Telegram Web Link
"የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት” ኢያሱ. 3፤3

"+" እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ.... በቸርነቱ ለዚህች ቀን ስላደረሰን ስሙ የተመሰገነ ይሁን::"+"
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞ እንኳን አደረሳችሁ ✞✞
ጥር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
+በዓለ ኤዺፋንያ+
=>'ኤዺፋንያ' የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ 'አስተርእዮ: መገለጥ' ተብሎ ይተረጐማል::
በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤዺፋንያ ማለት 'የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት' እንደ ማለት ነው::
"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ:
እሳት በላዒ አምላክነ" እንዲል:: (አርኬ)
አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ ኤዺፋንያ ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ
ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ33 ዓመታት ተመላልሷል::
+ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ
የወረደው ጥር 10 ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::
+10 ሰዓት መሆኑም ርግብ (መንፈስ ቅዱስ) ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው::
ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::
+መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: (ሉቃ. ማቴ. ) ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::
+ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ
ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው::
+ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ:: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ እያልክ
አጥምቀኝ" አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::
+ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ ደነገጠች: ሸሸችም:: (መዝ) ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ
ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውሃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ
ግን ጸና::
+ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንም ቀዶ
ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::
+አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!"
ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::
+ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ
ባሕር ሆነ::
✞✞ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ✞✞
✞✞ ቅዱስ ወንጌል ላይ ቅዱስ ሉቃስ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ
የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
+እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው
ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን
ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
*ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ.
40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
*ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው
ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን
ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
*የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ
ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ
ተፈትቶለታል::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ
ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና
እሱንም ግደል" አሉ::
*እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን
እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::
*ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር
በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን
"ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23)
ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት
በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::
*ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት
ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል
ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን
ተናግሮ ነበርና::
*ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው
የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::
*ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ
ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ::
የሚገባበትም ጠፋው::
*"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን
"ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ
ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ
ለ7 ቀናት አሠረው::
*ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ
በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ
መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ
ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ.
1:6)
✞" አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ/ የመጥምቁ ዮሐንስ
ስሞች"
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5
.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)
✞አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ
ጥምቀቱም ያድለን::
✞ጥር 11 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.በዓለ ኤዺፋንያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
3.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ (ልደታቸው)
4.አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
5.አባ ዮሐንስ ሊቀ ዻዻሳት
6.ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት
✞✞ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውሃ ወጣ::
እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ
ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ:- ''በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ
ይህ ነው'' አለ:: (ማቴ. 3:16)
✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞
"+" አዋጅ አዋጅ አዋጅ "+"
ለህዝበ ክርስቲያን በሙሉ የሰማ ላልሰማ ያሳማ..

ጾመ ነነዌ የካቲት 11/ 2011 ዓም (feb. 18/2019) እንዲሁም ዐቢይ ጾም የካቲት
25/2011 ዓም (march 4/2019) የሚገባ መሆኑ ይታወቅ።

ጾሙ ለእኛ በረከትን የምናገኝበት ፤ ለሀገራችን ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት...
እንዲሰጥ አበክረን የምንጸልይበት ያድርግልን።
አሥሩ የቅድስና ማዕርጋት
1 ጽማዌ
2 ልባዌ
3 ጣዕመ ዝማሬ
4 ኩነኔ
5 ፍቅር
6 አንብዓ ንስሐ
7 ሑሰት
8 ተሰጥሞ
9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
10 ከዊነ እሳት ናቸው።
1 ጽማዌ
2 ልባዌ
3 ጣዕመ ዝማሬ፣ ንጽሐ ሥጋ ይባላሉ።
4 ኩነኔ
5 ፍቅር
6 አንብዓ ንስሐ
7 ተሰጥሞ፣ ንጽሐ ነፍስ ይባላሉ።
8 ሑሰት
9 ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ
10 ከዊነ እሳት፣ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ።
የሰው ልጅ በዚህ ምድር ሲኖር በቅድስናና በንጽሕና እያደገ ሲመጣ የሚደርስባቸው አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት አሉ፡፡
እነዚህ አሥር መንፈሳዊ ማዕረጋት በሦስት የሚከፈሉ ሲሆን፡- ንጽሐ ሥጋ ፤ ንጽሐ ነፍስና ፤ ንጽሐ ልቡና ይባላሉ፡፡
አሥሩንም ማዕረጋት በአጭሩ እንመለከታለን፡፡
1. ጽማዌ፡-
ይህ ማዕረግ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ትህትናን፤ ራስን ዝቅ ማድረግን፤ መታገሥንና ነገሮችን በውስጥ ይዞ ማሰላሰልን ወዘተ…ይይዛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው የዚህን ዓለም ውጣ ውረድ ከማውራት ይከለከላል በብዙ ነገሮች ላይ ዝምታን ይመርጣል፡፡
2. ልባዌ፡-
ይህ ማስተዋልና ልብ ማለትን ገንዘብ ያደረጉ ሰዎች የሚገኙበት ደረጃ ነው፡፡
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች ልናገር ሳይሆን ልስማ ፤ ላስተምር ሳይሆን ልማር ይላሉ፡፡
የመጽሐፉ ቃል የሚለውን ማስተዋልና አብዝተው ኃጢአታቸውን ያሰላስላሉ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡
3. ጣዕመ ዝማሬ፡-
እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው አንደበቱን ከንባብ ልቡናውን ከምሥጢር ያቆራኛል፡፡
እዚህ ደረጃ የደረሱ ቅዱሳን አንደበታቸው ዝም ቢል በልባቸው ግን ዝም ብለው አያውቁም ከሰውነታቸውም ንጽሕና አይለይም፡፡
የሚያነቡትን መጽሐፍና የሚጸልዩትን ጸሎት ምሥጢሩን በደንብ እየተረዱት ስለሚያደርጉት አይሰለቻቸውም፡፡ እነዚህ ከ1-3 ያሉት የንጽሐ ሥጋ ማዕረጋት ናቸው፡፡
4. አንብዕ፡-
እዚህ ማዕረግ ላይ የደረሱ ሰዎች የጌታቸውን ፍቅር እያሰቡ እስከ ሞትና መከራ የተጓዘውን ጉዞ እያሰቡ ዘወትር ያለቅሳሉ፡፡ ያለምንም ተጽዕኖ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይወርዳል፡፡
ይህንንም የሚያደርጉት ለዚህ ዓለም ፍላጎታቸው መሟላት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ምሕረትና ቸርነት በመናፈቅ ነው፡፡
5. ኩነኔ፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ሥጋዊ ፈቃድ ሁሉ ለነፍስ ፈቃድ ይገዛል ፤ ነፍስ በሥጋ ፍላጎት ላይ ትሰለጥናለች፡፡ ምድራዊ (ሥጋዊ) ፍላጎቶች ይጠፉና ሰማያዊ (የነፍስ) ፍላጎቶች ቦታውን ይወርሳል፡፡
6. ፍቅር፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ ማንንም ሳይመርጡ ወዳጅንም ጠላትንም መውደድ ይጀምራሉ፡፡ እግዚአብሔር ወልድ ያደረገውን ታላቁን የፍቅር ሥራ እርሱን በመምሰል ሕይወት በመኖር በተግባር ይገልጻሉ፡፡
7. ሁሰት፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ቅዱሳን ባሉበት ቦታ ሆነው ሁሉን ነገር ማየት ይችላሉ፡፡ የቦታ ርቀትና የገዘፉ ቁሶች ሳያግዳቸው ፤ ሁሉን ያያሉ፡፡
እነዚህ ከ4-7 ያሉት የንጽሐ ነፍስ ማዕረጋት ናቸው፡፡
8. ንጻሬ መላእክት፡-
ከዚህ ማዕረግ ሲደርሱ መላእክትን ሲወጡና ሲወርዱ ማየት ይቻላል፡፡
9. ተሰጥሞ፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሰ ሰው በብርሃን ባሕር እየተመላለሰ በምድሪቱ ላይ ያለውን ሁሉ ማወቅ መረዳትና መመልከት ከመቻላቸውም አልፈው ሥሉስ ቅዱስ ከመመልከት በስተቀር በሰማያት ያለውንም ምሥጢር ወደ መረዳት ይደርሳሉ፡፡
10. ማዕረገ ከዊነ እሳት/ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/፡-
ከዚህ ማዕረግ የደረሱ ሰዎች ሥላሴን በዙፋኑ ላይ ሆኖ እንደ እስጢፋኖስ መመልከት ይጀምራሉ፡፡
እንዲሁም እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በአካለ ነፍስ ተነጥቀው ወደ ሰማያት በመውጣት ሰማያትን መጎብኘት ወደ መቻል ይደርሳሉ፡፡
ይቆየን፡፡
......................................................................
@rituaH @rituaH @rituaH
"+" በስመአብ ወወለድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። "+"

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት በየዓመቱ የካቲት 16 ቀን በታላቅ ድምቀት የቅድስተ ቅዱሳን የድንግል ማርያም ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ይከበራል ። በዓሉም ታለቅነት እንደምንድ ነው ቢሉ የኃጥአን ተስፋ የደካሞች ምርኩዝ ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከአኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የምሕረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ቀን እና የቃል ኪዳን ፍጻሜ የተከናወነበት ዕለት ሰለሆነ ርዕሰ ኪዳናት ይባላል። ድንግል ማርያምም የኪዳናት መደምደሚያ ናተ እና እርሷም ኪዳነምሕረት ትባላለች ።በቅዱሳት መጻሀፍት ታሪክ እንደምንማረው በብለይኪዳን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከቅዱሳንወዳጆቹ የፈጸማቸው አምሰት ልዩልዩ ኪዳናት ተከናውነዋል እነዚህም ኪዳናት የራሳቸው አስደናቂ ባህሪያት የነበሯቸውእናበኃላዘመንለሚፈጸመውአማናዊውውልመርገፍምሳሌነበሩ።የኪዳናቱምባለቤትየሠራዊትጌታእግዚአብሔርለመረጣቸው ለቅዱሳኑ የገባው የተማማለው ውል(ስምምነት) ቃል ኪዳን ይባላል።

"+" ቃል ኪዳን "+"

ቃል ኪዳን የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ለ33 ጊዜ ያህል ተጠቅሷል <<ኪዳን>>ተካየደ ተማማለ ቃል ተገባባ ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን <<ቃል>> የሚለው ጋር ሲያያዝ<<ቃለ ኪዳን>> ይባላል ትርጉሙም< ውል ስምምነት >ማለት ነው።ስለዚህ
በብሉይ ኪዳን የተፈጸመት ኪዳናት የቆዩ ውሎች ስምምነቶች ይባላሉ፤ምክንያቱም ኪዳናቱ የተፈጸሙበት ዘመናት ርዝመተ እና በዓመተ ፍዳ የተፈጸሙ ስለሆኑ የመከራውን ጊዜ ያወሳሉ፤ በሐዲስ ኪዳንም የተፈጸሙ ኪዳናት ሐዲሱ ውል ከተፈጸመ በኃላ የተከናወኑ ስለሆኑ ዘመነ ምህረትን የሚያውጁ ጸጋቸው የበዛ አማናዊ ኪዳናት ናቸው። ቃልኪዳን ሲፈጸም የቃልኪዳኑ ባለቤት እና ቃልኪዳኑንበሚቀበለውመካካልመሐላቸውን ስምምነታቸውን ለማጽናት ምልከትን ማኖር የተለመደ ሥርዓት ነው።

"+" ኪዳነ አዳም"+"
በብሉይ ኪዳን ከተከናወኑት ኩዳናት የመጀመረያው በአዳም እና በእግዚአብሔር መካካል የተደረገ ሲሆን፤ ምልከቱም እጸ በለስ ነው ሰምምነቱም ቀዳማይ ሰው አዳም ከፈጣሪው የተሰጠውን ትህዛዝ ቢጠብቅ በህይወት እንደሚኖር ባይጠብቃት ግን የሞት ሞት እንደሚሞት ነገረው እርሱም ለ7 ዓመታት ሕግን ስለጠብቃት በፍጹም ክብር ይኖር ነበር። በኃላ ግን ሕግን በመጣሱ ምክንያት ቃልኪዳኑን ስላፈረሰ ሞት ተፈረደበት በዚህም እያዘነ ፈጣሪውን ይቅርታ ቢጠይቅ ከአምስተ ቀን ተኩል በኃላ ከልጅልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው የምህረት ተስፋን ሰጠው።ዘመኑም ሲደርስ የአዳም ተስፋ ከሆነች ከቅድስተ ቅዱሳን ከድንግል ማርያም እግዚአብሔር ወልድ በቤተልሔም ተወለደ ዓለሙንም አዳነ ።

"+" ኪዳነ ኖኅ ኖኅ "+"
ኃጢአታቸው እጅግ በበዛ እና በረከሱ ሰዎች መካካል የነበረ ንጹሕ እና ጸድቅ የነበረ ሰው ነው፡፡ ፍጥረቱ በሙሉ ቢበድሉም እግዚአብሔርም ሰውን በመፍጠሩ ቢጸጸትም ሰብአ ትካትመመለስ ባለመቻላቸው አምላካዊ ፍርዱን ግን አልተወም ምድርንም በንፍር ውኃ አጠፋት ዘፍ6፥18። ጻድቁ ኖኅ ግን ስምንት ነፍስ ይዞ ከመዓቱ ቢያተርፈው ለእግዚአብሔር መሠዋያን ሠራ መሥዋዕትን አቀረበ እግዚአብሔርም የኖኅን መሥዋዕት በመቀበል ቃልኪዳንን ፈጸመ ውሉም <<ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ አቆማለው----ቀስቲቱም በደመና ነሆናለች---በህያው ነፍስ መካካል ያለውን የዘለዓለምቃል ለማሰብ አያታለው፡፡>> ዘፍ9፥8-17 ምደርቱንም ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንደማያጠፋት በስሙ ማለለት ይህም እስከዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፡፡

"+" ኪዳነ አበርሃም "+"
አብርሃም አባታችን ከሚኖርበት ሀገሩን ቤተሰቡን ትቶ እንዲወጣ ከእግዚአብሔር ቢታዘዝ እርሱም ፈቃደኛ በመሆን ወደ ማያውቀውሀገርሲሰደድበልቡየታመነውከአምለኩየተቀበለውየተስፋቃልኪዳንይዞነበር።የቃልኪዳንምልክቱም<<ከእናንተወንድሁሉይገረዝየቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ በእኔ እና በእናንተመካካልላለው ቃል ኪዳንምልከክት ይሆናል ።-- ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላላም ቃል ኪዳን ይሆናል ።>>በማለት አብርሃምን ከወገኖቹ ጋር የእግዚአብሔር ሕዝብ ለርስቱ የተለየ የተመረጠ እንዲሆኑ አድርጓል።

"+" ኪዳነ ሙሴ "+"
ኪዳነሙሴ ይህ ኪዳን ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የተሰጠ ሲሆን ሕዝቡትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንዲጠብቁ እና ከእርሱ ሌላ አምላክ እናዳያመልኩ መመሪያ ይሆናቸው ዘንድ በነብዪ አማካኝነት የመጀመሪያቱን ጽላት በመስጠት ቃል ኪዳኑን አጽንቷል ።ይህም ለዘለዓም ሥርዓት ሆኖ ይኖራል ሕዝቡም ታቦተ ጽዮንን ባከበሯት ጊዜ በረከተ እግዚአበሔር ይበዛላቸው ነበር። የኪዳኑም ምልክት ታቦተ ጽዮን ነበረች ለእሰራኤል ዘነፍስ ክርስቲኖችም ምህረት የምታሰጥ አማናዊት ታቦት ዘዶር ድንግልማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘናት የቃልኪዳን ምልከታችን ኪዳነ ምሕረት ናት ።ዘጸ24፥1-20

"+" ኪዳነ ዳዊት "+"
ይህ ኪዳን በብሉይ ኪዳን ከተፈጸሙት ዐበይት ኪዳናት አንዱ ሲሆን
ከእረኝነት አንስቶ የመረጠው እግዚአብሔር በታናሽነቱ እዝበ እስራኤልን ይመራ ዘንድ የመረጠው በትረ መንግሥትን ከቤቱ ለዘላዓለም እንዳማይጠፋ ቃል ኪዳን ገብቶለታል መዝ131፥11-13 ትዕዛዙን ለሚጠብቁት በሙሉ መሐላውንጽም ሲፈላቸው እንደሚኖር አረጋግጦለታል ።የዚህ መሐላ ምልክቱ በትረመንግሰት ሲሆን የይሁዳ አንበሳ ከርስቶስ የዳዊት ዘር ከሆነች ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በእስራኤል ዘነፍስ ለመንገሱ ምሳሌ ዳዊት በመናገሻው ከተማ በጽዮን እንደነገሰባት የዓለም ንጉሥ ክርስቶስም በመናገሻ ከተማው በደብረ ጽዮን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅጸን ለመንገሱ ምሳሌ ነው እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው ኪዳናት በሙሉ የእግዚአብሔር ምሕረት የተገለጠባቸው የቅዱሳኑ ጸጋ የታየባቸው ደኅነተ ሥጋን ብቻ ያሰጡ የነበሩ ቃልኪዳናት ነበሩ።ምክንያቱም <<እነሱ ያለእኛ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ አይችሉም እና>>እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በመልክቱ አማናዊው እና እውነተኛው ኪዳን ሲደርስ የአባቶችን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ ጠላቶቹ ሳለን ወዳጆቹ ያደርግን ዘንድ የጥልን ግድግዳ አፍርሶ የምሕረትን ጸጋ አበዛልን፣ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ህይወትን አደለን። ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ከዳግማዊት ሔዋን ከኪዳነምሕረት ተወልዶ ሰላማችንን አወጀልን ፍኖተ ጽድቅንም አቀናልን። ጠፍተን እንዳንቀርም ለርስቱ የመረጣቸውን፣ የወደዳቸውን፣ ያከበራቸውን፣ ያጸደቃቸውን፣ ቅዱሳንን ለእኛ ተስፋ እንዲሆኑ የማይጠፋ መሐላንም ሰጣቸው ።የቀደሙት አባቶቻችን የልባቸው ማረፊያ ትሆን ዘንድ
ወልድ በተለየ አካሉ ማደሪያው ያደረጋት መቅደሰ ሰሎሞን፣ የአዳም ተስፋው፣ የኖህ መርከቡ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ የሙሴ ጽላት ፣የዳዊት በገና፣ የኢሳይስ ድንግል ታቦት ዘዶር ድንግል ማርያምም የምህረት ቃልኪዳንን የካቲት16 ቀን ተቀብላለች ይህም ቃልኪዳን የተለየ የምሕረት ቃልኪዳን ነው።ከፍጡራን መካከል እንደእርሷ የተለየ ቃል ኪዳንን የተቀበለ የለም፤ ወደፊትም አይኖርም፣እርሷ ከሁሉም ተለይታ የከበረች ምልዕተ ጸጋ ስለሆነች የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ታሳርጋለች በተሰጣት ጸጋም ለዘለዓለም ስታማልድ ስታስምር ትኖራለች።በዚህ መሰረት ኪዳምህረት፣ ድንግልማርያም፣ ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በመካነ ጎሎጎታ በተቀበለችው የምህረትቃልኪዳን ከተፈጸማላቸው ተስፈኞች መካከል አንዱ ስምዖን የሚባል ደግሰው ነበር፡፡

"+" ከበላዔሰብ (ስምዖን ) "+"
እንግዳ ተቀባይ ስለነበር በዚህ ምግባሩ ሰይጣን ቀናበት እንግዳ መሰሎ ከቤቱ መጣ ስምዖንም ምግብ አዘ
ጋጅቶ አቀረበለት ይህን አልበላም አለ ።ሙኩት አርዶ አሰናድቶ አቀረበለት ።ይህም አይስማማኝም አለው እንኪያስ ምን ላምጣልህ አለው ።ልጅህን አርደህ አሰናድተህ ብታመጣልኝ እበላለው አለው።ለጊዜው አዘነ ኃላ ግን አብርሃም ክብር ማግኘት ልጁን ሰጥቶ አይደለምን የእግዚአብሔር እንግዳ ማሳዘን አይገባኝም ብሎ ልጁን አርዶ አሰናድቶ ሰጠው ቅመስልኝ አለው ።አይሆንም አለ ግድ ቢለው ጥፍሩን አስነክቶ ቀመሰለት ከመረቁ ጋር ተዋህዷታል ያን ቢያጣጥመው ቢጣፍጠው ያቀረበውን ጥርግ አድረጎ በለ ።ከዚህ በኃላ እህል የማይቀምስ ሆነ ቤተሰቦቹን ጨርሶ ጐረቤቶቹን፣ጐረቤቶቹን ጨርሶ መንገኞችንእየያዘሲበላሰባሰምንት ሰውበላ።የማይታወቅበት ሲሆን ሸሽቶ ወደ ሌላ ሀገር ሄደ ከመንገድ ቢየደባ የማያገኝ ሆነ ተነስቶ ሲሄድ አንድ ነዳይ ከመንገድ ተቀምጦ አየ ሊበላው ቢሄድ ሰውነቱ ከቁስል ነዶ አይቶ ተጸየፈው ውኃ በመንቅል ይዞ ነበር ነዳዪም በሥላሴ አለው ዝም አለው።በሚካኤል በገበርኤል አለው። ዝም አለው በድንግል ማርያም አለው ይህችስ እንደምታድን በልጅነት ሰምቻለው ብሎ መንቀሉን ሰጠው።ንቃቃቱ እንዃን ስይርስለት ጨረስህበኝ ብሎ ነጥቆት ሄደ።ከዚያም ከዋሻ ገብቶ ሞተ መላእክተ ጽልመት ነፍሱን እጅ አድርገው ሊያስፈርዱ ከጌታፊት ቀረቡ፤ እመቤታችን ልጄ ሆይ ይህቺን ነፍስ ማርልኝ አለችው ጌታም ሰባሰምንት ነፍስ ያጠፋ ፈጣሪውን የካደ ውሻ ይማራልን?አላት በስሜ የተጠማ አጠጥቶ አይደለምን አለችው እንኪያስ ይመዘን አለ።ቢመዘን ሰባስምንት ነፍስ የሚመዝን ቢሆን እመቤታችን በጥርኝ ውኃ ጥላዋን ጣል አድርጋበት ያች ጥርኝ ውኃ መዝናለች መላእክተ ጽልመትም እርሷ እያለች ምን እናገኛለን ብለው አፍረው ተመለሱ ።ያቺንም ነፍስ መላእክተ ብርሃን በዕልልታ ወደገነት አስገብተዋታል።እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው ኪዳናት በሙሉ የእግዚአብሔር ምሕረት የተገለጠባቸው የቅዱሳኑ ጸጋ የታየባቸው ደኅነተ ሥጋን ብቻ ያሰጡ የነበሩ ቃልኪዳናት ነበሩ።ምክንያቱም <<እነሱ ያለእኛ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ አይችሉም እና>>እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በመልክቱ አማናዊው እና እውነተኛው ኪዳን ሲደርስ የአባቶችን ተስፋ ይፈጽም ዘንድ ጠላቶቹ ሳለን ወዳጆቹ ያደርግን ዘንድ የጥልን ግድግዳ አፍርሶ የምሕረትን ጸጋ አበዛልን፣ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ህይወትን አደለን። ዳግማዊ አዳም ክርስቶስም ከዳግማዊት ሔዋን ከኪዳነ ምሕረት ተወልዶ ሰላማችንን አወጀልን ፍኖተ ጽድቅንም አቀናልን። ጠፍተን እንዳንቀርም ለርስቱ የመረጣቸውን፣የወደዳቸውን፣ያከበራቸውን፣ያጸደቃቸውን፣ቅዱሳንንለእኛተስፋእንዲሆኑየማይጠፋመሐላንምሰጣቸው።ነፍስመላእክተብርሃንበዕልልታወደገነትአስገብተዋታል።
ከበላዔሰብ (ስምዖን ) ታሪክ እንደምንማረው ቸርነት ያባህሪ ገንዘቡ የሆነ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በሰጣት ቃል ኪዳን መሰረት አትግደል የሚለውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያፈረሰውን ሰው የእርሷ አስዳነቂ ልመና እና የማይታበለው የልጇ የኢየሱስ ከርስቶስ ችርነት ታክሎበት ከሞት እንደዳነ እንመለከታለን ።ይህ ታሪክ በዕለተ አርብ ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስረቶስ በስተቀኝ ተሰቅሎ የነበረው ፋያታዊ ዘየማን በህይወት ዘመኑ ሁሉ በበደል እና በእርኩሰት እንዲሁም ነፍስ በማጥፋት የታወቀ ሲሆን በበደሉም ምክንያት ሞት ተፈርዶበት በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ በአጠገቡ የተሰቀለው ያለምንም በደል እንደሆነ እና አምላክነቱን በሚሰራው ታምራት ከተረዳ በኃላ ኣብቱ በመንግሰትህ አስበኝ በማለት ይቅርታን በለመነ ጊዜ ቸርነቱ የማይቅበት አምላክ እውነት እልሃለው ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ በማለት የሞት ሰለባ የነበረውን ሰው ለ5500 ዓመት ያህል በእሳት ነበልባል ትጠበቅ የነበረቸውን ገነትን ከተስፈኞቹ ተቀድሞ የገነት በር ከፋች ለመሆን በቅቷል፡፡
ኪዳነምሕረት ስንል የምሕረት ውል ሰምምነት ማለት ሰለሆነ ድንግል ማርያምም በቀደመ ልመናዋ ለምና የምታስምር እንደሆነች እንረዳልን ።እመቤታችን ዝክሯን ለሚዘክሩ መታሰቢያዋን ለሚደርጉ ታምሯን ለሚሰሙ፥ ለሚያሰሙ፥ ለሚተረገሙ ፥ውዳስዋን ለሚያደርሱ ፣ቅዳሴዋን ለሚቀድሱ ቤተ መቅደሷን ለሚሰሩ ፣በአጠቃላይ ሰሟን ለሚጠሩ ፈጥና የምትደርስ አፍጣኒተ ረድሔት ናት ። ከከበሩት ይልቅ የከበረች ናት እና እነከብራታለን ከፍ ከፍ እናደርጋታለን ስሟ ጠርተን አንጠግብም እና ደጋግመን እናወድሳታለን ከጥፋት ውኃ የዳንባት የመዳናችን አርማችን ምልክታችን የመዳችን ትምክህት ሰለሆነች እንደ ልጇ ዳዊት እምነ ጽዮን እያልን እንጠራታለን አምባ መጠጊያ መመኪያችን ከክፋ ቀን መከለያችን እናተታችን እመአቤታችን ታቦት ዘዶር ድንግልን እንደ ቅዱሳኑ ኪዳነምሕረት እመቤትለዓም ሁሉ መድኃኒት እያልን ሰንማጸናት ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍ ነጻ ታወጣናለች እና እስከመጨረሻው ድረስ በሃይማኖት በምግባር ተወስነን እንድንኖር የእግዚአሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

"+* ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር "+"
-----------------------------------
@rituaH @rituaH @rituaH
"+"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዐድዋ ድል የነበራት ድርሻ"+"

“ኢትዮጵያዊሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ”...

ለጦርነቱ በቤተ ክርስቲያን ጸሎተ ምህላ ታውጇል፤ ዘማች ታቦታት ተመርጠው የአዝማች ኮሚቴም ተቋቁሟል፤ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘማች ታቦታቱ መሪ ነበር፤ ለመላው ዘማች ሠራዊት ሥነ ልቡናዊ ጥንካሬን (የሰማዕትነት ወኔን) የሰጠ የሰባት ቀናት የቁም ፍትሐት ተደርጓል፤ ሊቃውንቱ ከጦርነቱ በድል እንደምንመለስ በቅኔያቸው ትንቢት ተናግረዋል፤ ዐፄ ምኒልክ የክተት ዐዋጅ ካስነገሩ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው “አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን ቤተ ክርስቲያን የሣር ክዳኑን ለውጨ ባማረ ሕንጻ አሠራዋለሁ” ብለው ብፅዓት አድርገዋል፡፡ ከምርኮኛ የጣሊያን ወታደሮች አንዱ በዐውደ ውጊያው “በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተመላለሰ ‹ወደ ጦርነቱ ግቡ፤ ኢጣሊያኖችን ማርኩ› እያለ ትእዛዝ ሲሰጥ እና ሲወጋን የዋለ ማነው?” ብሎ ጠይቋል፡፡ በጦር ሜዳ ለበቁት ሰዎች ተገልጦ እየታየ ከአርበኞቻችን ጋራ የዋለው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ዐቃቤ መልአክ (Patron Saint) ነው፡፡ በዐድዋ ድል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአንበሳ ድርሻ አላት፡፡
“ኢትዮጵያ ሥጋችን ቤተ ክርስቲያን ነፍሳችን ናት፤ ነፍስ እና ሥጋ ደግሞ አንድ ነው፡፡ አገር ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለአገር የለም፤ ኢትዮጵያን ያህል አገር ማጣት እግዚአብሔርን ከሚያህል ጌታ መለየት ሞት ነው፡፡ ሃይማኖትን እና ነጻነትን ማጣት ሽንፈት ነው፤ ስለ አገር፣ ሃይማኖት እና ነጻነት መሞት ደግሞ ክብር ነው፡፡” (የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ)
“በቀደሙት የጦርነት ታሪኮች ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ለሚፈራረቅባት መከራ አንዱ ምንጭ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀጥተኛ ቅኝ አገዛዝን በመቃወም ሀገራዊ ሉዓላዊነትን እና ነጻነትን ከማረጋገጥ አልፋ ኢትዮጵያዊነት የጥቁሮች ኩራት እና ክብር እንዲሆን ማድረጓ ያልተዋጠላቸው የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ኀይሎች ሤራ ነው፡፡ የሀገራዊ ነጻነቱ ተቋዳሽ የሆነ ሁሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ውለታ አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋም በዓለም ቅርስነት ደረጃ ተመዝግባ ልትጠበቅ የሚገባት ናት፡፡”
“ሰብእሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ” የሚለውን የቅዱስ ዳዊት ቃል “ኢትዮጵያዊሰ እንዘ ክቡር ውእቱ ኢያእመረ” በሚል ተክተነዋል፤ ዐድዋ በየትኛው የአገሪቱ ክፍል እንደሚገኝ እንኳ የማያውቁ ኢትዮጵያውያን ይስተዋላሉ፤ ‹ዛሬ ደ'ሞ የምን በዓል ነው?› የሚሉ ጋዜጠኞች ጭምር አሉ፤ ከዐድዋ ድል ይልቅ የቫለንታየን ቀን ነው በልዩ ትኩረት የተከበረው፤ ዐድዋ እኛ በሲዲ ከምናስተማረው በላይ ጥቁርነትን፣ ኢትዮጵያዊነትን፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በአንድ ጊዜ በላቲን አሜሪካ፣ በአፍሪካ እና በአውሮፓ ያበሠረ ሰባኪ ነው፤ አሁን በግሎባላይዜሽን ስም የምንሰብከው እና የምንዘምረው ሁሉ ዐድዋ የሰበከውን እያጠፋው ነው፡፡ ማንነቱን ያጣ ትውልድ ለመገዛት የተመቸ ነው፤ ለሚሆነው እና ለሆነው ነገር ሁሉ ግድየለውምና፡፡ የታሪክ ትምህርታችን ምን ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው? ስለ ባህሉ በምልዓት የሚያውቅ አለን ወይስ ዐፄ ምኒልክ አሁንም ‹ማርያምን አልምርህም› እንዲሉን እንፈልጋለን? ራሳችንን፣ ባህላችንን እስካላወቅን ድረስ ማሸነፍ አንችልም፡፡ ከየት እንደመጣን ካላወቅን ወዴት እንደምንሄድ አናውቅም፤ ወደፊት ለመገስገስ ወደ ኋላ መመለስ (ሳንኮፋ) ይኖርብናል፤ የኋላቀርነታችን መንሥኤው ታሪካችንን በመጠበቃችን ሳይሆን ማንታችንን በማጣታችን ነው፡፡ ታሪኩን የማያውቅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ በማያውቅ ልጅ ይመሰላል፡፡ ታሪካችን ተኝተን የምናንቀላፋበት መከዳ (headrest) ሳይሆን እንደ ጥንቱ ሥልጣኔያችን የዕድገታችን መስፈንጠሪያ (fulcrum) ልናደርገው ይገባል፡፡”
- - - - - - - - - -- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም - የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ሀገርነት እና ነጻነት ያረጋገጠው፤ ምዕራባውያን ቅኝ ገዥዎች በበርሊኑ ኮንፈረንስ የወጠኑትን የመስፋፋት እና አፍሪካን የመቀራመት ፖሊሲያቸውን ዳግመኛ እንዲመረምሩ ያደረገው፤ ለፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መፋፋም ምክንያት የሆነው፤ ኢትዮጵያኒዝምእየተባለ የሚጠራው ከነጮች ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የጥቁሮች የሃይማኖት እንቅስቃሴ በተለይም በአሜሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያስጀመረው የዐድዋ ድል የተመዘገበበት ነው፡፡ ዘንድሮ ድሉን ለ115ኛ ዓመት ለማክበር ዕድል አግኝተናል፡፡ አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች የበርሊኑን ጉባኤ ተከትሎ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚይዙት ቦታ የእነርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙ የተጭበረበሩ እና የማታለያ ስምምነቶችን አድርገዋል፡፡ በ1881 ዓ.ም በኢጣሊያዊ ተወካይ አንቶሎኒ እና በዐፄ ምኒልክ መካከል የተደረገው የውጫሌ ስምምነት ለዚህ ዋናው ማሳያ ነው፡፡
የውጫሌ ውል ሃያ አንቀጾች ያሉት እና በሁለት ቋንቋዎች የተጻፈ ሲሆን የግጭቱ መንሥኤ የሆነው በጣሊያንኛ ቋንቋ የተጻፈው 17ኛው አንቀጽ ነበር፡፡ የአማርኛው ውል፡-”የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የውጭ ግንኙነቱን በኢጣልያ አጋዥነት ማድረግ ይቻላቸዋል” በማለት ምርጫው የዐፄ ምኒልክ መሆኑን ያሳያል፡፡ የጣሊያንኛው ትርጉም ግን፡- “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የውጭ ግንኙነቱን በኢጣሊያ በኩል ማድረግ ይገባዋል” በማለት ኢትዮጵያን የጣሊያን ጥገኛ ያደርጋታል፡፡ በዚህም አንቀጹን አዛብተው በመተርጎም ኢትዮጵያ በኢጣሊያ የሞግዚት አስተዳደር ሥር ሆናለች ብለው ለዓለም መንግሥታት ያሳወቁበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ከሩስያ በስተቀር ኀያላን መንግሥታት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ የውጫሌ ውል ሰጥቶኛል የምትለውን ዕውቅና ለመስጠት ዝግጁ ነበሩ፡፡ ውሉ የተጭበረበረ መሆኑ ስለታወቀ ተቀባይነት ዐጣ፣ የዐድዋ ጦርነት ሊመጣ ግድ ሆነ፡፡
የዐድዋ ጦርነት በአንድ ዐውደ ውጊያ ያበቃ ሳይሆን ሂደት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ውጊያ ዐምባላጄ ላይ ኅዳር 29 ቀን 1888 ዓ.ም ተደርጎ በራስ መኮንን እና በፊታውራሪ ገበየሁ የጦር መሪነት በድል ተጠናቀቀ፡፡ ሁለተኛው፣ የጠላት ጦር መቀሌ መሽጎ ነበር፡፡ በእቴጌ ጣይቱ ዘዴ ውኃ የሚያገኙበት ምንጭ ስለተዘጋ ጠላት ለቆ ወጣ፡፡ ዋናው የዐድዋ ጦርነት የካቲት 23 ቀን በዕለተ ሰንበት በስድስት ሰዓት ውስጥ በኢትዮጵያ የበላይነት እና ድል አድራጊነት ተጠናቀቀ፡፡ የተሳሳተ የንባብ ካርታ፣ የመንገድ መሳሳት፣ ጠላት በታጠቀው ዘመናዊ መሣሪያ እና በሠለጠነው ሠራዊቱ የተነሣ ለኢትዮጵያውያን የሰጠው አነስተኛ ግምት፣ ኢትዮጵያውያን በሰንበት እና በድርብ በዓል ጦርነት አይገጥሙም ብለው ማሰባቸው ለወራሪው ሽንፈት የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የዐድዋ ድል በአራቱም ማእዝናት የሚገኙ ድፍን ኢትዮጵያውያን የከተቱበት (የተሳተፉበት)፣ የኢትዮጵያን ነጻነት ከማረጋገጥ አልፎ ዓለምአቀፋዊ እንቅስቃሴን የፈጠረ፣ በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች ነጮችን ያሸነፉበት ዐቢይ ወታደራዊ እና ሞራላዊ ድል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ድል እንዲያደርግ የረዱት ትልቅ የአገር ፍቅር ስሜቱ፣ ጦርነቱ ለአገር እና ለሃይማኖት ጭምር መሆኑን ሠራዊቱ ማመኑን፣ የላቀ ጦር ስልት እና አመራር፣ ጠንካራ የሠራዊት ሞራል እና የሥነ ልቡና ዝግጅት፣ ሕዝብን የማንቀሳቀስ እና የመምራት ብቃት ናቸው፡፡ የዐድዋ ድል በውጤቱ ለኢትዮጵያውያን የትብብር፣ የአንድነት፣ የኩራት እ
ና የክብር ምንጭ ሆኗል፤ ዓለም አቀፍ ዝናን አጎናጽፏታል፤ አውሮፓውያኑ ድሉን ተከትሎ/ጣሊያን በቅድሚያ/ ኤምባሲዎችን በመክፈት ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ረድቷታል፡፡ በቅኝ ገዥዎች የተከበበችው ኢትዮጵያ ድንበሯን እንድትካለል ምክንያት ሆኗል - ሉዓላዊ ሀገርነቷ እና ነጻነቷ ተረጋግጧል፡፡
በዐድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከመነሻው እስከ መጨረሻው፣ ከዘመቻው እስከ ድሉ፣ ከዋዜማው እስከ ጦርነቱ በመሪነት እና በተሳታፊነት ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ክብሪ ሀገር ባላት አስተምህሮ ሕዝብን በመቀስቀስ፣ አመራር በመስጠት፣ አብራ በመዝመት፣ የሥነ ልቡና ዝግጅት በማድረግ፣ በጦርነቱ በመሳተፍ፣ መረጃ በመስጠት እና በማስቀመጥ የአንበሳውን ድርሻ ትወስዳለች፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደቀደመው ዘመን ያላት ሁለገብ ሚና እና ተደማጭነት በአመራር እና አስተዳደራዊ መዋቅር ችግሮች፣ በሉላዊነት(ግሎባላይዜሽን
) ተጽዕኖ፣ በምእመናን መንፈሳዊ ሕይወት መዳከም፣ በቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ምእመናን ትስስር መላላት፣ ዘመኑን የዋጀ እና ስልታዊ(ስትራተጂያዊ) አካሄድ ጉድለት የተነሣ በአሁኑ ወቅት ስጋት ተጋርጦባታል፡፡
“ኢትዮጵያ ካልተበታተነች በአፍሪካ ያለው ቅኝ ግዛት አይረጋም፤ ኢትዮጵያን ለመበታተን ደግሞ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን መውረስ ወይም ማዳከም” የወራሪዎች ቁልፍ ተግባር ነበር ፡፡ ዛሬም ትውልዱን ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለማስመቸት ታሪኩን እንዳያውቅ እና እንዲያናንቅ በውስጥም በውጭም የሚደረገውን ዘመቻ ሊነቁበት ይገባል፡፡ ለዚህም የዐድዋን ድል ከወሬ እና ከመፈክር በላይ ከነሙሉ ክብሩ በማሰብ እና በማስታወስ የትውልዱ ሥነ ልቡና በአኩሪ ታሪኩ ላይ እንዲገነባ፣ ስደተኛ መንፈሱ እንዲያበቃ የሚያደርግ ተጨባጭ ሥራ መሥራት እንደሚገባ ተመክሯል፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያጋጠሟትን ከ137 በላይ ጦርነቶች በድል ብትወጣም የወራሪዎች ቀዳሚ ዒላማ ሆነው በታረዱባት መነኮሳቷ፣ ካህናቷ እና ሊቃውንቷ፣ በተቀሰጡባት እና በተሰደዱባት ምእመናኗ፣ በተቆነጠሉባት እና በተዘረፉባት ቅርሷቿ፣ በተቃጠሉባት አድባራቷ እና ገዳማቷ ከባድ መሥዋዕትነት የከፈለችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዐድዋ በመሳሰሉት ታላላቅ ድሎች የነበራት ሚና ከነገሥታቱ ጋራ እያቆራኙ በሚከሷት ወገኖች እና በሚዲያው ተገቢው ትኩረት አልተሰጣትም፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመናት ሀገራዊ ሓለፊነት እና ሚና ይዛ በመቆየቷ፤ አገር ያለሃይማኖት፣ ሃይማኖት ያለሀገር የሌለ በመሆኑ፤ በቀደሙት የግራኝ ወረራ፣ የመቅደላ ጦርነት እና የድርቡሽን ጥቃት እንደመሳሰሉት አስከፊ ወቅቶች ከሁሉም በላይ ጥቃት የደረሰባት መሆኑ፤ በዐድዋ ጦርነት የወራሪው መንገድ ጠራጊዎች እንደ አባ ማስያስ እና ሳሌንቢኒ/በጦር መሐንዲስ ስም/ ያሉት ሚስዮናውያን መሆናቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዐድዋ ጦርነት ለነበራት አገባብ አመክንዮ ናቸው፡፡ ዳንኤል ሮፕስ የተባለ ታዋቂ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ “አክሌዚያ” በተባለው ጋዜጣ የመስከረም 1963 ዓ.ም እትም “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታውቋታላችሁ?” ሲል ባሰፈረው ጽሑፍ “ወራሪዎች ምድሯን የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤ ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴ መሣሪያ ሆኖ በመገኘቱ ነጻነት ተመልሳ ተገኝታለች፤” ብሏል፡፡ “ከሐን ኢንተርናሽናል” የተባለ ሌላ ጋዜጣ በመስከረም 1964 ዓ.ም እትሙ ስለ ኢትዮጵያውያን ሲጽፍ፣ “ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ሃይማኖት እና ክብር ከመጠበቅ አልፈው ለሌሎች መብት እና ነጻነት የሚታገሉ ሕዝቦች ናቸው፤” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዐድዋ ድል የነበራት ድርሻ በቅድመ ዝግጅት፣ በዝግጅት እና በድርጊት ደረጃ ከፋፍለን ማየት እንችላለን ፡፡ በቅድመ ዝግጅት ደረጃ ሲደረግ በቆየው የሰላም ጥረት ሜጀር ሳልሳ የተባለው ጣሊያናዊ “ከዚህ ቀደም ባንዲራችን ተተክሎ እስከነበረበት አስከ ዐላጄ ድረስ ያለውን አገር ልቀቁልንና ባንዲራችንን እንትከል” በሚል የትዕቢት ቃል በተናገረ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ምኒልክ “እኔ የመጣሁት እናንተ የተከላችሁትን ባንዲራ ለመንቀል እና ለመጣል ነውና ይህን የመሰለውን ውል አልቀበለውም፡፡ በተረፈ ግፍን በማይወደው በእግዚአብሔር ተማምኜ በመጣችሁበት መንገድ እቀበላችኋለሁ፤ በአገሬ በኢትዮጵያ ላይ የሮማ ሰንደቅ ዓላማ እንዲተከልበት አልፈቅድም፤” በሚል መልሰውለታል፡፡ በዚህም ቅድመ ዝግጅቱ ቀጥሎ በአብያተ ክርስቲያን የአዝማች ኮሚቴ ተቋቁሟል፤ ዘማች አብያተ ክርስቲያንም ተለይተዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በአዲስ አበባ የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም፣ ከሸዋ የግንባሮ ማርያም፣ የበር ግቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ከአክሱም ጽዮን በገዳሙ አስተባባሪነት ታቦተ መድኃኔዓለምን እና ታቦተ ማርያምን ይዘው በርካታ ካህናት ተመድበዋል፡፡ ከሊቃውንቱ እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ፣ የደብረ ሊባኖስ ፀባቴ፣ የእንጦጦ ማርያም ደብር አስተዳዳሪ፣ ከቀራንዮ መድኃኔዓለም እና ከሆለታ ኪዳነ ምሕረት ተመድበዋል፡፡ ከንዋያተ ቅድሳቱም ከታቦታቱ በተጨማሪ መስቀል፣ ቃጭል፣ ጥላዎች እና ድባቦች ተይዘው ከሊቃውንቱ እና ካህናቱ ጋራ ዘምተዋል፡፡
ሌላው ሁነኛ የቅድመ ዝግጅቱ አካል የዐፄ ምኒልክ የክተት ዐዋጅ ይዘት ነው፤ እርሱም እንዲህ ይላል፡-
“ስማ፣ ስማ፣ ተሰማ፤
የማይሰማ የእግዚአብሔር እና የወላዲተ አምላክ ጠላት ነው፡፡
ስማ፣ ስማ ተሰማማ፤ የማይሰማ የእግዚአብሔር እና የቤተ ክርስቲያን ጠላት ነው፡፡
ስማ፣ ስማ፣ ተሰማማ፤ የማይሰማ የእግዚአብሔር እና የንጉሡ ጠላት ነው፡፡
እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ ፤ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ ፡፡ እንግዲህ ግን ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ለኔ ሞት አላዝንም ፡፡ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም ፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብየ አልጠረጥረውም።
አሁንም አገር የሚያጠፋ ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን ባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ ፣ የሰውንም መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር ። አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጥውም ። ያገሬ ሰው ካሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም፤ አንተም እስካሁን አላስቀየምኸኝም አሁንም ጉልበት ያለህ በጉልበት እርዳኝ ፤ጉልበትም የሌለህ ለልጅ ፣ ለምሽትህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በኀዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን ኋላ ትጣላኛለህ አልተውኸም ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም ፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረኢሉ ከትተህ ላግኝህ።
ከዚህ በኋላ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምኒልክ ወደ አዲስ አበባ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አምርተው ጸሎት አቀረቡ፤ ብፅዓትም አደረጉ፡፡ ብፅዓታቸውም “አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሉን ቢሰጠኝ ይህን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሣር ክዳኑን ለውጬ ባማረ ሕንጻ አሠራዋለሁ፤” የሚል ነበር፡፡
ወደ ዐድዋ በተደረገው ጉዞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዋን በመቀጠል የዘማቹን ወኔ በመገንባት፣ ስለ አገር ፍቅር በመስበክ የሕዝቡን አንድነት በመሪነት ደረጃ አስተሳስራለች፡፡ ጾም እና ጸሎቱ ቀጥሏል፡፡ በሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ እና በእጨጌው ወልደ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት መንፈሳዊ አገልግሎቱ በመዓልት እና በሌሊት በሰዓታት፣ በማሕሌት፤ በቅዳሴ፣ በነግህ እና በሰርክ ጸሎት ሳይቋረጥ ጉዞው ቀጥ
ሏል፡፡ በጉዞው ወቅት ዘማቹ ሁሉ ሃይማኖታዊ ግዴታውን ይወጣ ነበር፡፡ ለምሳሌ፡- በሰንበት ቀን አይጓዙም፤ ዐበይት በዓላትን ያከብራሉ፤ ለድኃው ይመጸውታሉ፡፡
ልዑል ራስ መኮንን ዓምባ አላጌን ለማስለቀቅ በነበራቸው ጥረት በጦርነቱ ኀይል እና ድል እንዲሰጣቸው ለአምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎታቸውን አቅርበዋል፤ በመጨረሻም በአንገታቸው ላይ ባለው የወርቅ መስቀል አማትበው ጦርነቱን ለመግጠም ወሰኑ፤ ድልም አድርገው ዓምባ ኣላጌን ነጻ አወጡ፡፡ እቴጌ ጣይቱ በመቀሌ የመሸገው ጠላት የውኃ ምንጩ እንዲያዝበት ዘዴውን ከፈጠሩ በኋላ ሌሊቱን ሙሉ “ጌታዬ እኔን ባርያህን አታሳፍረኝ፤ በነገሬ ሁሉ ግባበት፤ ርዳታ ትችላለህና” እያሉ ይጸልዩ ነበር፡፡ ዐፄ ምኒልክ የካቲት 14 ቀን 1888 ዓ.ም ዐድዋ ሲደርሱ ከመላው ትግራይ የተውጣጡ ካህናት እና ሊቃውንት የየደብራቸውን ታቦታት ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በደማቅ ሁኔታ ተቀብለዋቸዋል፡፡
እስከ ጦርነቱ ጅማሬ ድረስ በዐድዋ በነበረው ቆይታ በመላዋ ትግራይ ለአንድ ሱባኤ ምሕላ ተይዟል፡፡ ዐፄ ምኒልክ እና እቴጌ ጣይቱ ከጦርነቱ በፊት ሱባኤ ይዘው የቆዩት በሥነ ጽሑፍ እና ሥነ ሥዕል ቅርሱ በዳበረው በእንዳባ ገሪማ ገዳም ነበር፡፡ ለጦርነቱ ዝግጅት እና መሰናዶ ሲጀመር አስቀድሞ የታወጀው የጸሎት እና ምሕላ ዐዋጅ ነበር፡፡ በመጨረሻም ለመላው ዘማች ለሰባት ቀናት የቁም ፍትሐት ተካሂዷል፡፡ ጀግናው ባሻይ ኣውኣሎም ሓረጎት እና መሰል አርበኞች ለኢጣሊያ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ለዐድዋ ድል አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም እቴጌ ጣይቱ ለባሻይ ኣውኣሎም ምግብ አቅርበው፣ “እንካ ይህን እንጀራ እንደ ሥጋወደሙ ቆጥረህ ብላው፤ ብትከዳ እግዚአብሔር ይፈርድብሃል፤” ብለው ሰጥተውታል፡፡ የካቲት 22 ለ23 አጥቢያ በባሻይ ኣውኣሎም መረጃ ምክንያት ጥላት ከምሽጉ እንዲወጣ ስለተደረገ ሌሊት ሲጓዝ አድሮ ዐድዋ እንደገባ በመረጋገጡ ቅዳሴው ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ላይ እንዲፈጸም ተወሰነ፡፡
ዐፄ ምኒልክ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ እና ፊታውራሪ ገበየሁ ዐድዋ በሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ያስቀድሱ ነበር፤ ቀዳሹም አቡነ ማቴዎስ ነበሩ፡፡ አቡነ ማቴዎስም “ልጆቼ ሆይ፣ ዛሬ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚፈጸምበት ጊዜ ነው፡፡ ሂዱ! ለሃይማኖታችሁ ሙቱ፤ እግዚአብሔር ይፍታህ” ሲሉ መኳንንቱ ሁሉ እየተሽቀዳደሙ የአቡኑን መስቀል ተሳልመው ለጦርነት ወጡ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ወደ ጦርነት የሚገባውን ወታደር ሁሉ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እያሉ ይናዝዙ ነበር፡፡ “ኢጣሊያ በግፍ፣ በትምክህት እና በትዕቢት ተወጥሮ ባሕር ተሻግሮ ቢመጣብህ አንተ በእግዚአብሔር ስም ቁመህ መክተው፤ ታሸንፈዋለህ፤ አለዚያ ይህ ጠላት በመጀመሪያ አገርህን ወሮ ከያዘ በኋላ አንተንም ነጻነትህን ገፎ፣ ሃይማኖትህን አስክዶ ረግጦ በሥቃይ እና በመከራ ይገዛሃል፡፡ ስለዚህ ለሀገርህ፣ ለነጻነትህ እና ለሃይማኖትህ ስትል ጠንክረህ ተዋጋ፤ በርታ ታሸንፈዋለህ፡፡” በጦርነቱ ጊዜም ዐፄ ምኒልክ ነጋሪት እያስጎሰሙ ሠራዊቱን እንዲህ እያሉ ያበረታቱ ነበር፤ “ጦርነት እና የጦርነት ድምፅ ብትሰሙም አትደንግጡ፤ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ሆኖ ጠላቶቻችሁን ስለሚዋጋ አትፍሩ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ እየሄደ ጠላቶቻችሁን ስለሚዋጋላችሁ እናንተንም ስለሚያድናችሁ ከፊታቸው አትሽሹ፡፡” ነጋሪቱ ዛሬ በመንበረ ፀሐይ እንጦጦ ማርያም ይገኛል፡፡ በጎራዴያቸው ላይ የተቀረጸው ጽሑፍም “የምኒልክ ተስፋው እግዚአብሔር ነው” የሚል ነው፡፡
ከምርኮኛ የጣሊያን ወታደሮች አንዱ በዐውደ ውጊያው “በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተመላለሰ ‹ወደ ጦርነቱ ግቡ፤ ኢጣሊያኖችን ማርኩ› እያለ ትእዛዝ ሲሰጥ እና ሲወጋን የዋለ ማነው?” ብሎ ጠይቋል፡፡ በጦር ሜዳ ለበቁት ሰዎች ተገልጦ እየታየ ከአርበኞቻችን ጋራ የዋለው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ዐቃቤ መልአክ(Patron Saint) ነው፡፡ የዐድዋ ድል በዓል ሲታሰብ ይዘምሩበት የነበረውን ግጥም ,፤
“የዐድዋ አርበኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣
ከምኒልክ ጋራ አብሮ ሲቀድስ፣
ምኒልክ በመድፉ ጊዮርጊስ በፈረሱ፣
ጣሊያንን ጨረሱ ደም እያፈሰሱ፤”
“የዐድዋ ድል የኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ/የዘመን አቆጣጠር/ ጭምር የተከበረበት ትልቅ በዓል ነው፤” የዐድዋ ድል ባይገኝ ኖሮ ቋንቋችን ብቻ ሳይሆን ባሕረ ሐሳባችን ጠፍቶ በ”ዓመተ ፋሽስት”/በአውሮፓውያኑ ካሌንደር/ ይተካ ነበር ፡፡
ከድሉ መገኘት አንድ ወር በኋላ ዐፄ ምኒልክ ለመስኮብ ንጉሥ ኒኮላስ መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በጻፉት ደብዳቤ “እንዳውሮፓ ነገሥታት ሥራት ሁሉ ጠብ መፈለጉን ሳያስታውቀኝ እንደ ወንበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግንባር ካደረገው ዘበኛ ጋራ ጦርነት ጀመረ፡፡ ጥንት ከአሕዛብ እና ከአረመኔ አገራችንን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኀይል ድል አደረግሁት” ብለዋል፡፡ የዐድዋ ድል በጸሎት ተጀምሮ በጸሎት የተጠናቀቀ የጸሎት ውጤት ነው፡፡ አባቶቻችን በከፈሉት መሥዋዕትነት ታሪክ እና ቅርስ ብቻ ሳይሆን ሀገርንም አቆይተውልናል፡፡ ይህ ትውልድ እንደ አባቶቹ ታሪክ መሥራት ቢያቅተው እንኳ በመሥዋዕትነት የቆየለትን ታሪክ እና ቅርስ ማወቅ፣ መጠበቅ እና መጠቀም ይኖርበታል፤ ታሪኩን የማያውቅ ከብዙ ሴቶች መካከል እናቱን ለይቶ በማያውቅ ልጅ ይመሰላልና፡፡
በዐድዋ ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል በአጠቃላይ ከ80000 - 100000 የሰው ኀይል እንደተሰለፈ የሚገመት ሲሆን ከእኒህም ውስጥ 12000 ያህሉ በስንቅ እና ትጥቅ አቅርቦት በደጀንነት የተሰለፉ፣ የቆሰሉትን በማግለል መድኃኒትነት ባላቸው ሥራ ሥር፣ ቅጠላቅጠል እና ፍራፍሬ ሕክምና የሰጡ ሴቶች እናቶቻችን ናቸው፡፡ በውጊያው 6000 ኢትዮጵያውያን የሕይወት መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡
አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን!
ከማህበረ ኢትዮጵያውያን ከሚል ደ facebook ገፅ የተወሰደ፡፡
"+" ዘወረደ "+"

“ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው”ዮሐ፫፥፲፫
ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዐዋጅ ከምትቀበላቸው አጽዋማት መካከል አንዱ ነው፡፡ ዐቢይ ጾም ወይም ጾመ እግዚዕ (የጌታ ጾም) ይባላል፡፡ ይኸውም አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንጦስ በፈቃዱ ፵ መዓልትና ሌሊት የጾመው በመሆኑ ዐቢይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡ የዚህ ጾም ሳምንታት የየራሳቸው ስያሜ ተሰጥቷቸው ይከበራሉ፡፡
ከነዚህም የመጀመርያው ሳምንት ከላይ በርዕሳችን እንደጠቀስነው ዘወረደ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የድኅነት ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተጸነሠ ተወለደ፣ ተጠመቀ፣ ጾመ፣ አስተማረ ወዘተ…. ከመባሉ በፊት ወረደ ይቀድማልና ነው፡፡ ኃይለ ቃሉም የተወሰደው ዮሐ፫፥፲፫ “ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” በማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአስተማረው ትምህርት ነው፡፡
የቃሉ ትርጉም
ከሰማይ ከወረደው በቀር ሲል ጌትነቱን፤ የባሕርይ አምላክነቱን፤ ልዕልናውን ሲገልጽልን ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ለተልዕኮ ከመኖሪያቸው ከሰማይ ወርደዋል ወደ ሰማይም ወጥተዋል፡፡ የእርሱን ግን ብቸኛ ልዩ መሆኑ ለማስረዳት “… ከወረደው በቀር” በማለት ገለጸው፡፡ ይኸውም በነቢይ ”አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ” ሚኪ፭፥፫ ተብሎ የተነገረለት ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ የተወለደ ድኅረ ዓለም ለድኅነት ከሰማይ የወረደ ከእመቤታችን የተወለደ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው የአብ አንድያ ልጅ መሆኑን ሲናገር ነው፡፡
ከወረደውም በቀር ወደ ሰማይ(ወደ አብ ቀኝ) የወጣ የለም ሲል አብን በመልክ የሚመስለው፤ በባሕርይ የሚተካከለው የጌትነት ሥልጣን ከአባቱ እኩል ከሆነው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ወይም በአብ ቀኝ(ዕሪና) የተቀመጠ የለም በማለት አምላክነቱን አስረድቷል፡፡ ሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደ ቃል) ክርስቶስ በምድር እያስተማረ ሳለ በሕልውና ከእግዚአብሔር አብ እንዳልተለየ ሲያስተምራቸው “….እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው” አለ፡፡
የወረደው እርሱ ማነው?
እግዚአብሔርን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ፣ በሥልጣን፣ በመለኮት፣ በአገዛዝ የሚተካከለው ነው፡፡ ዮሐ፲፥፴ ፲፬፥፲-፲፩ ፲፯፥፲ ፲፮፥፲፭
 የእግዚአብሔር አብ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ነው መዝ፻፱፥፩ ዘካ ፪፥፰-፱
የእግዚአብሔር አብ እና የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የፈቃዳቸው መገለጫ፣ የሐሳባቸው መታወቂያ አንደበታቸው ነው፡፡ ይኸውም የእግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ ከእግዚአብሔር የተለየ አይደለም ፡፡ በእግዚአብሔር ሕልው ሆኖ የሚኖር ነው እንጂ፡፡ እንዲሁ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃልም ከእግዚአብሔር የተለየ አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ያለ እግዚአብሔር ነው እንጂ፡፡ ዮሐ፩፥፩-፲፬ ፩ኛ ዮሐ፭፥፯
በፍጥረታትና በሕይወትና በሞት ሁሉ ላይ መለኰታዊ ሥልጣን ያለው፤ የሚሰገድለትና ጸሎትን የሚቀበል፤ በሁሉ ቦታ የሚገኝ፤ በዘመን የማይወሰን፤ ቀዳማዊና ደኃራዊ፤ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር፤ አዳኝና ነጻ አውጪ፤ መጋቤ ዓለማት፤ አኃዜ ዓለማት፤ የሚሳነው የሌለ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡
እንዴት ወረደ?
በሕልውና ከባሕርይ አባቱ ከአብና ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ እግዚአብሔር ወልድ በማኀፀነ ድንግል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ተወለደ ፡፡ ኢሳይያስ በትንቢቱ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ያየዋል”(ኢሳ፵፥፩‐፭)እንዳለ በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት ተወስኖ ለፍጥረቱ ተገለጸ፡፡ በዚያ ዘመን የነበሩትን ይልቁንም አምነው የተከተሉትን ከዘመኑ ደርሰው እርሱን በማየታቸው እድለኞች እንደሆኑ እንዲህ በማለት ቅዱስ ማቴዎስ ተናግሯል “የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ፣ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብጹአን ናቸሁ፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም፡፡” ማቴ፲፫፥፲፮‐፲፯
ለምን ወረደ?
እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማየት የወረደው የድኅነት ሥራ ለመፈጸም ነው፡፡ ሕግ በማፍረስ ከገነት የወጣውን ከጸጋ እግዚአብሔር የተለየውን ሰው ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ለመባል ሊወለድ ወረደ ገላ ፬፥፩-፯
የእዳ ደብዳቤያችንን ሊቀድልን፣ የጥል ግድግዳችን ሊያፈርስ ወልደ እግዚአብሔር ወረደ ተወለደ ቆላ፪፥፲፫፣፩፣፳
ታላቁ የቤተክርሰትያናችን መምህር ቅዱስ አትናቴዎስ የአምላክን ወደዚህ ዓለም መውረድና መምጣት እንዲ ሲል በማስተዋልና በአድናቆት ገልጾታል ፡፡ “እርሱ አምላካችን የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ በመካከላችን በመግኘቱ ጥሩ የትሕትና መምህር ሆነን፡፡እርሱ በባሕርይው አምላክ ሆኖ ሳለ እርሱ ራሱ ወደ እኛ መጣ፡፡
እንደእኛም እየበላ እየጠጣ የመጣበትን ዓላማ አስተማረን (ነገረን) ዳሩ ግን በእርሱ ፈንታ እኛ ወደ እርሱ እንድንሔድና ይቅርታ እንጠይቅ ዘንድ ብንገደድ ኖሮ ከኛ የተፈጥሮ ድክመት የተነሳ እንዴት እንችል ነበር ?
ስለዚህ ጌታችንም ኃጢአተኛ፣ ጉስቋላ፣ ደካማ ወደ ሆንነው ወደ እኛ መጣ፡፡ ሥጋችንንም ተዋሕዶ በመካከላችንም ተገኝቶ በሚረዳን፣በሚገባን ቋንቋ ፍቅሩንም አሳየን፡፡ እርሱነቱንም እንድናደንቀው ባሕርይውንም እንድንረዳ አደረገን፡፡ ክብርንም ተጎናጸፈን ወደ መንግሥቱ እንድንገባ ገለጸልን፡፡ ››
ምሳሌ እና ትንቢት
እግዚአብሔር ወልድ ከሰማየ ሰማያትወርዶ ከድንግል ማርያም ከመወለዱ በፊት ትንቢት አናግሯል፡፡ ብዙ ምሳሌዎችን መስሏል፡፡ ከእነዚህም መካከል እስራኤል ዘሥጋ በግብፅ ለ ፬፻፴ ዓመታት በባርነት ተይዘው ሳለ የደረሰባቸውን ጽኑ መከራ ተመልክቶ ሊያድናቸው በወደደ ጊዜ ለነቢዩ ሙሴ በአምሳለ ነበልባል በሐመልማል ላይ ወርዶ አናግሮታል፡፡ እንዲህ ሲል ”እግዚአብሔርም አለ በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ አየሁ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሳ ጩኸታቸውንም ሰማሁ፣ ስቃያቸውንም አውቄአለሁ ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ ወረድኩ፡፡” ዘፀ፫፥፯-፲፪ ይህ ምሳሌነቱ የአዳምን ዘር ከሲኦል እሥራት ከአጋንንት አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት ለማሥገባት በሐመልማል ከመሰላት ከድንግል ማርያም ለመወለድ መውረዱን ያሳየናል፡፡
አባታችን ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሲሔድ በመንገድ ፀሐይ ጠልቃ ነበርና በፍኖተ ሎዛ አደረ፤ በዚያም ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ ሳለ ሕልም አለመ፡፡ እነሆ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ የሰማይ መላእክትም ሲወጡባት ሲወረዱባት አየ፡፡ በጫፏም እግዚአብሔር ተቀምጦባት ነበር፡፡ ዘፍ፳፰፥፲፪ ይህ ለሐዲስ ኪዳን ምሳሌ ነበር፡፡ የወርቅ መሰላሏ ለአግዚአብሔር ቃል (ለወልድ መውረድ፤ ለሥጋ ዕርገት ምክንያት ለሆነችው ለድንግል ማርያም ምሣሌ ነበረች፡፡ በወርቅ መሰላሉ ላይ መላእክት ከእግዚአብሔር ወደ ያዕቆብ መውረዳቸው አምላክ ወረደ ተወለደ፤ ከያዕቆብ ወገን ሥጋን ተዋሐደ(አምላክ ሰው ሆነ)ማለታቸው ነው፡፡ እንዲሁም ከያዕቆብ ወደ ሰማይ መውጣታቸው በተዋሕዶ ሰው አምላክ ሆነ ለሚለው ምሳሌ ነው፡፡
እስራኤል በበረሃ ሳሉ ይመሩበት ዘንድ (ለእግዚአብሔር ይገዙ ዘንድ) ለሙሴ ሕግን ለመስጠት በሲና ተራራ ላይ የወረደውን አምላክ ቅዱስ ኤፍሬም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ላይ እንዲህ ሲል አመስግኗል፡፡ “ወደ ደብረ ሲና የወረደ፤ ለሙሴ ሕግን የሰጠ፤ የተራራውን ራስ በጭጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ፤ ፈርተው የቆሙትንም በነጋሪቶች ድምጽ የገሰጸ የአብ አካላዊ ቃል ነው፡፡ ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡” ይህም ጊዜው ሲደርስ የአዲስ ኪዳን ሕግ ሊሰራልን በተራራ ከተመሰለች ድንግ
ል ማርያም ለመወለድ ምሳሌ ነበር፡፡
ነቢያትም በትንቢት እንዲህ ይሉ ነበር “ሰማዮችን ቀደህ ምነው ብትወርድ፡፡ ተራሮችም ምነው ቢናወጡ፤ እሳት ጭራሮን እንደሚያቃጥል እሳትም ውኃን እንደሚያፈላ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ አህዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ” በማለት ኢሳ፷፬፥፩-፪
እንግዲህ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረ “…. እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቆጠረውም፡፡ ነገር ግን የባርያውን መልክ ይዞ በሰው ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደረገ፡፡” ፊሊ፪፥፯ ስለ እኛ መወለዱ፣ መሰደዱ፣ መከራን መቀበሉ፣ ሲዖል ድረስ በአካለ ነፍስ መውረዱ ከኃጢአት ርቀን በጽድቅ ጎዳና እንድንጓዝ ነውና ከትዕቢት፣ ከመለያየት፣ ከክርክር፣ ከዝሙት…. በአጠቃላይ ከክፉ የሥጋ ፈቃድ ተለይተን በትሕትና፣ በንስሐና በፈሪሃ እግዚአብሔር ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡
ይቆየን
ዘጋጅ፡-በአዲስ አበባ ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
የምክሐ ደናግል ማርያም ወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር (ሰንበት ት/ቤት) ትምህርት ክፍል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር !
"እየፆማችሁ ነውን?"
(በቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)
እንግዲያስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ፡፡
"እንዴት አድርገን እናሳይህ?"
ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስላችኋለሁ፡-
ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርጉለት፤
የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ከእርሱ ጋር ፈጥናችሁ ታረቁ ፤
ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ፤
ቆነጃጅትን በመንገድ ሲያልፉ ስታዩ በዝሙት ዓይን አትመኙ፡፡
እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል
መጾማችሁን አሳዩኝ፡፡
*
በሌላ አገላለጽ አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችሁ፣ እግራችሁ፣ እጃችሁ፣ በአጠቃላይ የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡
+ እጆቻችሁ ከመስረቅና የእናንተ ያልሆነውን ከመውሰድ ይጹሙ፤
+ እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም ከመፋጠን ይጹሙ፤
+ ዐይኖቻችሁ ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጹሙ፡፡
*

ጥሉላትን ፥ (የፍስክ ምግብ) እየበላችሁ አይደለም አይደል?
☞ እንግዲያስ በዐይኖቻችሁም ክፉ ነገርን አትብሉ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና፡፡
***
☞ ጀሮዎቻችሁም ይጹሙ፡፡ የጀሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማትና ይህን የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡
☞ ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናኝካቸውና የምንበላቸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው?
ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል ፤ ሥጋውንም ይበላል፡፡
ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" /ገላ.5፡15/።
ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም፡፡ በክፉ ንግግራችሁ ግን የወንድማችሁን ነፍስ ትነክሳላችሁ ፤ ታቆስሉትማላችሁ፡፡ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን ፣ ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡
☞ አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጦመ ጉዳቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡
በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁም የሐሜታችሁ ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ ማለት ነው፡፡ እርሱም የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ በዚህም የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጦሙ
ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል ስለዚህ አንደበታችሁም ክፉ ከመናገር ይጹም፡፡
የበረከት ጾም ያድርግልን። ይቆየን።
"ስብሐት ለእግዚአብሄር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ - እንድናመልከው እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሄር ክብር ምስጋና ይሁን"፡፡
+++--+++--+++--+++--+++--+++-+++-+++
@rituaH @rituaH @rituaH
"+" ምኩራብ "+"

"+" የአብይ ፆም ሦስተኛ ሳምንት "+"
++++++++++++++++++++++++++++++

በዚህ በሦስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦
"እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ"
በአማርኛ፦
"የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።" መዝ.፷፰፡፱

በዚህ የሦስተኛ የአብይ ጾም ሳምንት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ እየገባ የወንጌልን ትምህርት እንዳስተማረ፤ ብዙ ድውያንን እንደፈወሰ፤ የሰንበት ጌታ እንደሆነ፤ የአባቴ ቤት የጸሎት ቤት እንጂ የንግድ ቦታአይደለም በማለት በቤተ መቅደሱ አካባቢ የሚነግዱ ነጋዴዎችን ስለ መገሰጹ ትምህርትይሰጥበታል። በተለይም በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈ ጌታ በአይሁድ ምኩራብ ገብቶመጽሐፍ እንዲሰጡት ጠይቆ የሚሰሙት ቃል ዛሬ በጆሯቸው እንደተፈጸመ እንዲህ ሲል እንደነገራቸው ይዘከርበታል፦

" ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው
አገር ሁሉ ዝና ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር።
ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤
ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም። ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ። ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር። እርሱም። ያለ
ጥርጥር ይህን ምሳሌ። ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም
እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ
አላቸው። ሉቃ.፬፡፲፬-፳፫

ጌታችን በምድር ሲመላለስ ከዚህ ቀደም በምኩራቦቻቸው ተሰምቶ የማይታወቅ የወንጌል ትምህርት እንዳስተማራቸውና ዕውራን እንዲያዩ፤ ደንቆሮዎች
እንዲሰሙ፤ ዲዳዎች እንዲናገሩ በማድረግ እንዲሁም ደግሞ ሙታንን በማሥነሳትየተለያዩ ድንቅ ተኣምራቶችን በማድረግ የወንጌልን ኃይል ስለማሳየቱ ይተረክበታል።የቤትህ ቅናት በላኝ ተብሎ እንደተጻፈ ሕገ እግዚአብሔር እንዲፈጸም፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዳይፈርስ፤ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳይበላሽ በአይሁድ ምኩራብ በመግባትእንዳስተማረ ሁሉ ዛሬም እያንዳንዳችን የቤተ ክርስቲያንን ነገር ለቤተ ክርስቲያን በማድረግበቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ነገርን ብቻ በመሥራት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን በመከተል ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንደሚገባን ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል። ቤተክርስቲያን የጌታ ሥጋ እና ደም የሚፈተትባት፤ ሰዎች ዘላለማዊ ሕይወትን የሚያገኙባትመሆኗም ይነገርባታል። ጌታችን በቅፍርናሆም ምኩራብ የሕይወት እንጀራ እርሱ እንደመሆኑ ያስተማረበት አብይ ክፍል በዚህ በሦስተኛው ሳምንት የአብይ ጾም በሰፊውይነገራል። አይሁድ የእውነትን ቃል ሰምተው አንገታቸውን እንዳደነደኑ፤ ሥጋዬን የበላደሜን የጠጣ የዘላላም ሕይወት አለው በሚለው የጌታ ትምህርት እንዴት ሊሆን ይችላልበማለት ማጉረምረማቸው በዚሁ ክፍል አብሮ ተጠቃሽ ነው። ጌታም እስራኤል በምድረበዳ በልተውት የነበሩት መና እና እውነተኛው የሕይወት እንጀራ ያላቸውን ልዩነትበማነፃፀር እንዲህ ሲል
አስተምሯቸዋል፦

" አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል። እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤ ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት
የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። እንግዲህ አይሁድ። ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል? ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ። ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል። ከሰማይ
የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደ ሞቱ አይደለም፤ ይህን
እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል በቅፍርናሆም ሲያስተምር ይህን በምኵራብ አለ። ዮሐ.፮፡፵፮-፶፱

በዚህ በሦስተኛው ሳምንት በቅዳሴ ላይ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉውምንባብ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
* እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው። ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም
ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ።
እንደዚህ ያለ ሰው ራስ ወደሚሆነው አይጠጋም፥ ከእርሱም አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ ምግብን እየተቀበለ እየተጋጠመም፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ያድጋል። ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ እንደ
ሰው ሥርዓትና ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና። ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥
ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም።
ቆላ.፪፡፲፮-፳፫

* ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን
ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል። እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል። አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን? አባታችን
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ
ትመለከታለህን? መጽሐፍም። አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን
በሥራ እንዲጸድቅ
ታያላችሁ። እንደዚሁም ጋለሞታይቱ ረዓብ ደግሞ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቀችምን?
ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው። ያዕ.፪፡፲፬-፳፮

* በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ።
ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል። ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ። ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው። ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ። አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው
በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል። የተናገረውም መልአክ በሄደ ጊዜ፥ ከሎሎዎቹ ሁለቱን፥ ከማይለዩትም ጭፍሮቹ እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንዱን ወታደር ጠርቶ፥ ነገሩን ሁሉ ተረከላቸው ወደ ኢዮጴም ላካቸው። እነርሱም በነገው ሲሄዱ ወደ ከተማም ሲቀርቡ፥ ጴጥሮስ በስድስት ሰዓት ያህል ይጸልይ ዘንድ ወደ ጣራው ወጣ። ሐዋ.፲፡፩-፱

በዚህ በሦስተኛው ሳምንት ከመዝሙረ ዳዊት ላይ የሚሰበከው ምስባክ፦
በግዕዝ፦ "እስመ ቅንዓተ ቤተከ በልዓኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትኤየሩከ ወድቀ ላዕሌየ ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ"
በአማርኛ፦ "የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።" መዝ.፷፰፡፱
በዚህ በሦስተኛው ሳምንት የሚነበበው የወንጌል ክፍል፦
"ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ። የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም
ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም
ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥ ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። ስለዚህ አይሁድ
መልሰው። ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉት። ኢየሱስም መልሶ።ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው። ስለዚህ አይሁድ። ይህቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀንታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። ስለዚህ ከሙታንከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውንቃል አመኑ። በፋሲካ በዓልም በኢየሩሳሌም ሳለ፥ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ ብዙ ሰዎችበስሙ አመኑ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሰውም ማንም ሊመሰክርአያስፈልገውም ነበርና አይተማመናቸውም ነበር፤ ራሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።ዮሐ.፪፡፲፪-፳፭

"ወስብሐት ለእግዚአብሔር "
የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት
*********************************
የዐቢይ ጾም አምስተኛ እሑድ ደብረ ዘይት ተብሎ ይጠራል፡፡ የጌታችን ዳግም መምጣትና የዘመኑ ምልክት የሚነገርበት ቀን በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት
ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ መምጣቱ ምልክት የተናገረው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ
በመሆኑ ዕለቱ ደብረ ዘይት ተባለ (ማቴ. 24÷ 3)፡፡
ቅዱስ ያሬድ ዕለቱን ደብረ ዘይት ብሎ መሰየሙ ብቻ ሳይሆን በዕለቱም ያቀረበው ዝማሬ እንዲህ የሚል
ነው፡-
“ወአመ ምጽአቱሰ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይትከወሰ ኲሉ
ኃይለ ሰማያት ወምድር አሜሃ ይበክዩ ኲሎሙ ኃጥአን ምድር ወይወርድ እግዚእነ እምሰማይ ዲበ ምድር በትእዛዙ ወበቃሉ ወበአእላፍ መላእክቲሁ በንፍሐተ ቀርን ዘእም ኀበ እግዚአብሔር ይምሐረነ አብ በይእቲ ሰዓት እሞተ ኃጢአት
እስመ ገባሬ ሕይወት”
ትርጉም፡-
“የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ የሰማይና የምድር ሠራዊት ሁሉ ይነቃነቃል። ያን ጊዜ በምድር የሚኖሩ ኃጢአተኞች ሁሉ ያለቅሳሉ፡፡ ጌታችንም ከአእላፍ
መላእክት ጋር በትእዛዙና በቃሉ መሠረት ከሰማይ ወደ ምድር ይወርዳል፡፡ የእግዚአብሔር መለከትም
ይሰማል፡፡ በዚያች ሰዓት እርሱ ያድነን። እርሱ የሕይወት ባለቤት ነውና።”
ቅዱስ ያሬድ የዘመረው የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24ን ነው፡፡ ጌታችን ሲመጣ ፍጥረት እንደማይፀና ኃጢአተኞች ደስታ እንደማይሰማቸው
ይገልጣል፡፡ በኃይሉ ፊት ፍጥረት፣ በፍርዱ ፊት ኃጥአን መቆም አይችሉምና፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣል። በብሉይ ኪዳን እመጣለሁ ብሎ መጥቷል፡፡ በአዲስ ኪዳንም እመጣለሁ ብሎ ቤተ ክርስቲያንን በተስፋ አስገዝቷታል፡፡
ፍጥረት ሁሉ የሚጠብቀው አንድ ታላቅ እንግዳ ከፊታችን ባለው ባልራቀው ዘመን ይመጣል፡፡ የሚመጣው በትሕትና ሳይሆን በልዕልና ነው፡፡
በከብቶች በረት ሊጣል ሳይሆን በደመና በዙፋን ተገልጦ ይመጣል፡፡ ስምዖን አረጋዊ እንደ ታቀፈው ሆኖ አይመጣም፣ ሰማይና ምድር የማይችሉት ሆኖ
ይመጣል፡፡ ከእናቱ ጡትን እየለመነ አይመጣም፣ ለፍጥረት ሁሉ የሩጫውን ዋጋ ለመስጠት ይመጣል፡፡
ከሄሮድስ ፊት የሚሸሽ ሆኖ አይመጣም፡፡ ሰማይና ምድር ሲያዩት ከፊቱ ይሰደዳሉ፡፡ ለእኛ ለክርስቲያኖች መጣልን የምንለው እንግዳችን፣ ፈራጃችን እንጂ
መጣብኝ የምንለው አይደለም፡፡
የጌታችን ዳግም ምጽአት፡-
1. የጸሎታችን መልስ ነው።
2. የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው።
3. የዘመናት ናፍቆት መልስ ነው።
4. የተስፋችን ፍጻሜ ነው።
5. የእምነታችን ክብር ነው።
6. የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው።
7. የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው፡፡
የጸሎታችን መልስ ነው::
ብዙ ሰዎች ክርስቶስ ዳግም ይመጣል ሲባሉ ይፈራሉ፡፡ ፍርሃታቸው ግን ለንስሐ አያዘጋጃቸውም። ልበ ሙሉ ሆነው ኃጢአት እንዳይሠሩ የመምጣቱ ዜና
ስለሚረብሻቸው ነው፡፡ የጌታችን ዳግም ምጽአት በሚታሰብበት ቀን እንኳ ብዙ የኃጢአት መታሰቢያ ሲደረግ ይውላል፡፡ ለብዙ ሰዎች እኩለ ጾም ከሥጋና
ከስካር ከተላቀቁ አንድ ወር መሆኑን ለመገናኘትም ወር እንደሚቀራቸው የሚያስቡበት ቀን ነው፡፡ በጊዜያዊ
ጨዋነት የሰነበቱትም ሲሰክሩ የሚውሉበት የተውኔት ቀናቸው ነው፡፡ ሃይማኖት የማይሞት ኃይል ነው፡፡ ከሰው
ልብ ግን ሊሞት የሚችለው ሰዎች እንደ ባሕል ቆጥረውት ሲኖሩ ነው፡፡
የጌታችን መምጣት ግን የጸሎታችን መልስ ነው፡፡ የምንፈራውና ያርቅልኝ የምንለው ሳይሆን በየዕለቱ “መንግሥት ትምጣ” እያልን የምንጸልይበት
ትልቅ ርዕሳችን ነው፡፡ የዚህ ዓለም መንግሥት በግፍ ተጀምሮ በግፍ የሚጠናቀቅ፣ በውሸትና በሐሰተኛ ተስፋ
ሰውን የሚያደክም፣ በጭካኔ ሲወዳደር የሚኖር፣ ደም በደም የሆነ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ክፉ ሥርዓት የተጨነቁ ሁሉ ጽድቅና ሰላም የነገሠባትን የክርስቶስን
መንግሥት ይናፍቃሉ (ሮሜ. 14÷17)፡፡ የክርስቶስ መንግሥቱ የምትገለጠው ጌታችን ምድራውያን ነገሥታትን አሳልፎ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ በሚነግሥበት
በዳግም ምጽአቱ ነው፡፡ ዳግም ምጽአቱ ምድራዊውን ሥርዓት አሳልፎ አንድ መንግሥትን በሁሉ የሚያፀና
ነው፡፡ የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው
ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ የፍጥረት ናፍቆት
የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና” ይላል (ሮሜ. 8÷19)፡፡ ዳግመኛም “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን
ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን
እናውቃለንና” ይላል (ቁ.22)፡፡ በሰው ኃጢአት የተጨነቀው ሰው ብቻ ሳይሆን ፍጥረት በሙሉ ነው፡፡ እንስሳቱ አራዊቱ ሁሉ የሰውን ኃጢአት ቅጣት
እየተካፈሉ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ የሚያርፉት ክርስቶስ ልጆቹን በክብር በሚገልጥበት በምጽአቱ ቀን ነው፡፡
ስለዚህ ፍጥረት ሳይወድ በግድ የሰውን ማረፍ ይናፍቃል፡፡ የራሱም ዕረፍት ነውና፡፡ ዛሬ በብዙ ነገር እናለቅሳለን፡፡ ብዙ ጭንቀቶችም ከበውን እንኖራለን፡፡
የክርስቶስ መምጣት ግን የፍጥረት ምጥ ዕረፍት ነው፡፡ የዘመናት ናፍቆት እርካታ ነው::
ማራናታ ማለት ጌታ ይመጣል ወይም ጌታ መጣ ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 609)፡፡ ይህ ቃል ዮሐንስ ራእዩን ሲዘጋ ተጠቅሞታል፡- “ አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና” (ራእ. 22÷20) ። ዮሐንስ በራእዩ ስለሚመጣው የዘመናት
ጣር ካየ በኋላ የዚህ ሁሉ ማብቂያው ምንድነው? ብሎ ሲያስብ የጌታ መምጣት ነው፡፡ ስለዚህ ማራናታ አለ፡፡
የጌታችን መምጣት የመከራው ድንበር ነው፡፡ በመጀመሪያ ምጽአቱ ሞት ተገደበ፣ በዳግመኛ ምጽአቱ መከራ ገደብ ያገኛል፡፡
የተስፋችን ፍጻሜ ነው:: የምንጠባበቃቸው ብዙ ተስፋዎች ቢኖሩም ትልቁ ተስፋችን ክርስቶስ ነው፡፡ የምንጠብቃቸው ነገሮች ቢሆኑልን እንኳ ሌላ መመኘታችን አይቀርም፡፡
ክርስቶስ ከመጣልን ግን ምንም እስከማያምረን ለዘላለም ያረካናል። ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “የተባረከው
ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር መገለጥ እየጠበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ
እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል” (ቲቶ. 2÷12-13) ይላል፡ ሰዎች ተስፋ
ካላቸው ራሳቸውን ከሚጎዳ ነገር ይከላከላሉ፡፡ እንዲሁም ክርስቶስ ተስፋቸው የሆነ ይቀደሳሉ፡፡
በኃጢአት መጫወት ተስፋ መቁረጥ ነው፡፡ የክርስቶስ ምጽአት የተስፋችን ፍጻሜ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያን
የቀረላት ተስፋ የክርስቶስ መምጣት ነው፡፡ የእምነታችን ክብር ነው ጌታችን ዳግመኛ የሚመጣው በናቀን ዓለም
ፊት እምነታችንን ሊያከብር ነው፡፡ የዘበቱብንናያስጨነቁን ለዘላለም ያፍራሉ፡፡ ዛሬ ቃሉን የረገጡ፣ ያን
ቀን ፍርዱን መርገጥ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች የሆንም በዚያን ቀን በዘላለም ክብር ተውበን በጉን
እረኛችን አድርገን ወደ ፍስሐ ዓለም እንገባለን፡፡
የአዲስ ዓለም ጅማሬ ነው በዮሐንስ ራእይ ላይ እንደ ተጻፈው “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድርን አየሁ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደፊት የለም” ይላል (ራእ. 21÷1)፡፡ አዲስ ነገር የሚያስፈልገው ፊተኛው ሲያረጅ ነው። ያረጀ ነገር መልኩ የወየበ፣ ጉልበቱ ያለቀ፣ ወደፊት ሊጠቅም የማይችል ነው፡፡
አሁን ፍጥረት አርጅቷል፡፡ በረዶ እየቀለጠ፣ የምድር ሙቀት እየጨመረ፣ መሬቱ ማዳበሪያ እየፈለገ፣ ሰውም
በብዙ መድኃኒት እየኖረ ነው። ይህ የማርጀት ምልክት ነው፡፡ ይህን አዲስ የሚያደርገው የክርስቶስ መምጣት
ነው፡፡ ሰውም ሞት ላይዘው በትንሣኤ፣ የሚመጣው ዓለምም ማርጀት ላያገኘው በአዲስነት ይኖራል፡፡
የዘላለም ሕይወት መክፈቻ ነው
ጌታችን ሲመጣ ዘላለማዊት የምትሆን
መንግሥተ ሰማያት ትከፈታለች፡፡ ዛሬ በክርስቶስ ያመኑ በበጎ ሥራ
2024/06/27 02:11:17
Back to Top
HTML Embed Code: