Telegram Web Link
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን የሥራ አመራር ልዑክ ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መሀመድ አሚን የሱፍ ጋር በመሆን የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ትግበራን ጎብኝተዋል።

ኩባንያችን ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጋር የሚያከናውነው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን፤ ቀሪ ስራዎችም በአፋጣኝ ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ፕሮጀክቱ ኮምቦልቻን ለኢንዱስትሪና ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ይበልጥ ተመራጭ በማድረግ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ ሲሆን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ እንደሚያደርጋት አጽንዖት ተሰጥቷል።

በተጨማሪም የስማርት ሲቲ ፕሮጀክቱ የመስተዳድሩን አገልግሎቶች፣ የግብር አሰባሰብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ክፍያዎችን በቴሌብር በማቀላጠፍ የዜጎችን ጊዜና ገንዘብ ከመቆጠብ ባሻገር የአሰራር ቅልጥፍናንና ተደራሽነትን ይጨምራል።

በመጨረሻም ልዑኩ በከተማዋ ከሚገኙ ውብ እና አርአያነት ያላቸው የአረንጓዴ ልማት ፓርኮች መካከል አንዱን ጎብኝቷል።

#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ!

#RealizingDigitalEthiopia #SmartCity #Kombolcha #DigitalEthiopia
የካቲትን ለወደቁትን አንሱ!!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች (Followers) ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ ልጥፎች (Share) ልክ 10 ብር ለወደቁትን አንሱ የነዳያን በጎ አድራጎት ማኅበር እንለግሳለን!

🤝 እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ቲክቶክ

በተጨማሪም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ለበጎ አድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን በመለገስ ለወገንዎ ተስፋ ይሁኑ!

🙏 ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!


#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
መደበኛ ክፍያዎን በአንድ ጊዜ ታፕ በቀላሉ ይፈጽሙ!

💁‍♂️ ዋንታፕ ፔይ የክፍያ አገልግሎት በቋሚነት የሚፈጽሟቸውን እንደ ድኅረ ክፍያ የቴሌኮም፣ መብራት፣ ውሃ፣ ትምህርትና ሌሎችም ክፍያዎችን ጊዜያቸው ሲደርስ የሚስጥር ቁጥርዎን ብቻ በማረጋገጥ ለመፈጸም ያስችልዎታል!

🔗 ዋንታፕ ፔይ በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ይገኛል!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
💡 በኩራዝቴክ ራስዎን ያብቁ!!

በስኬት የፈተና መለማመጃ ፕላትፎርም ለሀገር አቀፍ መውጫ ፈተናዎች ይዘጋጃሉ!

ኮርሶችን ከጥልቅ ማብራሪያ ጋር በቪዲዮ ለመመልከት ተጨማሪ ነጻ ዳታ ይበረከትልዎታል!

👉 ከ10 ብር ጀምሮ ለዕለታዊ A፣ ለሳምንታዊ B እንዲሁም ለወርሃዊ C ብለው ወደ 9155 ይላኩ፤ መተግበሪያውን ከ https://onelink.to/r4u6q4 አውርደው ይጠቀሙ።


ለተጨማሪ kuraztech.com ይጎብኙ!


#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ዝክረ አድዋ - ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅት!!

ታላቁ የጥቁር ሕዝብ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በዓል በማስመልከት #ዝክረ_አድዋ_ኢትዮጵያዊነት ልዩ የኪነጥበብ ዝግጅት ተዘጋጅቷል፡፡

🗓 አርብ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ
📍 ፒያሳ አድዋ ሙዚየም አዳራሽ

የመግቢያ ትኬቱን ባሉበት ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ ይቁረጡ!

❇️ መደበኛ፡ 300 ብር
❇️ VIP: 500 ብር

👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr

ቴሌብር ሱፐርአፕ ➡️ ክፍያ ➡️ ዝግጅትና ትኬቶች ➡️ ዝክረ አድዋ ኢትጵያዊነት


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ምዝገባ ካልፈጸሙ በአካል ቀርበው በነጻ ይመዝገቡ!

የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ምዝገባ በሁሉም የአገልግሎት ማዕከሎቻችን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ውስጥ በተካተተው አቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ በመታገዝ አቅራቢያዎ የሚገኘውን የምዝገባ ማዕከል ይወቁ፤ በአካል ቀርበው በነጻ ይመዝገቡ!

ለተጨማሪ መረጃ https://bit.ly/45NUZRy ይጎብኙ!

#DigitalID #Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅት ደንበኞች እና ተቋማት በክላውድ ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ የዲጂታል ሶሉሽኖች በይፋ አስጀመረ!

ኩባንያችን የተቋማት አቅም የሚገነቡ፣ አሰራሮችን የሚያዘምኑ እንዲሁም ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው የላቀ አገልግሎት በማቅረብ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማስመዝገብ የሚያስችላቸው ሰባት የኢንተርፕራይዝ ሶሉሽኖችን ተግባራዊ ማድረጉን ስናበስር ታላቅ ደስታ ይሰማናል፡፡

ይፋ ያደረግናቸው ሶሉሽኖችን የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ፣ ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ፣ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን፣ የትምህርት አመራር ስርዓት ሶሉሽን እንዲሁም የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን፣ ቴሌ የጥሪ ማዕከል እና ኢ.አር.ፒ ሶሉሽኖችን ናቸው፡፡

እነዚህ የዲጂታል ሶሉሽኖች ድርጅቶች መሰረተ ልማት መገንባትም ሆነ የመረጃ ማዕከል መገንባት ሳያስፈልጋቸው እንዲጠቀሙና የኦፕሬሽን ስራቸውን በማስተዳደር ላይ ብቻ በማተኮር ተወዳዳሪነታቸው እና ምርታማነታቸው እንዲጨምር አስተዋጽኦ ያበረክታሉ፡፡

ኩባንያችን እስካሁን ከ456 በላይ የድርጅት ደንበኞችንና አጋሮችን በቴሌ ክላውድና በዳታ ማዕከል አገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ለባንኮችና አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት በሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ የማርኬት ፕሌስ ሶሉሽን አቅርቧል።

ኩባንያችን የተቋማትን አሰራር የሚያዘምኑ እና ምርታማነትን የሚያሳድጉ አስቻይ ሶሉሽኖችን በማቅረብ የሀገራችን ዘላቂ ልማት እና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያፋጥኑ ተግባራትን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/43c67bG
2025/03/15 06:12:56
Back to Top
HTML Embed Code: