Telegram Web Link
ሳውዝሀምፕተን ወደ ፕርሚየር ሊግ ተመልሷል !

ባለፈው አመት ወደ ሻምፒየን ሽፑ የወረደው ሳውዝሀምፕተን ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በማሸነፍ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የሳውዝሀምፕተንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዳም አርምስትሮንግ ማስቆጠር ችሏል።

ሳውዝሀምፕተን ከአንድ የውድድር አመት የሻምፒየን ሽፕ ቆይታ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መመለስ ችለዋል።

ወደ ፕርሚየር ሊግ ያደጉ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ሌስተር ሲቲ

- ኢፕስዊች ታውን

- ሳውዝሀምፕተን

ከሊጉ ወደ ሻምፒየን ሽፑ የወረዱ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ሉተን ታውን

- በርንሌይ

- ሼፍልድ ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች እስራኤል እሸቱ እና ዓሊ ሱለይማን ከመረብ ሲያሳርፉ ለሀድያ ሆሳዕና ዳዋ ሁቴሳ አስቆጥሯል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስድስት በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

9️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 36 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 35 ነጥብ

*ከሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች በኋላ ያለው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሙሉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት የፕርሚየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲዎች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ፊል ፎደን ፣ ሮድሪ እና ኤርሊንግ ሀላንድ የማንችስተር ሲቲ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport      @kidusyoftahe
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲዎች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የማንችስተር ሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ፊል ፎደን ከዚህ በፊት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ይታወቃል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ሜሰን ግሪንውድ ከሄታፌ ጋር ይለያያል !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከላሊጋው ክለብ ሄታፌ ጋር እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የስንብት መልዕክት አረጋግጧል።

ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለሄታፌ እየተጫወተ አመቱን ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ ክለቡ ላደረገለት ጥሩ አቀባበል በስንብት መልዕክቱ አመስግኗል።

ሜሰን ግሪንውድ በውድድር አመቱ ለሄታፌ አስር ግቦች አስቆጥሮ ስድስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ተጨዋቹ በቀጣይ የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
የሻምፒዮን ሺፕ ፍፃሜ ብዙ ተመልካች አግኝቷል !

በሳውዝሀምፕተን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ ጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ ከእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የበለጠ ተመልካች ማግኘቱ ተነግሯል።

በዌምብሌይ ስታዲየም የተደረገው የሳውዝሀምፕተን እና ሊድስ ዩናይትድ የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ ጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ 85,862 ተመልካቾች በስታዲየም እንደተከታተሉት ተገልጿል።

በማንችስተር ዩናይትድ አሸናፊነት የተጠናቀቀውን የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 84,814 ተመልካቾች ተከታትለውት እንደነበረ ተዘግቧል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
#TkvahGoal

ለአራት ተከታታይ አመታት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ያሳካው ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር አክብረዋል።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#SerieA 🇮🇹

በጣልያን ሴርያ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብሮች ኢንተር ሚላን ከሄላስ ቬሮና ጋር 2ለ2 ሲለያዩ ሮማ በኢምፖሊ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የሴርያው አሸናፊ ኢንተር ሚላን የውድድር አመቱን ዘጠና አራት ነጥቦች በመሰብሰብ ማጠናቀቅ ችለዋል።

ሮማ በበኩላቸው በስልሳ ሶስት ነጥቦች ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ኢምፖሊ ማሸነፉን ተከትሎ ከወራጅ ቀጠናው በመውጣት በሊጉ መቆየታቸውን ሲያረጋግጡ ፍሮሲኖን ለመውረድ ለገደዋል።

ፍሮሲኖን ፣ ሳሱሎ እና ሳለርኒታና ከጣሊያን ሴርያ መውረዳቸው የተረጋገጡ ሶስት ክለቦች ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታውን በድል አጠናቋል !

በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ባርሴሎና ከሲቪያ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ሮበርት ሌዋንዶውስኪ እና ፌርሚን ሎፔዝ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሲቪያ ኢን ነስሪ አስቆጥሯል።

ባርሴሎና የውድድር አመቱን ሰማንያ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅ ችሏል።

ሲቪያ በበኩሉ አርባ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

በጨዋታው ስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን መርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5
•Playstaion 5 Slim

•PlayStation 4 Slim
•PlayStation 4 Pro

•Playstaion portal
•PlayStation VR

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ቼልሲ ማንን በሀላፊነት ይሾማል ?

ከአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ጋር የተለያዩት ቼልሲዎች ስማቸው ከበርካታ አሰልጣኞች ጋር ሲያየዝ ቢቆይም የመጨረሻ እጩዎቹ ከታወቁ ሰንብቷል።

አስቀድሞ እጩ የነበሩት የ 38ዓመቱ ኬረን ማኬና የመጨረሻ ዝርዝር ውስጥ #ሳይካተቱ መቅረታቸው ተዘግቧል።

የቅጥር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ የተገለፀው ቼልሲዎች ኢንዞ ማርሴካ እና ቶማስ ፍራንክ ክለቡን ለመረከብ የቀረቡ የመጨረሻ እጩዎች ሆነዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መቆየት ብፈልግም እንደማልችል ተነግሮኛል “

ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር የተለያዩት አሰልጣኝ ዣቪ ቀጣዩ የቡድኑ አሰልጣኝ ትግስተኛ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።

የመጨረሻ ቆይታቸውን ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን ባደረጉበት ወቅትም “ በተለያዩ ጊዜ ጫናዎች ነበሩብኝ ፣ በአጠቃላይ ስራዬን በአግባቡ መስራት አልቻልኩም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ዣቪ አዲስ የሚሾመው አሰልጣኝ እንደሚቸገር ሲያሳውቁ “ ትግስተኛ “ መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

“ በክለቡ ለተጨማሪ ጊዜያት በሀላፊነት መቆየት እፈልግ ነበር ፣ ነገር ግን መቆየት እንደማልችል ተነግሮኛል” አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ

በክለቡ የሁለት አመት ከግማሽ የአሰልጣኝነት ቆይታ ሁለት ዋንጫዎችን ያሳኩት ዣቪ “ ለባርሴሎና ሁሌም መልካሙን እመኛለሁ “ ሲሉ ንግግራቸውን አገባደዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/04 19:22:16
Back to Top
HTML Embed Code: