Telegram Web Link
📌🗓📕 የሕይወት ክህሎተት ስልጠናችን ነገ ቅዳሜ እነ እሁድ ይጀምራል

ሙሉ መረጃውን ከላይ ይገኛል

ያሉን ፈረቃዎች
📆📆➊ ቅዳሜ 3-5
➋ እሑድ 3-5
➌ እሑድ 8-10


በመደወል ወይም በአካል መጥታችሁ የተመዘገባችሁ ሰዎች በሰአቱ እንድትገኙ እናሳስባ ባሉን ቀሪ ቦታዎች ለመመዝገብ -
0912664084 በመደወል ወይም
በአካል በመምጣት መመዝገብ ይቻላል፡፡
🏢የስልጠና አድራሻ : 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሃን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 219 (Nova Training Center)

✿አላማችን የሰው ህይወት መለወጥ ነው፡፡ 📖
ለሰልጣኞቻችን በሕይወት ለውጥ ዙሪያ(በስራ፣ በትምህርት፣ በንግድ፣ በቤተሰብ፣ በግንኙነት) በግል የማማከሪያ ጊዜ እናመቻቻለን
@psychoet
# የአለም__እውነታወች
1. የሚከተልህ ሁሉ አድናቂህ አይደለም

2. ውሻ ጭራውን የሚቆላው ላንተ ሳይሆን
በእጅህ ላለው ዳቦ ነው፣ አስመሳይና
ተለማማጭ ሰውም እንዲሁ ነው።

3. ሕይወት ድልድይ ናት፣ አቋርጣት እንጂ
በላይዋ ላይ ቤት አትስራ።

4. ውሀ ቅርፁን ከመያዣው ጋር እንደሚስማማ
ሁሉ ብልህም ራሱን ከሁኔታው ጋር ይስማማል።

5. ምንም ያህል ርቀት በተሳሳተ መንገድ
ብትጓዝም ወደኋላ ተመለስ።

6. ዝቅ ብለህ ብትመለከት ምን ያክል ከፍ
እንዳልክ ታውቀዋለህ።

6. አንድ ሰው ስትተዋወቀው በልብሱ
ልትመዝነው ትችላለህ፣ ስትለየው ግን
በአስተሳሰቡ ትመዝነዋለህ።

7. ሠርግ እና ቀብር አንድ ናቸው። ልዩነቱ
የሠርግ አበባን ባለቤቱ ማሽተት መቻሉ ብቻ
ነው።

8. አምላክህን ደስታህን በቅንነት ብትጠይቀው
ይሰጠሀል። ብቻ በቤትህ በሀቀኝነት ኑር።

9. ማንክያ የሾርባን ጣዕም እንደማያውቅ ሁሉ
ለስሙ የተማረም የጥበብን ጣዕም አያውቅም።

10. ሀገር እንዳትጠፋ ትልቅ ነገርን አታጥፋ።
"ሰው ሆይ በትዕቢትና በንቀት መወጠርህን
አቁም። የውሸት መኖርህን፣ ሰዎችን መበደልህን፣
ፈጣሪህን ማሳዘንህን አቁምና መልካም ነገርን
አድርግ። ልብ በል ሺህ ጊዜ የውሸት ብትኖር
አንድ ጊዜ የእውነት መሞትህ አይቀርም።

ስንት ቁጥር ተመቻችሁ. ?
ፔጁን ሼር፣ ላይክ ያድርጉ
@psychoet
በእርቀት ለሚኖሩ ባለትዳሮችና ፍቅኞች የተዘጋጀ ምክር https://youtu.be/-rhsE0knCS8
14 ወርቃማ #አባባሎች!
------------------------ሼር
1) ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው!

2) #ወንድ #ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ #ሕፃን ነው..ለእናቱ!

3) በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ #ፈተና ነው!

4) #ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው!

5) ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል!

6) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና!

7) የተሸናፊዉ #ፈገግታ ያሸናፊውን #ደስታ ይቀንሳል!

8) የሁሉን #ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው!

9) #ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው!

10) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም!

11) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና!

12) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤ እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።

13) ብዙ ሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን ሳያልፍለት ይሞታል!

14) በሕይወት ትልቁ ስኬት የሕይወትን ትርጉም ማግኘትና አላማ ያለው ኑሮ መኖር ነው፡፡

@PSYCHOET
ውሸት
#ክፍል_1
ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???

ከሜክሲኮ ወደ አራት ኪሎ ለመሄድ የታክሲ ሰልፍ  መጨረሻ ላይ ተሰልፌያለሁ፡፡ መቼም የስራ መውጫ ሰዓት ስለነበር የሰልፉን እርዝመት ልነግራችሁ አልችልም ደግነቱ የታክሲው ቶሎ ቶሎ መምጣት በጊዜ ወደ ቤት የመግባት ተስፋዬን አለምልሞታል፡፡ ከኋላዬ አንዲት ወጣት ሴት ልጅ መጥታ ተሰለፈች በስልኳ እያወራች ነበር  ልጅቷ የምታወራውን የጽሁፌ መነሻ ስለሆነ እነግራችኋለሁ በስልኩ በዛኛው ጫፍ ሆኖ የሚያወራውን ወዳጅዋን ደግሞ የሚመልሰውን መልስ ከእርሷ መልስ ጋር እያሰናሰልኩኝ በምናቤ እመልሳለሁ፡፡

ልጅቷ፡- በጣም ነው የደከመኝ ብታይ በጊዜ ነው ወደ ቤት የምገባው

ልጁ፡- ትንሽ አንቆይም ናፍቀሽኛል እኮ

ልጅቷ፡- Me too ግን ደክሞኛል እረፍት እፈልጋለሁ የት ነህ አሁን??

ልጁ፡- (የሆነ ቦታ ይላታል)

ልጅቷ፡- አሪፍ፣ እዛው ነሀ ከ 25 ደቂቃ በኋላ እደርሳለሁ

ስልኩ ይዘጋል የታክሲ ተራችንም ይደርስና ሶስተኛው ወንበር ላይ ጎን ለ ጎን ተቀምጠን ጉዞ ወደ አራት ኪሎ፡፡ እንቅስቃሴ የሚበዛበት ሰዓት ስለነበር መንገዱ በመጠኑም ቢሆን ተዘጋግቷል፡፡ ፓርላማ አካባቢ ስንደርስ ስልኳን አውጥታ መልሳ ደውላ ደርሼያለሁ ትለዋለች፡፡ እሱም ምን እንዳላት በእርግጠኝነት ባላውቅም ከመልሷ ግን መረዳት የቻልኩት ልጁ በቦታው አልነበረም፡፡ ቆይ ግን መዋሸት ምን አስፈለገህ ?? መቼ ነው ይሄን ውሸትህን የምታቆመው ?? ብላ ስልኩን ድርግም፡፡ ስልኳ በተደጋጋሚ ቢጠራም መልሳ አላነሳችም፡፡ መጨረሻቸው እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡የእነሱን ጉዳይ እንተውና እስኪ ስለ ውሸት ትንሽ እናውራ፡-

ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም  ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡ በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡

ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም በድርጊትም ጭምር እንጂ  ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ (Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት  የውሸት ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification) ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡ ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡

ለምን እንዋሻለን ??

ይቀጥላል ......

#Share
በቁምላቸው ደርሶ
©Zepsychologist
@psychoet
ውሸት
#ክፍል_2
ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

(በቁምላቸው ደርሶ)
©Zepsychologist
@psychoet
<እብዱ> መጽሐፍ ትረካ
ጸሐፊ - ኅሩይ ሚናስ
/የብዕር ስም- አውግቸው ተረፈ /
ክፍል 1
https://youtu.be/W2hsg_560Zo
ክፍል 2
https://youtu.be/fpEKcAcBYTs
ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)
https://youtu.be/1JzswWFOOnk
አንድ ባለ ትዳር ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ"ሚስቴ ጠፍታለች" ብሎ ያመለክታል፡፡

ፖሊስ ፡- "ከጠፋች ምን ያህል ግዜ ሆናት?"

ባል ፡- "አንድ ወር ሆኗታል"

ፖሊስ ፡- "ለምን እስከዛሬ አላመለከትክም?"

ባል ፡- እስከ ትናንት ድረስ መጥፋቷ ህልም ነበር የመሰለኝ፡፡ ከዛ ምንም የታጠበ ልብስ እንደሌለኝ ሳይ መጥፋቷን አመንኩ፡፡

ጭብጥ፡- አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው፡፡ በህይወታቸው ውስጥ ምንም ቦታ የለክም፤ ነገር ግን ካንተ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር መቃብር ድረስ ወርደውም ቢሆን ይፈልጉሀል፡፡

"የሰው ልጅ ያልተነበበ መፅሐፍ ነው" ወዳጄ ሁሌም ሰዎችን መርምራቸው፤ የዛኔ እውነተኛ ወዳጅህን እና ጠላትህን ነጋሪ ሳያስፈልግህ አንተው ትረዳዋለህ፡፡

©ከFB የተገኘ
@Psychoet
የምስራች ለአንባቢያንና ለወዳጆቼ

ሜሎሪና ክፍል ኹለት <<ሜሎሪና - ቴሎስ>> ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከአንባቢዎች እጅ ይደርሳል፡፡ መጽሐፉ፣ የሰው ልጅ በሕይወት ሲኖር ከሚጠይቃቸው ጥየያቄዎች አንዱና ዋነኛው የኾነውን "ወደዚኽ ምድር ለምን መጣኹ? የሕይወት አላማዬንስ እንዴት አገኛለሁ? >> የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚጥር #የሳይኮሎጂ_ልብወለድ መጽሐፍ ነው፡፡

በዚኽ መጽሐፍ ዝግጅት ወቅት በተለያየ መንገድ ስትረዱኝ ለነበራችሁ ወዳጆቼ በሙሉ ምስጋናዬ ካላችሁበት ይድረስልኝ፡፡ <<ሜሎሪና - ቴሎስ>> ከሰኞ ጀምሮ በኹሉም መጽሐፍ አከፋፋዮች ዘንድ ታገኙታላችኹ ። ሜሎሪና

መልዕክቱን #Share በማድረግ ላልሰሙ ታደርሱልኝ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ

@PSYCHOET
ስለ ዝምተኛ ሰዎች እውነታዎች /FACTS ABOUT QUIET PEOPLE

1. ዝም ያሉ ሰዎች በልባቸው ውስጥ ብዙ ያወራሉ፣ አንዳንዴ ብቻቸውን ያወራሉ።
(Quiet people talk a lot inside of their heart, sometimes they talk alone.)

2. አንዴ ካንተ ጋር ከተግባቡና ከተመቻቹህ በኋላ ግን እብዶች ይሆናሉ።
(Once they get comfortable with you they get crazy and wild.)

3. በሃሳብ እና በልብ ይናገራሉ።
( They speak in thoughts and heart.)

4. ዓይን አፋር ናቸው, የአይን ግንኙነትን ብዙ መጠበቅ አይችሉም.
( They are shy, they can't maintain eye contact a lot.)

5. በጣም ብዙ ንዴት አለባቸው አታናድዱአቸዉ። እና ቁጣቸውን እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ያውቃሉ.
( They have too much anger don't get them pissed off. And they know how to micromanage their anger issues.)

6. ጠንካራ እና በጣም ብልህ ናቸው.
(They are strong and very intelligent.)

7. በማህበራዊ ሚዲያ (አንዳንድ ጊዜ) በጣም ብርቱ ናቸው. ይፖስታሉ፣ ይፅፋሉ፣ ያደንቃሉ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸውም ይተቻሉ
(They are very crazy on social media (sometimes))

8. በጣም አሪፍ ስብዕና አላቸው እና ከነርሱ ጋር አብረው መሆንም አስደሳች ነው።
(They have very cool personalities and are fun to be with.)

9. አእምሯቸው ሁል ጊዜ ያሰላል, ከመጠን በላይ ያስባሉ. መጥፎ ነገሮች እና ጥሩ ነገሮች. እንደዛ ነው የታዘብኩት። ( Their minds are always calculating, they are overthinking too much. Bad things and good things. That's how I have noticed. )

10. እነሱ ታማኝ ናቸው እና በግንኙነቶች ውስጥ በጣም ይወዳሉ. እንደዚህ ያሉ ሰዎች በግንኙነት ውስጥ ሲሆኑ በሙሉ ልባቸው ሠዉን ይወዳሉ። ጥልቅ ፍቅርም አሏቸው . እነሱ ካልወደዱህ ግን ፍቅራቸው በጣም ጠንካራ ስለሆነ ሙሉ ለሙሉ ይተውሃል።
(They are loyal and love the most in relationships. When quite people they are in a relationship they love you wholeheartedly. They love deep. But if they don't love you, they leave you completely due to their love is very strong. )

11. በውስጥ ስሜታቸው ቢጎዳና Sensitive ቢሆኑም እንኳን፤ሕመማቸውን ፈጽሞ አያሳዩም,
(They never show their pain, and they are emotional people. )

12. አንዳንዶቹ የተጨነቁ እና ብቸኛ ናቸው, ነገር ግን ምንም እንዳልሆኑ አስመስለው, በጥልቅ ብቻቸውን መሆን ይሰማቸዋል, ስሜታቸዉን ለመግለፅ አይደፍሩም ስለዚህም ድብቅ ሰዎች ናቸው.
(Some of them are depressed and alone but they pretend, deep down they feel like to be alone, they are introvert people. )

13. በጣም ቆንጆ ፈገግታ እና ያልተለመደ ሳቅ አላቸው ። (They've got the cutest smile and weirdest laughter. )

14. አብዛኞቻቸው እውነትን ይወዳሉ። እነርሱም ሐቀኞች ናቸው።
(Most of them they like facts, and they are honest. )

15. ጸጥ ያሉ ሰዎች ሚስጥራዊ ሊሆኑ ይችላሉ, እንዲሁም ብዙ ነገሮችን ይደብቃሉ, ነገር ግን ምቾት እንዲሰማቸው ወይም እንዳይረበሹ ማድረግ ከፈለጉ ያለ ምንም ፍርሃት እውነቱን ይናገራሉ.
(Quiet people are likely to be secretive, also they hidecholy they will tell the truth as it is without any fear. )

16. ጸጥ ያሉ ሰዎች ብቻቸውን በሚሆኑበት ጊዜ በእውነት ደስተኛ ይሆናሉ። በሚወዱት ነገር እስከተጠመዱ ድረስ። ችግር የለም.
(Quiet people are introverts they are actually happy when they are alone. As long as they are busy with what they love. It's okay. )

17. ጸጥ ያሉ ሰዎች, እና ውስጣዊ ሰዎች በአእምሮአቸው ውስጥ የራሳቸውን ትዕይንቶች ፈጥረው ያምናሉ.
( Quiet people, and introvert people create their own scenes in their mind and believe them. )

18. ዝምተኛ ሰዎች,ማንበብ ይወዳሉ። የሚወዷቸው መጽሃፍትን በተለይም ልብ ወለድ እና ልብ ወለድ ያልሆኑ መጽሃፎችን ነዉ። አንዳንድ ጊዜ አነቃቂ መጽሐፍት (የራስ አገዝ መጽሐፍትንም ማንበብ ያስደስታቸዋል ።
( Quiet people, and introverted people they love to read. Reading books, especially novels both fiction and nonfiction books. Sometimes inspirational books (self help books).)

👉ዝምተኛ ሠዎችና የዚህ ፔጅ አምድ ተከታዮችና አንባቢዎች ይህ ሙያዊ ትንታኔ ምን ያህል ስለእናንተ ወይም ስለምታውቋቸዉ ዝምተኛ ሰዎች ባህሪ እንደገለፀ ትዝብታችሁን Comment በማድረግ አጋሩን።

©#Inspirational #stories & #life #hacks
አነቃቂ ታሪኮችና የሕይወት ዘዴዎች
@Psychoet
ከኢትዮጵያ ውጭ ለምትኖሩ የቻናላችን ቤተሰቦች መልካም ዐዲስ አመት እንዲኾንላችሁ እመኛለኹ፡፡

🎊🎊🎊🎁2022🎁🎉🎉🎉

HAPPY NEW YEAR!
ምን ያህሎቻችሁ ትስማማላችኹ?
@psychoet
ሜሎሪና ክፍል ኹለት (ሜሎሪና - ቴሎስ) ለአንባቢዎች ቀርቧል፡፡

#በዐዲስ አበባ በ #ጃዕፈር #ሀሁ #እነሆ #ኮሜርስ መደብር እንዲኹም በሚቀርቧችኹ ቦታዎች ታገኙታላችኹ

መልካም ንባብ ይኹንላችኹ፡፡

‹‹በርግጥ ወደዚች ምድር የመጣነው እኛ ፈልገን ሳይኾን ምድር ስለፈለገችን ነው፡፡ እንዴት እንደምንኖር ግን እኛና አካባቢያችን እንወስናለን፡፡ ትልቁ መኖርም እኛ እንደፈለግን ሳይኾን፣ በምድር እንደተፈለግን መኖር ነው፡፡ በዚኽች ምድር በቢሊዮን የሚቈጠር ሰው አለ፤ ፈጣሪ አንዱንም ሰው ያለ ምክንያት አልፈጠረም፡፡ ኹሉም ሰው በዐላማ መልካም ሥራ እንዲሠራ በዚኽም ምድር ላይ ተደስቶ እንዲኖር ተፈጥሯል፡፡ ሕይወታችንም የሚለካው በኖርንበት ዐላማ እንጂ በኖርንበት ዕድሜ ብዛት አይደለም፡፡... ››
@psychoet
ሠላም ወዳጆች፣
ኑ! "ሜሎሪና - ቴሎስ" መጽሐፍን እንመርቅ፣

″ሜሎሪና ክፍል ፪ -ቴሎስ‶
የተሰኘው የናሁሰናይ ፀዳሉ ዐዲስ መጽሐፍ
ቅዳሜ፣ ጥር 21 ከ 7:30- 10:00
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡

በዕለቱ የአንጋፋ የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች ዲስኩር፣
የግጥም፣ የጃዝ ሙዚቃ ፕሮግራም እንዲኹም
በደራሲው መጽሐፍ የማስፈረም ሥነስርአት ይከናወናል፡፡ እርስዎም በዕለቱ ተገኝተው አብረውን እንዲመርቁ በክብር ተጋብዘዋል፡፡

‹‹ቴሎስ ማለት በግሪክ ፣ የአንድን አካል ‹ዐላማ፣› ‹ግብ› እና ‹ፍጻሜ› የሚወክል ቃል ነው፡፡

የምርቃት ቦታ ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
ቀን፦ ያኹኑ ቅዳሜ ጥር 21 ቀን 2014.ዓ.ም.
ሰአት ከ 7:30 - 10:00

መግቢያ . . . . በነፃ፣
"ሜሎሪና" መጽሐፍን በዕለቱ በዐማርኛ እንዲኹም በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ያገኙታል

ኹላችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፣ መልዕክቱን ለሌሎች ያጋሩ

@Psychoet
ነገ ቅዳሜ ጥር 21 ከ 7:30-10 ሰአት በብሔራዊ ቴአትር አይቀርም፡፡
ወዳጆቻችሁን እየጋበዛችሁ፡፡
2024/09/30 16:31:34
Back to Top
HTML Embed Code: