Telegram Web Link
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  21ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5293

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 21
ኢትዮጵያ ቡና ከሀምበሪቾ ዱራሜ
ዛሬ 09:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
ፒኤስጂ በዝውውር መስኮቱ በትኩረት ይሳተፋል !

ከፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ጋር የሚለያየው ፒኤስጂ በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርግ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ገልጸዋል።

ኪሊያን ምባፔን የሚተካላቸው ተጨዋቾች ፈፅሞ ማግኘት እንደማይቻል የገለፁት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ከእሱ የተለየ ተጨዋች ለማስፈረም እንጥራለን ብለዋል።

አሰልጣኙ ሲናገሩም በዝውውር መስኮቱ ፒኤስጂ #ስድስት የሚደርሱ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች ለማስፈረም የተቻለውን ጥረት እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TkvahGoal

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ ኤቨርተን ላይ ያስቆጠረው የመቀስ ምት ግብ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ግብ በመሆን መመረጥ ችሏል።

ግቡን በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጫማውን ሰቀለ !

ጣልያናዊው የቀድሞ ጁቬንቱስ አንጋፋ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሊዮናርዶ ቦኑቺ በአመቱ መጨረሻ ራሱን ከፕሮፌሽናል እግርኳስ እንደሚያገል በይፋ አስታውቋል።

የ 37ዓመቱ ተከላካይ ሊዮናርዶ ቦኑቺ አሁን ላይ ለቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ የሊግ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደርጋል።

ሊዮናርዶ ቦኑቺ ለቀድሞ ክለቡ ጁቬንቱስ ሶስት መቶ ሀምሳ አምስት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን ሀያ ሰባት ግቦችንም ማስቆጠር ችሏል።

ሊዮናርዶ ቦኑቺ በእግር ኳስ ህይወቱ ከጁቬንቱስ ጋር #ስምንት የጣሊያን ሴርያ እንዲሁም አንድ የአውሮፓ ዋንጫን ጨምሮ አስራ ስምንት ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከሀምበሪቾ ዱራሜ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ናስር 2x ፣ አማኑኤል ዮሀንስ ፣ አማኑኤል አድማሱ ፣ ጫላ ተሺታ እና ምንታምር መለሰ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል።

የሀምበሪቾ ዱራሜን ብቸኛ ግብ አላዛር አድማሱ ማስቆጠር ችሏል።

በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

ሀምበሪቾ ዱራሜ በውድድር አመቱ ሀያኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

4️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 44 ነጥብ

1️⃣6️⃣ ሀምበሪቾ ዱራሜ :- 8 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

ልዩ ዲዛይን እና ቴክኖሎጂ አጣምሮ የቀረበዉ Tecno Camon30 Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ!

#Camon30Et #Camon30Pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ባየር ሊቨርኩሰን የዋንጫ ድሉን በማክበር ላይ ነው !

የጀርመን ቡንደስሊጋ እና የጀርመን ፖካል ካፕ ዋንጫዎችን በማሳካት ጥሩ የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ባየር ሊቨርኩሰን የሁለት ዋንጫ ድሉን በስታዲየም ከደጋፊው ጋር በማክበር ላይ ነው።

ባየር ሊቨርኩሰን ሁለቱንም ውድድሮች ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ በማሳካት ደማቅ ታሪክ መፃፉ አይዘነጋም።

በጎል ቻናላችን በቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳውዝሀምፕተን ወደ ፕርሚየር ሊግ ተመልሷል !

ባለፈው አመት ወደ ሻምፒየን ሽፑ የወረደው ሳውዝሀምፕተን ከሊድስ ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በማሸነፍ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የሳውዝሀምፕተንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አዳም አርምስትሮንግ ማስቆጠር ችሏል።

ሳውዝሀምፕተን ከአንድ የውድድር አመት የሻምፒየን ሽፕ ቆይታ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መመለስ ችለዋል።

ወደ ፕርሚየር ሊግ ያደጉ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ሌስተር ሲቲ

- ኢፕስዊች ታውን

- ሳውዝሀምፕተን

ከሊጉ ወደ ሻምፒየን ሽፑ የወረዱ ክለቦች እነማን ናቸው ?

- ሉተን ታውን

- በርንሌይ

- ሼፍልድ ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች እስራኤል እሸቱ እና ዓሊ ሱለይማን ከመረብ ሲያሳርፉ ለሀድያ ሆሳዕና ዳዋ ሁቴሳ አስቆጥሯል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስድስት በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

9️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 36 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 35 ነጥብ

*ከሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብሮች በኋላ ያለው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሙሉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት የፕርሚየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲዎች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ፊል ፎደን ፣ ሮድሪ እና ኤርሊንግ ሀላንድ የማንችስተር ሲቲ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @tikvahethsport      @kidusyoftahe
የሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲዎች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የማንችስተር ሲቲ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ፊል ፎደን ከዚህ በፊት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጡ ይታወቃል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ሜሰን ግሪንውድ ከሄታፌ ጋር ይለያያል !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከላሊጋው ክለብ ሄታፌ ጋር እንደሚለያይ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የስንብት መልዕክት አረጋግጧል።

ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ለሄታፌ እየተጫወተ አመቱን ያሳለፈው ሜሰን ግሪንውድ ክለቡ ላደረገለት ጥሩ አቀባበል በስንብት መልዕክቱ አመስግኗል።

ሜሰን ግሪንውድ በውድድር አመቱ ለሄታፌ አስር ግቦች አስቆጥሮ ስድስት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ተጨዋቹ በቀጣይ የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ማንችስተር ዩናይትድን በቋሚ ዝውውር ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
የሻምፒዮን ሺፕ ፍፃሜ ብዙ ተመልካች አግኝቷል !

በሳውዝሀምፕተን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ ጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ ከእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የበለጠ ተመልካች ማግኘቱ ተነግሯል።

በዌምብሌይ ስታዲየም የተደረገው የሳውዝሀምፕተን እና ሊድስ ዩናይትድ የእንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ ጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ 85,862 ተመልካቾች በስታዲየም እንደተከታተሉት ተገልጿል።

በማንችስተር ዩናይትድ አሸናፊነት የተጠናቀቀውን የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ 84,814 ተመልካቾች ተከታትለውት እንደነበረ ተዘግቧል።

@tikvahethsport            @kidusyoftahe
2024/09/28 01:28:35
Back to Top
HTML Embed Code: