Telegram Web Link
የቡንደስሊጋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ይፋ ሆነ !

በባየር ሌቨርኩሰን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጀርመን ቡንደስሊጋ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የባየር ሌቨርኩሰን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፍሎሪያን ዊርትዝ የጀርመን ቡንደስሊጋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል በአብላጫ ድምጽ መመረጡ ተገልጿል።

የ 21ዓመቱ ፍሎሪያን ዊርትዝ በውድድር አመቱ ባደረጋቸው ሰላሳ ሁለት ጨዋታዎች አስራ አንድ ግቦችን አስቆጥሮ አስራ አንድ ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርጀንቲና ስብስቧን አሳውቃለች !

በአሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የሚመራው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ለሀያ ዘጠኝ ተጨዋቾች ጥሪ አቅርቧል።

ብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ካደረገላቸው ከሀያ ዘጠኝ ተጨዋቾች ውስጥ ለቀጣዩ የ2024 ኮፓ አሜሪካ ውድድር ሶስት ተጨዋቾች እንደሚቀንስ ተገልጿል።

ለኮፓ አሜሪካ ውድድር ዝግጅት የሚጀምረው ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ሳምንታት ከኢኳዶር እና ጓቴማላ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በመስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🏆 #የ2016_የኢትዮጵያ_ሴቶች_ከፍተኛ_ሊግ_ሻምፒዮን 🏆

የ2016 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ በቂርቆስ ክፍለከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ዋናው ስፖርትም ለክለቡ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አስቶን ቪላ ሮስ ባርክሌይን ማስፈረም ይፈልጋል !

አስቶን ቪላ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮስ ባርክሌይ ወደ ሻምፒዮን ሽፑ ከወረደው ሉተን ታውን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ከሉተን ታውን ጋር በግሉ ጥሩ የሚባል የውድድር አመት ማሳለፍ የቻለው ሮስ ባርክሌይ አስቶን ቪላን መቀላቀል እንደሚፈልግ ተገልጿል።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው ክለብ አስቶን ቪላ ሮስ ባርክሌይ ቡድኑን ለማጠናከር ትክክለኛው ተጨዋች ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርኔ ስሎት ሊቨርፑልን እንደሚረከቡ ይፋ አደረጉ ! ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሚቀጥለው የውድድር አመት የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል። አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በዛሬው እለት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕን በመተካት የሊቨርፑል ቀጣይ አሰልጣኝ በመሆን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል። አሰልጣኙ በንግግራቸውም " በሚቀጥለው የውድድር አመት የሊቨርፑል…
ሊቨርፑል በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ምትክ ኔዘርላንዳዊውን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በትላንትናው ዕለት በይፋ ክለቡን ተሰናብተው ሊቨርፑልን መልቀቃቸው ይታወቃል።

ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሶስት አመት ውል መፈረማቸው ሲነገር ከአስር ቀናት በኋላ ሊቨርፑልን ተረክበው ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቴንሀግ የሚቀጥል አይመስለኝም "ፈርዲናንድ

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንዴ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በሚቀጥለው የውድድር አመት በሀላፊነታቸው ላይቆዩ እንደሚችሉ ተናግሯል።

" አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቀጣይ አመት በክለቡ ይቀጥላል ብዬ አልጠብቅም " ያለው ሪዮ ፈርዲናንድ የምፈልገው ይህንን ነው ማለቴ ሳይሆን የማስበው ይህ ነው በማለት ተናግሯል።

ሪዮ ፈርዲናንድ አያይዞም ማንችስተር ዩናይትድ በኤፌ ካፕ የሚያስመዘግበው ውጤት በአሰልጣኙ ቀጣይነት ላይ በ " INEOS " በኩል የሀሳብ ለውጥ ያመጣል ብሎ እንደማያምን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መሐመድ ሳላህ በሊቨርፑል ቤት ይቆያል !

ግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በሚቀጥለው አመት በሊቨርፑል ቤት እንደሚቀጥል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አረጋግጧል።

" ዋንጫ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን በሚቀጥለው አመት ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ደጋፊዎቻችን ይገባቸዋል ፣ ለዚህ በደንብ እንፋለማለን።"ሲል ሳላህ በማህበራዊ ጉፁ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ከቦሎኛ ነጥብ ተጋርተዋል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከቦሎኛ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቦሎኛን ግብ ሪካርዶ ካላፊዮሪ 2x እና ካስትሮ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለጁቬንቱስ የአቻነት ግቦችን ቼሳ ፣ ሚሊክ እና ይልዲዝ አስቆጥረዋል።

ሶስት ለባዶ ሲመራ የቆየው ጁቬንቱስ በጨዋታው መጋባደጃ ደቂቃዎች በሰባት ደቂቃዎች ውስጥ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር አቻ መሆን ችለዋል።

ጁቬንቱስ ያለፉትን #ስድስት የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ቦሎኛ :- 68 ነጥብ

4️⃣ ጁቬንቱስ :- 68 ነጥብ

በሊጉ የመጨረሻ መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከሞንዛ እንዲሁም ቦሎኛ ከጂኖኣ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•MacBook Air, M1
•MacBook Pro, M1

•MacBook Air, M2
•MacBook Pro, M2

•MacBook, M1 Pro
•MacBook, M2 Pro

•MacBook, M1 Max
•MacBook, M2 Max

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ፎደን ባሎን ዶር ሊያሸንፍ ይችላል " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋቻቸው ፊል ፎደን የዘንድሮውን የባሎን ዶር ሽልማት ሊያሸንፍ እንደሚችል ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በንግግራቸውም " ፊል ፎደን ከእንግሊዝ ጋር የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድርን ማሳካት ከቻለ የባሎን ዶር ሽልማት ሊያሸንፍ ይችላል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ፊል ፎደን በዚህ አመት ለማንችስተር ሲቲ ጥሩ ግልጋሎት ሲሰጥ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎም መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤንጃሚን ሴስኮ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

የጀርመኑ ክለብ ሌፕዚግ የፊት መስመር ተጨዋች ቤንጃሚን ሴስኮ በሳውዲ አረቢያ ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ ወኪሉ ገልጿል።

ወኪሉ አያይዞም ተጨዋቹ አሁን ላይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የመሄድ እቅድ እንደሌለው የገለጸ ሲሆን የፕርሚየር ሊግ እና ሴርያ ክለቦችም ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግሯል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በሚቀጥለው ክረምት ለማስፈረም በዝርዝራቸው ውስጥ ከያዟቸው አጥቂዎች አንዱ ቤንጃሚን ሴስኮ መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፕርሚየር ሊግ ተፎካካሪነቱ ጠፍቷል " - አግቦላሆር

የቀድሞ እንግሊዛዊ የአስቶን ቪላ ተጨዋች ጋብሬል አግቦላሆር የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በአሁን ሰዓት ተፎካካሪነቱን በማጣት በማንችስተር ሲቲ ቁጥጥር ስር መሆኑን ገልጿል።

" ማንችስተር ሲቲ ለአራት ተከታታይ አመታት ሊጉን በማሳካት የሚደንቅ ስኬት አስመዝግቧል " የሚለው የቀድሞ ተጨዋቹ ፕርሚየር ሊግ በአሁን ሰዓት ተፎካካሪነቱን አጥቶ " Farmers league " ሆኗል ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ወደ ፈረንሳይ አምርተዋል !

የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በዛሬው ዕለት ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ማምራታቸው ተገልጿል።

ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ በፓሪስ ቆይታቸው ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በኦሎምፒክ ተሳታፊ የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ሪያል ማድሪድ በቀጣዩ ኦሎምፒክ ፈረንሳዊ ተጨዋቾችን ለመላክ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ቀድሞ ያሳወቀ ሲሆን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው በውድድሩ ምርጥ ተጨዋቾች ማካተት እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

በተጨማሪም የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቅርቡ ኪሊያን ምባፔ የኦሎምፒክ ቡድኑን እንዲመራ ቀጣይ ማረፊያው የሚሆነውን ክለብ እንደሚያነጋግሩ ጠቁመው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሄንደርሰን ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ አይቀርብለትም !

እንግሊዛዊው የአያክስ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን በብሔራዊ ቡድኑ የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ስብስብ ውስጥ አለመካተቱ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ዛሬ ከሰዓት ስብሰባቸውን ይፋ እንደሚያደርጉ ሲጠበቅ የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ጆርዳን ሄንደርሰን ጥሪ እንደማይቀርብለት ተነግሯል።

በሌላ በኩል የሊቨርፑሉ ተጨዋች ከርትስ ጆንስ እና የበርንሌይ ግብ ጠባቂ ጄምስ ትራፎርድ ለብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የቡድን ስብስብ ጥሪ ይቀርባላቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲን ሊለቅ ይችላል !

ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በሚቀጥለው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ተገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች አሁን ላይ ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ከቀረቡለት በውድድር አመቱ መጨረሻ ለመመልከት ዝግጁ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

Tech – art leather ቴክኖሎጂ በመጠቀም እጅግ ዘመናዊ ዲዛይን የተላበሰው አዲሱ Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድረጉ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt  #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
2024/10/05 15:25:08
Back to Top
HTML Embed Code: