Telegram Web Link
ኢትዮ ቴሌኮም የ5ጂ ኔትወርክ ማስፋፊያ አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በደሴና በኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡

ይህ ኩባንያችን የሀገራችንን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያደርገው ሀገራዊ ጥረት አካል ሲሆን፣ የላቀ ፍጥነት ያለው ኢንተርኔት በማዳረስ ለአዳዲስ ፈጠራዎችና ኢኮኖሚያዊ የዕድገት ዕድሎች በር ለመክፈት ያስችላል።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ፣ ሉሲ ሆቴልና ደሴ ሙዚየም አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

በኮምቦልቻ ደግሞ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ ኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ካምፓስ አካባቢዎችን ይሸፍናል፡፡

አገልግሎቱ አዳዲስ የዲጂታል እና የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለኦንላይን ትምህርት፣ ለጀማሪ የንግድ ተቋማት ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ፣ የስማርት ስልክ አቅርቦት ለማሳደግና ዲጂታል ክህሎትን ለመጨመር ያስችላል።

5ጂ የግል እና የመንግስት ተቋማትን አሰራር ያዘምናል፤ እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ማኑፋክቸሪንግን፣ ማዕድን፣ ትራንስፖርት እና ቱሪዝምን የመሳሰሉ ቁልፍ ዘርፎችን በማዘመን ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

በአዲስ አበባ በ2022 እ.ኤ.አ ያስጀመርነው 5ጂ ደሴ እና ኮምቦልቻን ጨምሮ በ14 ከተሞች ማለትም በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በጅግጅጋ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በባህር ዳር፣ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በሆሳዕና፣ በአርባ ምንጭ፣ ቢሾፍቱና ጅማ አገልግሎት ላይ ውሏል።

ክቡራን ደንበኞቻችን፣ የ5ጂ አገልግሎት ማስተናገድ የሚያስችሉ ቀፎዎች እና ሲም በአገልግሎት ማእከላችን በማግኘት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንጋብዛለን፡፡

ለተጨማሪ፡- https://bit.ly/3F2QyJe
በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን የተመራ የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ አመራር የደሴ ከተማ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት አፈጻጸም ጎበኘ፡፡

በጉብኝቱ የደሴ ከተማን አስተዳደር በስማርት ሲቲ ለማዘመን በምዕራፍ በመካሄድ ላይ ያለው ፕሮጀክት በጥሩ ትግበራ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ቀሪ የፕሮጀክቱ ሥራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ሁሉን አቀፍ የዲጂታል ትግበራ በመሆኑ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ የግብር አሰባሰብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች አገልግሎቶች ክፍያዎችን ከእጅ ንክኪ በጸዳ መልክ በቴሌብር መከናወን እንደሚገባው አጽንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም ስማርት ሲቲ የከተማን ደህንነት አስተማማኝ ከማድረግ እና ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባሻገር የነዋሪዎች አሰፋፈር፣ የአካባቢ ጽዳትና የትራፊክ ፍሰት የመሳሰሉ መረጃዎችን በቀላሉ በማግኘት የመልሶ ልማትን እንደሚያፋጥን አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ኢ-ጋቨርናንስ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የዲጂታል መሰረተ ልማት መደላድል መፈጠሩን የተገለጸ ሲሆን ይህም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡


#ዲጂታልኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ

#Dessie #SmartCity #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👉🏼 ከ9-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ጠቃሚ የትምህርት ማቴሪያሎች በተጨማሪ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን በልዩ ሁኔታ የሚያዘጋጅ ፕላትፎርም ከኢተማሪ ያግኙ!
ራስን መገምገሚያ ኩዊዞች፣ አጫጭር ኖቶች እንዲሁም ያለፉት ዓመታት ጥያቄዎች ከጥልቅ ማብራሪያ ጋር በኢተማሪ!

💬 ለዕለታዊ A፣ ለሳምንታዊ B ብለው ወደ 9429 ይላኩ!

🌐 ለኢተማሪ ብቻ የሚያገለግል የኢንተርኔት ጥቅል ለዕለታዊ 75 ሜ.ባ፣ ለሳምንታዊ 500 ሜ.ባ ነፃ ይበረከትልዎታል፡፡

ለበለጠ መረጃ http://www.etemari.net ይጎብኙ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
telebirr pinned a photo
2025/03/15 04:23:50
Back to Top
HTML Embed Code: