Telegram Web Link
ካናዳ ተጋጣሚዋን በመሰለል ቅሬታ ቀረበባት !

የካናዳ ሴቶች እግርኳስ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት በኦሎምፒክ መክፈቻ ጨዋታ የሚገጥመውን የኒውዝላንድ አቻው በመሰለል ቅሬታ እንደቀረበበት ተገልጿል።

የኒውዝላንድ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባለፈው ሰኞ የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ ሲያደርገው የነበረውን ልምምድ በድሮን ሊሰልሉ ሞክረዋል በማለት ለፈረንሳይ ፖሊስ ማሳወቁ ተነግሯል።

ድሮኑን ሲጠቀሙ የነበሩ ሰራተኞች በፖሊስ መያዛቸው ሲገለፅ የወቅቱ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ካናዳም ተጋጣሚዋን በይፋ ይቅርታ መጠየቋ ተዘግቧል።

በተጨማሪም የካናዳ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተጠያቂ ያላቸውን ሁለት የኦሎምፒክ ልዑክ ቡድኑ አባላትን ወደ ቤታቸው መመለሱን አስታውቋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የኦሎምፒክ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ነገ ምሽት 12:00 ሰዓት የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አርሰናል በቅርቡ ትልቅ ነገር ያሳካል " ዚንቼንኮ

ዩክሬናዊው የመድፈኞቹ የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር ዚንቼንኮ አርሰናል በትክክለኛው መንገድ ላይ እየተጓዘ እንደሚገኝ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" አርሰናል በትክክለኛው መንገድ ላይ ነው " የሚለው አሌክሳንደር ዚንቼንኮ በቅርቡ ትልቅ ጥሩ ነገሮችን ማሳካት ይችላል የሚል ትልቅ እምነት ነው ያለኝ በማለት ተናግሯል።

" ማንችስተር ሲቲን መምሰል ያለብን አይመስለኝም እነሱ በአሁን ሰዓት የአለም ምርጥ ቡድን ሊሆኑ ይችላሉ ነገርግን እኛ ምርጥ ለመሆን እንጂ እነሱን ለመምሰል መስራት የለብንም።" ዚንቼንኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ወደ አሜሪካ የሚያመራውን ስብስብ አሳውቋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ ይዞ የሚጓዘውን የቡድን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ቡድን ስብስብ ውስጥ ተካቷል።

ከረጅም ጊዜ ጉዳት የተመለሰው ማላሽያ በካሪንግተን በመቆየት ከህክምና ቡድኑ ጋር ዝግጅቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ራስሙስ ሆይሉንድ በሚቀጥለው የውድድር አመት የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ParisOlympics2024

የፓሪስ ኦሎምፒክ እግርኳስ ጨዋታዎች ሲጀምሩ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ከአርጀንቲና አቻው ጋር ያደረጉትን የመክፈቻ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሞሮኮን ግቦች ሶፍያን ራሂሚ 2x ከመረብ ሲያሳርፍ ለአርጀንቲና የአቻነት ግቦች ጅዩሊያኖ ሲሞን እና ክርስቲያን ሜዲና አስቆጥረዋል።

በጨዋታው አስራ አምስት የባከኑ ደቂቃዎች ሲጨመሩ አርጀንቲና በመጨረሻ ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጥራ ነጥብ ተጋርታለች።

በሌላ ጨዋታ የስፔን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የኡዝቤክስታን አቻውን በማርክ ፑቢል እና ሰርጂዮ ጎሜዝ ግቦች 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#ParisOlympics2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ እግርኳስ ጨዋታዎች ሲጀምሩ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ከአርጀንቲና አቻው ጋር ያደረጉትን የመክፈቻ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። የሞሮኮን ግቦች ሶፍያን ራሂሚ 2x ከመረብ ሲያሳርፍ ለአርጀንቲና የአቻነት ግቦች ጅዩሊያኖ ሲሞን እና ክርስቲያን ሜዲና አስቆጥረዋል። በጨዋታው አስራ አምስት የባከኑ ደቂቃዎች ሲጨመሩ አርጀንቲና በመጨረሻ ደቂቃ የአቻነት…
የአርጀንቲናን ግብ ከሰዓታት በኋላ በቫር ተሻረ !

ከሁለት ሰዓታት በፊት ሁለት አቻ እንደተጠናቀቀ የተገለፀው የአርጀንቲና እና ሞሮኮ የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ጨዋታ ከሰዓታት በኋላ በዳኛው አዲስ ውሳኔ ተላልፎበታል።

ዋና ዳኛው አርጀንቲና 116ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረችውን የአቻነት ግብ በቫር ተመልክተው ከጨዋታ ውጪ በሚል ሽረውታል።

በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የሞሮኮ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ መግባታቸውን ተከትሎ ዋና ዳኛው ጨዋታውን በይፋ አለማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ የተቆጠረውን አጨያያቂ ግብ ተከትሎ ዋና ዳኛው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጡ ተጨዋቾቹ በመልበሻ ክፍል ለሰዓታት ሲጠብቁ ነበር።

ዋና ዳኛው የአርጀንቲናን የጨዋታ ውጪ ግብ ሽረው ተጨማሪ ሶስት ደቂቃዎች ያጫወቱ ሲሆን በመጨረሻም ጨዋታው በሞሮኮ 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ተጨዋቾቹ እንዲጠብቁ የተደረገው የአርጀንቲና ግብ በቫር ታይቶ ከጨዋታ ውጪ ከሆነ ሶስት ደቂቃ ለመጫወት ሲሆን ትክክለኛ ግብ ከሆነ ጨዋታው እንደተጠናቀቀ ሊመዘገብ እንደነበር ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአርጀንቲናን ግብ ከሰዓታት በኋላ በቫር ተሻረ ! ከሁለት ሰዓታት በፊት ሁለት አቻ እንደተጠናቀቀ የተገለፀው የአርጀንቲና እና ሞሮኮ የኦሎምፒክ የመጀመሪያ ጨዋታ ከሰዓታት በኋላ በዳኛው አዲስ ውሳኔ ተላልፎበታል። ዋና ዳኛው አርጀንቲና 116ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረችውን የአቻነት ግብ በቫር ተመልክተው ከጨዋታ ውጪ በሚል ሽረውታል። በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ የሞሮኮ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ መግባታቸውን…
" የማይታመን ነው " ሊዮኔል ሜሲ

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የአቻነት ግብ ከሁለት ሰዓታት በኋላ በቫር ከጨዋታ ውጪ በሚል መሻሩን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ በሰጠው አስተያየት " በህይወት ዘመኔ ካየኋቸው የማይታመኑ ትርኢቶች ሁሉ ትልቁ ነው " ሲል ገልጿል።

ማሼራኖ ቀጥሎም " ትላንት ዝርፊያ ተፈፀሞብን ነበር ፣ ዛሬ ሰባት ጊዜ ሜዳውን ጥሰው ገብተዋል ተቀጣጣይ ነገርም ሲወረውሩብን ነበር " ሲሉ ቅሬታውን አቅርቧል።

ጨዋታው በአቻ ውጤት እንደተጠናቀቀ ተነግሯቸው እንደነበር የገለፀው አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ “ ተጋጣሚያችን ሞሮኮ እንኳን መጫወት አልፈለገችም ነበር “ ሲል ተናግሯል።

የአርጀንቲና ዋናው ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በበኩሉ " የማይታመን ነው " ሲል በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፁ ሁኔታውን ገልፆታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
CFR Cluj (Rou) - Neman (Blr)
Braga - Maccabi Petah Tikva
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" ስሚዝ ሮው ያልገባው የሚፈፅመው ነገር ስላለ ነው  " አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከሰዓታት በፊት በአሜሪካ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ በመለያ ምት 5ለ4 ማሸነፍ ችሏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ " ስሚዝ ሮው የሚፈፅመው ነገር ስላለ በጨዋታው አለማሳተፍ መርጠናል " ሲሉ ተደምጠዋል።

መድፈኞቹን እንደሚለቅ የሚጠበቀው የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ኤሚል ስሚዝ ሮው አሁን ላይ ፉልሀምን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።

አርሰናል ከተጨዋቹ ዝውውር 35 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያገኙ ሲገለፅ ሽያጩ የፉልሀምን የተጨዋች ግዢ ሪከርድ እንደሚሰብር ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

ሪያል ማድሪድ የፈረንሳዊውን የግራ መስመር ተጨዋች ፌርላንድ ሜንዲ ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ተጨዋቹ በሪያል ማድሪድ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ አዲስ የሶስት አመት ውል ለመፈረም መስማማቱ ተነግሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ካናዳዊውን የባየር ሙኒክ የመስመር ተጨዋች አልፎንሶ ዴቪስ የሚያስፈርሙ ከሆነ ፌርላንድ ሜንዲ ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲገለፅ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል የካላፊዮሪን ዝውውር ሊያጠናቅቁ ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል። መድፈኞቹ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚያስችላቸው ሙሉ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ሲገለፅ በቀጣይ የህክምና ምርመራ እና ፊርማ ብቻ እንደሚቀራቸው ተነግሯል። በቀጣይ አርሰናል ሁሉም በእቅዳቸው መሰረት ከሄደ ተጫዋቹ…
ካላፊዮሪ ዝውውሩን አሜሪካ ውስጥ ያጠናቅቃል !

አርሰናልን ለመቀላቀል ሙሉ ስምምነት ላይ የደረሰው ጣልያናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ የመጀመሪያ የህክምና ምርመራውን ለንደን እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በመቀጠልም መድፈኞቹ የመጨረሻ ህክምናውን አሜሪካ ውስጥ በማድረግ የአምስት አመት ኮንትራት እንዲፈርም እቅድ መያዛቸው ተነግሯል።

በቀጣይ ተጫዋቹ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት በአሜሪካ የሚገኘውን የቡድኑ ስብስብ ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

ለሀያ አራተኛ ጊዜ የሚደረገው የ 2017ዓ.ም የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ህዳር 8/2017ዓ.ም የተሳታፊ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።

ቀጣዩ የ 2017ዓ.ም የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የታሳታፊ ቁጥሩን ከዚህ በፊት ከነበረው 45,000 ወደ 50,000 ከፍ በማድረግ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዘንድሮው የ2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሉሲ ( ድንቅነሽ ) የተገኘችበት 50ኛ አመት ክብረ በዓል ተያይዞ እንደሚከበር ተነግሯል።

የሩጫው 30,000 ማልያዎች ከወዲሁ ለድርጅቶች መሸጣቸውን እና ቀሪ 20,000 ቲሸርቶች ብቻ መቅረታቸውን አዘጋጆቹ በዛሬው ዕለት አሳውቀዋል።

ምዝገባ ከነገ ጀምሮ በቴሌ ብር እንዲሁም በዳሽን ባንክ ስድስት የተመረጡ ቅርንጫፎች በይፋ እንደሚጀመር ተያይዞ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤደርሰን ኦርቴጋ ያገኘው ውዳሴ አላስደሰተውም ተባለ !

ማንችስተር ሲቲን መልቀቅ የሚፈልገው ኤደርሰን በክለቡ ላለመቆየት ተፅዕኖ ያሳደረበት አንዱ ኦርቴጋ የሰን ሁንግ ሚንን የግብ ሙከራ አድኖ ያገኘው ከፍተኛ ውዳሴ መሆኑ ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም በነበራቸው ወሳኝ የሊግ ጨዋታ ስቴፋን ኦርቴጋ ከሰን ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ከፍተኛ አድናቆት ያስገኘለትን ሊቆጠር የተቃረበ የግብ ሙከራ ማዳኑ አይዘነጋም።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በተለይም የማንችስተር ሲቲ ደጋፊዎች ኤደርሰን ቢሆን አይመልሰው ነበር የሚሉ አስተያየቶች መስጠታቸው ተፅዕኖ እንዳሳደረበት ተነግሯል።

ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲን የሚለቅ ከሆነ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስቴፋን ኦርቴጋን የቡድኑ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እዚህ ያለሁት ከባርሴሎና ጋር ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው " ሀንሲ ፍሊክ

ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በቀጣይ ከባርሴሎና ጋር ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚፈልጉ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" እዚህ ያለሁት ከባርሴሎና ጋር ዋንጫዎችን ለማሸነፍ ነው " ያሉት አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የእኔ የአጨዋወት ፍልስፍና ከባርሴሎና ጋር አይራራቅም ኳስ ተቆጣጥሮ መጫወትን እመርጣለሁ ብለዋል።

" ልምምድ ከጀመርን የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጠንክረን ሰርተናል እያንዳንዱ ተጨዋች ያለውን ሁሉ ለመስጠት ይፈልጋል ታዳጊ የአካዳሚ ተጨዋቾች ጥራት አስደናቂ ነው።" ሀንሲ ፍሊክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጁሊያን አልቫሬዝ የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ?

አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ማንችስተር ሲቲን መልቀቅ እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ጁሊያን አልቫሬዝ እንዲሁም ቤተሰቡ የማንችስተር ከተማ አየር ንብረት እንዳልተስማማቸው እና ሞቃታማ የአየር ንብረት እንደሚመርጡ ተነግሯል።

በተጨማሪም የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ የተሻለ የጨዋታ ሰዓታ ማግኘት እንደሚፈልግ ተዘግቧል።

ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ተጨዋቱ የሚለቅ ከሆነ ለዝውውሩ ከ70 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚፈልግ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
እስማኤል ሳር ወደ ፓላስ ለማምራት ተስማማ ! የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር ከማርሴይ ለማስፈረም በግል ከተጨዋቹ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል። ማርሴይ ክሪስታል ፓላስ ያቀረበውን የመጀመሪያ ሒሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ሲገለፅ በሁለቱ ክለቦች መካከል ንግግሮች መቀጠላቸው ተዘግቧል። ማርሴይ እስማኤል ሳርን ባለፈው አመት ከሻምፒዮን ሽፑ ክለብ ዋትፎርድ…
ክሪስታል ፓላስ ጥያቄው በማርሴ ተቀባይነት አገኘ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር ለማስፈረም ከማርሴይ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።

ክሪስታል ፓላስ ተጫዋቹን ለማስፈረም ያቀረበው 15 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ በማርሴይ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በግል ከስምምነት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ የህክምና ምርመራውን ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው × ስፖርትን ከኛ ጋር 🇪🇹

💪🏾 ስፖርት፣ አነቃቂ ተዝናኖት፣ ጤናማ እንቅስቃሴ! 💪🏾

👉🏾 እርሶስ ምን ይጠብቃሉ? ጥራትና ውበትን የተላበሱ #የዋናው የጂምና የስፖርት እንቅስቃሴ አልባሳትን ይሸምቱ፣ #ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
2024/10/04 07:33:58
Back to Top
HTML Embed Code: