Telegram Web Link
በዛሬው ዕለት ኢትዮ ቴሌኮም እና የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓትን፣ የተቀናጀ ነዳጅ ክፍያ ስርዓትን እና ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቅጣት የሚያዘምኑ ሶስት የዲጂታል ሶሉሽኖች ተግባራዊ አድርገዋል፡፡

የመጀመሪያው የሀገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሶሉሽን ሲሆን ነባሩን የወረቀት አሰራር በማዘመን እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ አሰራር በማስፈን የፈቃድ አሰጣጥንና የትራንስፖርት ስምሪትን ለማቀላጠፍ፣ ተገልጋዮች በስልካቸው የጉዞ ትኬት በመቁረጥ የጊዜ ብክነትንና እንግልትን ለመቀነስ የላቀ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ሁለተኛው ሶሉሽን የተቀናጀ የነዳጅ ክፍያ ስርዓት ሲሆን በነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ያሉ ዘልማዳዊ የአሰራር ሂደቶችን ለማዘመንና ሁሉንም የፋይናንስ ተቋማት ከማዕከል የነዳጅ ማኔጅመንት ሲስተም ጋር በማገናኘት በቅንጅት እንዲሰሩ፣ የነዳጅ ክምችትንና ሥርጭትን ከማዕከል ለመከታተል እንዲሁም ቴሌብርን ጨምሮ በሁሉም ባንኮች እና ዋሌቶች የነዳጅ ክፍያዎችን ለማስተናገድ ያስችላል፡፡

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቅጣት ማኔጅመንት ሶሉሽን ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተናበበ የትራፊክ ቅጣት ስርዓትን ለማስፈን፣ የትራፊክ ህግ ጥሰቶችን በዲጂታል መንገድ ለመቆጣጠር፣ አሽከርካሪዎች ቅጣት በመክፈል ሂደት የሚደርስባቸውን እንግልት በመቅረፍ ተጠያቂነት ያለው አሰራርን ለመተግበር የሚያስችል ነው።

ተግባራዊ የተደረጉት ሶሉሽኖች ከግል ሶፍትዌር አልሚ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የተከናወነ መሆኑ ኩባንያችን የግሉን ዘርፍ በማበረታታት አካታች የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት አካል ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/3Szg4td

#Ethiotelecom #MOTL
👍9632👌7👏2
telebirr pinned a photo
ኢትዮ ቴሌኮም እና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ይፋ ያደረጓቸው የዲጂታል ሶሉሽኖች፡-

🚌 የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሶሉሽን

⛽️ የተቀናጀ የነዳጅ ክፍያ ሥርዓት

🚦አገር አቀፍ የትራፊክ ቅጣት ማኔጅመንት ሶሉሽን


ለበለጠ መረጃ፡- https://bit.ly/3Szg4td


#Ethiotelecom #MOTL
👍438👌4🤩3😁2
የቀድሞው ቴክኒሽያናችን በሥራ ላይ!

አዲስ አበባ
1952 ዓ.ም


#ትውስታ
#throwbackthursday
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍387👌7
🪪 የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የካርድ ኅትመት አገልግሎት በተጨማሪ በርካታ የክልል ከተሞች ተጀምሯል!!

ምዝገባዎን በአገልግሎት ማዕከሎቻችን በነጻ አካሄደው በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ‘’NID (Fayda) Printing’’ መተግበሪያ የካርድ ኅትመትዎን በቀላሉ ይዘዙ፡፡

👉 እንደምርጫዎ በ6 የሥራ ሰዓታት፣ በ2 ቀናት ወይም በ7 ቀናት ውስጥ በመረጡት የመረከቢያ ቀንና ቦታ ይረከቡ!

🔗 በአቅራቢያዎ የሚገኙ የመረከቢያ ቦታዎችን ለመመልከት፡ https://bit.ly/40efSUZ


ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍4826👏1
ግንቦትን ለአሜን የበጎ አድራጎት ድርጅት!!

በዚህ ወር በማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችን በሚቀላቀሉ አዲስ ተከታዮች ብዛት ልክ 30 ብር እንዲሁም በሚጋሩ Share ልክ 10 ብር ለአሜን የበጎ አድራጎት ድርጅት እንለግሳለን!

🤝 እርስዎም ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ፤ ፖስቶቻችንን ያጋሩ፤ ለወገን ድጋፍ ይተባበሩ!

ቴሌግራም | ፌስቡክ | ኢንስታግራም | ሊንክዲን | ዩትዩብ | ቲክቶክ

በተጨማሪም በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ለበጎ አድራጎት በሚለው አማራጭ የፈቀዱትን የገንዘብ መጠን በመለገስ ለወገንዎ ተስፋ ይሁኑ!

🙏 ዘላቂ የጋራ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለወገን ብሩህ ተስፋ!


#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
👍3310🙏3👏2
🔊🎁 በአነስተኛ ዋጋ ብዙ ይነጋገሩ!!

ዕለታዊ
📊 ሳምንታዊ እና
🗓 ወርኃዊ

የድምጽ ጥቅሎችን በ*999#፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም አርዲ ቻትቦት ከ100% ስጦታ ጋር ይሸምቱ!

👉 በቴሌብር ሱፐርአፕ https://bit.ly/telebirr_SuperApp ሲገዙ ተጨማሪ 10% ስጦታ ያገኛሉ!


#VoicePackage
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalEthiopia #DigitalAfrica #RealizingDigitalEthiopia
👍307💯5👌4🙏1
ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም በምሥራቅ አፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ዋና አጋር (ታይትል ስፖንሰር) በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማናል!

ይህ በሀገራችንና በምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የሆነው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ዛሬ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል!

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩን ጨምሮ የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ታላቅ የቴክኖሎጂ መድረክ ላይ በመገኘት መልዕክቶችና ገለጻዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

ኤክስፖው እንደ ሳይበር ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ስማርት ከተሞች እና የቴክኖሎጂ ክህሎት ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ላይ ያተኩራል።

ዲጂታል ተኮር  አውደ ጥናቶች እየተካሄዱ ሲሆን በኩባንያችን የዲጂታል ፈጠራ ውጤቶች አውደ ርዕይ ለዕይታ ቀርበዋል።

በውይይት መድረኮቹ ከመላው ዓለም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ መሪዎችና ምሁራን በስፋት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ሁነቱ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል።

በዚህ ልዩ እና አስደማሚ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይ በመገኘት በቴክኖሎጂው ዓለም የሚስተዋሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን እንዲመለከቱ በአክብሮት እንጋብዛለን!

ለመመዝገብ https://etexethiopia.com/register-now/

#Ethiotelecom #ETEX2025 #Titlesponsor
👍4613👏7
2025/07/14 16:45:14
Back to Top
HTML Embed Code: