Telegram Web Link
@Orthodox_Mastawekiya_bot
@Welde_kirkos
ለ ሁለቱ ቻናላችሁ ላይ add አድርጉና Admin አድርጋቸው
ትንቢተ ኢሳያስ 53፥4
4፤በእውነት፡ደዌያችንን፡ተቀበለ፡ሕመማችንንም፡ተሸክሟል፤እኛ፡ግን፡እንደ፡ተመታ፡በእግዚአብሔርም፡
እንደ፡ተቀሠፈ፡እንደ፡ተቸገረም፡ቈጠርነው።
5፤ርሱ፡ግን፡ስለ፡መተላለፋችን፡ቈሰለ፥ስለ፡በደላችንም፡ደቀቀ፤የደኅንነታችንም፡ተግሣጽ፡በርሱ፡ላይ፡
ነበረ፥በርሱም፡ቍስል፡እኛ፡ተፈወስን።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ
ክፍል አንድ
መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው? 🗝
መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ እንደሚያመለክተው መጽሐፍ እና ቅዱስ የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ነው ፡፡
★“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች የሚጠቀለል መጽሐፍ ያመለክታል፡፡ ይህ ስም ቢብሎስ (byblos) ከተባለ ከተማ ስም የተገኘ ነው ፤ እርሱም ከኒቂያ ወደቦች መካከል በቤይሩት 25 ማይል ያህል ርቆ የሚገኝ አገር ነው ፡፡ ለመጽሐፍ ያገለግል ዘንድ ፓፒረስ (ደንገል) የተባለውን ተክል እንደ ወረቀት አድርገው ይሠሩበት የነበረ ቦታ ነው ፡፡ቢብሎስ በእንግሊዘኛው ባይብል ተብሎ ሲተረጎም በአማርኛው ደግሞ መጽሐፍ በሚለው የግብር ስም ቃል ተተረጐመ ፡፡
★“ቅዱስ” (holy)የሚለውን ስናይ ደግሞ ልዩ፣ክቡር ለእግዚአብሔር የተለየ ማንኛውንም ነገርን ያመለክታል፡፡እግዚአብሔር በራሱ ከፍጥረታት ልዩ ነው፣ ከጣኦታት የተለየ ነው መንፈሱም(ሐሳቡም) ከክፋት ሐሳብ የተለየ ስለሆነ ቅዱስ ነው፡፡ጠቅለል አድርገን ስናየው ስለ ቅዱሱ እግዚአብሔር ያለፈውም መጪውም ስራ፣በመረጣቸውና ባመኑበት ሰው ልጆች ላይ ያደረገውንና ያለው ሐሳቡ ፈቃዱ ወዘተ ላይ የሚያወራ መጽሐፍ ስለሆነ ቅዱስ መጽሐፍ ተብሏል፡፡በእንግሊዘኛውም “holy bible” በማለት ይጠራል፡፡
☞ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት ክፍሎችን የያዘ ነው::የመጀመርያው ክፍል #ብሉይኪዳን ሲሆን የእግዚአብሔር የድሮው መሐላ(የአብርሐም ዘር እንደሚበዛና ከንአን ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው ምድር እንደሚሰጠው በዘሩም አለሙ ሁሉ እንደሚባረክ)የሚገልጽ ሲሆን
እግዚአብሔር ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ጀምሮ ስለ ሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ክብር መለየት አወዳደቅና በምድር ላይ መብዛት
በእግዚአብሔር ስለ ተወደደ አብርሐምና በዘሩ ዓለም እንደሚባረክ መሐላ
ስለ የያእቆብ ልጆች ወደ ግብጽ መሰደድና ከባርነት በእግዚአብሔር ድንቅ ረዲኤት መመለስ
ስለ እስራኤል መንግስት መመስረት መስፋትና የነገሥታቱ ታሪክ
መዝሙራትና ምሳሌያዊ የጥበብ ትምህርቶችን
ስለ ሰው ልጅ ወደ እግዚአብሔር ክብርና ፍቅር መመለስ ትንቢት ማለትም እግዚአብሔር ዓለሙን እንደሚያድንና ስለ እስራኤል ህዝብ ትንቢቶችን ይዟል::
☞ሁለተኛው ክፍል ደግሞ #ሐዲስኪዳን ሲሆን ለአብርሐም በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ ያለውን ያ ዘር ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ አለሙን በደሙ መስዋዕትነት ቀድሶ የሰውን ልጅ እንዳዳነ ያመኑበትም የእግዚአብሔር ልጆች የቅዱስ መንፈሱም ማደርያ ማድረጉን ለዓለሙ ሁሉ በደሙ በኩል አዲስ መሐላን ማድረጉ የሚገልጽ ሲሆን
❖ከእመቤታችን ብስራትና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ጀምሮ ስላስተማራቸው ትምህርቶች ስላደረጋቸው ተአምራት ስለ ሰው ልጆች ሐጢአት ዋጋ ካሳ እንዲሆን መከራ መቀበሉ መሞቱ ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱ ለብዙዎች መታየቱን ማረጉን #በወንጌላት
❖ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ እንደተቀበሉና በጌታችን ኢየሱስ ስም የሐጢአት ስርየት መስበካቸውን ብዙ መከራ መቀበላቸውንና ብዙዎችን ማጥመቃቸውን #በሐዋርያት ሥራ
❖ስለ ጌታችን ኢየሱስ ማንነት፣ስለ አዲሱ መሐላ፣ስለ አማኞች ስነ ምግባር በእምነትም ስለመጽናት ፣በክርስቲያኖች መኖር ያለበት ፍቅር #በመልእክታት
❖ስለ መጪዋ ቤተ ክርስቲያን፣ ዲያብሎስ በዚህ ምድር ስለሚኖረው የክፋት አሰራርና ስለ ቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች፣ስለ ሐሳዊው ክርስቶስና ስለ አዲሱ የአለም መንግስት አሰራር፣ ስለ ጌታችን ክርስቶስ ዳግም መምጣትና ስለዚህ አለም ማለፍ፣ስለ ክርስቲያኖች ተስፋ በአዲሲቷ ምድርና ሰማይ ከክርስቶስ ጋር ያለው ኑሮ #በራእይ ይዟል፡፡
በቀጣዩ የመግቢያ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ጥራዝ መቼና እንዴት ተደረገ የሚለውን እናያለን
✞❀✞❀✞❀✞❀✞❀✞❀✞
"የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:17፤)
✞❀✞❀✞❀✞❀✞❀✞❀✞
"የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:14፤)
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
እባካችሁ ይህን መልዕክት ለሁሉም ጓደኞቻችን ለማድረስ እንሞክር
​​#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም)
ኅዳር ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም

ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ በዓለ ልደት ዋዜማ ድረስ የሚጾም፤ #ከሰባቱ አጽዋማት መካከል አንደኛው ጾም ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ ስለ መልበሱ፤ ወደ ግብጽ ስለ መሰደዱ፤ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ፤ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ፤ ለሰው ልጆች ድኅነት ልዩ ልዩ መከራን ስለ መቀበሉ፤ ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ትንቢት ተናግረዋል፤ ትንቢቱ ደርሶ፣ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው የሚኾንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡

ይህ ጾም የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎት በጌታችን መወለድ ፍጻሜ ያገኘበት ወቅት በመኾኑ ‹‹ጾመ ነቢያት (የነቢያት ጾም)›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ ስለ ተፈጸመበትም ‹‹ጾመ አዳም (የአዳም ጾም)›› ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም ‹‹ጾመ ስብከት (የስብከት ጾም)››፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ ‹‹ጾመ ልደት (የልደት ጾም)›› በመባል ይታወቃል፡፡

እንደዚሁም ‹‹ጾመ ሐዋርያት›› ይባላል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?›› በማለት ነቢያት የጾሙትን ከልደተ ክርሰቶስ በፊት ያለውን ጾም ጾመዋልና፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ ጾም ‹‹ጾመ ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም)›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡

ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ስለ ተሰወረባቸው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ ሱባዔ ይዘው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ልመናቸውን ተቀብሎ በ፫ኛው ቀን መልሶላቸው ሥጋውን (አስከሬኑን) በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት ‹‹ጾመ ፊልጶስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሠራት በኋላ እመቤታችን ‹‹ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?›› በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማዋለችና ይህ ጾም ‹‹ጾመ ማርያም›› በመባልም: ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በገና ጾም ነቢያትም ሐዋርያትም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም እንደ እነርሱ በረከትን እናገኝ ዘንድ ይህንን ጾም መጾም እንደሚገባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ሥርዐት ሠርተውልናል፡፡

በዚህም መሠረት የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን፤ መንግሥቱንም እንዲያወርሰን ዅላችንም በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባል፡፡

ምንጭ፡- ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭፡፡
ጾምና ምጽዋት፣ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ፤ ገጽ ፵፯ -፶፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
Via ortodoxmezmur
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Abdul Mesid)
#ዝክረ_ሰማዕታት_በኢትዮጵያ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
@orthodoxprofilicpicture ቻናል ቤተሰብ እንደምን ከረማችሁ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን
በተለያዩ የሀገራችን ኢትዮጵያ ክፍሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ሆነ በምዕመናን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ እና ሰቆቃ የምንዘክርበት የማህበራዊ ሚድያ ጉባኤ ከታህሳስ 20-23 ለ ተከታታይ 3 ቀናት የሚቆይ ጉባኤ አዘጋጅተናል በዚህ ጉባኤ ላይ በጸጋችሁ መሣተፍ የምትፈልጉ

@orthodoxprofilicpicture_bot
@Welde_kirkos
ላይ ያናግሩን
በስሜ አንድም ሁለትም ሁናችሁ ብትሰባሰቡ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ ባለው ቃሉ መሠረት እዚህ ጉባኤ ላይ ሌሎች ወንድም እና እህቶችን ይጋብዙ

www.tg-me.com/orthodoxprofilicpicture

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን
ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ? ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ? ፍቅር ? ሰላም ? መቻቻል ? ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ? እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?
ስለዘገየን በእግዚአብሄር ስም ይቅርታ እንጠይቃለን መልካም ገና ይሁንላችሁ በአሉን በማስመልከት 75 % ቅናሽ ያለው ማስታወቂያ ሠአት አገልግሎት ማቅረባችንን ስንገልጽ በደስታ ነው የኦርቶዶክስ ቻናል ያላችሁ ብቻ አናግሩን

@orthodoxprofilicpicture_bot
Forwarded from New Fashion sale
✞✞✞ በየቀኑ አዳዲስ መንፈሳዊ የ profile Picture ለማግኘኘት ከፈለጉ ተቀላቀሉን ✞✞✞
@Tewahdo_1

Join Us Today
@tewahdo_1
🇯 ‌🇴 ‌🇮 ‌🇳 👇 🇺 ‌🇸 
https://www.tg-me.com/joinchat-TeBKfxzygTaIygCX
2025/02/22 16:10:38
Back to Top
HTML Embed Code: