Telegram Web Link
#TkvahGoal

ለአራት ተከታታይ አመታት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ያሳካው ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር አክብረዋል።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#SerieA 🇮🇹

በጣልያን ሴርያ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብሮች ኢንተር ሚላን ከሄላስ ቬሮና ጋር 2ለ2 ሲለያዩ ሮማ በኢምፖሊ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የሴርያው አሸናፊ ኢንተር ሚላን የውድድር አመቱን ዘጠና አራት ነጥቦች በመሰብሰብ ማጠናቀቅ ችለዋል።

ሮማ በበኩላቸው በስልሳ ሶስት ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ኢምፖሊ ማሸነፉን ተከትሎ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት በሊጉ መቆየታቸውን ሲያረጋግጡ ፍሮሲኖን ለመውረድ ለገደዋል።

ፍሮሲኖን ፣ ሳሱሎ እና ሳለርኒታና ከጣሊያን ሴርያ መውረዳቸው የተረጋገጡ ሶስት ክለቦች ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታውን በድል አጠናቋል !

በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ባርሴሎና ከሲቪያ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ እና ፌርሚን ሎፔዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሲቪያ ኢን ነስሪ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና የውድድር አመቱን ሰማንያ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

ሲቪያ በበኩሉ አርባ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

በጨዋታው ስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን መርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ቼልሲ ማንን በሀላፊነት ይሾማል ?

ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች ስማቸው ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ሲያየዝ ቢቆይም የመጨረሻ እጩዎቹ ከታወቁ ሰንብቷል።

አስቀድሞ እጩ የነበሩት የ 38ዓመቱ ኬረን ማኬና የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ #ሳይካተቱ መቅረታቸው ተዘግቧል።

የቅጥር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለፀው ቼልሲዎች ኢንዞ ማርሴካ እና ቶማስ ፍራንክ ክለቡን ለመረከብ የቀረቡ የመጨረሻ እጩዎች ሆነዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መቆየት ብፈልግም እንደማልችል ተነግሮኛል “

ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር የተለያዩት አሰልጣኝ ዣቪ ቀጣዩ የቡድኑ አሰልጣኝ ትግስተኛ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

የመጨረሻ ቆይታቸውን ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን ባደረጉበት ወቅትም “ በተለያዩ ጊዜ ጫናዎች ነበሩብኝ ፣ በአጠቃላይ ስራዬን በአግባቡ መስራት አልቻልኩም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ዣቪ አዲስ የሚሾመው አሰልጣኝ እንደሚቸገር ሲያሳውቁ “ ትግስተኛ “ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

“ በክለቡ ለተጨማሪ ጊዜያት በሀላፊነት መቆየት እፈልግ ነበር ፣ ነገር ግን መቆየት እንደማልችል ተነግሮኛል” አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ

በክለቡ የሁለት አመት ከግማሽ የአሰልጣኝነት ቆይታ ሁለት ዋንጫዎችን ያሳኩት ዣቪ “ ለባርሴሎና ሁሌም መልካሙን እመኛለሁ “ ሲሉ ንግግራቸውን አገባደዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሉካ ሞድሪች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች የ2023/24 የውድድር አመት የክሮሽያ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

የአንድ ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሉካ ሞድሪች ለተከታታይ ስምንተኛ ጊዜ የክሮሽያ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።

ሉካ ሞድሪች አጠቃላይ የክሮሽያ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል ሲመረጥ ለአስራ ሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ቫላዶሊድ ወደ ላሊጋው አድጓል !

ሁለተኛውን የስፔን ሊግ በበላይነት እየመሩ የሚገኙት ሪያል ቫላዶሊድ ወደ ስፔን ላሊጋ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል።

በቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን እና ሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋች ሮናልዶ ናዛሪዮ በባለቤትነት የተያዘው ሪያል ቫላዶሊድ ከአንድ አመት በኋላ ወደ ላሊጋው መመለስ ችለዋል።

ሮናልዶ ናዛሪዮ በቅርቡ ከደጋፊዎች በሚደርሱት ለክለቡ ትኩረት አልሰጠህም የሚሉ ከፍተኛ ተቃውሞዎች ምክንያት ሪያል ቫላዶሊድን ለመሸጥ እንዳሰበ ገልፆ ነበር።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
"ዶርትመንድ ጠንካራ አጥቂዎች አሏቸው " አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሳምንቱ መጨረሻ ከዶርትመንድ ጋር ካለባቸው የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ምን አሉ ?

- " ጨዋታውን ቀለል አድርገን አንመለከተውም ዶርትመንድ ብቃት እንዳላቸው አሳይተዋል ፍፃሜ መድረስ ይገባቸዋል ከባድ ፍልሚያ እንደሚገጥመን እናውቃለን።

- ተጨዋቾቹ ሙሉ ትኩረታቸው ፍፃሜው ላይ ነው በድጋሜ ፍፃሜ ላይ በመገኘታችን ደስተኞች ነን ለእኔ ስድስተኛዬ ነው።

- ሪያል ማድሪድ ለእኔ የተለየ ክለብ ነው ከዚህ በፊት ላሰለጠንኳቸው ክለቦች ተመሳሳይ ነገር አልልም እኔ የሪያል ማድሪድ ደጋፊ ነኝ በክለቡ ውጤት እደሰታለሁ እበሳጫለሁ።

- በጨዋታው ለመከላከል መዘጋጀት አለብን ምክንያቱም ዶርትመንድ እንደ ሳንቾ እና አዴይሚ አይነት ጠንካራ አጥቂዎች አሏቸው ልክ እንደኛ ተፎካካሪ ቡድን ናቸው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ!

#Camon30Et #Camon30proEt #Camon30 #Camon30Pro #TecnoEt
Forwarded from WANAW SPORT
ብናሸነፍም፣ ብንሸነፍም - ሁሌም ተግተን እንስራ!
በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ይበልጥ ወደፊት እንግፋ።


#ዋናነት እሱ ነው!

እርስዎስ ዛሬ ምንድነው የሚሰሩት?

መልካም የስራ ሳምንት!
Happy Work Week!


Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ፖቼቲኖ መባረር አልነበረበትም " ሀዛርድ

ቤልጂየማዊው የቀድሞ የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲን ሀዛርድ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን ማሰናበታቸው የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑን ገልጿል።

" ውሳኔው ትንሽ አበሳጭቶኛል እንደእኔ ፖቼቲኖ ጥሩ ነገር ሰርቷል ፣ ሰዎች ቼልሲ ምርጥ አራት ውስጥ መመልከት እንደሚፈልጉ አውቃለሁ ነገርግን ቡድኑ ሽግግር ላይ ነበር ማን እንደሚተካው እናያለን።ሲል ኤዲን ሀዛርድ ተናግሯል።

ኤዲን ሀዛርድ አክሎም አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ታላቅ አሰልጣኝ መሆናቸውን በመግለፅ በቀጣይ ትልቅ ስኬት እንዲገጥማቸው እንደሚመኝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ በቅርቡ እንደሚወስን ተስፋ አደርጋለሁ “

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጫዋች ቪንሰስ ጁኒየር ምባፔ ቀጣይ ማረፊያውን በቅርብ ያሳውቃል የሚል እምነት እንዳለው ገልጿል።

“ በቅርቡ ከውሳኔ ላይ እንደሚደርስ ተስፋ አደርጋለሁ “ የሚለው ቪንሰስ “ ሁሌም የምፈልገው ከአለም ምርጦች ጋር አብሮ መጫወት ነው “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኬረን ማኬን ኮንትራታቸውን ሊያራዝሙ ነው !

በሊጉ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለጉ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬን አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ሊፈራረሙ መሆኑ ተዘግቧል።

ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ኬረን ማኬን ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል።

ቼልሲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ብራይተን የ 38ዓመቱን አሰልጣኝ ኬረን ማኬንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት የነበራቸው ክለቦች ነበሩ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/09/28 03:24:26
Back to Top
HTML Embed Code: