Telegram Web Link
1 ' አስቶን ቪላ 0 - 1 ሊቨርፑል

ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
12 ' አስቶን ቪላ 1 - 1 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ             ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
23 ' አስቶን ቪላ 1 - 2 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ       ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )
ጋክፖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | አስቶን ቪላ 1 - 2 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ             ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )
                                  ጋክፖ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
47 ' አስቶን ቪላ 1 - 3 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ             ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )
                                  ጋክፖ
ኳንሳህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
84 ' አስቶን ቪላ 2 - 3 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ             ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )
  ዱራን                   ጋክፖ
                                   ኳንሳህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 ' አስቶን ቪላ 3 - 3 ሊቨርፑል

ቴሌማንስ             ማርቲኔዝ ( በራስ ላይ )
  ዱራን                ጋክፖ
                                   ኳንሳህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ድል አድርጓል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ ሰላሳ አምሰሰተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባርሴሎናንን የማሸነፊያ ግቦች ላሚን ያማል እና ራፊንሀ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሁለቱ ክለቦች ደረጃ ምን ይመስላል ?

2️⃣ ባርሴሎና - 76 ነጥብ

7️⃣ ሪያል ሶሴዳድ - 54 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - አልሜርያ ከ ባርሴሎና

ሐሙስ - ሪያል ሶሴዳድ ከ ቫሌንሽያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ነጥብ ተጋርተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐግብር ሊቨርፑል ከአስቶን ቪላ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሊቨርፑልን ግቦች ኮዲ ጋክፖ ፣ ኳንሳህ እና ማርቲኔዝ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ለአስቶን ቪላ የአቻነት ግቦችን ጆን ዱራን 2x እና ዩሪ ቴሌማንስ ማስቆጠር ችለዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ ሊቨርፑል :-  79 ነጥብ

4️⃣ አስቶን ቪላ :- 68 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ሊቨርፑል ከ ዎልቭስ

እሁድ - ክሪስታል ፓላስ ከ አስቶን ቪላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 WANAW 🤝 ESFNA 🇺🇸

ዋናው ስፖርት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው 41ኛው ዓመታዊ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ስፖንሰር እና የተወዳዳሪዎች ይፋዊ የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ በመሆኑ የተሰማውን ታላቅ ኩራት ይገልፃል።

Wanaw Sport is very proud to announce that it is the Official Kit Supplier and Festival Sponsor of the 41st ESFNA 2024 ATLANTA Festival and Sports Competition organized by The Ethiopian Sports Federation in North America.

#ውድድር ካለ #ዋናው አለ!

When there's
#competition, there's #Wanaw!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ካናዳ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት ሾመች !

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣዩ የኮፓ አሜሪካ ውድድር የሚሳተፈው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑን የቀድሞ የሊድስ ዩናይትድ አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ በሀላፊነት በሀላፊነት መረከባቸው ተገልጿል።

አሜሪካዊው አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ የካናዳ ብሔራዊ ቡድንን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ለማሰልጠን መስማማታቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰርጅዮ ራሞስ ወደ አሜሪካ ?

ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሰርጅዮ ራሞስ በቀጣይ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ አሜሪካ ሊያመራ እንደሚችል ተገልጿል።

ሰርጅዮ ራሞስ አሁን ላይ ከስምምነት ባይደርስም ከአሜሪካው ክለብ ሳን ዲያጎ ጋር ንግግር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተከላካይ ሰርጅዮ ራሞስ ከሲቪያ ጋር ያለው የአንድ አመት ውል በአመቱ መጨረሻ ሲጠናቀቅ ከኮንትራት ነፃ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዩናይትድ ቴንሀግን የሚሰራውን የማያውቅ አስመስሎታል "

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድን መረከባቸው የሚሰሩትን የማያውቁ አሰልጣኝ እንዳስመሰለው ተናግሯል።

" ከሁለት አመታት በፊት ኤሪክ ቴንሀግ በአውሮፓ ካሉ ምርጥ አዲስ አሰልጣኝ አንዱ ተደርገው ይታሰቡ ነበር " የሚለው ጋሪ ኔቭል አሁን ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርጉትን የማያውቁ አስመስሏቸዋል ብሏል።

ጋሪ ኔቭል ቀጥሎም በማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ያለው በተከታታይ አሰልጣኝ የማሰናበት ነገር ሊቆም እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአርሰናል ደጋፊዎች የሲቲን ተጨዋቾች ለመረበሽ ሞክረዋል !

በበሊጉ ዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኙት አርሰናል ደጋፊዎች የተፎካካሪያቸው ማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች አርፈውበታል ተብሎ የታሰበ ሆቴል ለመረበሽ መሞከራቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ከቶተንሀም ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ሰሜን ለንደን በማምራት የሚያደርግ ይሆናል።

የመድፈኞቹ ደጋፊዎች የሲቲ ተጨዋቾች አርፈውበታል ወደተባለ ሆቴል በመሄድ ተጨዋቾቹ ላይ የርችት ድምፅ በማሰማት እና ተቀጣጣይ ነገሮች በመያዝ ለመረበሽ መሞከራቸው ተነግሯል።

ይሁን እንጂ የማንችስተር ሲቲ ልዑክ ለንደን መድረሱ አለመረጋገጡ እና ሆቴል አርፈዋል ተብሎ የተነገረው መረጃ እውነተኝነቱ ያልተረጋገጠ መሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኛ ገንዝብ ሳይሆን ልዩ ነገር አለን " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከባድ ውድድር እንዲሆን ያደረገው ቡድናቸው በየአመቱ በመኖሩ መሆኑን ገልጸዋል።

" ፕርሚየር ሊግ ከባድ ነው ምክንያቱም እኛ በየአመቱ እዚህ አለን " ያሉት ጋርዲዮላ ይህ በገንዘብ ወይም ለተጨዋቾቹ በምነግራቸው ጥሩ ቃላት ምክንያት አይደለም የምናደርገው ነገር ሁሉ ልዩ ነገር ስላለን ነው ብለዋል።

" ምክንያቱ ገንዘብ ከሆነ ዩናይትድ ፣ ቼልሲ እና አርሰናል በተከታታይ ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ አለባቸው ባለፉት አምስት አመታት ከማንችስተር ሲቲ በላይ አውጥተዋል።" ጋርዲዮላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራፋኤል ቫራን ከዩናይትድ ጋር ይለያያል !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በውድድር አመቱ መጨረሻ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ይፋ አድርጓል።

ተጨዋቹ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ውሉን ለማራዘም ከስምምነት መድረስ እንዳልቻለ እና በነፃ ዝውውር ክለቡን እንደሚለቅ ተገልጿል።

ራፋኤል ቫራን ለደጋፊዎቹ ባስተላለፈው የስንብት መልዕክትም " ሁላችሁንም ለመሰናበት በአመቱ የመጨረሻ የኦልድትራፎርድ ጨዋታ አገኛችኋለሁ ቀኑ ለእኔ አሳዛኝ ይሆናል " በማለት ተናግሯል።

የ 31ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ባሳለፈባቸው ሶስት የውድድር አመታት

- ዘጠና ሶስት ጨዋታዎች አደረገ

- ሁለት ግቦች አስቆጠረ

- አንድ የካራባኦ ካፕ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚽️ የፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች አጓጊነታቸው ጨምሯል፡፡

👉 ዛሬ ምሽት ቶተንሃም ከማን ሲቲ የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ በኳስ ወዳጆች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ቶተንሃም ቻምፒየንስ ሊጉን መሳተፍ ይችላል?

🤔 እርስዎስ ምን ይላሉ?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ሁሉንም የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎችን ይከታተሉ።

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
" ለማድሪድ የምባፔ መምጣት ዋንጫ አያረጋግጥለትም "

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን ማስፈረሙ የላሊጋውን ዋንጫ በበላይነት ለማሸነፍ ዋስትና እንደማይሆነው ተናግረዋል።

" የኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ መምጣት ዋንጫ የማሸነፍ ዋስትና አይሆንም " ያሉት ፕሬዚዳንቱ ባርሴሎናም ከላሚን ያማል ፣ ፔድሪ እና ጃቪ ጋር ተፎካካሪ ይሆናል ብለዋል።

ስለ ዝውውሩ የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ " ኪሊያን ምባፔ ማድሪድን ተቀላቅሏል ማለት ይቻላል ከቀጣይ አመት ጀምሮ ለአምስት አመታት ስፔን ውስጥ እንመለከተዋለን " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ስለ አርሰናል አይመለከተንም ሲቲን ለማሸነፍ እንገባለን " ኩሉሴቭስኪ ስዊድናዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ኩሉሴቭስኪ ቡድናቸው በነገው ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል። እግርኳስ ከተጫወትክ ለማሸነፍ መሆን አለበት በማለት ያስረዳው ተጨዋቹ ስለዚህ ነገ ወደ ሜዳ የምንገባው ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ነው ሲል ተደምጧል። " ማንችስተር ሲቲን ካሸነፍነው…
" የቶተንሀም ተጨዋቾች እንደ ደጋፊው አያስቡም "

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ዊሊያም ጋላስ በዛሬው የቶተንሀም እና ማንችስተር ሲቲ ጨዋታ የቶተንሀም ተጨዋቾች እንደ ደጋፊው አይነት አስተሳሰብ እንደማይኖራቸው ገልጿል።

ቶተንሀም ከአርሰናል ጋር ትልቅ ባላንጣ እንደሆኑ እናውቃለን ነገርግን ይህ የሚያሳስበው ደጋፊዎችን ብቻ
ነው የተጨዋቾቹን ሀሳብ አይቀይረውም በማለት ዊሊያም ጋላስ ተናግሯል።

" የቶተንሀም ደጋፊዎች አርሰናል ዋንጫ ከሚያሸንፍ ቡድናቸው በሲቲ ተሸንፎ በሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍ እንደሚመርጡ እናውቃለን ነገርግን ተጨዋቾቹ የተወለዱት ሰሜን ለንደን አይደለም አስተሳሰባቸው ይለያያል።" ዊሊያም ጋላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 20:52:04
Back to Top
HTML Embed Code: