Telegram Web Link
የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜን ማን ይመራዋል ?

የፊታችን እሁድ በስፔን እና እንግሊዝ መካከል የሚደረገውን የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

በግዙፉ ኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ፍራንኮይስ ሌቴዤር በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ ይለብሳል ! ሪያል ማድሪዶች ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን ለስድስት ተጨዋቾች አዲስ ቁጥር ማልያ አስተዋውቀዋል። ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ሲገለፅ ከነገ ጀምሮ በማድሪድ የሽያጭ ሱቅ በገበያ ላይ ይቀርባልም ተብሏል። በተጨማሪም በሚቀጥለው አመት :- ካማቪንጋ 6 ቁጥር ፣ ቫልቬርዴ 8 ቁጥር ፣ ቹዋሜኒ 14 ቁጥር ፣…
የምባፔ ማልያ ከፍተኛ ፈላጊዎች ማግኘቱ ተገለጸ !

በቅርቡ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ማልያዎች በክለቡ የሽያጭ ሱቅ ከፍተኛ ፈላጊዎች ማግኘቱ ተገልጿል

የማልያው ፈላጊዎች ቁጥር ከተጠበቀው በላይ በመሆኑ ምክንያት ማልያውን ለመረከብ ከአራት እስከ ስድስት ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ሪያል ማድሪድ አሳውቋል።

በዚህም ምክንያት ዛሬ ማልያውን የሚያዙ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች እስከ ላሊጋው የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ድረስ እንደማይቀበሉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ዋናው በቴሌግራም የስፖርት አልባሳትን እንዴት ያዛሉ?

👉🏾 በቴሌግራም ሊንክ @Wanawsales በመጠቀም የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ቡናማዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ቡና የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከኬንያው ኬንያ ፖሊስ እግርኳስ ክለብ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ቡናማዎቹ ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታ ከግብፁ ክለብ ዛማሊክ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ ?

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች :- የመጀመሪያው ጨዋታ ከነሀሴ 10-12/2016 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታ ከነሀሴ 17-19/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ይደረጋሉ።

ሁለተኛ ዙር :- የመጀመርያ ጨዋታዎች ከመስከረም 3-5/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንዲሁም የመልስ ጨዋታ ከመስከረም 10-12/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንኮች ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

ሀገራችን ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፈው የሊጉ ሻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅድመ ማጣሪያ ተጋጣሚውን አውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታውን ከዩጋንዳው ቪላ ጆጎ ክለብ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ንግድ ባንክ ይህንን ጨዋታ ካሸነፉ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ጨዋታ የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ እና የቡሩንዲውን ቪታሎ እግርኳስ ክለብ አሸናፊን የሚያገኙ ይሆናል።

ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ ?

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች :- የመጀመሪያው ጨዋታ ከነሀሴ 10-12/2016 ዓ.ም እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከነሀሴ 17-19/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች ይደረጋሉ።

ሁለተኛ ዙር :- የመጀመርያ ጨዋታዎች ከመስከረም 3-5/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከመስከረም 10-12/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናቶች እንደሚደረጉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ዝውውሮቹን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ !

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች የማትያስ ዴሊትን እና ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ከባየር ሙኒክ ጋር በማትያስ ዴሊት የዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር ለማጠናቀቅ የተወሰኑ ስራዎች እንደሚቀሯቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ ወደ ማንችስተር ለመጓዝ በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲገለፅ በሚቀጥሉት ቀናት ዝውውሩ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የርገን ክሎፕ ወደ አሜሪካ ያመሩ ይሆን ?

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጀርመናዊውን አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀጣይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት ለመሾም ጥረት ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ ካዘጋጀችው የዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ምድብ ጨዋታ መሰናበቷን ተከትሎ አሰልጣኝ ግሬግ ቤርሀልተርን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቷ ይታወቃል።

አሜሪካ በቀጣይ በጣምራ በምታዘጋጀው የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ቡድኑን እንዲመሩ ፍላጎት እንዳላት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ዝውውሮቹን በፍጥነት ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ ! በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ማንችስተር ዩናይትዶች የማትያስ ዴሊትን እና ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ከባየር ሙኒክ ጋር በማትያስ ዴሊት የዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ለስምምነት መቃረባቸው ተነግሯል። ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ጆሽዋ ዚርክዜን ዝውውር ለማጠናቀቅ…
ጆሽዋ ዚርክዜ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ ያመራል !

ኔዘርላንዳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ ከቦሎኛ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ ምሽት ወደ እንግሊዝ እንደሚያመራ ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ጆሽዋ ዚርክዜ በነገው ዕለት የህክምና ምርመራውን በማድረግ በይፋ ማንችስተር ዩናይትድን ይቀላቀላል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን በ 42.5 ሚልዮን ዩሮ በሆነ የዝውውር ሒሳብ በአምስት አመት ኮንትራት እንደሚያስፈርሙት ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም ሩድ ቫን ኔስትሮይ እና ሬኔ ሀኬን በክለቡ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ማካተታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ከቫን ዴ ቢክ ዝውውር ስንት ያገኛል ? የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊውን የስፔን ክለብ ጂሮና ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል። ቀያዮቹ ሴጣኖች ከተጨዋቹ ዝውውር 500,000 ዩሮ እንደሚቀበሉ ሲገለፅ በውሉ ውስጥ ታይቶ የሚጨምር እስከ አራት ሚልዮን ዩሮ የሚሆን ክፍያ እንደሚካተት ተነግሯል። ኔዘርላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች…
ዶኒ ቫን ዴ ቢክ በይፋ ጂሮናን ተቀላቀለ !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው የስፔኑ ክለብ ጂሮና ኔዘርላንዳዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጂሮና ለተጨዋቹ ዝውውር 500,000 ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማንችስተር ዩናይትድ መክፈላቸው ተገልጿል።

ዶኒ ቫን ዴቢክ በጂሮና እስከ 2028 የሚያቆየውን የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የርገን ክሎፕ ወደ አሜሪካ ያመሩ ይሆን ? የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጀርመናዊውን አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በቀጣይ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት ለመሾም ጥረት ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል። አሜሪካ ካዘጋጀችው የዘንድሮው የኮፓ አሜሪካ ምድብ ጨዋታ መሰናበቷን ተከትሎ አሰልጣኝ ግሬግ ቤርሀልተርን ከአሰልጣኝነት ማሰናበቷ ይታወቃል። አሜሪካ በቀጣይ በጣምራ በምታዘጋጀው የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር…
ክሎፕ የአሜሪካን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ !

በቅርቡ ከሊቨርፑል ጋር የተለያዩት ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን የቀረበላቸውን የአሰልጣኝነት ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የአሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው ሳምንት ከአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ጋር ተነጋግረው የነበረ ቢሆንም ብሔራዊ ቡድኑን የሚቀላቀሉበት እድል አለመኖሩ ተነግሯል።

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ከዚህ በፊት እንደተናገሩት አሁን ላይ ወደ ሀላፊነት መመለስ እንደማይፈልጉ እና እረፍት ማድረግ እንደሚፈልጉ ማረጋገጣቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#BiniyamGirmay🇪🇷 ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል። ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ…
ቢኒያም ግርማይ ለሶስተኛ ጊዜ አሸናፊ ሆነ !

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢኒያም ግርማይ በታላቁ የቱር ደ ፍራንስ ውድድር በአስራ ሁለተኛው ቀን ውድድር ቀድሞ በመግባት ለሶስተኛ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በመጨረሻዎቹ መቶ ሜትሮች የነበረውን ከባድ ፉክክር መርታት የቻለው ቢኒያም ግርማይ በቱር ደ ፍራንስ በርካታ ነጥብ በመሰብሰብ አረንጓዴ ማሊያውን ( Green Jersey ) አስጠብቋል።

ቢኒያም 203 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የ12ኛ ቀን ውድድር በ4 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት አጠናቋል።

በዘንድሮው ውድድር በአጠቃላይ ውጤት ታዴ ፖጋቻር የቢጫ ማሊያውን ውድድር እየመራ ሲሆን ፣ ቢኒያም ግርማይ ደግሞ በርካታ ነጥብ በመሰብሰብ የአረንጓዴ ማሊያ መሪ ነው።

ቢኒያም ግርማይ ከድሉ በኋላ በሰጠው አስተያየት " ከአሁን ጀምሬ የአረንጓዴ ማልያውን ለማስቀጠል ትኩረት ማድረጌን እቀጥላለሁ ፣ ይህንን ክብር ካገኘሁ በኋላ ፈጣንነት እየተሰማኝ ነው።"ሲል ተደምጧል።

ቢኒያም ባለፈው ሳምንት ሶስተኛውን መድረክ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ ሆኖ ታሪክ መፃፉ አይዘነጋም።

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢኒያም ግርማይ በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገባቸው ስኬቶች “ የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ “ የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶታል።

Credit - BBC News Amharic

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮድሪ ማድሪድ እንዲመጣ እየጠየቅኩት ነው " ካርቫል

ስፔናዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ ሪያል ማድሪድን እንዲቀላቀል እየጠየቀው መሆኑን ገልጿል።

" ሮድሪ ማድሪድ እንዲመጣ በየቀኑ እየነገርኩት ነው ሲቲን እንዲለቅ ጠይቄዋለሁ እሱን እንፈልገዋለን ፣ ኮንትራት እንዳለው ነግሮኛል ነገርግን ለእኛ ቢፈርም ትክክለኛው ተጨዋች ይሆናል።"ሲል ዳኒ ካርቫል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ለዎልቭስ ስንት አቅርቦ ነበር ? የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ከዎልቭስ ለማስፈረም የመጀመሪያ የዝውውር ሒሳብ አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። መድፈኞቹ ዳንኤል ቤንትሌይን ለማስፈረም አቅርበው ውድቅ የሆነባቸው ሒሳብ 50,000 ፓውንድ እንደነበር ለዎልቭስ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል። በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች የ 30ዓመቱን…
አርሰናል ወጣት ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጠየቀ !

አማራጭ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው አርሰናል የአያክሱን እንግሊዛዊ ወጣት ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ባለ ጥሩ ተሰጥኦ ባለቤት መሆኑ የተነገረው የ 18ዓመቱ ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ በአያክስ ያለው ውል በ2025 የሚጠናቀቅ ሲሆን መድፈኞቹን መቀላቀል ይፈልጋል ተብሏል።

መድፈኞቹ ከቀናት በፊት እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ ዳንኤል ቤንትሌይ ከዎልቭስ ለማስፈረም 50,000 ፓውንድ አቅርበው ውድቅ እንደሆነባቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ተጫዋቹን በውሰት ሊሰጥ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሳምቢ ሎኮንጋ በውሰት የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል።

ሲቪያ የተጫዋቹን ሙሉ ደሞዝ ለመክፈል ከስምምነት መድረሳቸው ሲገለፅ እንዲሁም በሚቀጥለው አመት በ12 ሚልዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ እንደሚካተትላቸው ተነግሯል።

ቤልጂየማዊው ተጨዋች ሎኮንጋ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ሲቪያን እንደሚቀላቀል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Al Ahly - Pyramids
Dundalk - Drogheda
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
2024/10/03 06:32:50
Back to Top
HTML Embed Code: