Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው! እንዳያመልጥዎ!
Barcelona - Real Sociedad
Aston Villa - Liverpool
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 60,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ቦሎኛ በሻምፒየንስ ሊጉ ይሳተፋል !

ጥሩ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የጣልያን ሴርያው ክለብ ቦሎኛ ለሚቀጥለው የውድድር አመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

ቦሎኛ ከስልሳ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናሉ።

በአሰልጣኝ ቲያጎ ሞታ የሚመራው ቦሎኛ ካለፉት አስራ ስድስት የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፈው በሻምፒዮኑ ኢንተር ሚላን ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አሁን መጸለይ ነው ያለብን " ሳሊባ

ፈረንሳዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ ቡድናቸው አሁን ማድረግ ያለበት መፀለይ መሆኑን ተናግሯል።

ቀጣይ ለእኛ ጥሩ ሳምንት እንደሚሆንልን ተስፋ አደርጋለሁ ያለው ዊሊያም ሳሊባ " ነገርግን አሁን ሁላችንም መጸለይ አለብን ፣ ማመን እና ኤቨርተንን ማሸነፍ አለብን " ሲል ተደምጧል።

አርሰናል የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ ቀሪ አንድ ጨዋታውን አሸንፎ የማንችስተር ሲቲን ነጥብ መጣል ይጠብቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ አመታዊ ፕሮግራሙን ሰርዟል !

ማንችስተር ዩናይትድ በየአመቱ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ የሚያዘጋጀውን አመታዊ የሽልማት ስነ-ስርዓት በዚህ አመት መሰረዙ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የሽልማት ስነ-ስርዓቱ እና የክለቡ የእራት ምሽት ቢቀርም ተጨዋቾቹ ሽልማቱ እንደሚበረከትላቸው ተነግሯል።

ክለቡ የሽልማት ስነ-ስርዓቱን ከኤፌ ካፕ ፍፃሜ አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም የተጨዋቾች ትክረት ላለመከፋፈል እና ፍፃሜው ላይ ለማተኮር መሰረዙን ገልጿል።

ጥሩ ያልሆነ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት ከማንችስተር ሲቲ ጋር በኤፌ ካፕ ፍፃሜ ይፋለማሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ተጨዋች ታውቋል !

የፈረንሳይ ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ጋቦናዊው የኦሎምፒክ ማርሴይ የፊት መስመር ተጨዋች ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ የፈረንሳይ የአመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ በዘንድሮው የውድድር አመት በአርባ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ በማድረግ ድንቅ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል።

የፒኤስጂው ተጨዋች አሽራፍ ሀኪሚ እና የሊሉ ተጨዋች ናቢል ቤንታሌብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሮማንያው ክለብ ምርመራ መጀመሩን ገለፀ !

የሮማንያው ክለብ ዳይናሞ ቡካሬስት በቅርቡ ያስፈረሙት የክለቡ ተከላካይ ኤጃር ሊ መንታ ወንድሙ ቢያንስ በአምስት ጨዋታዎች ተተክቶ እንዲጫወት ልኮታል በሚል ለማጣራት ምርመራ መጀመሩን ገልጿል።

ክለቡን ለምርመራ ያነሳሳው የቀድሞ የባርሴሎና ታዳጊ ተጨዋች ኤጃር ሊ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ተዘዋውሮ ቢጫወትም እንግሊዝኛ ቋንቋ አለመቻሉ እና በፖርቹጊዝ ብቻ መግባባቱ መሆኑ ተነግሯል።

መንታ ወንድሙ በአንፃሩ ሙሉ የእግርኳስ ህይወቱን ያሳለፈው ፖርቹጋል ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የሲቲ ታዳጊዎችን እንኳን ማቆም ከባድ ነው " ሞይስ

የዌስትሀም ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ቡድናቸው እሁድ ማንችስተር ሲቲን ዋንጫ ከማሸነፍ ያስቆማል የሚል ሙሉ እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ማንችስተር ሲቲ ጠንካራ መሆኑን የገለፁት አሰልጣኝ ዴቪዲ ሞይስ እሁድ ዌስትሀም ሲቲን ማስቆም ይችል እንደሆነ ሲጠየቁ " ከ 14ዓመት በታች ቡድናቸውንም ማቆም ከባድ ነው " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🚀 #ነፃ ዴሊቨሪ አገልግሎት ከ #ዋናው! 🚀

👉🏾 ከዋናው ከ 20 ብዛት በላይ የመረጡትን የስፖርት አልባሳት ሲያዙና ሲገዙ ባሉበት የሚያመጣልዎ የነፃ የዴሊቨሪ አገልግሎት ያገኛሉ። ስለሚመርጡን እጅግ እናመሰግናለን።

👉🏾 ምርጫዎትን ይንገሩን፣ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ናይጄሪያ አዲስ አሰልጣኝ በይፋ ሾመች !

የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ተፋላሚ የነበረው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

የናይጄሪያ ስፖርት ሚኒስቴር ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ የቀድሞ ናይጄሪያዊ ተጨዋች ፊንዲ ጆርጅ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል።

ዘ ሱፐር ኤግል በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በምክትል አሰልጣኝነት ሌላኛውን የቀድሞ ተጨዋች ዳንኤል አሞካቺ መሾሙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንማውዝ የአሰልጣኙን ውል አራዘመ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ በርንማውዝ የአሰልጣኝ አዶኒ ኢራኦላን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ስፔናዊው አሰልጣኝ አዶኒ ኢራኦላ በበርንማውዝ ቤት አስከ 2026 የሚያቆያቸውን የተጨማሪ ሁለት አመት ኮንትራት መፈረማቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቶተንሀምን ካላሸነፍን ሊጉን አናሸንፍም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው በነገው የቶተንሀም ጨዋታ ከማሸነፍ ውጪ ምንም ምርጫ እንደሌለው ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

" ቶተንሀምን ካላሸነፍን ዋንጫውን ማሸነፍ አንችልም " ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ ነገ ምንም አማራጭ የለንም ምርጫው አንድ ነው ማሸነፍ ብቻ የምንጓዘውም ለዚሁ ነው ብለዋል።

" እንግሊዝ ውስጥ ለአራት ተከታታይ አመታት ሊጉን ለማሳካት እና የተለየ አዲስ ታሪክ ለመፃፍ እድሉ በእጃችን ነው ልንጠቀምበት ይገባል።" ጋርዲዮላ

ማንችስተር ሲቲ በነገው ጨዋታ ማንን ያጣል ?

- ጃክ ግሪሊሽ ከህመሙ አገግሞ ወደ ልምምድ ተመልሷል።

- ናታና አኬ ያጋጠመው ጉዳት ቀላል ነው ቀሪ ቡድኑ ዝግጁ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከሲቲ ያለንን ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን " ፖስቴኮግሉ

የቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በነገው እለት ከማንችስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን ጨዋታ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ በንግግራቸውም " ለማንችስተር ሲቲ ክብር አለን ፔፕ ጋርዲዮላ ትልቅ ነገር እየሰሩ ነው ነገርግን ነገ ከእነሱ ጋር ያለንን ጨዋታ ለማሸነፍ ነው ወደ ሜዳ የምንገባው።"ብለዋል።

የቶተንሀምን መሸነፍ ስለሚፈልጉ የቶተንሀም ደጋፊዎች የተጠየቁት አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ " በማህበራዊ ሚዲያ ያሉ ደጋፊዎች እንድንሸነፍ ይፈልጋሉ ነገርግን አብዛኛውን ደጋፊ አይወክሉም።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዲ ዘርቢ ለምን ምርጥ እንደሚባል አይገባኝም " ካፔሎ

የቀድሞ ጣልያናዊ ተጨዋች ፋቢዮ ካፔሎ የብራይተኑ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከምርጥ አሰልጣኞች አንዱ እንደሆኑ መነገሩ እንዳላሳመነው ተናግሯል።

" ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በአሰልጣኝነት ህይወቱ ምን ያሳካው ነገር አለ ? " ሲል የሚጠይቀው ፋቢዮ ካፔሎ በዚህ አመት ከዘጠኝ እስከ አስራ አንድ ቢጨርሱ ነው ለምን ከምርጥ አሰልጣኞች አንዱ ተደርጎ እንደሚወራ አይገባኝም ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦሊቬ ጅሩ ሎስአንጀለስን ለመቀላቀል ተስማማ ! ፈረንሳዊው የኤሲ ሚላን የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ሎስአንጀለስ እግር ኳስ ክለብን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። በጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ቤት ያለው ውል ቀጣይ ክረምት የሚጠናቀቀው ኦሊቬ ጅሩ ለሎስአንጀለስ የሁለት አመት ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል። @tikvahethsport    …
ኦሊቬ ጅሩ ከኤስ ሚላን ጋር ይለያያል !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦሊቬ ጅሩ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ከኤሲ ማላን ጋር እንደሚለያይ ይፋ ተደርጓል።

ኦሊቬ ጅሩየአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩን ሎስአንጀለስ እግር ኳስ ክለብን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ አይዘነጋም።

ኦሊቬ ጅሩ ሲናገርም " እዚህ ኤሲ ሚላን ውስጥ ባደረኩት ነገር እኮራለሁ የመጨረሻ ጨዋታ በማድረግ በቀጣይ ወደ አሜሪካ አመራለሁ " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታን ማን ይመራዋል ?

ሪያል ማድሪድ ከ ቦርስያ ዶርትመንድ ጋር የሚያደርጉትን የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት የመሐል ዳኛ ይፋ ተደርገዋል።

እንግሊዝ ለንደን ዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ ስሎቬኒያዊው ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

የ 44ዓመቱ ዳኛ ስላቭኮ ቪንቺክ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሪያል ማድሪድ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመሩ ይሆናል።

ቦርስያ ዶርትመንድ በስላቭኮ ቪንቺክ እየተመራ ያደረገውን አንድ ጨዋታ በአሸናፊነት መወጣት ችሏል።

የሁለቱ ክለቦች ተጠባቂ የፍፃሜ ጨዋታ ከአስራ ዘጠኝ ቀናት በኋላ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስለ አርሰናል አይመለከተንም ሲቲን ለማሸነፍ እንገባለን " ኩሉሴቭስኪ

ስዊድናዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ኩሉሴቭስኪ ቡድናቸው በነገው ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል።

እግርኳስ ከተጫወትክ ለማሸነፍ መሆን አለበት በማለት ያስረዳው ተጨዋቹ ስለዚህ ነገ ወደ ሜዳ የምንገባው ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ነው ሲል ተደምጧል።

" ማንችስተር ሲቲን ካሸነፍነው አርሰናል ሻምፒዮን ስለመሆኑ አይመለከተንም እኔ የደረጃ ሰንጠረዡን አልከታተልም።" ሲል ኩሉሴቭስኪ ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፓላስ ለአሰልጣኙ ከፍተኛ የካሳ ክፍያ ጠየቀ !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሙኒክ የክሪስታል ፓላሱን አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነር የአሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ተተኪ ለማድረግ ያደረጉት ሙከራ አለመሳካቱ ተገልጿል።

ባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ኦሊቨር ግላስነርን ለመውሰድ ለክሪስታል ፓላስ 18 ሚልዮን ዩሮ የካሳ ክፍያ ቢያቀርቡም ፓላስ ለመልቀቅ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ተነግሯል።

ክሪስታል ፓላስ ለአሰልጣኙ የካሳ ክፍያ የሚሆን 100 ሚልዮን ዩሮ ባየር ሙኒክ እንዲከፍላቸው መጠየቃቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አስቶን ቪላ ከ ሊቨርፑል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/25 22:59:07
Back to Top
HTML Embed Code: