Telegram Web Link
​​​​ . . . . . . . . . ምንድነሽ ? . . . . . . . . . . .


ብልጥ ነሽ አንዳልል
የዋህ ትመስያለሽ
ጅል ነሽ እንዳልልሽ
ብልህ ትመስላያለሽ
ይኸው ተጃጅለሽ
ታጃጅዪኛለሽ
ይሄንን ጅል ግጥም
ያው ታፅፊኛለሽ!! ♥️🥰

♦️ @Kedutii ♦️

😂😂😂😂❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
መግለጫ
.
.
"የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፤
የላብ አደሮች ቀን፤
የፍቅረኛሞች ቀን፤
የዓለም የውሸት ቀን፤
የዓለም እንትን ቀን፤
የቅብርጥስ ቀን
የምንትስ ቀን "
ቀን ሁሉ በቀን ላይ ፣ ተከብሮ እየዋለ
የኢትዮጵያዊነት ቀን ፣ ለምን ተዘለለ ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሀገርን የሚያህል ፣ አንድነት በትኖ
ከእኛነት በላይ ፣ እኔነት ጀግኖ
ቀን አይከበርም ፣ ጨለማ ላይ ሆኖ!!!
።።።
😘😘😘😘😘😘❤️❤️❤️❤️
@poemers
@poemers
@poemers
እኔ ለሀገሬ"
እኔ ለሀገሬ
ይነጋል እያልኩኝ ፣ ጨለማው ገዘፈ
አንዱ ለፍቅረኛው
ብርሐኔ ነሽ የሚል ፣ ብዙ ግጥም ፃፈ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ ለሐገሬ...
በተስፋ እያልኩኝ ፣ ሁሉም ነገር ያልፋል
አንዱ ለፍቅረኛው...
የኔ አለም አንቺ ነሽ ፣ የሚል ወግ ይፅፋል፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ ለሀገሬ
ለዘላለም ኑሪ ፣
በማለት ስፀልይ ፣ ቆሜ ከመቅደሱ
የሴት ፀሎት ሰማሁ...
"ለኔ ዘላለም ነው ፣ አንድ ቀን ያለሱ፡፡"
።።።።።
እኔ በሀገሬ...
ንፁ ደም መፍሰሱ ፣ ልቤ እያዘነ
አንዱ ለፍቅረኛው...
በደሜ ውስጥ አለሽ ፣ በማለት ዘፈነ፡፡
፡፡፡፡፡፡
እኔ ለሀገሬ...
ተወርቶ የማያውቅ ፣ የሐዘን እንጉርጉሮ
ተፈቶ የማያልቅ ፣ የኑሮ ቋጠሮ
ርሐብ ቸነፈሩ
ዘሩ ዘር ማንዘሩ
ጦርነት ችግሩ
ጉድጓድ መቃብሩ
ስቃይ ስንክሳሩ፣
ሚያበቃበትን ቀን ፣ ስናፍቅ በልቤ
"ካንተ ናፍቆት በቀር...
እጅጉን ደና ነኝ ፣ አንተው ነህ ሀሳቤ
ብላ ትፅፋለች...
አንዲት ሴት ለፍቅሯ ፣ በሚላክ ደብዳቤ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ ለሀገሬ...
ስፀልይ ስማፀን ፣
የጠፋ ሰላሟን ፣ እያልኩ እንዳይጠፋ
"ሰላሜ አንቺ ነሽ"
ይላታል ለፍቅሩ ፣ አፍቃሪ ፈላስፋ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ ለሐገሬ...
አንድቀን እያልኩኝ
ለአመታት ሲመረኝ ፣ የመኖር ትርጉሙ
ብዙ ገጣሚዎች...
ስለ ከንፈር ጣዕም ፣ ግጥም አሳተሙ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡
እኔ እኔ ማለት ያበዛሁኝ እኔ
ችግርና ስቃይ
ግፍና መከራ
ደም እና ደምባራ
መቼም የማይለቃት ፣ አንድ ሀገር ወድጄ
ስቃጠል ከምኖር ፣ ሲኦል ላይ ተጥጄ
ከዚ በላይ ስቃይ
ከዚህ በላይ ጤና ፣ ጤናዬን ሳይነሳኝ
አንቺን ባፈቅርሽስ...
ፍቅርሽ እውር አርጎኝ ፣ ሁሉን እንዲያስረሳኝ?
።።።፣፣፣
አፈቀርኩሽ በቃ!
እኔ አንቺን ሳፈቅርሽ
ሀገሬን ረሳሁ
ችግሬን ረሳሁ
ስቃዬን ረሳሁ
ሁሉንም ስረሳ...
"ኢትዮጵያ ሀሳቤ ነሽ!"
የሚል ግጥም ልፅፍ ፣ብእሬን አነሳሁ፡፡
ርእሱን ፅፌ ግጥሙንም ረሳሁ፡፡
ኢትዮጵያ ሀሳቤ ነሽ።
ኢትዮጵያ ሀሳቤ ነሽ።
ኢትዮጵያ ሀሳቤ ነሽ፡፡
( በላይ በቀለ ወያ )
#Share
@poemers
@poemers
@poemers
@poemers
"""ማን በነገራት"""

በ-ሀይልአብ

Join 😝👇👇👇👇
@poemers @poemers
ሁላቹም እዚ channel ያላቹ በሙሉ channelun unmeut በማረግ ተባበሩን ብትኖሩም እንደማትኖሩ ስለሚያሳይ ነው። ፊት ለ ፊታቹ mute ሚለው ከሆነ ልክ ነው ማለት ነው🙏
ግጥም-በእኛ 💌 pinned «ሁላቹም እዚ channel ያላቹ በሙሉ channelun unmeut በማረግ ተባበሩን ብትኖሩም እንደማትኖሩ ስለሚያሳይ ነው። ፊት ለ ፊታቹ mute ሚለው ከሆነ ልክ ነው ማለት ነው🙏»
Audio
ተፃፈ- ናትናኤል ገረመው
ግንባሬን አትንኩ

Join this channel
@poemers @poemers
ውብ ባህላችን

@poemers @poemers
ትርጉም !
(በረከት በላይነህ)
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ ጥፉ፤
እንደ ደሀ ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!

የማትባል እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ ፣ ማማር አልባ!

ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ ያይጥ ፞ ድምር
ባትታይም የማታምር! !!"

እረ ! ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!

ለምን ብትይ?

መልኬ ከሸለመሽ የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ


@poemers
@poemers
ጮሃለሁ!
=========
አባቴ ተሰቅሎ፣
ወንድሜ ተቃጥሎ።
እህቴ ታግታ፣
እናቴ ተቀልታ።
አያቴ ተሰ'ዶ
ህፃን ልጄ ታርዶ... አሞኛል!
ወገን ሞቶብኛል!
ሰው ተገ'ሎብኛል
በማያውቀው ጉዳይ ባልገባው ጨዋታ፣
በሌለበት ግንባር ባልዋለበት ሜዳ ቀድሞ እየተመታ፣
ተጨምቆ ተጨምቆ ጠብ ላይልለት የድላቸው ፋይዳ፣
መከራ የሚገፋው እየወደቀበት የማያውቀው እዳ...።
ሞት እያንዣበበ... ደክሞት ካረፈበት ከደሳሳ ቤቱ፣
ለማይሞላ ኑሮው ለማይነጋው ሌቱ።
ዛች ጥርስ እያፋጨ፣
ጥይት እያፏጨ።
ካራ እየተሳለ፣
ቀስት እየተሾለ...
አለ!
ከተፈጥሮ ታግላ፣
ጎታች ባህል ጥላ፣
ልትማር የተጋች ቀን ይወጣል ብላ።
መድረሻ ተነፍጋ መንገድ ላይ የቀረች
እህቴ.... የታለች?
አሞኛል!
ሰው ተገድሎብኛል!
ሰው ተሳዶብኛል! ተፈናቅሎብኛል! ከኖርበት ቀዬ፣
የአቅሜን እጮሃለሁ ...
"የሰላም፣ ፍትህ፣ የህግ ያለህ!" ... ብዬ።
"የኔ አቅም ለቅሶ ነው ድምፅ ልሁናቸው ልጩህላቸው" ስል
ይመጣል ሳይፈራ አሳ'ቆ ሊያፍነኝ ቃላቱን የሚስል
"ምንድነሽ?" ይለኛል "ለእገሌ ለእንትና" ጉዳቴ ሳይገደው
"የሟች ወገኑ ነኝ!" ንፁህ ሆኖ ሳለ ለሞት 'ሚማገደው።
"የት ነበርሽ?" ይለኛል
"ለምን ዛሬ?" ይለኛል... ይሳለቅብኛል ድምፄን እየለካ
ስጮህም ዝምም ስል ለ'ሱ ፖለቲካ
"መርጠሽ ነው" ይለኛል...
መርጦ ገዳይ ካለ በየአደባባዩ፣
መርጬስ ባለቅስ ማን ይሆን ከልካዩ?
መርጬ አለቅሳለሁ ለተገፋው ህዝቤ ለሞተው ወገኔ
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
ፈቃጅ አልፈልግም ለራሴ ስብራት ሀዘን አስተማሪ
አስታዋሽ አልሻም ላጣሁት ወገኔ የ'ጩሂለት' ጥሪ
በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ
ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ
"የማን ነሽ? ምንድነሽ? ከየት ነሽ?" ይለኛል ከየትስ ብመጣ?
ገድዬ አልፎከርኩኝ ሞቶብኝ ነው እንጂ አቅሌን የማጣ
ገዳይ ንፁህ ፈጅቶ በኮራበት ሀገር
ለተገፋ ማልቀስ ለምነው 'ሚያስወግር?
ገድሎም አይበቃውም "እሰይ" ብሎ አይረካ
እንባዬን አድርቆ ሀዘኔን መቀማት አዲስ ፖለቲካ
እጮህለታለሁ...
ንፁሁ ሲጎዳ ባልመረጠው ደሙ ባልመረጠው መልኩ
ክርስቲያንም ሙስሊም ጥፋት ከሆነበት በምርጫ ማምለኩ
ለአማራ እጮሃለሁ በጅምላ ለሚያልቀው ለሚፈሰው ደሙ
ለትግራይ እጮሃለሁ ጦርነት ሲጎሰም በልቶት ሰቀቀኑ፣
ስደት ለመረጠው ከገዛ ሀገሩ፣ ከገዛ ወገኑ።
ለተደፈረችው፣ ለተሰበረችው እንግልት እህቴ፣
ላዘነች እናቴ
ለኦሮሞ ወንድሜ፣ ለደቡብ አባቴ፣ ለሀረሪ፣ ሱማሌ፣
ቤኑሻንጉል፣ አፋር፣ ድሬደዋ ላለው ወይ አዲስ አበቤ።
ለተበዳይ ህዝቤ፣ ለሞተ ወገኔ...
እጮህለታለሁ!
ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ።
ትናንት ጮኼያለሁ፣ እጮሃለሁ ዛሬ፣ እጮሃለሁ ነገ
ሁሉም ወገኔ ነው ድምፅ የተነፈገ።
እጮህለታለሁ! ... እጮሃለሁ!

©በአርቲስት ሜሮን ጌትነት
=ጥር 2013 ዓ.ም
@wisdomic

@poemers
"አንዴ ነው " ይሉኛል ፣ "በፍቅር መጎዳት"
"አንዴ ነው" ይሉኛል ፣ "ባመኑት መከዳት።"
እኔ ግን አላምንም!
ካለፈ ህይወቴ ፣ አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ ፣ ብዙጊዜ አፍቅሬ፡፡
።።።
በፍቅር መንገድ ላይ ፣ ተክዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ ፣ ጠባሳ ልብ ይዤ
አንቺ ጋራ ስደርስ...
ልብሽና ልቤ ፣ እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር...
ወደ ነፍሴ ምድር ፣ ጥያቄ ዘነበ፡፡
።።፣
ቆይ ስንቴ ነው መውደድ ፣ ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ፣ ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም ፣ ሲመጡ መመረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
እርሜ ነው እያሉ ፣ በመሃላ መታረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻላ ፣ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ ፣ ስንቴ ነው መገፍተር?
።።።
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ ፣ በአብሮነት መቀጣት?
ለካንስ ለካንስ
ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው ፣ መሄድና መምጣት!
አቦ ወግጅልኝ!
መልስ ነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ ፣ ተራ መልስ ማጣት!!
@poemers
@poemers
❤️❤️❤️❤️
@poemers
@poemers
❤️❤️❤️❤️
@poemers
@poemers
@አታውቂም
በ-ኤልያስ ሽታሁን

"""አታቂም"""

አንጀት አርስ ግጥም
Join guys
@poemers @poemers
@poemers
Track 3
Dawit Melese
ዳዊት መለሰ

"""ቁንጅና"""

መጠሪያ አልተገኘም
የሚሆንሽ ላንቺ ሚስማማ
ቁንጅና ራሱ ነሽ
ውበት ነብስ ሂወትም ዘርቶ

አልተፈጠረም ሰው
የለሽም ሀምሳያ የቁንጅና ጣሪያ
የውበት ማሳያ
በሰፈር መንደሩ የሚያማምር ሞልቶ
ውበትሽ እንዳርማ የሚታየው ጎልቶ...

ያድምጡት ይወዱታል።
Join
@poemers @poemers
🤍😘የኔ ውድ አውቃለሁ ፤ ዝምታሽ ቋንቋ ነው
አይንሽ ሲርገበገብ ፤ ለእኔ መልክት አለው
ከንፈርሽ ሲረጥብ ፤ ልቤ ትቀልጣለች
ጉንጮችሽ ሲቀሉ ፤ ነፍሴ ትበራለች
ግን ቢሆንም ውዴ ፤ እጠራጠራለሁ
አታፈቅረኝ ይሆን...? ብዬ ተክዛለሁ
ዝምታሽ ሲበዛ ፤ ውስጡ ነገር አለው
እንደዛ እያሰብኩ ፤ እብሰለሰላለው
ያንን ለማካካስ ፤ አፈቅርሻለው እያልኩ እለፈልፋለሁ
እውነቱን ንገሪኝ ፤ እባክሽ ተንፍሺ እጎዳብሻለሁ፡፡😍😘💋

@shali6 @shali6
@poemers @poemers
‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
ግጥም-በእኛ 💌 pinned «🤍😘የኔ ውድ አውቃለሁ ፤ ዝምታሽ ቋንቋ ነው አይንሽ ሲርገበገብ ፤ ለእኔ መልክት አለው ከንፈርሽ ሲረጥብ ፤ ልቤ ትቀልጣለች ጉንጮችሽ ሲቀሉ ፤ ነፍሴ ትበራለች ግን ቢሆንም ውዴ ፤ እጠራጠራለሁ አታፈቅረኝ ይሆን...? ብዬ ተክዛለሁ ዝምታሽ ሲበዛ ፤ ውስጡ ነገር አለው እንደዛ እያሰብኩ ፤ እብሰለሰላለው ያንን ለማካካስ ፤ አፈቅርሻለው እያልኩ እለፈልፋለሁ እውነቱን ንገሪኝ ፤ እባክሽ ተንፍሺ እጎዳብሻለሁ፡፡😍😘💋»
#አይ_ገጣሚ_ሞኙ
:
:
የገጣሚው ግጥም ሀረጉ ስንኙ
ዘንድሮስ ያስብላል አይ ገጣሚ ሞኙ።
:
:
የዋህን እና ሞኝን ባንድ ላይ ሚያዋዛ
የዋህ የዋህ ሚሸት
ሞኝ ሞኝ የሚሸት
ዛሬስ ግጥም በዛ።
:
:
ተቀጥራ ምትቀር ሴት
ባትመጪም ቅጠሪኝ
ደግሞም የኔ ፍቅር
አትመጪም አውቃለው
ቢሆንም ሳልታክት እጠብቅሻለው።
እያለ ገጠመ እያለ ተቃኘ
አይ ገጣሚ ምስኪን እጅጉን ተሞኘ።
:
:
ማይመጣ ሰው መቅጠር
የሚቀር ሰው መቅጠር
እንደው ምን ይባላል ከሞኝነት በቀር።
:
:
ኮከብ ነው እንትንሽ
ፀሀይ ነው እንትንሽ
ያ እንትንሽ ደግሞ ጨረቃን ያስንቃል
ዘንድሮው ገጣሚው
መሬት እየኖረ
መሬትን እረስቶ ሰማይን ያደንቃል።
:
:
ለተሸከመችው እትብቱ ላለበት ግጥም ካልነቀሰ
ያጠገቡን ትቶ ውበትን ፍለጋ ሰማይ ከጠቀሰ
ሰማይ ካንዣበበ ሰማይ ካንጋጠጠ
ብልሀት ኮስሶ ሞኝነት በለጠ።
:
:
በየግጥሞቹ ቃል እያረቀቀ
በየስንኞቹ ሴት እያደነቀ
ውይ እንትኗ ሲያምር ውይ እንትኗ እያለ
ባንባቢ ምናብ ውስጥ ቁንጅና እየሳለ
ውይ እንትኗስ ይባስ ውይ እንትኗ ደግሞ
ሰውነቷን ሙሉ ባድናቆት ቃል ስሞ
ወረቀት ብዕሩን ብዙ ጊዜ አናድፏል
እራሱን የሚያደንቅ አንድ ግጥም እንኳን ለራሱ ሳይገጥም እየው ዛሬም አልፏል።
:
:
ገጣሚው በሞላ ከራስ በላይ ንፋስ መሆኑን ከረሳ
በስንኝ ቋጠሮ በየግጥሞቹ ሌላ ሰው ካወሳ
ከሞኝነት ውጪ ምን ይባላል እሳ።
:
:
ያለማንም ግፊያ ያለማንም ሽሚያ ሊያፈቅራት አስቦ
ዘንድሮ ገጣሚው ያለ የሌለውን ክፉ ቃል ሰብስቦ
የሚያፈቅራትን ልጅ በርግማን አጥቧትል
ቁንጅናዋን ነስቶ አስቀያሚ እንድትሆን ስለት አስገብቷል።
:
:
የሚያፈቅሯትን ሴት የሚወዷትን ሴት ክፉዋን መመኘት
ከዚህ የተሻለ አይገኝም ሞኝነት።
:
:
ዘንድሮ ...
እንዲ ነው ገጣሚው
እንዲ ነው ስንኙ
አይ ገጣሚ ምስኪን
አይ ገጣሚ ሞኙ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb
@getem
@poemers @poemers
@poemers
🎶🔊Teddy afro

"""በዚ ጨረቃ"""

Join👇👇👇👇👇
@poemers @poemers
ርዕስ በ ባዶ---
-----------
የግጥም ትርጉሙ
የግጥም ህግጋት
እንዲሁ ተረስቶ
ቤት የመታ ሁሉ
ከመሬት ተነስቶ፡
ገጣሚ ነኝ ካለ
ቤት ሁሉ ፈረሰ
ጥበብ ኮበለለ
ምን ይላል ጸጋየ
ቢኖር በ ህይዎት
ይመርጥ ነበር በ እርግጠኝነት
ይህን ግጥም ከማይ
ከ አንድም አስር ሞት።
ይልቅ አንድ ምክር
ለጥበብ አፍላዎች
የግጥም ቤት እንደው
ዝም ብሎ አይመታም
ያለ ሙያ ገብቶ
ሙያየ አይባልም
ይልቅ
ቢያቅታችሁ እንኳን
የግጥም ቤት መምታት
ሃገሬ ሃብታም ናት
የ ግንብ እንኳን ባይሆን
ቆርቆሮ ቤት አላት
እና
ቤት መምታት ሲያምራችሁ
ብዙ አትጠበቡ
ቤት እንደው ለጉድ ነው
ወታቹ ደብድቡ😂
የግጥም ወጉ
እንዲህ አልነበረም
ምጣኔው ተሳክቶ
ቀለሙ ተለክቶ
ስንኙ ተነክሮ
ምቱ ተሰድሮ
ለ አዕምሮ በሚጥም
ለ ነፍስ በሚያረካ
ከ ውስጠተ ውስጠት
ልብን የሚነካ
ብቻ ነበር ሆኖ
እንዲሁ ቀረ እንጅ
የኔም ግጥም ጀዝባ
ለምንም አይበጅ።😜

Join this channel 👇👇@poemers @poemers
ግጥም-በእኛ 💌 pinned «ርዕስ በ ባዶ--- ----------- የግጥም ትርጉሙ የግጥም ህግጋት እንዲሁ ተረስቶ ቤት የመታ ሁሉ ከመሬት ተነስቶ፡ ገጣሚ ነኝ ካለ ቤት ሁሉ ፈረሰ ጥበብ ኮበለለ ምን ይላል ጸጋየ ቢኖር በ ህይዎት ይመርጥ ነበር በ እርግጠኝነት ይህን ግጥም ከማይ ከ አንድም አስር ሞት። ይልቅ አንድ ምክር ለጥበብ አፍላዎች የግጥም ቤት እንደው ዝም ብሎ አይመታም ያለ ሙያ ገብቶ ሙያየ አይባልም ይልቅ ቢያቅታችሁ…»
2024/10/01 21:51:13
Back to Top
HTML Embed Code: