Telegram Web Link
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ዋንጫውን ማሳካት እንፈልጋለን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩን ማሸነፍ እንደሚፈልግ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን በንግግራቸውም " የአውሮፓ ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን የምናሳካ ከሆነ ስኬታማ ውድድር ይሆንልናል የማናሳካው ከሆነ ለእኛ ስኬታማ አይሆንም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በአውሮፓ ዋንጫው ማን ብዙ ተጨዋች ያሳትፋሉ ?

በነገው ዕለት በሚጀምረው የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዘጠና ስድስት ተጨዋቾችን በማሳተፍ ቀዳሚው ሊግ መሆን ችሏል።

በክለቦች ደረጃ የጣልያን ሴርያ አሸናፊው ክለብ ኢንተር ሚላን እና የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ አስራ አራት ተጨዋቾችን ለውድድሩ በመላክ በቀዳሚነት መቀመጥ ችለዋል።

ብዙ ተጨዋቾች ያሳተፉ ሊጎች የትኞቹ ናቸው ?

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ :- 96 ተጨዋቾች

- የጣልያን ሴርያ :- 92 ተጨዋቾች

- የጀርመን ቡንደስሊጋ :- 75 ተጨዋቾች

- የስፔን ላሊጋ :- 57 ተጨዋቾች

- የፈረንሳይ ሊግ :- 29 ተጨዋቾች

- የቱርክ ሱፐር ሊግ :- 26 ተጨዋቾች

ብዙ ተጨዋቾች ያሳተፉ ክለቦች የትኞቹ ናቸው ?

- ኢንተር ሚላን :- 14 ተጨዋቾች

- ማንችስተር ሲቲ :- 14 ተጨዋቾች

- ሪያል ማድሪድ :- 13 ተጨዋቾች

- ባርሴሎና :- 11 ተጨዋቾች

- ፒኤስጂ :- 11 ተጨዋቾች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዳኛን ማነጋገር የሚችለው የትኛው ተጨዋች ነው ?

በነገው ዕለት በሚጀምረው የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመሐል ዳኛውን ማነጋገር የሚችሉት የብሔራዊ ቡድን አምበሎች ብቻ መሆናቸው ተገልጿል።

ሌሎች ተጨዋቾች ዳኛውን ለማነጋገር እንደማይችሉ እና ለማነጋገር የሚሞክሩ ከሆነ እንዲሁም አላስፈላጊ ባህሪ ሲያሳዩ ከተስተዋሉ የማስጠንቀቂያ ካርድ እንደሚመለከቱ ተነግሯል።

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ግብ ጠባቂ የሚሆን ከሆነ በሜዳ ውስጥ ዳኛውን ማነጋገር የሚችል ተጨዋች እንደሚመረጥ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በቀጣዩ የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሀምሳ ስምንት የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው ተጨዋቾች በተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች ተሰልፈው በውድድሩ ይጫወታሉ።

በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ታላላቅ ተጨዋቾቿን ጨምሮ አስራ አራት ተጨዋቾቿ የአፍሪካ የዘር ሀረግ ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ዘጠኝ ተጨዋቾቹ የዘር ሀረጋቸው ከአፍሪካ የሚመዘዝ መሆኑ ተነግሯል።

እንዲሁም ስዊዘርላንድ ( ስምንት ) ፣ እንግሊዝ ( ስድስት ) ፣ ጀርመን ( አምስት ) ፣ ኔዘርላንድ ( አራት ) ፣ ፖርቹጋል ( አራት ) ፣ ጣልያን ( ሁለት ) ፣ ስፔን ( ሁለት ) ተጨዋቾችን ያሳትፋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የ 2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የማጣርያ ጨዋታ ምድብ ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

ብሔራዊ ቡድኖች የምድብ ተጋጣሚያቸውን ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት እንደሚያውቁ ይፋ ተደርጓል።

በምድብ ድልድሉ የቅድመ ማጣሪያውን ያለፉ አራት ሀገራትን ጨምሮ አርባ ስምንት ብሔራዊ ቡድኖች እንደሚካተቱ ተገልጿል።

በአስራ ሁለት ምድብ ተክፈለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ብሔራዊ ቡድኖቹ የምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የመጀመሪያ ሀያ አራት ቡድኖች ለአፍሪካ ዋንጫው የሚያልፉ ይሆናል።

የማጣሪያ ጨዋታዎቹ ከሚቀጥለው አመት መስከረም ወር ጀምሮ መካሄዳቸውን እንደሚጀምሩ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኤሲ ሚላን ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ ! የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር ለመለያየት መወሰኑን በይፋ አስታውቋል። አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ኤሲ ሚላን ነገ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ። ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ክለቡን የሴርያ…
ኤሲ ሚላን በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር የተለያየው የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ኤሲ ሚላን ፖርቹጋላዊውን የቀድሞ የሊል እና ሮማ አሰልጣኝ የነበሩትን ፓውሎ ፎንሴካን በሀላፊነት መሾማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ ኤሲ ሚላንን ለሚቀጥሉት ሶስት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከሀላፊነታቸው ለቀቁ !

ጀርመናዊው የቡንደስሊጋው ክለብ ቦርስያ ዶርትመንድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከክለቡ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸው ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር በጋራ ስምምነት መለያየታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 41ዓመቱ አሰልጣኝ ኤዲን ቴርዚች ቦርስያ ዶርትመንድን እየመሩ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚ እንደነበሩ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ወደ ማርሴይ ሊያመሩ ነው !

ጣልያናዊው የቀድሞ የብራይተን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የፈረንሳዩን ክለብ ኦሎምፒክ ማርሴይ ለመረከብ ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከማርሴይ የሶስት አመት ኮንትራት እንደቀረበላቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ ማርሴይን ለመረከብ አሁን ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ ባይደርሱም ንግግሮች በጥሩ መልኩ መቀጠላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዌስትሀም ዩናይትድ ተጨዋች አስፈርመዋል !

ዌስትሀም ዩናይትድ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ከፓልሜይራስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ሉዊስ ጉልሄርሜ ለዌስትሀም ዩናይትድ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር 30 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማውጣታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  22ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን በተከታዩ ሊንክ ማግኘት ይችላሉ

https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5329

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 22
ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 12:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
#EthiopianPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባሕር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የጣና ሞገዶቹቹን ግቦች የአብስራ ተስፋዬ እና ፀጋዬ አበራ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለንግድ ባንክ የአቻነት ግቦችን አዲስ ግደይ 2x አስቆጥሯል።

የፕርሚየር ሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ #ሲመራ ቢቆይም በጨዋታው መጠናቀቂያ ከ86ኛው ደቂቃ በኋላ ባስቆጠረው ሁለት ግብ ነጥብ መጋራት ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ተጨዋች አዲስ ግደይ በውድድር ዘመኑ አስራ አንደኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

1️⃣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 57 ነጥብ

3️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 46 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- አዳማ ከተማ ከ ባሕር ዳር ከተማ

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በፈረንሳዊው ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ዝውውር ዙሪያ ክለቡ ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ለማነጋገር ከክሪስታል ፓላስ ፍቃድ መጠየቃቸው ተነግሯል።

ባየር ሙኒክ እና ኒውካስል ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል።

እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ የ 22ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሂሮኪ ኢቶ ከስቱትጋርት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ባየር ሙኒክ የ 25ዓመቱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሂሮኪ ኢቶ በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን አስታውቀዋል።

ባየር ሙኒክ ለተጨዋቹ ውል ማፍረሻ ለስቱትጋርት 30 ሚልዮን ዩሮ መክፈላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ መቼ አቀባበል ይደረግለታል ?

በቅርቡ በይፋ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ለኪሊያን ምባፔ ሐምሌ 9/2016 ዓ.ም ይፋዊ አቀባበል በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ማዘጋጀታቸው ተነግሯል።

ከአውሮፓ ዋንጫው ፍፃሜ ሁለት ቀናት በኋላ በሚደረገው ይፋዊ አቀባበል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከአመታት በፊት በ80,000 ደጋፊዎች ፊት የተደረገለት አቀባበል አይነት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጀርመንን ለመግጠም ዝግጁ ነን ማንንም አንፈራም " ስቴቭ ክላርክ

የውድድሩ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ከአዘጋጇ ሀገር ጀርመን ጋር የሚያደጉት ስኮትላንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ ከአንዲ ሮበርሰን ጋር በመሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ በሰጡት አስተያየትም " በአውሮፓ ዋንጫው በመሳተፋችን ደስተኞች ነን ለውድድሩም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን በእንዲህ አይነት ውድድሮች ብዙም ልዩነት የለም ጀርመንን ለመግጠም ዝግጁ ነን ብለዋል።

አሰልጣኝ ስቴቭ ክላርክ አያይዘውም የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ውድድሩን ያሸንፋሉ ተብለው ከታጩ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ቡድናቸው መጠንቀቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

" ሁሉንም ቡድኖች በተገቢው መልኩ እናከብራለን ነገርግን የትኛውንም ብሔራዊ ቡድኝ አንፈራም።" ስቴቭ ክላርክ

አንዲ ሮበርትሰን በበኩሉ " የውድድሩን አሸናፊ እጩ መግጠም አስቸጋሪ እንደሚሆን እናውቃለን ፣ በመጀመሪያ ጨዋታችን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ያለንን ሁሉ መስጠት አለብን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች አማኑኤል አድማሱ መሐመድ ናስር ፣ ስንታየሁ ወለጬ እና አንተነህ ተፈራ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና አራተኛ ተከታታይ ድሉን በማሳካት ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።

ወልቂጤ ከተማ ሰባተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ ላይ አስር ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 47 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

- ሀዋሳ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

- ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሌኒ ዮሮ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ፈረንሳዊው የሊል የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ አሁን ላይ በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

አሁን ላይ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊጎቹ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ለማስፈረም በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ሌኒ ዮሮን ለማስፈረም ቀደም ብሎ እንቅስቃሴ የጀመረው ሪያል ማድሪድ የተሻለ እድል እንዳለው ሲገለፅ ተጨዋቹ በበኩሉ ለሎስ ብላንኮዎቹ ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚችል ተዘግቧል።

የ 19ዓመቱ የመሐል ተከላካይ ሌኒ ዮሮ የዝውውር ሒሳብ 50 ሚልዮን ዩሮ ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ነው !

ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ ለመቀላቀል ንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድን በዚህ ክረምት እንደሚለቅ የሚጠበቀው ናቾ ዝውውሩን ባያጠናቀቅም ከአል ኢትሀድ ጋር እያደረገ የሚገኘው ንግግር በጥሩ ሁኔታ መቀጠሉ ተዘግቧል።

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ለናቾ 40 ሚልዮን ዩሮ የሚያስገኝለትን የሁለት አመት ኮንትራት ማቅረባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 09:24:59
Back to Top
HTML Embed Code: