Telegram Web Link
ኦርቶዶክስ ቻናልከ100-1k ያላችሁ ፕሮሞሽን የምትፈልጉ @Welde_kirkos ላይ አናግሩኝ
በ ነጻ ነው
የቻናሉን link በመላክ ይመዝገቡ
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
ንስሐ-ሐዘን፣ ቁጭት፣ ቅጣት፣ የኃጥያት ካሳ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ንስሐ ገባ ሲባል አዘነ፣ ተፀፀተ፣ ተመለሰ፣ ክፉ ዐመሉን ተወ፣ ጠባዩን ለወጠ ማለት ነው፡፡
ሊሰሩት የማይገባ ስራ ወይም ኃጢአት ከሰሩ በኋላ ምነው ባልሰራውት ምነው ባላደረኩት ብሎ ማዘን መቆጨት ነው።

በሰራነው ኃጢአት ተፀፅተን የምንመለስበት ነው።
ማቴ 12፥31

ኃጢአታችን በመናዘዝ ማለትም የሠሩትን ኃጢአት በመዘርዘር ልቡናን ታዛቢ አንደበተን ከሳሽ፣ ካህኑን ዳኛ አድርጎ ራስን መውቀስ ማለት ነው፡፡
ንስሐ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት ባደረገው ስህተት በፈፀመው ክፉ ስራ ማዘኑን መቆርቆሩ ዳግመኛ ያንን የመሰለ ኃጢያት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ንስሐ በሰዎች ሕይወት ውስጥ ደግሞ የተለያየ ትርጓሜዎች ይኖሩታል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፡-
ንስሐ - ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው
ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ነው
ወደ መንፈሳዊ ህይወት መመለስ ነው
ስለ አለፈው ስህተት አብዝቶ ማልቀስ ያለፈውን የኃጥያት ኑሮ ማውገዝና መኮነን ነው
የአእምሮ መታደስ ነው
የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ የሚያስችል ወደ መንግስተ ሰማያትም የሚያስገባ ቁልፍ ነው፡፡

በዘመነ ሐዲስ ምስጢረ ንስሐን የመሰረተ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ትምህርቱንም የጀመረው ‹‹ንስሐ ግቡ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና›› በሚል ነበር (ማቴ 4/17) ኃጢአትን ማስወገድ የሚችለው ይቅርታና ምሕረት ለመስጠት ሥልጣን ያለው እርሱ ብቻ ስለሆነ ከወደቅንበት ሊያነሳን ምሕረትን ሊያድለን ወደ ምድር መጣ (ማቴ 9/6)
ከዚህም በኋላ እርሱ ለመረጥነው አገልጋዮቹ ‹‹ እናንተ ኃጢአቱን የተዋችሁለት ይተውለታል የያዛችሁበት ይያዝበታል ---- (ማቴ 18/18) በማለት ኃጢአትን የማስተሰረይ የምስጢረ ንስሐን አገልግሎት የመፈፀም ሥልጣንን ሰጥቷቸዋል፡፡
እንዴት ንስሐ ይገባል?

ካህናት ዘንድ ቀርበን መሆን እንዳለበት መጽሃፍ ቅዱስ ይነግረናል።
ኢያ 7፥16፤
ማቴ 18፥13

አንድ ሰው ንስሐ መግባት የፈለገ እንደሆን ሊመራባቸው የሚገቡ ነጥቦች ይኖራሉ፡፡
ከእዚህም ውስጥ፡-
ከራስ ጋር መሆን አለበት

ንስሐ ለመግባት የራስ ፈቃድ ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር ሰው ሁሉ ንስሐ ገብቶ እንዲድንለት ይፈልጋል ሰይጣን ራሳችንን ስንገዛና የሰራነውን ኃጢአት ስናስተውል እግዚአብሔርም ኃይልና ብርታትን እንደሚሰጠን ስለሚያውቅ ይፈራል፡፡ ከራሳችን ጋር ስንሆን መንፈስ ቅዱስ ስለሚቀርበን ንስሐ ለመግባት ሁኔታዎች የቀለሉ ይሆናሉ፡፡

ምክንያተኝነትን እንዲሁም ለራስ ይቅርታ ማድረግን ማስወገድ

በንስሐ ሕይወት መሆን የሚፈልግ ሰው ለሰራነው ኃጢአት ምክንያትን በመደርደር ለራሳችን ይቅርታን የምናደርግ ከሆነ ኃጢአትን እየተለማመደ ስለሚሄድ ንስሀ ከመግባታ ይልቅ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ምንም ምክንያት ብንደረድር ኃጢያት ያው ኃጢያት ነውና ምክንያተኝነትን ማስወገድ ወደ ንስሐ ሕይወት ይመራናል፡፡

ንስሀ ለመግባት አለመዘግየት፣ አጋጣሚዎችን መጠቀም

ንስሐ መግባት የሚፈልግ ሰው ዛሬ፣ ነገ እያለ መዘግየት የለበትም ዕድሉን ጊዜውን መጠቀም መቻል አለበት፡፡ ዛሬ ነው እንጂ የኛ ነገ የእኛ ላይሆን ይችላልና፡፡

ልብን አለማደንደን

የሰዎችን ሁሉ ድህነታቸውን እንጂ ጥፋታቸውን የማይወደው እግዚአብሔር በመምህራኑ፣ በሊቃውንቱ አድሮ ንስሐ እንድንገባ ልብን አለማደንደን ያስፈልጋል፡፡ ልባችን የምናደነድ ከሆነ ኃጢአትን እየተለማመድን ስለምንሄድ ወደ ንስሐ ሕይወት የመሄጃው መንገድ እየጠበበ ይሄድብናል፡፡

ኃጢአት ምንድን ነው

ኃጢያት-ቀጥታ ትርጉሙ ማጣት ማለት ነው፡፡ ይህም እግዚአብሔርን የመሰለ ጌታ ገነትን የመሰለ ቦታ ማጣት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን ያጣች ነፍስ የሞተች ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልዕክቱ ‹‹ ኃጢያት ስታደርግ ሞትን ትወልዳለች›› ካለ በኋላ በሮሜ መልዕክቱ ደግሞ ‹‹የሐጢአት ደሞዝ ሞት ነው›› ሲል ገልፆታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኃጢያት የሚለውን ዘርዘር አድርገን በሕይወታችን ስንመለከተው ተጨማሪ ትርጉሞችን ይሰጠናል፡፡

ኃጢአት

ከእግዚአብሔር መለየት ነው
በዓለም መታለልና መጥፋት ነው
ርኩሳትና ውርደት ነው
የእግዚአብሔር አርአያና ምሳሌ መሆንን ማጣት ነው
ክብርን፣ ንጽህናን ማጣት ነው


በንስሃ ከተመለስን በኋላ

ዳግመኛ መበደል አይኖርብንም።

ንሰሃ የሚደገም ቢሆንም ከኃጢያት መራቅ አለብን። ዩሐ 5፥14፤
ሮሜ 6፤14

ሥጋ ወደሙን መቀበል ይገባናል።
ዩሐ 6፥56፤
1ኛ ቆሮ 11፥26

ፍጹም ሰላምን እናገኛለን። ዩሐ 14፥27

አስተውሉ

ማንኛውም ክርስቲያን ነፍስ ካወቀ በኋላ የንስሃ አባት መያዝ አለበት፡፡

የንስሃ አባት የሚሆነው ካህን በአጥቢያው ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም በየጊዜው እየተገናኙ ለሠሩት ኃጢአት ቀኖና ለመቀበል እንዲሁም መንፈሳዊ ምክርን ለማግኘት ሲባል ነው፡፡

ቀኖና ማለት ምን ማለተ

መስፈሪያ፣ መለኪያ ማለት ነው።

በአንድ ሰው ንሰሃ መግባት በሰማይ ሳይቀር ደስታ እንደሚሆን ተገልጿል።
ሉቃ 15፥7፤
ማቴ 9፥13
ሰው ክቡር ነው

ድንግል ማርያም ክርስቶስን ይዛ ግብፅ በተሰደደችበት ጊዜ ውሃ ይጠማትና አንድ ቤት አንኳኩታ የሚጠጣ ውሃ ትለምናለች ። ሴትዮዋም ድንግልን አይታ መልክሽ የንግስት ይመስላል ልጅሽም የንጉስ ልጅ ይመስላል ይሄን የመሰለ መልክ ይዘሽ ባልሽ ያባረረሽ ፀባይሽ ቢከፉ ነው አለቻት ። አረጋዊዉ ዮሴፍም ለሚለምን ሰው ወይ ይሰጡታል ወይ ደሞ ከሌለ ካለበት ቦታ ያድርስህ ብለው ይመርቁታል እንጂ እንዴት እንዲ ይናገሩታል አላት ። ሴትዮዋም ጭራሽ ድንግል በጥፊ መታ ክርስቶስን ደሞ ከእቅፏ ተቀብላ ትወረውረዋለች ። ድንግልም ልጄን ብላ ልታነሳው ስትል ዮሴፍም እጇን ይዞ ተይው ተዓምሩን ያሳያቸው አላት ። ወዲያውኑ ሴትዮዋ ከነ አሽከሯ ወደ ጦጣነት ተቀይራ የራሷ ውሾች እያባረሯት ጫካ ገባች ። የኛ የአሁን ጊዜ አስተሳሰባችን እና ድርጊታችንም ፈጣሪ መአቱን እንዲያመጣብን ተአምሩን እንዲያሳየን እያስጨከነው ይመስላል ። ሰው በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ክርስቶስ የሞተለት እነሆም በደጁ ቆሞ ደጁን የሚያንኳኳለት ለሚከፍትለትም ገብቶ ከሱ ጋር እራቱን የሚበላለት ፍጡር ነው ። ተራራውን እየው አያምርም ? የጨረቃ ድምቀት የከዋክብቱ ፍካት የፀሀዩዋ ውበት የአእዋፏቱ ዝማሬ ድንቅ ነው
አበቦች ፍካታቸው ፏፏቴዎች ፏጨታቸው ደስ አይልም ? በጣም ይላል

ግን 1 ነገር ልንገርህ እነዚህ ሁሉ ያልፉሉ ሰው ግን ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ፍጡር ነው ።[ ሞት እንኳ ቦታ መቀየሪያ እንጂ የህይወት ማብቂያ አይደለም ። የሰው ህይወት ትቀጥላለች። ሰው እኮ የባህር አሶችን የሰማይ ወፎችን የምድር አራዊትን ግዛ ተብሎ የፀጋ አምላክነት የተሰጠው ፍጡር ነው ። ሰው እኮ አምላኩ ስጋዬን ብላ ደሜንም ጠጣ ያለው ፍጡር ነው ። ይህ እኮ ለመላዕክትም አልተሰጠም ። ሴጣን እኮ በኛ ቢቀና የተሰጠንን ፀጋ ስለሚያውቅ ነው እኛስ በፈጣሪ አይን እኩል ሆነን አንዳችን አንዳችንን ለማጥፉት መነሳታችን ለምን ይሆን ? አዳም የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው

በኛ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን ሲገነባ ጉልላት ሲደረግለት ያ ህንፃ ቤተክርስቲያን አለቀ ይባላል ። እግዚአብሔርም ስነ ፍጥረትን ሁሉ ከፈጠረ ቡሃላ አዳምን ፈጠረ ከዛ ሄዋንን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጥሮ አስቀመጣት ። ሴትነት ክቡር ነው ። ክርስቶስ ወደዚህ አለም ሲመጣ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም ። የሀገር መሪዎች ጀግና የጦር ሜዳ ወታደሮች ጳጳሶች ... ሁሉም ከሴት የተወለዱ ናቸው ። ወንድም ሁን ሴት ሁኚ ሰውነት ክቡር ነው ። ከሰውነት ወጥተን እንደ እንስሳ ባናስብ መልካም ነው ። በፍቅር በይቅርታ በመቻቻል ልዩነታችን ውበታችን አርገን ኢትዮጵያን ወደ ልዕልናዋ እንመልሳት

የነ ላሊበራ ከጣራው ተጀምሮ በመሰረቱ ያለቀ ውብ ፍልፍል መቅደስ ከአንድ ድንጋይ የተቀረፀ ውብ የአክሱም ሀወልት በውሀ ላይ የተገነባ የነ ይምርሀነ ክርስቶስ ቤተ መቅደስ ጣራው ክፍት ሆኖ ውሀ ማያስገባው የነ አቡነ አሮን መቅደስ እኮ የኛ ናቸው ። ቀደምት አባቶቻችን እኮ በዘር በሀይማኖት ተከፉፍለው አይደለም እኚን ሁሉ የገነቡት ። እንደ ሰው እናስብ እንደ ሰው እንኑር ። ሰውነት ክቡር ነውና ። አሁን እየሆኑ ያሉት ነገሮች የኛ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም ። ከየት ይሆን ያመጣነው ? ከአልሸባብ ? ከIsis ? ከልባችን አመነጨነው ? ከአክቲቪስቶቻችን ወሰድነው ? ወይስ ከሌላ ? ብቻ አይበጀንምና ወደ ቀድሞ ባህላችን ፍቅራችን መቻቻላችን እስላም ክርስቲያኑ አስደናቂ የጋራ ኑሯችን እንመለስ
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
፨ጥቅምት 22/2/2013፨

ወድ ቆላስይስ ሰዎች፦ም ፬:፲፪ (4:12-ፍጻሜ)

1ኛ #የዩሐንስ መልእክት ም ፩:፬ (1:4-ፍጻሜ)

#ግብረ_ሐዋርያት ፦ ም ፩:፩-፯ (1:1-7)

ምስባክ፦መዝ ፲፰:፫ (18:3)
፨አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ።
ውስተ ኩሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ።
ወእስከ አጽናፍ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ። ፨

ወንጌል፦ #ቅዱስ_ሉቃስ ም ፩:፩-፭ (1:1-5)

#ቅዳሴ_ዘሐዋርያት። (ነአኩተከ)
✟ የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች

✟ የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች

✟ የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል

✟ የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች

✟ የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም

✟ የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች

✟ የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች

✟ የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች

✟ የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
ጸልዩ በእንተ ሀገር
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (Dimitri)
2025/02/22 22:45:50
Back to Top
HTML Embed Code: