Telegram Web Link
እረፍት | ሰርቢያ 0 - 1 እንግሊዝ

                       ቤሊንግሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ ድል አድርጋለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ጁድ ቤሊንግሀም ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በሶስት ታላላቅ ውድድሮች መሳተፍ የቻለ በእድሜ ትንሹ የአውሮፓ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የ 20ዓመቱ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም እስካሁን በሁለት የአውሮፓ ዋንጫ እና አንድ አለም ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍ ችሏል።

ሀሪ ኬን በአራት ታላላቅ ውድድሮች የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት የመራ የመጀመሪያው እንግሊዛዊ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንግሊዝ ከዴንማርክ እንዲሁም ሰርቢያ ከስሎቬኒያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Belgium - Slovakia
Austria - France
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Play More and Spend less!

•PS4 Slim, 34,999 Birr
•PS4 PRO, 41,999 Birr
•Original Controller 6,499 Birr

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
" ከሀገሬ ጋር ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ " ቤሊንግሀም

እንግሊዝ ሰርቢያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ብቸኛ የማሸነፊያ ግቧን ያስቆጠረው ጁድ ቤሊንግሀም ከሀገሩ ጋር ዋንጫውን ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

" በሚቀጥሉት ጨዋታዎችም ለቡድኑ ያለኝን ሁሉ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ " ያለው ቤሊንግሀም ከሀገሬ ጋር የአውሮፓ ዋንጫውን ማሸነፍ እፈልጋለሁ ብሏል።

ጁድ ቤሊንግሀም በዘንድሮው የውድድር አመት ለክለቡ ሀገሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አስራ አምስት ጊዜ የጨዋታው ኮከብ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በእንግሊዝ መሸነፍ አይገባንም ነበር "

የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ድራጋን ስቶኮቪች ቡድናቸው በምሽቱ ጨዋታ ካሳየው እንቅስቃሴ አንፃር በእንግሊዝ መሸነፍ እንደማይገባው ተናግረዋል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም " ጨዋታው በጣም ጥሩ ነበር እንግሊዝ ጠንካራ ቡድን ነው ፣ እኛ ድፍረት የታከለበት ጨዋታ አድርገናል የፈለግነው እግርኳስ ተጫውተናል።

በምንፈልገው መንገድ ተጫውተን እንግሊዝ እንድትከላከል አድርገናል ባደረግነው ነገር ደስተኛ ነኝ መሸነፍ አይገባንም ነበር በውጤቱ ደስተኛ አይደለሁም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ዱሳን ታዲችን ተጠባባቂ አድርገው ያስጀመሩት በታክቲካል ውሳኔ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ቀይረው ያስገቡትም ለታክቲክ መሆኑን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቤሊንግሀም ትልቅ ክብር ይገባዋል " ሀሪ ኬን

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አምበል ሀሪ ኬን ትላንት ምሽት የብሔራዊ ቡድኑን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ጁድ ቤሊንግሀም ትልቅ ክብር እንደሚገባው ተናግሯል።

" እሱ የተለየ ተጨዋች ነው እያገኘ የሚገኘው አድናቆት ሁሉ ይገባዋል " ሲል የተናገረው ሀሪ ኬን እሱ የሚጫወትበት መንገድ ፣ ያለው በራስ መተማመንና በጨዋታ ላይ ያለው ተፅዕኖ አስደናቂ ነው ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአልባንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ክስ ቀርቦበታል !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር አልባንያ ከጣልያን ጋር ባደረገችው ጨዋታ የተፈጠሩ ክስተቶችን ተከትሎ የአልባንያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይ ክስ መክፈቱን አስታውቋል።

ዩኤፋ ክሱን ያቀረበው በጨዋታው የአልባንያ ደጋፊዎች እግርኳስን የማይመጥኑ መልዕክቶች እና የተለያዩ ቡድኖችን የሚደግፉ አርማዎች አሳይተዋል በሚል መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ደጋፊዎቹ በስታዲየሙ ተቀጣጣይ ርችቶች መጠቀማቸው እንዲሁም ቁሳቁሶችን መወርወራቸው ተዘግቧል።

አልባኒያ በቀጣይ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት ሊጠብቃት እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሳዲዮ ማኔ በግብርና ዘርፍ ሊሰማራ ነው !

ሴኔጋላዊው የአል ናስር ተጨዋች ሳዲዮ ማኔ በቀጣይ ሀገሩ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ከስፖርቱ በተጨማሪ በግብርናው ዘርፍ ተሰማርቶ ለመስራት ማቀዱን ገልጿል።

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ሳዲዮ ማኔ በዘርፉ ለመሰማራት የወሰነው ከቀናት በፊት ከሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስቴር ኦስማን ሶንኮ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ነው።

የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስቴር ኦስማን ሶንኮ ሀገሪቱ በምግብ ራሷን እንድትችል እና የምግብ ዋጋ ንረት እንዲቀንስ ከማኔ በተጨማሪ ሌሎች ሴኔጋላዊያን በዘርፉ ከተሰማሩ መንግስታቸው ልዩ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ሳዲዮ ማኔ ከዚህ በፊት በሀገሩ ሴኔጋል ሆስፒታል ፣ ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች መሰረታዊ ነገሮችን ለማህበረሰቡ ሰርቶ ማስረከብ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰርጅዮ ራሞስ ከሲቪያ ጋር ተለያየ !

ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሰርጅዮ ራሞስ ከላሊጋው ክለብ ሲቪያ ጋር ከአንድ የውድድር ዘመን ቆይታ በኋላ መለያየቱ ይፋ ተደርጓል።

የ 38ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሰርጅዮ ራሞስ ባለፈው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በአንድ አመት ውል የቀድሞ ክለቡ ሲቪያን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሰርጅዮ ራሞስ በቀጣይ በነፃ ዝውውር አዲስ ክለብ የሚቀላቀል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ሮማንያ ከ ዩክሬን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ምሽት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር ካደረጉት ጨዋታ አስቀድሞ በሁለቱ ሀገራት ደጋፊዎች መካከል ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

በደጋፊዎቹ መካከል በተፈጠረው ግጭት ውስጥ የሰርቢያ ፕሬዝዳንት ልጅ የሆነው ዳኒሎ ቩቺች እንደነበር እና ጥቃት ለማድረስ ሲሞክር መስተዋሉ ተገልጿል።

የፕሬዝዳንቱ ልጁ ከሰርቢያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ቡድን እና ሌሎች የወንጀለኛ ቡድኖች ጋር ግኑኝነት እንዳለው ተዘግቧል።

ከትናንቱ ግጭት በኋላ ሰባት የሚደርሱ የሰርብያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ለእስር እንደተዳረጉ የአካባቢው ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

ከደቂቃዎች በኋላ የዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ከሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በጨዋታው ከ30,000 በላይ የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ቡድናቸውን ለማበረታታት ስታዲየም ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዩክሬን በጨዋታው በሀገራቸው ከሩስያ ጋር እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት ለማስታወስ የተለያዩ ምስሎችን ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 '  ሮማንያ 1 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ሮማንያ 1 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
68 ' ሮማንያ 3 -0 ዩክሬን

ስታንቺዩ
ማሪን
ድራጉስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮማንያ በውድድሩ በታሪክ ሁለተኛ ድሏን አሳካች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን ከዩክሬን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለሮማንያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ራቫን ማሪን ፣ ዴኒስ ድራጉስ እና ኒኮላ ስታንቹ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሮማንያ ብሔራዊ ቡድን በአንድ የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታ ከሶስት በላይ ግቦችን ሲያስቆጥር በታሪኩ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑ ተገልጿል።

ሮማንያ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታዋን ማሸነፍ ችላለች።

በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ሮማንያ ከቤልጂየም እንዲሁም ዩክሬን ከስሎቫክያ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 10:22:52
Back to Top
HTML Embed Code: