Telegram Web Link
24ቱ ካህናተ ሰማይ

1.አካኤል
2.ፋኑኤል
3.ጋኑኤል
4.ታድኤል
5.አፍድኤል
6.ዘራኤል
7.ኤልኤል
8.ተዳኤል
9.ዮአኬል
10.ገርድኤል
11.ልፍድኤል
12.መርዋኤል
13.ኑራኤል
14.ክስልቱኤል
15.ኡራኤል
16.ባቱኤል
17.ሩአኤል
18.ሰላትኤል
19.ጣውርኤል
20.እምኑኤል
21.ፔላልኤል
22.ታልዲኤል
23.ፐሰልዱኤል
24.አሌቲኤል።
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
Forwarded from ዘ ተዋህዶ
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
Forwarded from Orthodox Tewahdo profile photo (ምህርካ ክርስቶስ)
የግለ ወሲብ ሀጢያትን ለማቆም የሚረዱ አምስት ቀላል መፅሐፍ ቅዱሳዊ መንገዶች

እንግዲህ አብዛኛውን ጊዜ በሰወች ዘንድ "ግለ ወሲብ" የሚለው ቃል ሲነሳ ለመስማት የሚመች አይደለም። በችግራችን ዙሪያ የመወያየት ባህል ስለሌለንና "እንዲህ አይነት ችግር አለብኝ..." ብሎ መፍትሄ የመፈለግ ልምድ የለንም። እናም ብዙዎች ይህንን ችግራቸውን ለራሳቸው ብቻ ይዘው ይሰቃዩበታል።

ሆኖም ግን አሁን ይህን ቃል ለመስማትም ሆነ ለማንበብ ቢመችም ባይመችም ክርስትያን እንደመሆናችንና ብዙዎች በዚህ ክፉ ስራ የወደቁ እንደመሆናቸው መጠን ጉዳዩን ማንሳትና መፅሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሄዎችን ማበጀት የግድ ይሆንብናል። እስካሁን ድረስ ማህበረሰባችን በዝምታ ከዚህ ሀጢያት ጋር በራሱ መንገድ ሲታገል ቆይቷል።

በዚህ ሀጢያት የወደቁ ሰወች የሚያስፈልጋቸውን እርዳታ ለማግኘት ቢፈልጉም በጉዳዩ ላይ በግልፅ ለመነጋገር እጅግ በጣም የተሸማቀቁ በመሆናቸው የተነሳ ከዚህ ችግር ለመውጣት በራሳቸው መንገድ ይራመዳሉ። የሀጢያቱ ክፋት ደግሞ ከፈፀሙት በኋላ የከፋ ጭንቀት ላይ ስለሚጥል ጭንቀታቸውን ለማስታገስ ብቻ ከዚህ በኋላ ድርጊቱን እንደማይፈፅሙ ይምላሉ... ይገዘታሉ። ነገር ግን ሀጢያቱን በመፈፀማቸው ምክንያት የተፈጠረባቸው ጭንቀትና ፀፀት ጋብ ሲልላቸው እንደገና ይስታሉ። ምክንያቱም ግለ ወሲብን እንዲፈፅሙ የሚገፋፋና የሚያስገድድ ሌላ ጭንቀትና ድብርት በዲያቢሎስ ስለሚጫጫናቸው ነው። በዚህም የተነሳ የቆማችሁ የመሰላችሁ...ነገር ግን ደጋግማችሁ የወደቃችሁ ብዙዎች አላችሁ።

አሁን ግን በዚህ ሀጢያት ስር የወደቃችሁ ክርስትያን እህቶችና ወንድሞች በጠቅላላ እነዚህን አምስት መፅሐፍ ቅዱሳዊ መፍትሄዎችን እንደ ጠቋሚ ብርሀን ቆጥራችሁ ወደ ተግባር በመቀየር ከዚህ ችግር ሙሉ በሙሉ ትላቀቃላችሁ።

1.መፅሐፍ ቅዱስ ግለ ወሲብን እንደሚያወግዝና እንደሚነቅፍ በማመን ንስሃ መግባት

ብዙዎች ግለ ወሲብን በተመለከተ 'በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሀጢያት ስለመሆኑ በቀጥታ የተጠቀሰ ነገር የለም' ሲሉ ይደመጣሉ። ለዚህም ነው 'ግለ ወሲብ ለምን ሀጢያት ይሆናል?' ብለው የሚጠይቁት። ነገር ግን መፅሐፍ ቅዱስ በቀጥታ ግለ ወሲብ መፈፀምን አላወገዘም ማለት አልተከለከለም ወይም ተፈቅዷል ማለት አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ መፅሐፍ ቅዱስ በውስን ቃላት/በቀጥታ ነገሮችን ከመግለፅ ይልቅ በተዘዋዋሪ/በምሳሌ/በፈርጅ ይገልፃቸዋል።

እነዚህን ሁለት የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክቶች ተመልከቱ።

"ስለ ጻፋችሁልኝስ ለሰው ወደ ሴት አለመቅረብ ይሻለዋል። ነገር ግን እንዳትሴስኑ ሰው ሁሉ በሚስቱ 'ይወሰን'፤ ሴትም ሁላ በባልዋ 'ትወሰን'። ለሚስትም ባልዋ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንዲሁ ሚስትም ለባልዋ የሚገባውን ታድርግለት። ሚስት 'በራሷ አካል' ስልጣን የላትም፤ ስልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል 'በራሱ አካል' ስልጣን የለውም፤ ስልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። ለፀሎት እንድትተጉ ከምትስማሙበት ጊዜ ብቻ በቀር ባልና ሚስት 'አትለያዩ'፤ ዳግመኛም ሰይጣን ድል እንዳያደርጋችሁ 'በአንድነት' ኑሩ፤ ሰውነታችሁ 'ደካማ' ነውና።" 1ኛ ቆሮ. 7፡1-5

"ያላገቡት መታገስ ባይችሉ ያግቡ፤ 'በፍትወት' ከመቃጠል ማግባት ይሻላልና።" 1ኛ ቆሮ. 7፡9

እነዚህ ሁለት ጥቅሶች ላገቡትና ላላገቡት ወሲብን በተመለከተ እና ከእሱ ጋር ተያይዘው ስለተፈቀዱ እንቅስቃሴዎች የሚናገሩ መልዕክቶችን ያዘሉ ናቸው። እነዚህ ጥቅሶች በአንድነት የሚያስተላልፉት አንድ መልዕክት አለ።እሱም ከወሲብ ጋር በተያያዘ ትክክለኛና እግዚአብሔር የፈቀደው አንድ የህይወት ስርዓት መኖሩን ነው። ግለ ወሲብ ደግሞ ከዚህ ስርዓት የሚያፈነግጥ ነው። ስለዚህ በመፅሐፍ ቅዱስ በቀጥታ የተገለፀው ስርዓት ተገቢና ትክክለኛ በመሆኑ ምክንያቱም ግለ ወሲብ የተከለከለ ሀጢያት ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም ቅዱስ ጳውሎስ በመልዕክቱ... ከትዳር አጋር ውጪ የሚደረገውን ማንኛውም አይነት ወሲባዊ እንቅስቃሴ(ዝሙትን ጨምሮ) የሰይጣን እንደሆነና ለሰይጣንም ፈቃድ አሳልፎ እንደሚሰጥ ነው የሚነግረን። ስለዚህ ግለ ወሲብ ከባል/ከሚስት ውጪ ከሚፈፀሙ ድርጊቶች ውስጥ አንዱ ስለሆነ መፅሐፍ ቅዱስ እንደ ሀጢያት ይፈርጀዋል ማለት ነው።

(ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በእነዚህ መልዕክቶቹ ላይ ላላገቡ ሰወች "ማግባትን" እንደ መፍትሔ ማስቀመጡንም መዘንጋት የለበትም። ይህንምቃል መሰረት በማድረግ ያላገቡና በዚህ ሀጢያት ያሉት ሰወች እንዲያገቡ ወይም ተወስነው ጓደኛ እንዲይዙ ይመከራል )

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ ሀጢያት ለመላቀቅ መፅሐፍ ቅዱስ ይህንን ተግባር በፅኑ እንደሚያወግዘውና በእግዚአብሔር ዘንድም ሀጢያት እንደሆነ ተገንዝቦ ንስሃ መግባት የመጀመርያው እርምጃ ነው።

ወንድሞችና እህቶች፦ አሁን የፆም ወቅት ነው። ይህ የፆም ወቅት ደግሞ ንስሃ ለመግባት ምቹ ጊዜ በመሆኑ... የዲያቢሎስን ገርጋሪ ሀሳብ ባለመስማት ወደ አባቶች ዘንድ ቀርባችሁ ሀጢያታችሁን በመናዘዝና ንስሃን በመቀበል የህይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ አንድ ብላችሁ መጀመር ይኖርባችኋል። የሀጢያት ህይወት ትርፉ ጭንቀትና መረበሽ ነው። የሀጢያት መንገድ እሾህ ይበዛዋል። በሀጢያት ከሀዘን ውጪ ደስታ አይገኝም። ሁልጊዜ ለቅሶ፣ ሁልጊዜ መባከን፣ ሁልጊዜ ብቸኝነት። አሁኑኑ ንስሃ ግቡ... እና አዲስ ህይወት ጀምሩ። ደስታ የበዛበት አዲስ ህይወት፤ የእግዚአብሔር እርዳታ ያልተለየው የህይወትን ጉዞ፤ እግዚአብሔርን የሚያስደስት አዲስ ህይወት፤ መልካምን ፍሬ የሚሰጥ አዲስ ህይወት፤ ... ነገ ዛሬ ሳትሉ 'አሁኑኑ' እናት ቤተክርስትያን ያዘጋጀችውን የንስሃ በር ከፍታችሁ ጀምሩ።
አንዱ ወደ አንድ አባት ቀረብ ብሎ "ድንግል ማርያም እኮ እንደ እኛ ሰው ናት" አላቸው። እርሳቸውም "ልክ ነህ እርስዋ በተፈጥሮዋ ሰው ናት ፣ አንተ ግን ሰው ነህ?" አሉት።

ነገሩ ስድብ ይመስላል ፣ አስተውሎ ላየው ግን ሰው ነኝ ለማለትም መሥፈርት እንዳለው ያስታውሳል። "ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ" ነገር ግን ዝናምን በጸሎቱ ያቆመ መሆኑን ስንሰማ ሰው ነን ለማለት እንፈራለን። ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ሰሎሞን "ሰው ሁን" ያለው ሰው መሆን ማለት እንደ ሰው ክብርን አውቆ መኖር ስለሆነ ነው። ክቡር ሆኖ ሳለ ካላወቀና በኃጢአቱ ከጸና እንደሚጠፉ እንስሳት ይመስላል።

ሰው ለመሆን ብዙ መሥፈርቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጠዋል ፣ የድንግል ማርያምን እናትነት መቀበልም ሰው የመሆን ምልክት ነው።
"ሰው እናታችን ጽዮን ይላል" ተብሎ እንደተጻፈ "ጽዮን እናታችን" ማለት ያልቻለ ምኑ ሰው ይባላል?

"የእግዚአብሔር ከተማ ጽዮን ሆይ ይሉሻል የናቁሽ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ" ተብሎ ለዳዊት ከተማ ተነግሮላት ነበር። ስንት ኃጢአተኛ ሲራኮትባት ለሚውልባት ለዳዊት ከተማ የሚሰገድ ከሆነ ለንጽሕቲቱ ከተማው ለድንግል ማርያም አይሰገድም እንዴት ይባላል? ነቢዩ ከጽዮን ጫማ በታች ይሰግዳሉ ብሎ ለዳዊት ከተማ ከተናገረ ከድንግሊቱ ጫማ በታች እንዴት ይሰገድ ይሆን?

በእርግጥ የናቅዋት ሁሉ ወደ ጫማዋ ሊሰግዱ ይሆን? በፍጹም አይሆንም! የድንግልን ጫማዋንማ ለእኛ ለምናከብራትም ማን ባደለን? እኛ አክሱም ጽዮን ቁስቋም ግሸን በረከቷን ሽተን እየተጓዝን የናቋት እንዴት ጫማዋን ያገኛሉ?

አባ ጊዮርጊስ "ገሊላዊትዋ ድንግል ጫማን እሸከም ዘንድ ፣ ጥላዋ ያረፈበትን እስም ዘንድ ማን ባደለኝ?" ይል የለምን? ከእግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ ማለት ይዋረዳሉ ነው እንጂ ይህ ክብር ለናቋት የሚገባ አይደለም።
መ/ር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
2025/02/23 06:22:00
Back to Top
HTML Embed Code: