Telegram Web Link
ሪያል ቫላዶሊድ ወደ ላሊጋው አድጓል !

ሁለተኛውን የስፔን ሊግ በበላይነት እየመሩ የሚገኙት ሪያል ቫላዶሊድ ወደ ስፔን ላሊጋ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

በቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና ሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋች ሮናልዶ ናዛሪዮ በባለቤትነት የተያዘው ሪያል ቫላዶሊድ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ላሊጋው መመለስ ችለዋል።

ሮናልዶ ናዛሪዮ በቅርቡ ከደጋፊዎች በሚደርሱት ለክለቡ ትኩረት አልሰጠህም የሚሉ ከፍተኛ ተቃውሞዎች ምክንያት ሪያል ቫላዶሊድን ለመሸጥ እንዳሰበ ገልፆ ነበር።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
"ዶርትመንድ ጠንካራ አጥቂዎች አሏቸው " አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሳምንቱ መጨረሻ ከዶርትመንድ ጋር ካለባቸው የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ምን አሉ ?

- " ጨዋታውን ቀለል አድርገን አንመለከተውም ዶርትመንድ ብቃት እንዳላቸው አሳይተዋል ፍፃሜ መድረስ ይገባቸዋል ከባድ ፍልሚያ እንደሚገጥመን እናውቃለን።

- ተጨዋቾቹ ሙሉ ትኩረታቸው ፍፃሜው ላይ ነው በድጋሜ ፍፃሜ ላይ በመገኘታችን ደስተኞች ነን ለእኔ ስድስተኛዬ ነው።

- ሪያል ማድሪድ ለእኔ የተለየ ክለብ ነው ከዚህ በፊት ላሰለጠንኳቸው ክለቦች ተመሳሳይ ነገር አልልም እኔ የሪያል ማድሪድ ደጋፊ ነኝ በክለቡ ውጤት እደሰታለሁ እበሳጫለሁ።

- በጨዋታው ለመከላከል መዘጋጀት አለብን ምክንያቱም ዶርትመንድ እንደ ሳንቾ እና አዴይሚ አይነት ጠንካራ አጥቂዎች አሏቸው ልክ እንደኛ ተፎካካሪ ቡድን ናቸው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ!

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
Forwarded from WANAW SPORT
ብናሸነፍም፣ ብንሸነፍም - ሁሌም ተግተን እንስራ!
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ይበልጥ ወደፊት እንግፋ።


#ዋናነት እሱ ነው!

እርስዎስ ዛሬ ምንድነው የሚሰሩት?

መልካም የስራ ሳምንት!
Happy Work Week!


Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ፖቼቲኖ መባረር አልነበረበትም " ሀዛርድ

ቤልጂየማዊው የቀድሞ የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲን ሀዛርድ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን ማሰናበታቸው የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑን ገልጿል።

" ውሳኔው ትንሽ አበሳጭቶኛል እንደእኔ ፖቼቲኖ ጥሩ ነገር ሰርቷል ፣ ሰዎች ቼልሲ ምርጥ አራት ውስጥ መመልከት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ ነገርግን ቡድኑ ሽግግር ላይ ነበር ማን እንደሚተካው እናያለን።ሲል ኤዲን ሀዛርድ ተናግሯል።

ኤዲን ሀዛርድ አክሎም አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ታላቅ አሰልጣኝ መሆናቸውን በመግለፅ በቀጣይ ትልቅ ስኬት እንዲገጥማቸው እንደሚመኝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ በቅርቡ እንደሚወስን ተስፋ አደርጋለሁ “

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር ምባፔ ቀጣይ ማረፊያውን በቅርብ ያሳውቃል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል።

“ በቅርቡ ከውሳኔ ላይ እንደሚደርስ ተስፋ አደርጋለሁ “ የሚለው ቪንሰስ “ ሁሌም የምፈልገው ከአለም ምርጦች ጋር አብሮ መጫወት ነው “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኬረን ማኬን ኮንትራታቸውን ሊያራዝሙ ነው !

በሊጉ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለጉ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬን አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ሊፈራረሙ መሆኑ ተዘግቧል።

ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ኬረን ማኬን ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል።

ቼልሲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ብራይተን የ 38ዓመቱን አሰልጣኝ ኬረን ማኬንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት የነበራቸው ክለቦች ነበሩ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ሮናልዶ የሳውዲ ሊግ ሪከርድ ሰብሯል !

ፖርቹጋላዊው የአል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳውዲ አረቢያ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ መስበር ችሏል።

ትላንት ምሽት አል ናስር አል ኢትሀድን 4ለ2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ሰላሳ አምስት አድርሷል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ በአንድ የውድድር አመት ብዙ ግብ የማስቆጠር ሪከርድ ከዚህ በፊት በሰላሳ አራት ግቦች በሀምዳላህ የተያዘ ነበር።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስት የሊግ ግቦች አስቆጥሮ አስራ አንድ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአራት የተለያዩ ሊጎች የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ያጠናቀቀ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሏል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ማንን በሀላፊነት ይሾማል ? ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች ስማቸው ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ሲያየዝ ቢቆይም የመጨረሻ እጩዎቹ ከታወቁ ሰንብቷል። አስቀድሞ እጩ የነበሩት የ 38ዓመቱ ኬረን ማኬና የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ #ሳይካተቱ መቅረታቸው ተዘግቧል። የቅጥር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለፀው ቼልሲዎች ኢንዞ ማርሴካ እና ቶማስ ፍራንክ ክለቡን ለመረከብ የቀረቡ…
ቼልሲ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ሊሾሙ ነው !

ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልጉ ለክለባቸው ማሳወቃቸው ሲገለፅ ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ ጋር እንዲነጋገሩ ፍቃድ መስጠቱም ታውቋል።

ቼልሲዎች በቀጣይ ለአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአምስት አመት ኮንትራት ለመስጠት ማሰባቸው ተገልጿል።

ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ እንደሚያገኙ ሲገለፅ የአሰልጣኙ ዝውውር በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ በዝውውር መስኮቱ ይሳተፋሉ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ትልልቅ ዝውውሮች ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ በዝውውር መስኮቱ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ማሰባቸው ሲገለፅ አንድ ወይም ሁለት ጥሩ የመሐል ተከላካይ ለማስፈረም እንደሚንቀሳቀሱም ተዘግቧል።

በተጨማሪም ቼልሲዎች የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር በትኩረት ለመስራት መዘጋጀታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኩርቱዋ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አልቀረበለትም !

የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲቡዋ ኩርቱዋ በቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ስብስብ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።

በአሰልጣኝ ዶሜኒኮ ቴዴስኮ የሚመራው የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን በቀጣዩ የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ የሚጠቀመውን የቡድን ስብስብ አሳውቋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዳም ላላና ወደ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ ነው !

እንግሊዛዊው የብራይተን የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና በቀጣይ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሳውዝሀምፕተን ሊያመራ መሆኑ ተገልጿል።

በብራይተን ቤት ስድስት አመታትን ያሳለፈው አዳም ላላና በዚህ ክረምት ውሉ ሲጠናቀቅ ክለቡን እንደሚለቅ ማሳወቁ ይታወቃል።

የቀድሞ የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች አዳም ላላና አሁን ላይ ዝውውሩ ባይጠናቀቅም የቀድሞ ክለቡን ሳውዝሀምፕተን ከአስር አመታት በኋላ ይቀላቀላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ግሪንውድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

ሜሰን ግሪንውድ የላሊጋው ክለብ ሄታፌ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

ሜሰን ግሪንውድ በውድድር አመቱ ለሄታፌ ባደረጋቸው ጨዋታዎች አስር ግቦች አስቆጥሮ ስድስት ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

የውድድር አመቱን ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለሄታፌ በመጫወት ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ በሄታፌ እንደማይቀጥል ማሳወቁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አጓጊው ሪያል ማድሪድ ከ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት የሻምፒየንስ ሊጉ ፍፃሜ ጨዋታ ተቃርቧል!
ይህንን አጓጊ ጨዋታ አሸንፎ ማን የዋንጫው ባለቤት የሚሆን ይመስላችኋል? ይገምቱ!

ከሄኒከን ጋር አብረን እንመልከት
Forwarded from WANAW SPORT
📢 የአጋርነት ጥሪ ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች!

👉🏾 በሀገራችን ብሎም በተለያዩ የዓለማችን ክፍላት የተለያዩ የስፖርት አልባሳትን እያቀረበ የሚገኘው ዋናው ስፖርት ለስፖርት ዝግጅቶችና ፌስቲቫል አዘጋጆች ጋር ለተለያዩ የስፖርት ውድድሮች የሚሆኑ አልባሳትን በ5% ቅናሽ ከማቅረብ ጀምሮ በጋራ አብሮ ለመስራት ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ሊያበስርዎ ይወዳል።

👉🏾 #ያናግሩን#ውድድርዎን ከእኛ ጋር ያከናውኑ!

🔥 #ውድድር ካለ #ዋናው አለ! 🔥

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አንቾሎቲ ስራቸውን በማድሪድ ማጠናቀቅ ይፈልጋሉ !

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የአሰልጣኝነት ስራቸውን በሪያል ማድሪድ ቤት የማጠናቀቅ እቅድ እንዳላቸው በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በንግግራቸውም " አሰልጣኝነቴን በሪያል ማድሪድ ቤት አጠናቅቃለሁ ነገርግን መጀመሪያ ሌላ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማሸነፍ እፈልጋለሁ።"ብለዋል።

በሪያል ማድሪድ እስካለሁ በአሰልጣኝነቴ እቀጥላለሁ ያሉት አሰልጣኙ የአሰልጣኝነት ህይወቴ የሚያበቃው ግን እዚሁ ሪያል ማድሪድ ነው በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ሊሾሙ ነው ! ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ቼልሲን መቀላቀል እንደሚፈልጉ ለክለባቸው ማሳወቃቸው ሲገለፅ ሌስተር ሲቲ ከቼልሲ ጋር እንዲነጋገሩ ፍቃድ መስጠቱም ታውቋል። ቼልሲዎች በቀጣይ ለአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአምስት አመት ኮንትራት…
ቼልሲ አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሌስተር ሲቲውን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በሰማያዊዎቹ ቤት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የአምስት አመት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ አመት ከአንድ አመት በኋላ ወደ ፕርሚየር ሊግ የተመለሱት ሌስተር ሲቲዎች ከቼልሲ የካሳ ክፍያ እንደሚያገኙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 17:19:32
Back to Top
HTML Embed Code: