Telegram Web Link
"""""ጓደኛዬ 2"""""

በፍቅር መያዜ፡ ደስታው ለራሴ ነው፣
ሄዋን በመሄዷ፡ ጎጆን ሳልቀልሰው፣
ዝምታን መምረጤ፡ የኔ ባህሪ ነው፣
ይብላኝ እንጂ ላንተ...!
"ማፍቀሩንማ እኮ፡ አፍቅሬ ነበረ፣
በተጣላን ማግስት፡ ፍቅሬ በሮ ቀረ"፣
ብለኽ የሸለልከው፣
ተሰባሪነትን ለመካድ አስበህ፣
ስሜትህን የሻርከው!።

ተረባ--በየሱስራ

@poemers @poemers
""""እመን ማፍቀርህን"""

እኔ አምኛለው : በፍቅር መያዜን፣
በሴት ተማርኬ : እጅ መስጠቴን፣
አንተ ግን : ብለህ ታወራለህ....!
እኔ ለፍቅር : ልቤ ደንዳና ነው፣
የሚገርመው ግን...!
ከኔ ቀድመህ : አንተ መያዝህ ነው።

በ-ሀይልአብ
@poemers
ከትላንቱ የቀጠለ-------
"""ረቡኒ"""

አንተው ነበርክ እኮ፣
የፍቅር መምህሬ፣
"ሀ" ብዬ ስጀምር : ያስተማርከኝ ያኔ፣
ዛሬ ምን : ነክቶህ ነው፣
ፀባይህ ቅጥ ያጣው፣
አንደ አሮጌው ብር፣
ልብህን የጣልከው።

በ-ሀይልአብ
@poemers
""""ተማሪዬ""""

አዬ ጓደኛዬ...!
የተናገርከውን፡ አላልኩም ነው መልስህ፣
መምህሬ ብለኸኝ፡ ልስደብ ነው ፋሽንህ፣
ፍቅርን አስተምሬ፡ ደስታና ሀዘኑን፣
ባስተማርኩኝ እኔው፡ ሆንኩኝ ተወቃሹን፣
አወይ ጉድ!

ተረባ-- በ የሱስራ

@poemers @poemers
የሀን ደብዳቤ💌💌💌
ይድረስ ለምወድሽ.........📯📯
🎙በሀይለአብ የቀረበ👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
በሀና አዲስ
ሠናይ ጊዜ🙏🙏🙏🙏🙏
@yehangetem
@yehangetem
👆👆👆👆👆👆

@poemers
ተጓዡ ልቤ
በየሱስራ ተፅፎ👌👌👏👏🙏
🎙በሀና አዲስ የቀረበ👍👍👍
ሴት ልጅ እናትህ ህይወትህ ናት መናገርን ባሥተማረችህ አንደበትህ ክፉ ቃል አትናገራት።!!!!!!!!
@yehangetem
@yehangetem
Ye hiywet kbdetwa kaltayek trgumwa aygebakm slezi besew lay atfred😔😔😔
መልካም ቀን🙏🙏
""""እሱ ይሻለኛል""""

አጋድሞ ይረደኝ : ነጩ ይሻለኛል፣
ባዳ ነው ብዬው : ሆዴም ቆርጦልኛል፣
የወንዜ ከሆነ : ግን ይቆጨኛል፣
አደለም ጦር መዞ፣
ሲሰድበኝ ያመኛል፣
ሆድ ይብሰኛል።


በ-ሀይልአብ
15-02-2013

ፈጣሪ አንተ ጠብቀን 🙏
@poemers @poemers
አፄ ቴዎድሮስ ጀግናችን

@poemers
""" አይ መዘመን """"

ያ ትውልድ : የት አለ፣
አባሮሽ ተጫውቶ : ባኩኩሉ ያደገ፣
አውሎ ንፋስን : አይቶ የረገጠ፣
በአፈሩ መሀል....
ሴጣንን ለመግደል : ምላጭ የጨበጠ፣
--------%--------
ይሄ ትውልድማ...
አባሮሽ ሲያምረው : በ temple run ነው፣
እግርኳስ ካማረው : በ PlayStation ነው፣
ባህል መሠረቱን : አሽቀንጥሮ ጥሏል፣
ታሪክ ማንነቱን : ባደባባይ ሸጧል፣
በጠራራ ፀሀይ : እያየም ተዘርፏል.

አሯሯጡን አይተው ጭብጦውን የቀሙት ትውልድ!
በ-ሀይልአብ

10-02-2013

@poemers @poemers
"""ላደንቅሽ ነበረ""""

አይኖችሽ እንቁ : ካልማዝ የሚያበሩ፣
ፀጉርሽ ዞማ : ሀርንም ያስንቃል፣
በረዶ እንደጥርስሽ : ከቶ መች ይነፃል፣
አምላክ ጥበቡን : አንቺ ላይ ሰርቶብሽ፣
-------------------
ይሄን መልክ እያየው፣
ልቤ አብሮሽ በኖረ፣
ጉራ አለብሽ እንጂ
የሚል ግጥም ፅፌ : ላደንቅሽ ነበረ።

በ-ሀይልአብ

@poemers @poemers
@poemers
ስማ አንተ ቤተስኪያን : ስማ አንተ ደብር፣
አደራ አንተ ጉድጓድ : አንተ መቃብር፣
ስንቱን እንደበላህ እንድትመሰክር፣
---------------------------
እኔ አልኮነንም : ሀሰት ተናግሬ፣
አኔ አልታመም : ውሸት ተናግሬ፣
ድሀ አልኖረብሽም : ድሀዋ ሀነሬ፣
--------------------------
ደህና ሁኑ እንግዲ : አፈር ይቅለላቹ፣
ለእውነት ሞታችኋል : ገነት ትመቻቹ፣
ወዮ ለጨካኞች ለገዳዮቻችሁ።

ምንጭ-ያልታበሱ እንባዎች ከሚለው ልቦለድ መፅሀፍ

@poemers @poemers
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

@Kedutii

@Poemers @Poemers
ይድረስ👉 ለማይደርስልን መንግስት 😒

እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምን ነህልን?
እንደምን ነህልን ካልንህስ በኋላ ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን፣ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር፣እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው"፣በሚል ፍልስፍና !
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ፣የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ለአበቦች መጥፋት
እንደምን ነህ አንተ?!

#Belay #Bekele #Weya

Join more poems👇
@poemers @poemers
"""ያዋቂው ስህተት"""

ተፃፈ በ- ሀይልአብ
ቀን- 17-01-2013

@poemers @poemers
ሰው ነበር
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

በሚያሳንስ ሚዛን ወርደን ባንገምተው
በ'ርግጥ ብሄር ሳይሆን ሰው ነበር የሞተው


ኢዛና መስፍን

@poemers @poemers
"""""ተንኮል ነው"""""

ያኔ ስንገናኝ የምደነግጠው፣
አፍቅሬሽ አደለም፣
ያሰብኩት ተንኮል ነው።

ሀይልአብ

Join👇👇👇👇
@poemers @poemers
""""ትረገጫለሽ"""""

እንደ ሲጋራዬ : አቅፌ ልምጠጥሽ፣
ትንፋሽሽን ምጌ : ውስጤን ላሙቅብሽ፣
ወዝሽ ከተነነ : ጠረንሽ ካለቀ፣
ያኔ ግን እንጃልሽ፣
ልክ እንደ ሲጃራው ትረገጫለሽ፣
ሱሴ ነሽ ስልሽ ወድጄ እንዳይመስልሽ!

ሀይልአብ

Join👍 👇👇👇👍
@poemers @poemers
""""እንቅፋት""""

እግርህ ሲንቀለቀል : እሱን በደለቀው፣
እንቅፋትን መተኸው : መታኝ አትበለው፣
ድንጋዩ ፅኑ ነው : እመሬት ተጣብቆ፣
መች ይንቀሳቀሳል : ባለበት ተተክሎ፣

ከመታህም ደና : እሰየው ነው እንጂ፣
መመታቱ ኮ ነው : ላንተም የሚበጅ፣
እንደው ያሮጥሀል : መች ያስቀርሀል፣
ኋላ የነበርከው : ከፊት ይጥልሀል!

በ ሀይልአብ
09-02-2013

Join 👇👇👇
@poemers @poemers
""""በ ሀገሬ"""""

እንቅፋት ሲመታህ : ልደፋልህ ሚልህ፣
ከልቡ ነው : ባ'ላገር፣
ውሸት እንዳይመስልህ፤

ሀይልአብ

Join 👇👇👇
@poemers @poemers
2024/10/02 04:32:16
Back to Top
HTML Embed Code: