Telegram Web Link
ከትርምስ መሀል ከኖረ ፀጥታ
በክፉ ቀን መሀል ከበዛ ዝምታ
ያንን ነዉ መተርጎም አንድም ለአንድምታ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@kidapoim
Audio
እንዲያዉ እንዴት ልግለፅ በሰሙ በቅኔ
የሌለሽ እስኪመስለሸ በአካል በእዉኔ
ደርሶ ይጠፋኛል ልነግርሽ በወኔ
............
የአይኔ ብርሀኔ የፍቅሬ መስታወት
የሰማይ ዳርዳርታ
የህብራተ ከዋክብት የፀሀይ መኝታ
የጨረቃ ድምቀት ሲመሽ ወደማታ
ለቀስተ ደመና የተነጠፍሽ ምንጣፍ
ወለባ ሠኪ ነሽ ወይስ ምርግ አጥናፍ
........................
........................
..........................

በትዝታ ወልዴ አንደተፃፈ
👉👉http://www.tg-me.com/Tizita_wolde
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
(ምርጡ ወታደር )
ከጥንት አባቶችህ ፣ ጀግንነትን የወረስከው
ሰንደቅህን አስረህ ፣ ዘመቻ የጀመርከው

እንደው የት ላግኝህ ፣ አንተ የሀገሬ ጀግና
መስዋዕት የከፈልከው ፣ በእልፍኝ ጎዳና

የወታደር ፍቅር በልብህ ያደረው
ዘርህን ሳትቆጥር በላብ የከበርከው

አጥንትህን ከስክሰህ ፣ ያወጣኸኝ ከመከራ
የትብዬ ልፈልግህ ፣ ያኖርክልኝ አሻራ ።

ቃላት የማይገልጽህ ፣ የተስፋ ማጀቴ
ምን ብዬ ላወድስህ ፣ የጀርባ አጥንቴ

ምርጡ ወታደር የፍትህ ገመና
ፈፅሞ የማታውቅ አንኳር ፍልስፍና

የጥቁር እንቁ ፣ የአዳም መሰበወርቅ
ጥበብ ያሳደገችህ ፣ በደምህ የምትፀድቅ

ከእሳት ተማግደህ ፣ በጨለማ የዋተትከው
በእንባ ታጅበህ ፣ ጉልበትህን የዘራኸው

አንተ ብቻእኮ ነህ ፣ የፅናቴ ዋልታ
ቃልህን አክብረህ ፣ የሆንከኝ መከታ

እውነት እስቲ ንገረኝ ምርጡ ወታደር
አንተ ባትኖር ፣ ምን ይውጣት ነበር እቺን ሀገር ?
# ቤዚቾ

@kidapoim
ሕይወትን ቀለል ብናደርጋት ኖሮ!

ካነበብኩት ትንሽ ሰንበት ያለ አባባል ትዝ አለኝ . . .

📍 የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው፡፡
🔷 ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው፡፡
📍የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው፡፡
🔷ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
📍ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
🔷 ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል፡፡
📍እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
🔷 በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱና የበሉት ሌሎች ሰዎች፣ ስንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው፡፡

🔑ይህ ሁሉ እውነታ እያለ “ነኝ” እና “አለኝ” በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም፡፡ እስቲ ያወሳሰብናትን ሕይወትን ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር፡፡
ዶ/ር እዮብ ማሞ

@kidapoim
ዙቤይዳ
አልሀምዱሊላሂ ደህና ናት

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
/ የመኖር ሚሥጥሩ /

ከልባችን መሀል ፣ ንፋስ ገባአሉ
ምንድነው መፍትሄው ፣ መውጫ መሰላሉ?

ብዬ ብጠይቅ ኣንዱ ተነሳና - - -

እባክሽ እህቴ አትበይ እንደእሱ
ፍቅር ብርታት አለው ፣ ያመጣል ወደእሱ

ለግዜው ነው እንጂ እንከን ሚፈጠረው
ሁሉም አላፊነው ፣ የራሡ ቀን አለው ።

ይልቅስ እህቴ፣ ፋናሽንቀይሪ
የፅናትገመድ ፣ አጥብቀሽ እሰሪ

በተቻለሽ አቅም ፣ ቶሎ አትሰልቺ
ያዳለጠሽን ቦታ ዞረሽ ተመልከቺ

ከዛ ይገባሻል የመኖር ሚስጢሩ
ቃልሽም አይወድቅም ፣ በየጉራንጉሩ።

ሕሊናሽም ቢሆን እረፍቱን ያገኛል
ከውድቀቱ ይልቅ እድገቱን ይልቃል

በእውነት አንቺ ሴት እንከንን መርምሪ
ከጥንት አያቶችሽ ፣ ትህትናን ተማሪ

እያለ መከረኝ ፣ ከልቡ አውጥቶ
በጥበብ ጎዳና፣ እራሱን ገንብቶ

እኔም ተቀበልኩት በሳቅ በፈገግታ
መንገዴን ቀጠልኩ፣ትቼአሉባልታ
# ቤዚቾ
@kidapoim
ይህም ያልፋል

አንድ ባይሆን የሕይወት ውሏ
..........ስቃይ ደስታ መባባሏ
በአይን እንባ ፊት ቢታጠብ
አካል ዝሎ ውድቀት ቢያብብ
ግዴለም ይህ ቀን ያልፋል
................የታመመም ይፈወሳል
ይሄን ሲሉት ያኛው ቢያመልጥ
ቀን ባይሞላ ችግር ቢሰጥ
ይህ ከሆነ የሕይወት ክሱ
ትዕግስት ነው ለዚህ መልሱ
.........ዝም ማለት መታገሱ.........
ውስጥ ያጣውን ሳቅ ያገኛል
.......ልብ ያሻውን ይገናኛል
አንድ ባይሆን የሕይወት ውሏ
..........ስቃይ ደስታ መባባሏ
ቀን ይጥላል ቀን ያነሳል
ግን ግዴለም ይህም ያልፋል

Mekdi
@kidapoim
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል!

© ሲራክ ወንድሙ @siraaq
.
ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣
አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ
.................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤
የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣
ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ።

ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣
ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤
እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ።

አዎን ያስፈራኛል...
ወዲያ ሽሽ ይለኛል...
ወዲህ ግድም እሩጥ ፣
ወዲህ ግድም አምልጥ ፤
ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤
የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤
ወዲያ ሽሽ ይለኛል ።
.............. | ። | ...............
ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም
@poimFitsae
@poimFitsae
❤️ፍቅርን ስበኩ

💛ፍቅርን ለመስበክ እንደ ጦርነት መሳሪያ መደርደር ወታደር ማሰለፍ ፤ ግዳይ መጣል አያስፈልገንም ። ቅን እና በፍቅር የተሞላች ልብ ብቻ በቂ ነው ። ከጦርነት በኋላ የምናተርፈው ነገር የፈራረሰ ከተማና ማንነት ነው ። ጀግና ነኝ ብሎ ከሚፎክረው ገዳይ ልብ ውስጥ ጥልቅ ፍርሃት ፣ ጥላቻ ፣ ጥርጣሬና ትምክህት ነው የምታገኙት ።

💚ጦርነት እምቅ ሀብትን አውዳሚ
እምቅ እውቀትን በታኝ፣እምቅ ሀይል ያለው ትውልድን አጥፊ ስለሆነ አስተዋይ ነኝ የሚል ሰው ሊጫወተው የማይገባ ድራማ ነው።

💜ምላስ የጦርነቶች ሁሉ እናት ነው፡፡ ምላስ አዳኝ ነው፤ ምላስ ገዳይ ነው፡፡ ለአንዱ ንፁህ የሆነው ለሌላው መርዝ ነው፤ አንዱን የፈወሰው ሌላውን ይገድለዋል፡፡ ሰው ምላስን የሚያህል ስለት በአፉ ውስጥ ይዞ የሚዞር ፍጥረት ነው፡፡ በዚያች ስለታም ምላስ ራሱን ብቻ አይደለም፤ ሌላውን ብቻ አይደለም፤ ማሕበረሰቡን ሊያርድበት ይችላል፡፡ አገር ሊወጋበት ይችላል፤ምሰሶ ሊነቀንቅበት፤ ጦርነት ሊፈጥርበት ይችላል፡፡

❤️በአለም ላይ የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በስተመጨረሻ ሁሉም ሰው በሰላም ለመፍታት ቢሞክር ይህ ሁሉ ባልሆነ ነበር የሚሉ አንድምታ ይፈጥራሉ።እኔ ነኝ ልክ ፣ እኔ ነኝ አሸናፊ በማለት የሚነሳ ትውልድ በእልህ የታነቀ ፣ቂምን ያረገዘ ሰለሆነ የሚመጣውን የሀገር ውድመት አያስተውልም።

💛በፍቅር ግን የሚለመልም እንጂ የሚወድም ግለሰብም ማህበረሰብም ሆነ ሀገር አላየንም ።በፍቅር የተሞላች ልብ ውስጥ ጥንካሬ ፣ቅንነትና ለሁሉ አሳቢነት በአንድንት ጎጆ ሰርተው በፍቅር ሲኖሩ ታያላችሁ ።

❤️ሰው ከፍቅር ውጭ ሊኖር እንዴት ይቻለዋል ! ስለ ፍቅር ስበክ ፣ ስለ ፍቅር ኑር !

ውብ አሁን❤️
@kidapoim
የሀገሯ ~ ገመገም
Yohannes_Lawgaw @Sleenee ስለ እኔ ስለ ኔ ዮሀንስ ላውጋው
የሀገሯ ገመገም

ፀሀፊ
ሱራ ቢራቢሮ
@surabirabiro

አንባቢ ዮሀንስ
@Yohannn

ግልባጭ ለፊያሜታ

።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
#የግጥም_ቃና

የ እግዜር ስላቆች

ለፅድቅ : ፍትሀት : ሀጥያትን : ካረገ፣
መርገምን : በረከት : አርጎ : ከፈለገ፣
መሰዋዕት : አርጎ : እጣን : አሽቀንጥሮ : ቆሻሻ እያጨሰ፣
ገነትን : እያለ : ሲኦል : ከፈለሰ፣

......
በየቱስ : አምክሮ : ሞገስን : ይስባል፣
በነገር : ጎዳና : አቡዋራ : ያቦካል፣
ምሳሌውን : ንቆ : ፈጣሪው : ጋር : ቀርቦ፣
እንዲህ : ጠየቀ : አሉ : ጥጋብን : ተርቦ፣
አሳ : ስጠኝ : አለው፣
ዳቦ : ስጠኝ : አለው፣
እግዜርን : በእግዚአብሔር: ብሎ : እየለመነው፣
ፈጣሪም : ሊቀልድ : ይህን : አሰበና፣
ይሁን : ብሎ : ቸረው : ድንጋይ : እና : እባብ፣
ለንቀቱ : ክብር : ለጥጋቡ : ርሀብ፣

❗️ማሳሰቢያ የመጨረሻው አንጓ ላይ ያሉት ቃላቶች መልካም ክፉዎች ከሚለው ከሌላኛው ግጥሜ ጋር ቢመሳሰሉም። ፍፁም የተለያየ ሀሳብን ይዘዋል ።
ናታን ኤርምያስ
@UniqueDy

#የግጥም_ቃና
👇👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ
🙏የምንፈልገውን ለማግኘት ብቻ ከመማሰን ያገኘነውን በመውደድና በማመስገን ቀናችንን እናስውብ ፡፡

ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ.....አየሩን ስትተነፍስ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! ውለህ ስትገባ ተመስገን በል፣ ብዙዎች እንደወጡ የቀሩ አሉና።

💜በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!


ውብ ዛሬ!!!❤️

@kidapoim
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
#የራስ_ቦታ!
የኪነ_ጥበባት ምሽት!
ነገ እሮብ 12/12/2013
በኢትዮ ሳራ ቡና! …ናዝሬት/አዳማ
Join and share……………👇👇
@heranawi
@heranawi
Forwarded from Арбитражница dooradas (🦋ሱራ ቢራቢሮ 🦋)
ፀበል ፥ በሚፀበሉ ፥ የጋኔን ፥ ማደሪያ ፥ በሆኑ ፥ ሰዎች : መሀል : ተከብቤያለው ፥ እንደርቢ ፣ ቡዳ ፣ አዛዝኤል : መተት ፣ ሰላቢ ፣ ድግምት...ወ..ዘ.ተ..........እዝጎ: ብዛታቸው ፥ ግን : እግዜሩ : ብዙ : ተባዙ ያለው : እነሱን ፥ ሳይሆን ፥ አይቀርም። እንዲህ : አንደ : ምድር : አሸዋ : ያበዛቸው። ምናልባት :ውስጣቸው :ስለማይገኝ : ይሆናላ : ብዬ ፥ የጥያቄም ፥ አባት ፥ የመልሱም ፥ እናት ፥ ሆኜ ፥ ቁጭ አልኩ።

እኩለ : ሌት : ላይ ጋደም : ብዬ : ሳለ እማሆይ በደጃፌ : አለፉ ብሩኬ...... ብሩኬ........ በለሆሳስ : ተጣሩ

እ......... አቤት : እማሆይ .... በመደነባበር : ስሜት

አንት : ሙዠሌያም : በሩን : ክፈት .....

ቀጭን : ትእዛዝ ......

እጄ ፥ ወደበሩ ፥ መክፈቻው ፥ አኮበኮበ..... ሲጢጢጢጢጥ... በሩ ፥ ተከፈተ።

እማሆይ ፥ እርቃናቸውን ፥ ናቸው ደነገጥኩ ራሴን እማሆይ : ፃድቅ : ናቸው : የፀጋ : ልብስ : (ፀጉር) ፈጣሪ : አከናንቧቸዋል : ብዬ ራሴን : መሸወድ ፈለኩ።

በርግጥ ፥ እሳቸው ፥ አፍላ ፥ እድሜ ላይ ናቸው። ቁንጅናቸውም ፧ እንኳን ለንደኔ ፥ አይነቱ አለማዊ መናኝንም ፥ ከአቋሙ ፥ ያዋዥቃል።

የጌታ ፥ ፍቃድ : ሆነና : እማሆይም : በውበታቸው ማርከው : መደቡ : ላይ : አጋድመው ፧ ደጋግመው : ነጠሩብኝ....

መቼም ልጄ ነገር በሶስት ይፀናል አሉኝ...... ልክ አንደኛውን ፧ ዙር እንደጨረሱ....

በተወደደ ፥ መቅኔ ፥ መተኪያ በማይገኝበት ፥ ቦታ ላይ ምን ፥ ኩነኔ ፧ ገባሁ? ፥ ጃል! አዎንታዬን ፥ ራሴን በመነቅነቅ ፧ ሶስት ግዜ ፧ እንጢነጥሩብኝ ፈቀድኩላቸው።


ስብሀት ለአብ_____ ቸፍ
ስብሀት ለወልድ_____ ቸፍ
ስብሀት ለመንፈስ ቅዱስ____ ቸፍ

ጠበል ፥ የሚረጩኝ ፥ ግርማ ፧ የ ሞገስ ፥ ተላበሱ አባት በመስቀላቸው ፧ ጀርባዬን እየደለቁ። አንተ ማነህ ?
ፈርጠም ፧ ብለው ፧ በነጎድጓድ ፧ ድምፃቸው....

ሴት ነኝ ያውም መነኩሴ.....

ሴት......ምንድነሽ?

ሴት አይነጥላ ፣ ሴት ሳር

የምንኩስና ስምሽ ማነው?

#እማሆይ_ረታ_ነጠረች

ወደሲኦል ትገቢዘንድ በእግዚአብሄር ስም አዝሻለው ጮኸሽ ውጪ..

ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ ጮሄ ወደኩኝ .

ከወደኩበት ስነሳ ብዙ ምዕመን በቤተክርስቲያን ውስጥ ታድሞ የሚሆነውን በጥሞና ይመለከታል

ስምህ ማነው አሉኝ ግርማቸው የሚያስፈራ አባት

#ካሳ_ውቤ_ልዋጥህ

ህምምም ¡ አለ ነገር......

ፀሀፊ
ሱራፌል ጌትነት
🦋 ሱራ ቢራቢሮ

🦋
@surabirabiro🦋 ሀሳብ አስቀምጡልን


።።።።።👇👇👇👇።።።።።
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
🦋🦋
www.tg-me.com/sufafel 🦋🦋
ቡሄን በትዝታ

ቀናቱ ተዳርሶ ቡሄ መጣ ሲባል
ከልጅነት አለም ትዝታ ይነግሳል
* * *
ሆያ ሆዬ ስንል በ 'ሆ' ሲቀበሉን
በጭፈራ መሀል ሁሉን አሞግሰን
ሙልሙል ተከፋፍሎ
..ምርቃት ታድሎ በደስታ ሲሸኙን
.....እኛም በምስጋና እንመለሳለን
* * *
............በዳቦ መአዛ ሰፈሩ ታጥኖ
ሆዬ በሚል ዜማ ቀኑ ተሽሞንሙኖ
........ ሳይ
ውስጤ በትውስታ ኀላውን ይቃኛል
ከወደኔ አለም ቡሄን በትዝታ
ከኀላ ተገኝቶ ካለፈው ጨዋታ
........... ደስታን ይታደላል
ዛሬን ከእናንተ ጋር ቡሄውን ልካፈል
እኔም በተራዬ እንዲህ ሆዬ ልበል
ሆያ ሆዬ .. .. .. .. .. .. .. ሆ
ሆያ ሆዬ .. .. .. .. .. .. .. ሆ
እዛ ማዶ .. .. .. .. .. .. .. ሆ
ጅራፍ ይጮሀል
እዚህ ማዶ .. .. .. .. .. .. ሆ
ጅራፍ ይጮሀል
ቀኑ በድምቀት አሸበራርቋል
የጅራፉ ጩኸት ፍቅርን ሲያበስር
የጥላቻው ዜማ ቅላጼው ሲከስር
ፍቅር የዋለበት ደስታን ታድለናል
ነገን ከዛሬ ጋር ለአንድነት ታጭተናል

መልካም ቡሄ 🙏

Mekdi
@kidapoim
Forwarded from የ ዳግም ሔራን ግጥሞች (ሔራ…ቶ…ዳግ)
[ የአብሮነት ፀሓይ ሥር! ]
:
ስብር ቀኗ ቀንቶ
ምድሪቱ ስትነቃ : የኔ ኣለም ቆዝሞ
የሁለ ዕለት ፌሽታ
ደስታዬ እንያጠረ : እሪታዬ ረዝሞ
ክደት ባ‘ደከመው
ልቤ ላይ ሲከመር: ክብድ የዋይታ ቀንበር
በነጋ በመሸ : ልቤ እየጠለሸ :
እሪ ስል ሳነበ :ውብ ሳቄ ሲቀበር
:
ያየ ፍጥረት ሁሉ

ሽርቡ ረጋግቦ
ነትቦ ሳይበጠስ: በአንድ ያሰረን ገመድ
ወረት ያልታቀፈን
መጣመር አንግበን : አብረን ስንራመድ

አጀብ ጥምረታቸው
መገን ነው ፍቅራቸው : ሲል እንዳላወራ
(ዛሬ ብትለዪኝ:ብትርቂ ከእኔ ኣለም )
ያን ልሳን በሻረ:አደፎ በነተበ:
በክፉ ቃል ሆነ:ስምሽን ‘ሚጠራ
:
ደግሞ ቅድም

ከአሁን በፊት
መውደዴን በትና :
ርቃ እንደሄደች :ከወዲያ እንዳረፈች
ወዛም ቃል ኪዳኗን
: በክደት ለውሳ… ደርሳ እንዳሳደፈች
አሁን ተመልሳ
ከይቅር ፈሳሽ ወንዝ :
በቀዳች ውሃ :እንዳዲስ ብታጥበው
እንኳንስ የኔን ልብ :
ግትሩን ተራራ : ደስታ አቅበጠበጠው!
:
ይኼው ዛሬ: ቀኔ ቀንቶ
መሬት እኔነት ላይ
ደስታ ተገንብቶ : ፌሽታዬ ሲታነፅ
እንዲህ ነው ማይባል
ቅርፅ አላባ ኣለሜ : በይቅር ሲቀረፅ
እኔ ፈገግ አልክኝ
ሳቄን ሳቅ አነቀው: ደስታዬም አለው ደስ
በአብሮ መሆን ማጥንት:
ውስጠቱ ታጠነ :የአፍቅሮቴ መቅደስ
:
እያልኩኝ ሳወጋ

የነበር አንደበት
የትላንቱን ልሳን : እኩይ ቃሉን ጥሎ
አድናቆት ባጠረው
የአግራሞት ሀቁ ላይ: ምርቃት ቀጥሎ
አይለያችሁ አቦ
እርሱ አይነጥላችሁ :የሚል ቃል ያወጣል
የተናጥሎ ጀምበር
እስክትመጣ ድረስ:
የአብሮነት ፀሓይ ሥር:ሰናይ ቃል ያሰጣል!
:
ወትሮስ ይህ ዓይነቱ
እንዲህ ያለው የኛ ሰው
የለም ልቡን እርሻ …
ግር የማለት ተክል… አረም ከወረሰው
ቀን የሰጠውን ስም :
ውሎ ሳያደር ነው :መልሶ ‘ሚያፈርሰው!!
:
አጀብ ነው አንችዬ!
……………………………………**
[ ዳግም ሔራን #ቅዱሱ_እብድ ]
join and share……………………👇👇
@heranawi
@heranawi
@heranawi
#ጊዜ_ጌታ
#ናታን_ኤርሚያስ @UniqueDy

በልኬቱ : ወርዶች : ፍቅሩን : ደርድሮ፣
ነገ : አብሮሽ : ላይዘልቀው : ዛሬሽን አፍቅሮ፣
ልብሽን : ፈልጎ : ልቡ : ውስጥ ሊከትሽ፣
በሀሰት : ምህላው : የእውነት : ሲክብሽ፣

ትላንትን : ማልቀሱ፣
ሳትቆስል : ነብሱ፣
ከላይ : ከላዩ : ላይ፣
እንባውን : ዘርግፎት : መከፋቱ : እንዲታይ፣
.
.
እዘኚልኝ : ብሎሽ፣
አጥፎ : እያሳዘነሽ፣
በፍቅር : ለማረፍ : ብዙ : ተሰቃየሽ፣
ባለፍሽበት : መንገድ : እግሮችሽ ሲጣሉ፣
ዘመን : አሽከርክሮሽ : ወደቅሽ ከመሀሉ፣
መውደቂያው ቢደላሽ አልጎዳኝም ብለሽ፣
ራሱን : ለመያዝ : እግሩ : ስር : ተገኘሽ፣

ነግሬሽ : ነበረ : ጊዜ : ጊዜ : እንዳለው፣
ስንቱን : እያነሳ : ስንቱን : እንደጣለው፣
ላትረሺው : ረስተሽ : ዛሬ ላይ : ብትፈርጪ፣
ለጊዜ : ተስለሽ : ከራስሽ : አምልጪ !


#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ

__~°\°/°💚ሰናይ💛ግዜ°\°/°~__
ሆያ ሆዬ ጉዴ
እሷን እሷን ይላል ሆዴ!🤷‍♂

@ilovvll
@ilovvll

እንኳን ደረሰብን መልካም በአል💚💛
።።።።።። በጨዋው ልጫወት።።።።።።

"ሆያ ሆዬ" ሲሉ ሙልሙል መስጠት ትቼ፣
ከድምፅ አውጪው ጋራ ብሄድ መንገድ ስቼ፤
ይቅር!
ይቅር ብቻ በሉኝ የኔታ አይቆጡ፣
ለቀክፋት አይደለም ለ'አንድ ማታ አይምጡ።

ምን መሰሎት አባ፦

ቡሄ አልፎ ክረምት፣
ዶሮም ጮሆ ለሊት፤
ስለማይደገም ግዜም እንደ ትውፊት፤
ዝም ይበሉኝ እና በጨዋው ልጫወት፣
እርሶም አይፈሩ እኔም ልወቅ ልኬት።

መክሊት የ16ቷ

#የግጥም_ቃና
👇👇👇
@ilovvll
@ilovvll 👈 🙌ቤተሰቦች🙌

ለኢትዮጲያዊያን ቤተሰብዎ ያጋሩ

💚💛
ሰናይ ግዜ
2025/02/06 22:19:55
Back to Top
HTML Embed Code: