Telegram Web Link
የእንግሊዝ ደጋፊዎች እንዲጠነቀቁ ጥሪ ቀረበላቸው !

ከሰዓታት በኋላ ተጠባቂ የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት እንግሊዝ እና ኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ፀብ ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

ጨዋታው በሚደረግበት ዶርትመንድ ከተማ ከ100,000 በላይ የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች እንደሚገኙ ተነግሯል።

የኔዘርላንድ ደጋፊዎች ከጨዋታው አስቀድሞ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ፀብ ውስጥ መግባታቸውን እና ትንኮሳ ማድረጋቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ተዘዋውሯል።

በስፍራው የፀጥታ ስራውን በማገዝ ላይ የሚገኙ የዩናይትድ ኪንግደም ፖሊሶች የኔዘርላንድ ደጋፊዎች የእንግሊዝ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት ለማድረስ እየሞከሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አምስት የእንግሊዝ ደጋፊዎች መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠማቸው ሲገለፅ ሌሎች ደጋፊዎች ያሉበትን ቦታ እንዲያውቁ እና በአካባቢያቸው የጀርመን ፖሊሶች መኖራቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ እና ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድሮች የሚሳተፉት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚያቸውን የሚያውቁበት ቀን ታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ የውድድሮቹ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚዎች በነገው ዕለት ግብፅ ካይሮ በሚደረግ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በምድብ ድልድሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቋት አንድ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና በቋት ሁለት ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኔዘርላንድ ከ እንግሊዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አጥቅተን መጫወት ነው ፍላጎታችን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በምሽቱ ጨዋታ ቡድናቸው አጥቅቶ እንደሚጫወት በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

" እንግሊዝ ጥሩ ተጨዋቾች አሏት ነገርግን እኛ ዛሬ አጥቅተን መጫወት ነው የምንፈልገው ፣ ጨዋታው አሰልቺ ከሆነ በእኛ ምክንያት አይሆንም።"ሲሉ ሮናልድ ኮማን ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በበኩላቸው " ለጨዋታው ጓጉተናል በሩብ ፍፃሜ ጥሩ ተጫውተናል ዛሬ የምንገጥመው ከስዊዘርላንድ የተሻለ ቡድን ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
7 ' ኔዘርላንድ 1 - 0 እንግሊዝ

ሲሞንስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
17 ' ኔዘርላንድ 1 - 1 እንግሊዝ

ሲሞንስ ኬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
33 ' ኔዘርላንድ 1 - 1 እንግሊዝ

ሲሞንስ                ኬን

- ሀሪ ኬን በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ያስቆጠረ ቀዳሚው መሆን ችሏሌ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከ ኔዘርላንድ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የኔዘርላንድን ግብ ዣቪ ሲሞንስ ሲያስቆጥር ሀሪ ኬን እንግሊዝን አቻ ማድረግ ችሏል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በኔዘርላንድ በኩል ዴንዜል ዱምፍሪስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ እንግሊዝ 63% - 37% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ኔዘርላንድ 1 - 2 እንግሊዝ

ሲሞንስ                ኬን
ዋትኪንስ
                                  

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ ለአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን የአውሮፓ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።

የእንግሊዝን የማሸነፊያ ግቦች ሀሪ ኬን እና ኦሊ ዋትኪንስ ሲያስቆጥሩ ዣቪ ሲሞንስ የኔዘርላንድን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

ኦሊ ዋትኪንስ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በትልቅ ውድድሮች የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታዋን የፊታችን እሁድ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Elfsborg - Paphos
El Gaish - Zamalek
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
" እግር ኳስ በቫር ውሳኔ እየጠፋ ነው " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በምሽቱ የእንግሊዝ ጨዋታ ሀሪ ኬን ላይ የተሰራው ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት የማያሰጥ መሆኑን ገልጸዋል።

" በጭራሽ ፍፁም ቅጣት ምት አያሰጥም " ያሉት አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ተጨዋቹ ኳስ ለማውጣት እየሞከረ ነበር እግርኳስ በቫር ውሳኔ እየጠፋ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

" በመጀመሪያ አጋማሽ እንግሊዝ የተሻለች ነበረች በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው ተመጣጣኝ ነበር ወደ ተጨማሪ ሰዓት ማምራት ነበረብን ነገርግን እግርኳስ ነው።" ሮናልድ ኮማን

ቨርጅል ቫን ዳይክ በበኩሉ " በጣም ያበሳጫል ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ፣ ዳኛው ጨዋታ ሲጠናቀቅ በፍጥነት ነው የሄደው ይህ ስለተፈጠረው ብዙ ይናገራል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ሀሪ ኬን

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሀሪ ኬን ቡድናቸው ምንም ቢፈጠር የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩን ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" አሁን ለፍፃሜ ደርሰናል ታሪክ ለመስራት የሚቀረን አንድ ጨዋታ ነው " የሚለው ሀሪ ኬን በጣም አስደስቶናል አላማችን ሊሳካ አንድ ጨዋታ ቀርቶናል ለጨዋታው ጓጉተናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ብሏል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በበኩላቸው " ያሳካነው ፍፁም የሚገባንን ድል ነው " ሲሉ ቡድናቸው ጥሩ ተንቀሳቅሶ እንደነበር ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሀሜስ ሮድሪጌዝ የእኔ አርኣያ ነው " ሉዊስ ዲያዝ

የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ ለብሔራዊ ቡድኑ አምበል ሀሜስ ሮድሪጌዝ ትልቅ አድናቆት እንዳለው ተናግሯል።

ኮሎምቢያ ትላንት ሌሊት ዩራጓይን 1ለ0 በማሸነፍ ከአርጀንቲና ጋር ለሚደረገው የ2024 ኮፓ አሜሪካ ፍፃሜ ጨዋታ ማለፍ ችለዋል።

በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ስለቻለው የቡድን አጋሩ ሀሜስ ሮድሪጌዝ አስተያየቱን የሰጠው ሉዊስ ዱያዝ “ የብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታዬን ሳደርግ ጀምሮ እሱ የእኔ አርኣያ እንደሆነ ነግሬዋለሁ " ሲል ተደምጧል።

የቡድኑ አምበል ሀሜስ ሮድሪጌዝ በኮፓ አሜሪካ ጥሩ ጊዜን እያሳለፉ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንዱ ሲሆን ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአራቱ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ሀሜስ ሮድሪጌዝ በተጨማሪም በአንድ የኮፓ አሜሪካ ውድድር ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ በማቀበል በሊዮኔል ሜሲ በአምስት ተይዞ የነበረውን ሪከርድ ሰብሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲፋን ሀሰን በአራት ርቀቶች ልትወዳደር ነው !

ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በአራት ርቀቶች ልትወዳደር መሆኑን የሀገሪቱ ፌዴሬሽን አረጋግጧል።

አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ በ10000 ፣ 5000 ፣ 1500 ሜትር እና ማራቶን ውድድሮች እንደምትሳተፍ ተገልጿል።

የ 31ዓመቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በሁሉም ውድድሮች ፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ በድምሩ በዘጠኝ ቀናት ውስጥ 65.5 ኪሎ ሜትር ያህል መሮጥ የሚጠበቅባት ይሆናል።

አትሌት ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር በሶስት ርቀቶች መሳተፏ የሚታወስ ሲሆን ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገቧ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የባየር ሙኒክ ጥያቄው ተቀባይነት አገኘ ! የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ከተጨዋቹ ጋር ቀደም ብለው በግል ከስምምነት የደረሱት ባየር ሙኒኮች አሁን ላይ ለፉልሀም ያቀረቡት 56 ሚልዮን ዩሮ የሚደረሰስ ሒሳብ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል። ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር የሚያገኙት 51 ሚልዮን…
ባየር ሙኒክ በይፋ ተጨዋች አስፈረሙ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የፉልሀሙን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀን ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ፓልሂንሀ በባየር ሙኒክ ቤት እስከ 2028 የሚያቆየውን የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

ፉልሀም ከተጨዋቹ ዝውውር 50 ሚልዮን ዩሮ ቋሚ ክፍያ እና ተጨማሪ ታይት የሚከፈል ክፍያ እንደሚቀበሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩራጓይ ተጨዋቾች ከደጋፊዎች ጋር ለምን ተጋጩ ?

በትላንት ምሽቱ የኮሎምቢያ እና ዩራጓይ ኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ዳርዊን ኑኔዝ እና ሌሎች የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ፀብ ውስጥ ገብተው ነበር።

ዩራጓይ ሽንፈት ካስተናገደችበት ጨዋታ በኋላ ዳርዊን ኑኔዝ እና የቡድን አጋሮቹ ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበሮች በማምራት ከደጋፊዎች ጋር ሲደባደቡ ተስተውለዋል።

ተጨዋቾቹ ይህንን ያደረጉት የኮሎምቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የዩራጓይ ተጨዋቾች ቤተሰቦች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

የዩራጓይ አምበል ጆዜ ሂሚኔዝ በሰጠው አስተያየትም " የተፈጠረው አደገኛ ነበር ምንም ፖሊስ አልነበረም እኛም ቤተሰቦቻችንን መጠበቅ ነበረብን " ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 04:27:39
Back to Top
HTML Embed Code: