማሸነፍን አላማ በማድረግ ነው " ያሉት ኢንዞ ማሬስካ " ቼልሲን ስትረከብ ዋንጫ ማሸነፍ ካልሆነ ቢያንስ መፎካከር አለብህ ፣ መቼ እነደሆነ አላውቅም በፍጥነት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ " ብለዋል።

የኢንዞ ፈርናንዴዝን ጉዳይ ያነሱት አሰልጣኙ " ፈርናንዴዝ ይቅርታ መጠየቁ ጥሩ ነገር ነው ክለቡም በተመሳሳይ የምጨምረው የለም ሁሉም ግልጽ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ ሲመለስ ከባድ ይሆናል የሚል እምነት የለኝም ፣ ማንም መጥፎ ሀሳብ ያለው የለም ምንም ችግር ቢኖር በክለቡ እና ተጨዋቾች ይስተካከል።" ኢንዞ ማሬስካ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኦሎምፒክ እግርኳስ ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ !

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የፊታችን አርብ በይፋዊ ስነ ስርዓት ከመጀመሩ አስቀድሞ በዛሬው ዕለት የኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር ጅማሮውን ያደርጋል።

በኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር በወንዶች አስራ ስድስት እንዲሁም በሴቶች አስራ ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች በምድብ ተከፋፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በዛሬው ዕለት ሁሉም የወንዶች ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን ማድረግ ሲጀምሩ የሴቶች ውድድር ነገ የሚጀምር ይሆናል።

የወንድ ብሔራዊ ቡድኖች ከሶስት ተጨዋቾች ውጪ ያሉ ተጨዋቾቻቸው ከ 23ዓመት በታች መሆን ሲጠበቅባቸው በሴቶቹ የእድሜ ገደብ እንደሌለው ተገልጿል።

ብራዚላዊቷ ታሪካዊ የፊት መስመር ተጨዋች ማርታ በኦሎምፒክ ሀገሯን በአምበልነት ከመራች በኋላ በይፋ ጫማዋን ትሰቅላለች።

ማርታ በአምስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ግብ በማስቆጠር የመጀመሪያዋ እግርኳስ ተጨዋች ስትሆን በመድረኩ የወርቅ ሜዳልያ ለማሳካት የመጨረሻ ሙከራዋን ታደርጋለች።

አፍሪካ በዘንድሮው የኦሎምፒክ ውድድር በወንዶች በጊኒ ፣ ሞሮኮ ፣ ግብፅ እና ማሊ እንዲሁም በሴቶች በዛምቢያ እና ናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድኖች ትወከላለች።

*የዛሬ መርሐ ግብሮች ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዘዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል !

ኢትዮጵያን በካፍ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ማጣሪያ ውድድር የሚወክለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የማጣርያ የምድብ ተጋጣሚዎቹን አውቋል።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምድብ አንድ ከኬንያ ፖሊስ ቡሌት ፣ ዬ ጆይንት ስታርስ ( ደቡብ ሱዳን ) ፣ ዋርየርስ ክዊንስ ( ዛንዚባር ) እና ራዮን ስፖርት ( ሩዋንዳ ) ጋር ተደልድሏል።

የዘንድሮው የሴካፋ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር በሀገራችን ኢትዮጵያ አዘጋጅነት አዲስ አበባ ላይ እንደሚደረግ ይታወቃል።

የውድድሩ አሸናፊ ክለብ ምስራቅ አፍሪካን በመወከል በቀጣዩ የካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።

ውድድሩ ከነሐሴ 11/2016 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29/2016 ዓ. ም በአዲስ አበባ እና አበበ ቢቂላ ስታዲየሞች ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሬስ ኔልሰን ወደ ሌስተር ሲቲ ?

ወደ ፕርሚየር ሊግ የተመለሰው ሌስተር ሲቲ እንግሊዛዊውን የአርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ሬስ ኔልሰን ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሌሴተር ሲቲ ተጫዋቹን የመግዛት ግዴታ ባካተተ የውሰት ውል ለማስፈረም ከአርሰናል ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

በአርሰናል ቤት ብዙም የመጫወት እድል ያላገኘው የ 24ዓመቱ ተጨዋች ሬስ ኔልሰን ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈለግ ሲነገር ነበር።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሪያል ማድሪድ ለናቾ ይፋዊ ሽኝት ያዘጋጃል ! ሪያል ማድሪድ ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ ክለቡን ለለቀቀው ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ ይፋዊ ሽኝት እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል። ሎስ ብላንኮዎቹ የፊታችን እሮብ በልምምድ ማዕከላቸው ቫልዴቤባስ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በተገኙበት ለታሪካዊ ተጨዋቻቸው ናቾ ሽኝት እንደሚያደርጉ ተነግሯል። ናቾ በሪያል ማድሪድ ቤት ሶስት መቶ ስልሳ…
ናቾ ፈርናንዴዝ ሪያል ማድሪድን ተሰናብቷል !

ከሀያ ሶስት አመታት በኃላ ከሪያል ማድሪድ ጋር የተለያየው ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ በሎስ ብላንኮዎቹ ይፋዊ ሽኝት ተደርጎለታል።

በይፋዊ ሽኝቱ ላይ ንግግር ያደረገው ናቾ የሪያል ማድሪድን ሀላፊዎች ፣ አሰልጣኞች ፣ የቡድን አጋሮቹን እና የክለቡን ሰራተኞች ማመስገን እንደሚፈልግ ገልጿል።

" እኔን ከሪያል ማድሪድ አካዳሚ ተነስቶ ሁሉንም ነገር ለማሸነፍ ሁሉንም ነገሩን የሰጠ ተጨዋች አድርጋችሁ እንድታስታውሱኝ እፈልጋለሁ " ሲል ናቾ በእምባ ታጅቦ ተናግሯል።

በሽኝቱ ላይ የተገኙት የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በበኩላቸው " ዛሬ ለሪያል ማድሪድ አሳዛኝ ቀን ነው " ሲሉ የገለፁ ሲሆን " ምክንያቱም ሁሉንም ነገሩን የሰጠን ተጨዋች ከእኛ ጋር ተለያይቷል " ብለዋል።

ናቾ ፈርናንዴዝ በሪያል ማድሪድ በቆየባቸው ስኬታማ ሀያ ሶስት አመታት ሀያ ስድስት ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።

የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ ናቾ ከሳምንታት በፊት ከሪያል ማድሪድ በመልቀቅ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ በሁለት አመት ኮንትራት በይፋ መቀላቀሉ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ግብ ጠባቂ ማስፈረም ይፈልጋል ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ ተጨማሪ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በመመልከት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመሩት ሰማያዊዎቹ በአሁን ሰዓት የ 22ዓመቱን የቪያሪያል ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ሆርጌንሰንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ተነግሯል። ቼልሲ የግብ ጠባቂውን ዝውውር የሚያጠናቅቁ ከሆነ ያለፈውን አመት በውሰት በሪያል ማድሪድ…
ቼልሲ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ተቃርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የቪያሪያሉን ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ሆርጌንሰን ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ዴንማርካዊውን ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ሆርጌንሰን ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ለስምምነት መቃረባቸው እና ተጨዋች ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል።

ቼልሲዎቹ ግብ ጠባቂውን ከ20 እስከ 25 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት ለማስፈረም ከክለቡ ጋር በመደራደር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Update አርሰናሎች ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ማስፈረም ከጣልያኑ ክለብ ቦሎኛ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ተጫዋቹን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር መስማማታቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ ከእረፍት በተመለሰ በኋላ ለክለቡ ቦሎኛ ሀላፊዎች አርሰናልን በመቀላቀል ህልሙን እንዲያሳካ እንዲለቁት ጥያቄ ማቅረቡ ተዘግቧል።…
አርሰናል የካላፊዮሪን ዝውውር ሊያጠናቅቁ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚያስችላቸው ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ሲገለፅ በቀጣይ የህክምና ምርመራ እና ፊርማ ብቻ እንደሚቀራቸው ተነግሯል።

በቀጣይ አርሰናል ሁሉም በእቅዳቸው መሰረት ከሄደ ተጫዋቹ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በአሜሪካ የሚገኘውን የቡድኑ ስብስብ እንዲቀላቀል ማሰባቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📢 #ዋናው የስፖርት አልባሳትን ማዘዝ እጅግ ቀላል ነው!

📞 ለመረጃና ትዕዛዝ በስልክ ቁጥሮች 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

📌 በተጨማሪም ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ በሚገኘው ማሳያ ቦታችን በአካል በመምጣት ይዘዙን።

#ዛሬውኑ ይዘዙን፣ የስፖርት ፍቅርዎን ምቾት፣ ጥራትና ውበትን ባዘሉ ኢትዮጵያዊ አልባሳት ከፍ ያድርጉት!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/10/04 11:25:06
Back to Top
HTML Embed Code: