Telegram Web Link
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ሮማንያ ከ ዩክሬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ምሽት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ካደረጉት ጨዋታ አስቀድሞ በሁለቱ ሀገራት ደጋፊዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ግጭት ውስጥ የሰርቢያ ፕሬዝዳንት ልጅ የሆነው ዳኒሎ ቩቺች እንደነበር እና ጥቃት ለማድረስ ሲሞክር መስተዋሉ ተገልጿል።

የፕሬዝዳንቱ ልጁ ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ቡድን እና ሌሎች የወንጀለኛ ቡድኖች ጋር ግኑኝነት እንዳለው ተዘግቧል።

ከትናንቱ ግጭት በኋላ ሰባት የሚደርሱ የሰርብያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ለእስር እንደተዳረጉ የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ከደቂቃዎች በኋላ የዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ከሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በጨዋታው ከ30,000 በላይ የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ቡድናቸውን ለማበረታታት ስታዲየም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩክሬን በጨዋታው በሀገራቸው ከሩስያ ጋር እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት ለማስታወስ የተለያዩ ምስሎችን ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 '  ሮማንያ 1 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ሮማንያ 1 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
68 ' ሮማንያ 3 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ
ማሪን
ድራጉስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮማንያ በውድድሩ በታሪክ ሁለተኛ ድሏን አሳካች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ከዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለሮማንያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ራቫን ማሪን ፣ ዴኒስ ድራጉስ እና ኒኮላ ስታንቹ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን በአንድ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ከሶስት በላይ ግቦችን ሲያስቆጥር በታሪኩ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ተገልጿል።

ሮማንያ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታዋን ማሸነፍ ችላለች።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ሮማንያ ከቤልጂየም እንዲሁም ዩክሬን ከስሎቫክያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ቤልጅየም ከ ስሎቫኪያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ#ይሸለሙ እንደቀጠለ ነው!

🏆  በምሽቱ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ 4ኛ ቀን ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን?

🇦🇹 ኦስትሪያ ወይስ ፈረንሳይ 🇫🇷

💬 ግምትዎን #በፌስቡክ ገፃችን (https://www.facebook.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ሀገር እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ፕርሚየር ሊግ አዲስ ቴክኖሎጂ ሊሞክር ነው ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ አዲስ የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ( SAOT ) ለመሞከር በሙሉ ድምፅ መስማማታቸው ተገልጿል። በሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ዩኤፋ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ የሚጠቀመውን ካሜራ እና ሶፍትዌር እንደሚጠቀም ተነግሯል። አዲሱ ቴክኖሎጂ የጨዋታ ውጪ…
በፕርሚየር ሊግ በቀጣይ ምን አዲስ ነገር እንመለከታለን ?

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ የጨዋታው አሰላለፍ ጨዋታው ከመጀመሩ ሰባ አምስት ደቂቃዎች አቀድሞ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።

- ፕርሚየር ሊግ ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድኖች እረፍት በኋላ አዲሱን የጨዋታ ውጪ ቴክኖሎጂ ( SAOT ) ተግባራዊ ያደርጋል።

- አዲሱ ቴክኖሎጂ የጨዋታ ውጪ እንቅስቃሴን መስመር በፍጥነት በማስመር እንደሚያሳውቅ እና በአንድ ውሳኔ እስከ ሰላሳ ሰከንድ መቆጠብ እንደሚችል መዘገቡ አይዘነጋም።

- በሚቀጥለው የውድድር አመት የቫር ውሳኔ ስታዲየም በሚገኝ ስክሪን ለተመልካች ይቀርባል እንዲሁም ዳኞች ውሳኔውን ለደጋፊዎቹ ያብራራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
8 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
57 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

- ሮሜሉ ሉካኩ ለቤልጂየም ያስቆጠረው የአቻነት ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

ቤልጅየም 0-1 ስሎቫኪያ

        ሽራንዝ

- ሮሜሉ ሉካኩ ለቤልጂየም ያስቆጠረው የአቻነት ግብ በእጅ ተነክቷል በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤልጂየም ሽንፈት አስተናግዳለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ከስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

ለስሎቫኪያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ኢቫን ሽራንዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ስሎቫኪያ በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታ ድላቸውን ማሳካት ችለዋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ያደረጉት በታሪክ የመጀመሪያው የነጥብ ጨዋታ በስሎቫኪያ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ የፊታችን ቅዳሜ ቤልጂየም ከሮማንያ እንዲሁም ዩክሬን ከስሎቫክያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኦስትሪያ ከ ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

- የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ያለ ወሳኙ ተጨዋቻቸው ዴቪድ አላባ እንዲሁም ሌላኛውን የቡድኑ ቁልፍ ተጨዋች ዣቬር ሽላገር በጉዳት አጥተው በአውሮፓ ዋንጫው ይሳተፋሉ።

- ኦስትሪያ በተጨማሪም ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂዋን አሌክሳንደር ሽላገር እንዲሁ በጉዳት አጥታ በአውሮፓ ዋንጫው ለመቅረብ ተገዳለች።

- ምሽት ከፈረንሳይ ጋር የምትፋለመው ኦስትሪያ ካለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን ለቡድኑ ያስቆጠረውን የፍሬቡርግ አጥቂ ሚሼል ግሪጎሪትሽን እንደ ወሳኝ ተጨዋቿ ትመለከታለች።

- የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቬ ጅሩ በብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ውድድሩን የሚያደርግ ሲሆን በምሽቱ ጨዋታ በተጠባባቂነት ይጀመራል።

- የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ከዚህ በፊት በተጠባባቂነት የሚያስጀምሩትን የአርሰናል ተከላካይ ዊሊያም ሳሊባ በቋሚ አሰላለፍ አካተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 20:08:05
Back to Top
HTML Embed Code: