Telegram Web Link
Forwarded from ፋና ብዕር
ማረኝ
""""""
በእንባዋ እግሩን አጥባ ይቅር ለተባለች
አዳፋ ነብስያ ከሀጥያት እስራት ነፃ እንደወጣች
እንደ "ዘማዊቷ" እንደዛች ምስኪን ሴት
ህግህን የሻረች የኔን ነብስ ማራት
በሀጥያተኛ አይኖቼ እንባዬን ጨምቄ
እግሮችህን ልጠብ በጉልበቴ ወድቄ
ውብ ሽቶ የለኝም ጠረኑ የሚያውድ
ግብሬም የከፋ ነው ባንተ ማይወደድ
ባለፈው ስራዬ ከልብ ተፀፅቼ
ማረኝ እልሀለው ከእግርህ ተደፍቼ

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
Forwarded from ፋና ብዕር
ፀሎት ሀሙስ
"""""""""""""""""
ንዋይ የጋረደው የእርሱ ደቀ መዝሙር
ያስቆሮቱ ይሁዳ ሰይጣን ሆዱ ቢያድር
በንፁህ እጆቹ ሀጥህ እግሩን ባጠበ
መሀሪ ጌታው ላይ ክህደትን አሰበ

የአለሙን ገዢ ያንን ባለ ግርማ
በሰላሳ ዲናር ጌታውን አስማማ
ክፋት አገርሽቶ ለትውልድ ይተርፋል
እድሜ እያቆጠረ ሀጥያት ይዋረሳል
በፀሎተ ሀሙስ እጥበትህ ናፍቆናል
እንደ ካጅ እግራችን ልባችን አድፏል

አረጋኸኝ መንገሻ(ፋና ብዕር)
" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
(ኢሳ 53: 5)
Happy Easter for us & our beloved family's!!
"""""ትንሽ ታገሰኝ"""""
vocal challange

Join this channel
@poemers
@poemers
@poemers
""""""የታባቱ ክብሬን'''''''
Vocal challange

Join this channel
@poemers
@poemers
@poemers
( በላይ በቀለ ወያ )

.
አንጥሴ
አንጥሴ
በማለት ባስነጥስ ፣ ሁሉም አገለለኝ
ቀና ብየ ባየው ፣ ሰማዩም ቀለለኝ
"እግዚአብሔር ይማርህ"
ማያባብል ዘመን ፣ መጥቶ ነው መሠለኝ!

@poemers
@poemers
@poemers
2024/10/02 20:38:19
Back to Top
HTML Embed Code: