Telegram Web Link
ዛሬ አይቀርም!
ምን ያህሎቻችን ተግባቢና ተጫዋች ሰው መኾን እንሻለን https://youtu.be/givWWp8Q44Y
#ሰዎች_ሁልጊዜም_የሚሉት_ነገር_አያጡም
Telegram www.tg-me.com/psychoet

አባትና ልጅ ወደ አንድ አካባቢ ረጀም ጉዞ ለማድረግ አህያቸውን ጭነው ከቤታቸው ይወጣሉ፡፡ ጉዞውን እንደጀመሩ ልጅ በአህያው ላይ ቁጭ ብሎ አባት ደግሞ የአህያዋን ልጓም ይዘው በእግራቸው ይጓዙ ጀምር፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ ግን የልጅን በአህያ ላይ መቀመጥ የአባትን በእግር መጓዝ የተመለከቱ ሰዎች “አባቱ በእግሩ እየሄደ እንዴት ልጁ በአህያ ይሄዳል? ምን ዓይነት ስነ ምግባር የጎደለው ልጅ ነው?” በማለት ቅሬታቸውን እና ትችታቸውን ሰነዘሩ፡፡ ይህንን እንደ ሰሙ አባት እውነትም ስህተት የሰሩ መስሏቸው ልጃቸውን በእግሩ የአህያዋን ልጓም ይዞ እንዲሄድ አድርገው እሳቸው ደግሞ በአህያ ላይ ወጥተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አሁን ደግሞ ሰዎች አባት ላይ ትችታቸውን ማዥጎድጎድ ጀመሩ;፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ አባት ነው? ልጁን በእግሩ እያዳከረ እሱ በአህያ እንዴት ይሄዳል” አሉ፡፡ በዚህም አባት ይደናገጡና ከአህያዋ ላይ በመውረድ እንግዲያውስ ሁለታችንም በእግራችን እንሂድ ተባብለው በእግራቸው ጉዟቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ወደ ሌላ መንደር ሲቃረቡ አሁንም አህያዋን ያለ ምንም ጭነት ተዝናንቶ መሄድ እና የአባትና ልጅን በእግር መጓዝ የተመለከቱ የመንደሩ ሰዎች ሌላ ትችት መሰንዘር ጀምሩ፡፡ “ድሮም ሃብት ያላቸው ሰዎች ችግራቸው ይኼ ነው! እንዴት ያላቸውን ነገር መጠቀም እንዳለባቸው አያውቁም” አሉ፡፡

አሁንም ሰውን ማስደስት እንዳልቻሉ እና ልክ እንዳልሆኑ የተሰማቸው አባት እና ልጅ የሚቀጥለው መንደር ሰው አፍ ላለመግባት ሁለቱም በአህያዋ ላይ ወጥተው መጓዛቸውን ቀጠሉ፡፡ ቀጣዩ መንደር እንደደረሱ ግን አባት እና ልጅ የገጠማቸው አሁንም ሌላ ትችት ነው፡፡ “ምን ዓይነት ጨካኝ ሰዎች ናቸው? አንደበት የላትም ብለው ነው? የእግዜር ፍጥረት ላይ ይታያችሁ እስኪ እንዴት ሁለት ሆነው ጀርባዋ ላይ ተዝናንተው ተቀምጠው ይሄዳሉ አንዳቸውን ከተሸከመች አንሶ ነው” አሉ፡፡ አባት እና ልጅ ተደናግጠው ሁለቱም ከአህያዋ ጀርባ ላይ አፍታ እንኳን ሳይቆዩ ወረዱ፡፡ በየደረሱበት ትችት የገጠማቸው አባት እና ልጅም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ከተመካከሩ በኋላ ቢያንስ ከዚህ በኋላ የምናገኛቸውን ሰዎች ማስደሰት ይኖርብናል ብለው በማሰብ አህያዋን ተጋግዘው ለሁለት ተሸክመው ጉዟቸውን አሁንም ይቀጥላሉ፡፡ አህያዋን በመሸከማቸው ምክንያት እጅግ ተዳክመው ወደ ሚቀጥለው መንድር ይደርሳሉ፡፡ አህያ የተሸከሙትን የከተማዋን ሰዎች የተመለከቱት ሰዎች ወገባቸውን ይዘው መሳቅ ጀመሩ፡፡ ምን ዓይነት ጅል ሰዎች ናቸው አህያዋ ላይ ተቀምጠው እንደመሄድ እንዴት አህያ ተሸክመው ይጓዛሉ በማለት ተሳለቁባቸው፡፡ አባትና ልጅም ምንም ነገር ቢያደርጉ ከሰው ትችት ማምለጥ እንደማይችሉ እና ሁልጊዜም ቢሆን ሰዎች የሚተቹት ነገር ፈልገው እንደማያጡ ተረድተው ጉዟቸውን እነሱ ባሻቸው መንገድ ቀጠሉ፡፡

እውነትም ሰዎች ምንጊዜም ቢሆን የሚሉት አንድ ነገር አያጡም፡፡ የምታደርጉትን ነገር ቢወዱትም ባይወዱትም፤ ልክ ነው ብለው ቢያስቡም ባያስቡም ፤ ቢመለከታቸውም ባይመለከታቸውም አንድ የሚሉት ነገር አያጡም፡፡ መፍትሄው የገዛ ራስን ህይወት በራስ ፍላጎት መምራት ነው፡፡ የአንተ/የአንቺ ህይወት የተባለበትም ምክንያት ይኼ ነው፤ አንተ/አንቺ በአሻችሁ መንገድ ትመሩት ዘንድ ነው፡፡

ስለዚህ የትኛውም ጥሩ ነው፣ ዋጋ አለው፣ ይበጀኛል ወዘተ ብላችሁ ከልባችሁ እስካመናችሁ ድረስ ሰዎች ምንም ይበሉ ምን ከማድረግ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡

(በኤባ ተስፋዬ)
©zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
Forwarded from Ask Anything Ethiopia
#education

ኸረ ሰዎች ጭንቀት ይዞኛል! ለምን መሰላችሁ ሜሎሪና የሚለዉን መፅሐፍ አንብቤ ነበር ነገር ግን መፅሀፉ ያለቀዉ በጣም ልብ አንጠልጣይ የሆነ ቦታ ላይ ነዉ እና የያሬድ እና የታቤል መጨረሻውን ማወቅ እፈልጋለሁ እባካችሁ ቴሎስ(ሜሎሪና 2 መሰለኝ) የሚለዉን መፅሐፍ ካላችሁ?

By: MAYT 👨
Ask Anything Ethiopia
ምን ያህሎቻችን ለወዳጅ ቤተሰቦቻችን መጽሐፍ በስጦታ መልክ እንሰጣለን?

ለጀማሪና እንዲኹም ለነባር አንባቢ ጓደኞቻችሁ "ሜሎሪና" እና "ቴሎስ"ን በስጦታ እንድትሰጡ እጠይቃለሁ? 🙏 ራሳችንንና ሕይወትን የምንፈልግበትና መጽሐፍ ነው፡፡
@psychoet
ከወደ አርባምንጭ ቴሎስ እየተነበበ ነው

‹‹ልጄ ያሬድ፣ የሰው ልጆችን መከራ ማሸነፊያ መሣሪያ ስለኾነው ነገር ልንገርህ፡፡ ችግሮችን ሁሉ የምናሸንፍበትና ከገባንበት አረንቋ የምንወጣበት አንድ ትልቅ መሰላል አለ፤ እሱም መልካም ተስፋ ነው፡፡ ተስፋ፣ ከምንኖርበት ቦታና ካለንበት አካባቢ አልፈንና ተሻግረን አርቀን እንድናስብ የሚረዳን ነው። ተስፋ አሳብ ነው፤ ተስፋ ምኞት ነው። ዛሬያችንን፣ ከተወረሰበት ጨለማ አራግፈን የምናወጣበት ነው፡፡ ይቺ ዓለምም ብትኾን ለተስፈኞች የተለየ ቦታ ያላት ትመስላለች፡፡ ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይታይ፣ ሳይሰማ፣ ሳይዳሰስና ሳይጨበጥ በፊት በአሳብ ደረጃ እያለ የማይታየውን እንዲታይ፣ ያልተጨበጠውን እንዲጨበጥ የሚያደርጉት ትላልቅ ተስፈኞች
ናቸው፡፡ ተስፋ በርግጥ የወደቀውን ያነሣል፤ የተሰበረውን ይጠግናል፡፡

‹‹ስለዚህ ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ መልካም ተስፋ አድርግ፡፡ ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው፤ ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው፡፡ ሕይወትህ መከራ፣ ችግር፣ ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ፣ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን፡፡ በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው፡፡ በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ሥራ በደስታም ኑር፡፡››

የናንተንም ፎቶ ከወደዳችሁት ከመጽሐፉ የወጣ አባባል ጋር ላኩልን
📸 Kibre-ab Elias ĸébå
ቴሎስን እያነበባችሁ አስተያየት እየላካችሁልን ስለኾነ አብዝተን አናመሠግናለን፡፡
ለሌሎችም ወዳጆቻችኹ እንዲያነቡና የሕይወት ዘመን እውቀት እንዲቀስሙ ጋብዙ፡፡
@psychoet
"... የህይወትን አላማ የተረዳ ሰው የሚኖረው ለመብልና ለመጠጥ ሳይሆን ለህሊናው ነው።

ብዙ ሰው #ህሊናውን_ሸጦ #ለሆዱ_ያድራል

በዚህ አለም የሚኖርበትን አላማ የተረዳ ሰው ህሊናውን ከሆድ ፣ ከስልጣን ፣ ከዝና ጋር አያወዳጅም ።
ህሊናው የሚገዛው ስለተፈጠረለት አላማ ፣
#ለእውነትና_ለፍትህ ብቻ ነው ። ..."

ሜሎሪና - ቴሎስ

መልካም ቀን 💚
በእራስ መተማመን

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡

ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-

1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡

2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡

3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡

4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡

5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡

6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡

7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡

በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ……….
መልካም ቀን !
© (ቁምላቸው ደርሶ)
@psychoet
፩. ትናንትን የምታርመውም ኾነ የምታድሰው ዛሬ ላይ ኾነህ ነው፡፡
፪. ነገ ውብ የምትኾነው ዛሬን ስትንከባከባት ነው፡፡
፫. ነገ ከተስፋነቷ በስተቀር ያንተ አይደለችም፡፡

ተስፋህ እውን ኾኖ የምታገኛት ግን ዛሬን በተጠቀምክባት ልክ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ትዝታህ ላይ ተቀምጠህ በተስፋ ጋሪ ተሳፍረህ ዛሬን በደንብ ኑር።

ሜሎሪና❤️
ጥቆማ ለቻናላችን ቤተሰቦች
#ለሰርግ #ለክርስትና #ለልደት #ለመስክ #ለሁሉም ዓይነት ፕሮግራሞች የሚሆኑ😲
💛ፕሮግራምዎን የሚያደምቁ ውብ የዲዛይነር አልባሳትን ሀሞና ዲዛይን ይዞላችሁ ቀርቧል።
ይደውሉ 👉0985183077 ወይም 0944321791/0912405242
👇
አድራሻችን:- ቦሌ ከኤድናሞል ወደ አትላስ መንገድ ቴሌው ፊት ለፊት አለምደሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

አዳዲስ ዲዛይኖች ቶሎ እንዲደርስዎ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/HamonaDesign_12
ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ አሥር የሕይወት መርሆች አውቅ ከሆኑ የሳይኮሎጂ መፅሀፍቶች የተወሰደ እና ከሳይኮሎጂ ባለሞያዎች/አማካሪዎች የተገኘ መረጃ!

#ሼር ማድረግ ደስ ይላል፡፡ የዛሬ ደስታዎን #ሼር በማድረግ ይጀምሩ፡፡

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

11. የአዲስ መረጃ ቤተሰቦች፣ ሼር ማድረግ ምን ያህል ደስ እንደሚያሰኝ ስለሚያውቁ ቀናቸውን የሚጀምሩት የኛን መረጃ ሼር በማድረግ ነው፡፡

ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

----------------------

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)

🎡@🎡መልካም ቀን
#Join #Join #Join
🔸🔹 ↘️💯💯💯↙️🔸🔹
🚗 @Psychoet👍
🚕 @Psychoet👍
🚙 @Psychoet👍
‹‹በደስታችን ውስጥ ያለው ፈጣሪ በሐዘናችን ውስጥም አለ፤ በድላችን ውስጥ ያለ ፈጣሪ በሽንፈታችን ውስጥም አለ፡፡ እሱ ከሰበረህ እሱ ይጠግንሃል፡፡ በማንኛውም የጥያቄ ጕዞህ የሚያዋጣህ ከእሱ መሸሽና መኰብለል ሳይኾን፣ ከነችግርህና ከነሐዘንህ ከእሱ መጣበቅ ነው››

ሜሎሪና ገጽ 156
‘‘ውድቀት የስኬት ተቃራኒ ሳይኾን
የስኬት አካል ነው፡፡’’
@psychoet
2024/09/30 14:35:45
Back to Top
HTML Embed Code: