Telegram Web Link
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ሶሴዳድ የማንችስተር ሲቲውን የግራ መስመር ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ በዚህ ክረምት ማንችስተር ሲቲን እንደሚለቅ የሚጠበቅ ሲሆን ሪያል ሶሴዳድ በበኩሉ ተጫዋቹን ለማስፈረም በመስራት ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

የ 23 ዓመቱ ተጫዋች ሰርጂዮ ጎሜዝ ከሁለት አመታት በፊት ከአንደርሌክት ማንችስተር ሲቲን በአራት ዓመት ኮንትራት መቀላቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ለሽያጭ ሊቀርብ ነው !

በእንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ በሚመራው " INEOS " ባለቤትነት የተያዘው የፈረንሳዩ ክለብ ኒስ ለሽያጭ ሊቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

ሰር ጂም ራትክሊፍ በኒስ ያላቸውን ከፍተኛ ድርሻ ለሽያጭ ለማቅረብ የፈለጉት በቅርቡ የአነስተኛ ድርሻ ባለቤት በሆኑበት ማንችስተር ዩናይትድ ለማተኮር እንደሆነ ተነግሯል።

በተጨማሪም በፈረንሳይ ሊግ እየተቀዛቀዘ የመጣው የፋይናንስ ሁኔታ እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ኒሴን ለመሸጥ ካሳሰባቸው ምክንያቶች አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ዩኤፋ ባለቤቶቹ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒስን በዩሮፓ ሊግ ማሳተፍ እንዲችሉ የአንድ አመት ጊዜ የሰጠ መሆኑን ተከትሎ ሽያጩ ከዚህ ጋር እንደማይገናኝ ተጠቁሟል።

የፈረንሳይ ሊግ በሚቀጥለው የውድድር አመት ለማስተላለፍ ፍላጎት ያለው ተቋም እስካሁን አለማግኘቱ እና የስርጭት ገቢውም በግማሽ ሊቀንስ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Stock Clearance Discount

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

• iPhone 13, Black, 128 GB/ 80%
   54,000 ETB
• iPhone 13, Pink, 128 GB/ 85%
   56,000 ETB
• iPhone 13, White, 128 GB/ 86%
   56,000 ETB
• iPhone 13,  Black, 128 GB/ 90%
   57,000 ETB
• iPhone 13, Pink, 256 GB/ 84%
   58,000 ETB
• iPhone 13, Black, 256 GB 91%.  
   59,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Blue, 128 GB/ 90%
   61,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Black, 256 GB/ 83%
  65,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Gold, 256 GB/ 87%. 
   67,000 ETB
• iPhone 13 Pro, Blue, 512 GB/ 88%
   65,000 ETB ⚠️
• 13 Pro Max, Black, 128 GB/ 87%
   74,000 ETB
• 13 Pro Max, white, 128 GB/ 87%. 
   72,000 ETB
• 13 Pro Max, Blue, 128 GB/ 98%.
   77,000 ETB
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 83%
   79,000 ETB 
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 85%
   77,000 ETB ⚠️
• 13 Pro Max, Blue, 256 GB/ 85%
   81,000 ETB 
• 14 Pro, Purple, 512 GB/ 90%,  
   75,000 ETB (E-SIM)
• 14 Pro Max, Purple 256 GB/ 89% 
   97,000

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
❇️SMART ያልሆኑ TV SMART ለማድረግ ምን መግዛት እንዳለብዎ ካላወቁ  ይሄን እቃ ምርጫው ያድርጉ።

❇️የራሱ የሆነ BLUETOOTH ሪሞት ያለው ትክክለኛ 4K ምስል ጥራት ያለው

❇️የተለያዩ የፊልም እና የኳስ ቻናሎች የተጫኑበት በአጭር ጊዜ በሚቆ ይ ቅናሽ 3200 ብር ብቻ

Inbox Us 📩Admin @Sadikethio
Call 📱 +251 91 178 5693

የተለያዩ ነፃ የኳስ ቻናሎች የሚያገኙበት የዲሽ ቻናል 👇👇 https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEnaa5LpZrcwQ-E0Tw
TIKVAH-SPORT
ለቲያጎ ሲልቫ አቀባበል በርካታ ትኬቶች ተሸጡ ! ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ ከቼልሲ ጋር በመለያየት ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ ለመመለስ ፊርማውን ማኖሩ ይታወሳል። ከአስራ አራት አመታት በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ የሚመለሰው ቲያጎ ሲልቫ በሚቀጥለው ሳምንት አርብ በክለቡ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግለት ተገልጿል። በማራካኛ ስታዲየም ለቲያጎ ሲልቫ በሚደረገው አቀባባል…
ቲያጎ ሲልቫ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት !

በቅርቡ ከቼልሲ ጋር የተለያየው ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቲያጎ ሲልቫ በልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ ደመቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

ቲያጎ ሲልቫ ከአስራ አራት አመታት በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንሴ በመመለስ ፊርማውን ማኖሩ የሚታወስ ነው።

በማራካኛ ስታዲየም ለቲያጎ ሲልቫ በተደረገው ደማቅ አቀባበል 55,000 የክለቡ ደጋፊዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

በብራዚል እግርኳስ ታሪክ በርካታ ተመልካች የተገኘበት ይፋዊ የተጨዋች ትውውቅ በመሆንም አዲስ ሪከርድ መመዝገብ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ በሌላ አለም ዋንጫ ይሳተፍ ይሆን ?

አርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በቀጣዩ የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር ሊሳተፍ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

ሊዮኔል ሜሲ ሲናገርም በውድድሩ መሳተፌ " በአካል ብቃት ሁኔታዬ ፣ በሚሰማኝ ስሜት እንዲሁም መወዳደር በምችልበት ደረጃ እና ቡድኑን መርዳት በመቻሌ " ላይ የተመሰረተ ነው ብሏል።

የ2026 አለም ዋንጫ ውድድር ከሁለት አመት በኋላ በአሜሪካ ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቪንሰስ ባሎን ዶር ይገባዋል " ማርቲኔሊ

ብራዚላዊው የአርሰናል ፊት መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔሊ ቪንሰስ ጁኒየር የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት ማሸነፍ እንደሚገባው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" ከቪንሰስ ጋር አብሮ መጫወት እና አብሮ መዋል ትልቅ ክብር ነው " ያለው ማርቲኔሊ ብራዚላውያን ደምቀው ስናይ በጣም እንደሰታለን በእኔ አስተያየት ቪንሰስ የባሎን ዶር ሽልማትን ማሸነፍ አለበት ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሜሪካ ኮፓ አሜሪካን የማሸነፍ አቅም አላት "

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን እና ኤሲ ሚላን የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያን ፑልሲች ቡድናቸው ቀጣዩን የኮፓ አሜሪካ ውድድር ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

ክርስቲያን ፑልሲች በንግግሩም " ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ያለ ሲሆን በውድድሩ ከመጀመሪያው የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ለአላማችን ዋንጫ ማሸነፍ ነው ሲል ተደምጧል።

ለጁቬንቱስ የሚጫወተው ማኬኒ በበኩሉ " እኛ በትልቅ ክለብ የሚጫወቱ ጥሩ ተጨዋቾች አሉን ፣ ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ አሜሪካ የዋንጫ ተፎካካሪ የመሆን አቅም አላት ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስቴፋን ኦርቴጋ ውሉን ያራዝማል !

ጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ስቴፋን ኦርቴጋ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት የውድድር አመታት ለመቆየት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ግብ ጠባቂው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ሙሉ የቃል ስምምነት መፈፀሙ ሲገለፅ በቀጣይ በይፋ ውሉን ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል።

ስቴፋን ኦርቴጋ በእንግሊዝ እና አውሮፓ ክለቦች ቢፈለግም በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ውስጥ ለመቆየት መወሰኑ ተነግሯል።

ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ የ 38ዓመቱን እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ስኮት ካርሰን ኮንትራት ለአንድ የውድድር አመት ማራዘማቸው አይዘነጋም።

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በበኩሉ እስካሁን በክለቡ ያለው የወደፊት ቆይታ የተረጋገጠ አይደለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በቤቲካ ፋስታ ወዲያው ያሸንፉ!  አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Turning any art into lasting metal prints!

Custom prints available in various sizes:
A4
A3
A2

Order now by calling 0912689730 or 0913336591.

Follow us for more
Telegram: @silverpoint_printss
Instagram: https://www.instagram.com/silverpoint_prints/
TikTok: https://www.tiktok.com/@silverpoint.prints
TIKVAH-SPORT
ስቴፋን ኦርቴጋ ውሉን ያራዝማል ! ጀርመናዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ስቴፋን ኦርቴጋ በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት የውድድር አመታት ለመቆየት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ግብ ጠባቂው ከማንችስተር ሲቲ ጋር ሙሉ የቃል ስምምነት መፈፀሙ ሲገለፅ በቀጣይ በይፋ ውሉን ያራዝማል ተብሎ ይጠበቃል። ስቴፋን ኦርቴጋ በእንግሊዝ እና አውሮፓ ክለቦች ቢፈለግም በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ውስጥ ለመቆየት…
ሲቲ በይፋ የተጫዋቹን ውል አራዝሟል !

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የጀርመናዊውን ግብ ጠባቂ ስቴፋን ኦርቴጋ ኮንትራት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ግብ ጠባቂው በማንችስተር ሲቲ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን የሁለት አመታት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ስቴፋን ኦርቴጋ ውሉን ካራዘመ በኋላ " ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ለተጨማሪ አመት በመቆየቴ ተደስቻለሁ ይህ ክለብ ተጨዋቾች ምርጥ ለመሆን የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማቅረብ የሚችል ነው።"ሲል ተደምጧል።

ከሁለት አመት በፊት ማንችስተር ሲቲን የተቀላቀለው ስቴፋን ኦርቴጋ ለክለቡ ሰላሳ አራት ጨዋታዎች ሲያደርግ ሁለት የሊግ ፣ አንድ የሻምፒየንስ ሊግ እና አንድ የኤፌ ካፕ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከምርጥ ተከላካዮች አንዱ ነኝ " ሳሊባ

ፈረንሳዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ አሁን ላይ ከፕርሚየር ሊጉ ምርጥ ተከላካዮች አንዱ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ከፕርሚየር ሊጉ ምርጥ ሶስት ተከላካዮች አንዱ ነኝ " የሚለው ሳሊባ አሁን ላይ አጥቂዎች እኔን መፍራት መጀመራቸውን አይቻለሁ ከእኔ ጋር ሲገናኙ ምቾት አይሰማቸውም ወደኋላ ይመለሳሉ " ብሏል።

አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ስላለው የዋንጫ ፉክክር አስተያየት የሰጠው ሳሊባ " በሚቀጥለው አመት ከዚህ በተሻለ እንፋለማቸዋለን " ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄምስ ትራፎርድ ወደ ኒውካስል ዩናይትድ ?

በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ የበርንሌዩን ግብ ጠባቂ ጄምስ ትራፎርድን ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

ኒውካስል ዩናይትድ ምንም እንኳን እስካሁን ከስምምነት ባይደርሱም ከበርንሌይ ጋር ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል።

በተጨማሪም ኒውካስል ዩናይትድ የአርሰናሉን ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴልን በዝርዝራቸው ውስጥ መያዛቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥🔥 ለባልትና ቤቶች 🔥🔥
🫓🫓 ለወፍጮ ቤቶች 🫓🫓

አዲስ እና ዘመናዊ በኖርማል ቆጣሪ የሚሰራ ድንጋይ አልባ ዘመናዊ ማሽን ይዘንልዎ መጣን
ሩዝ፣ሽምብራ፣ገብስ አሳምሮ ይከካል ይፈትጋል ያበጥርራል
በሰአት  4 ኩንታል ይሰራል

ማንኛውም እህል፣ እንዲሁም ዛላ በርበሬን ጨምሮ በተለያየ ደረጃ ይፈጫል

የስፔር ፓርት ችግር እንዳያስቦ
ለበለጠ መረጃ መልእክት ይላኩልን
0951906772
@balagertech
https://www.tg-me.com/balager_technologies
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ዛሬም አዲስ ነገር እናስታውስዎ!

👉🏾 ከነፃ ዴሊቨሪ ጋር በ1399 ብር ብቻ።

👉🏾 #ይፍጠኑ፣ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportswear
" የጅሩን አጨራረስ ለማሳመር እንጥራለን " ግሪዝማን

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች አንቷን ግሪዝማን ቡድናቸው በቀጣዩ የአውሮፓ ዋንጫ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ለኦሊቬ ጅሩ ጥሩ ሽኝት ለማድረግ እንደሚጥር ገልጿል።

አንቷን ግሪዝማን በንግግሩም " የአውሮፓ ዋንጫው ለኦሊቬ ጅሩ በፈረንሳይ ማልያ የመጨረሻ ጨዋታው ነው ጥሩ ሽኝት እንደሚሆንለት ተስፋ አደርጋለሁ።

ለእሱ ጥሩ ነገር ይገባዋል ምርጥ ተጨዋች ነው በእግርኳስ ላደረገው ነገር ሁሉ ትልቅ ክብር አለኝ።"ሲል አንቷን ግሪዝማን ተናግሯል።

በሀምሳ ሰባት ግቦች የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነው ኦሊቬ ጅሩ ከአውሮፓ ዋንጫ በኋላ ከቡድኑ ራሱን እንደሚያገል ማስታወቁ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 13:31:20
Back to Top
HTML Embed Code: