Telegram Web Link
[  † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]

1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
3.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
4.አቡነ ስነ ኢየሱስ
5.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

" አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው::የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው::" [መዝ.፳፥፩-፭] (20:1-5)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


 #ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
በዛሬው ዕለት ታስበው እና ተከብረው ከሚውሉ ቅዱሳን አባቶች መካከል ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር አንዱ ነው

የዚህ ቅዱስ አባት ረድኤት በረከት ይደርብን አሜን🙏

መልካም ቀን


#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በገዳማውያንና በአብነት ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት ብንናገር የባሰ ችግር ስለሚፈጠር ሰቆቃውን በልባችን ተሸክመን እየኖርን ነው ሲሉ የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኀላፊ ገለጹ፡፡

በ43ኛው አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቀረበው ሪፖርት ባለፉት ሦስት ዓመታት በጦርነት ምክንያት 421 አብያተ ክርስቲያናት መውደማቸው፤ ከ100 በላይ ካህናት እና ገዳማውያን መገደላቸውን እንዲሁም 85 የተዘጉ አብነት ትምህርት ቤቶች ብሎም 25 ለመዘጋት የተቃረቡ ገዳማት እንደሚገኙ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በመሆኑም ገዳማት ባሉበት ሁሉ ችግር አለ የሚሉት በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ኀላፊ መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ዐሥራት ከግድያና ከማፈናቀል በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል የሚታገቱ ካህናትና እነርሱን ለማስለቀቅ የሚከፈለው ገንዘብ በርካታ መሆኑን ገልጸው ይህንን ብንናገር የባሰ ችግር ከማምጣት ውጭ መፍትሔ ስለሌለው ሰቆቃውን ተሸክመን እየኖርን ነው ሲሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

መጋቤ ካህናት ቆሞስ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ዐሥራት በሀገራችን ባለው ጦርነት ገዳማውያን እንዳይጸልዩና ልማት እንዳያለሙ ጦርነቱ ትልቅ ተግዳሮት እንደሆነባቸው ተገልጿል፡፡

በምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ኤልያስ፣ በጣቢት ገዳምና በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም እንዲሁም በሐረር ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው የሚኖሩ መናንያን በግፍ ተገድለዋልም ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

መነኩሴ መስለው ገዳማትንና ገዳማውያንን የሚያውኩና የሚያስገድሉ ግለሰቦችን የማጣራት ሥራም መሠራት ይገባል ብለዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና ማጠናከሪያ ምክትል ኀላፊ ዲ/ን ደረጀ ጋረደው በበኩላቸው በርካታ ገዳማት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችና አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙበት የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ባለው ጦርነትና ድርቅ ሳቢያ ገዳማውያኑና ደቀ መዛሙርት በረሃብ እየተፈተኑ ነው ብለዋል፡፡

ደቀ መዛሙርት ከምእመናንን ቁራሽ እየለመኑ የሚማሩ በመሆኑ አሁን ላይ ማኅበረሰቡ በችግር ላይ መሆኑን ተከትሎ ለደቀ መዛሙርቱ መድረስ አለመቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

ዲ/ን ደረጀ አክለውም ማኅበረ ቅዱሳን ችግሩን መፍታት ባይችልም የትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ ሀ/ስብከቶች ላሉ ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማድረጉን የገለጹ ሲሆን በቀጣይም 6 ሚሊዮን ብር በመበጀት ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ አክለዋል ገልጸዋል፡፡

ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ለገዳማትና ለአብነት ትምህርት ቤቶች የተሰጠው ትኩረት አንሳ መሆኑን ያነሱት ዲ/ን ደረጀ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም በማኅበረ ቅዱሳን ብቻ የሚፈታ ችግር ባለመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል ኀላፊነት ሊወስድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይ የአብነት ትምህርት ቤት ጠፍቷል ማለት ባንችልም ህልውናው በአስጊ ደረጃ ላይ እንደሆነ እያየነው ያለ እውነት ነው ሲሉ ለጣቢያችን አስተያየት የሰጡት ደግሞ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኀላፊ መልአከ ኃይል አባ ለይኩን ግፋወሰን ናቸው፡፡

የካህናትና የአብነት ደቀ መዛሙርት ግድያ እጅጉን የሚያስከፋና የሚያሳዝን ነው ያሉት የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኀላፊ “ይህንን ሁሉ ግፍ እየተመለከቱ ዝምታን የመረጡ ሁሉ እንዴትስ ተቻላቸው?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

መልአከ ኃይል አባ ለይኩን አክለውም ችግሩ በየጊዜው እየተበባሰ፤ ካህናት እየፈለሱ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እየተቋረጠ ስለሆነ በጊዜ መፍትሔ ሊሰጥ ካልቻለ መጨረሻው ከዚህ የከፋ ይሆናል ብለዋል፡፡

ጉባኤ ቤቶች ሲፈርሱ፤ ደቀ መዛሙርት ሲሞቱና ሲፈልሱ የሚያዝንና የተጎዱትን የሚደግፍ ማንነታችንን ተነጥቀናል ያሉት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩንቨርሲቲ የአቋቋምና የዶግማቲክ ቲዎሎጅ መምህር ደግሞ ሊቀ ጠበብት መሠረት ምሕረቱ ናቸው፡፡

አባቶቻችን ስለልጆቻቸው ሞትና ስደት በድፍረት የመንግሥት አካላትን ቀርቦ በማነጋገር መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ ማፈላለግ ይገባቸዋል ሲሉም ሊቀ ጠበብት መሠረት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ ለልጅሽ
አሳስቢ እዘክሪ ለሀጣን ሀኮ ለፃድቃን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በኦሮሚያ ክልል ያለችው ቤተ ክርስቲያን አሁንም በትልቅ ፈተና ውስጥ በመሆኗ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ ተገለጸ !

ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ቅዳሴና ሌሎች አገልግሎቶችን በራስ ልክ በመተርጎም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ባላገናዘበ መንገድ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ላለው እንቅስቃሴ መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ መምህራንና በተለያዩ አህጉረ ስብከቶች ያሉ አገልጋዮች ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

በ2014 ዓ.ም የተከሠተው ሕገ ወጥ ሹመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፍትሔ ያገኘ ቢመስልም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ያልተከተሉ እንቅስቃሴዎች መበራከታቸውን በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አገልጋዮች ተናግረዋል፡፡

በተለይ ከዜማ አገልገሎት ጋር ተያይዞ በግእዝ ቋንቋ የሚሰጠውን የቅዳሴ አገልገሎት ምንም ጥናት ባልተደረገበትና ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ ባልሰጠችበት ሁኔታ በኦሮምኛ እንቀድሳለን በማለት አግልገሎቱ ሥርዓት አልባ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ቋንቋን ምክንያት በማድረግ እየተስተዋለ ያለው የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ሥርዓት የማፍረስ እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ የመጣ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ የተሠራ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ተልእኮ ነው ያሉት ደግሞ የሥነ ልቡና አማካሪው ዲ/ን ዐቢይ ጌታሁን ናቸው፡፡

ዲ/ን ዐቢይ አክለውም የቋንቋ አገልገሎት ተደራሽነትን ከሚገባው በላይ እያራገቡ ያሉት የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና የምእመናን ጉዳይ አሳስቧቸው ሳይሆን በብሔር ፖለቲካ ተጠልፈው እንደሆነ የምንረዳው ነገር ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በቋንቋችን የሚያገለግለን አባት ይሾምልን ያሉ አካላት አባቶች ከተመደቡላቸው በኋላ አንቀበልም፤ የተሾሙት አባቶች ደግሞ ቦታ ቀይሩልን ማለታቸውን ያነሱት የሥነ ልቡና አማካሪ እየተነሳ ያለውን ጥያቄ እንዳለ ከመመለስ ባሻገር የጥያቄው አግባብነት ባያጠራጥርም በደንብ ጥናት ተደርጎ ወደ ተግባር ካልተገባ ቤተ ክርስቲያንን ለበለጠ ችግር ይዳርጋታል ብለዋል፡፡

ሰባኬ ወንጌል ዲ/ን ኢንጅነር እስጢፋኖስ ተስፋዬ በበኩላቸው የቋንቋ አገልገሎትን ለማስፋት በሚል ችግሩን ሲያራግቡ የነበሩትን አብረን እንፍታው ብለን ስንጠይቃቸው የሰጡን ግብረ መልስ የምእመናን ጉዳይ አሳስቧቸው እንዳልሆነ አሳይቶናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያን፣ መንፈሳዊ ማኅበራትና መምህራነ ወንጌል ዘመኑን በዋጀ መንገድ ኦርቶዶክሳውያንን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው እንዲያውቁ የማድረግ ኀላፊነትን መውሰድ ይኖርባቸዋል ሲሉ ዲ/ን ኢንጅነር እስጢፋኖስ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
☞ ጥቅምት 21 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወርሐዊ መታሰቢያዋ
ሲሆን ወርሐ ፅጌ ላይ ነን እና ስደቷን እናስባለን፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ የፊትሽን መልክ የያ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ
በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀን ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ምን ያህል ደስ ታስኚ
ኖሯል፡፡ በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና በሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን
ነው፡፡
☞ማርያም ሆይ የምስጋናሽ ፍሬ እጥፍ ድርብ እሰከሆነ ድረስ በፍቅርሽ ተክል
ቦታ ትርፍርፍ ያለ ጣዕም ልዮ ልዮ የሆነ የታምር አበባን አብቦ ተገኘ፡፡ ሽታ ያለው
መዓዛም ሰጠ፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ ወደ ተራራዎች ብወጣ ወደ ብርሃ ብወርድ እንቺ
የሚመስል አበባ ፈጽሞ አጣሁ፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ ክብርሽ ከአበባዎች እና ከዕንቁዎች መልክ ይበልጣል፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ እንደ ልብሽና እንደ አፍንጫሽ እንደአፍሽ መዓዛ
በገነትና በበረሃ ካሉት አበባዎች እንዲያዛ የሚሆን የለም፡፡
☞እመቤቴ ማርያም ሆይ የገነት ዛፍ አበቦችን ለሽማት እንደምታብብ የታምርሽ
ዜና ለልጅ ልጅ የምነግር እሆን ዘንድ የሥዕልሽን ወዝ ቀቢኝ፡፡
☞አበባዎችን ያይ ዘንድ በወደደ ጊዜ ወደ ተክል ቦታ የወረደ፡ሙሽራ
እንዲሚያስደስት ተክል ቦታ የወረደ ሙሽራ እንደሚሰት ድንግል ሆይ ከዚህ ይልቅ
በታምርሽ ፈጽሞ እደሰታለሁ ከኃጥአን ልይ ከባድ ኃዘን ሸክምን የሚያቀል ደስታን
የያዘ ጌታ ከእቺ ተወልዷልና፡፡
☞እንሆ በኤፍራታ የሰማሁት የልደትሽ ዜና አበባን በመንታዎች ዛፍ የመሰሉ
በኢያቄብ እና በሐና ላይ አገኙት ማርያም ሆይ ወደ አናትሽ ቤት አስገቢኝ ችግርን
እንዳላይ በሁለቱ ጡቶችሽ ወተት አጠጪኝ፡፡
☞በጥላሽ ሥር የሚያርፋ ፍሬሽ ተመግበው
☞በደሙ በሕይወት የሚኖሩ እርግቦች(ምእመናን) ቡርካን ናቸው፡፡
☞የመስቀል ምልክት አምሳል ያላት የሽቱ ዛፍ ማርያም ሆይ
☞አበባው አበባሽ ፍሬውም ፍሬሽ ነውና
☞ለሁለታችሁም (ላንቺና ለልጅሽ) ስግደት ይገባል፡፡
☞እንሆ የኅዘን ክረምት ካለየ አለፈ የምስጋናሽ አበባ ደስታም በልቤ ውስጥ
ሞላ ድንግል ሆይ ከሥዕልሽ ወዝ እንደምታፈሺ በጼዴንያ በተአምርሽ ተጽፎ
እንደሰማሁት በኢትዮጵያ ተትረፍርፎ አየሁ፡፡
☞አንድ ከሀዲ ሰው የልጅሽን ቁርባን በተፋበት ቦታ ሥዕልሽ ሕፃን ታቅፋ
በግልጥ ታየች
☞ዳግመኛም ከደሙ ጋር የቁርባን ኅብስት ሆነች
☞ይህን ድንቅ ሥራሽንም ያዩና የሰሙ ማርያም ሆይ ለተአምርሽ ምስጋና
አቀረቡ፡፡
☞የልጅሽ ተአምር አበባ ዐይኔን ያስደስታታል፤ ከእሱም ይልቅ ግርማን
የተላበሰች የሥዕልሽ ወዝ በእጅጉ ያስደስታል፡፡
☞የትንቢት ተክል ቦታ የአበባና የፍሬ ዘመን ማርያም ሆይ እስራኤል በጥዑም
ዜማ ያመሰግኑሽ ዘንድ ከበለስና ከወይናቸው ስር ከድካም አረፋ፡፡
☞አበባ ባለው የበዓል ልብስ አጊጣ፤ የአበባ ምንጣፍ እያነጠፈች ፤የቀጋ
አበባም እየነሰነሰች የልጅ ወንድሜ የዕጣን ቋጠሮ የእኔ ነው ብላ በጉ
ተአምርሽን ባመሰገነችበት ቦታ፤ማርያም ሆይ ነፍሴ ለሥዕልሽ ክብር
ትሰግዳለች፡፡
☞በወዝ የተዋበች ሥዕልሽ በዓለም እንደዚህ ካማረች
☞ማርያም ሆይ የፊትሽ ደም ግባትማ በሰማይ እንደምን ያምር
☞ዝናብ ያጠፋው ዘንድ የማይችል የፍቅርሽ እሳት ፍሕም አቃጥሎኛልና፤
የተአምርሽን ደስታ አይቼ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጭልኝ፡፡(ማኅሌተ ጽጌ)
☞ከሀገር ሀገር ይዘሽ ስለተሰድሽው ልጅሽ ብለሽ ኢትያጵያን እና ህዝቦቿን
አደራ፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞20-2-2017

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
#ጥቅምት_21 በዚህች ቀን 'ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ' ብሎ ለእመቤታችንን ትንቢት የተናገረላት የነቢይ ኢዩኤል የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው

« ማዕረረ ትንቢት ማርያም ዘመነ ጽጌ እንግዳ
ወዘመነ ፍሬ ጽጋብ ዘዓመተ ረኃብ ፍዳ
ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ
ያንጸፈጽፍ እምአድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ
ፀቃውዓ መዓር ጥዑም ወሃሊብ ፀዓዳ» [ ማኅሌተ ጽጌ ]

ትርጉም

«በመከር ጊዜ አበባ በአበባ ጊዜ ደግሞ መከር አዝመራ ማጨድና መሰብሰብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጊዜያቸው የተለያየ ስለሆነ፡፡ ለምሳሌ በመስከረም ወር የአበባ ጊዜ በመሆኑ አዝመራ መሰብሰብ የለም፡፡»

«የትንቢት መከር መካተቻ የሆንሽ. እንደ ዘመነ ጽጌ የረሃብን ዘመን ያስወገድሽ ማርያም ሆይ የኤልዳ ነቢዩ ኢዩኤል /ከይሁዳ ተራሮች ጣፋጭ ማርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ብሎ/ የተናገረው ትንቢት በአንቺ ታወቀ፤ ተፈጸመ፡፡»
እመቤታችን ነቢያት የተናገሩት የትንቢት ዘር ተፈጸመባት፡፡ ማለትም ነቢያት የአምላክን ሰው የመሆን ነገር በተለያየ ሁኔታ ተናግረዋል፡፡ ጌታችን ነቢያት የተናገሩት ትንቢት መፈጸሙንና ይህንን ፍጻሜ ለማየት የታደሉት ሐዋርያት መሆናቸውን «አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል እውነት ሆኖአል፡፡ እኔም እናንተ ያልደከማችሁበትን ታጭዱ ዘንድ ሰደድኳችሁ፡፡ ሌሎች ደከሙ እናንተም በድካማቸው ገባችሁ» በማለት ተናግሮአል፡፡/ዮሐ.4፡37/፡፡ ይህም ነቢያት የዘሩት ትንቢት በሐዋርያት ዘመን ለአጨዳ /ለፍሬ/ መድረሱን መናገሩ ነው፡፡ ስለሆነም «ማዕረረ ትንቢት፤ የትንቢት መካተቻ» ማርያም አላት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ፍሬ ክርስቶስን ያስገኘችና «ከእሴይ ስር በትር ትወጣለች» እየተባለ የተነገረላት በመሆንዋ በአበባ ትመሰላለች፡፡

ስለዚህ እመቤታችን በመከር ወራት የምትገኝ አበባ ናት፡፡ በመከር ጊዜ የአበባ መገኘት ያልተለመደ ስለሆነ «ወዘመነ ጽጌ እንግዳ፤ እንግዳ የሆነ አበባ» አላት፡፡

ከዚህ በኋላ
«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ነቢየ ኤልዳ፣
ያንጸፍጽፍ እም አድባሪሁ ወእም አውግሪሁ ለይሁዳ፣
ፀቃውዓ መዐር ጥዑም ወሀሊብ ፀዓዳ. . .» በማለት ነቢዩ ኢዩኤል የተናገረውን ትንቢት አፈጻጸም ይናገራል፡፡

ነቢዩ ኢዩኤል በዘመኑ ጽኑ ረኀብ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን በምሕረት እንደሚጎበኛቸውና ረሀቡ እንደሚጠፋ ይነግራቸው ነበር፡፡ «ብዙ መብል ትበላላችሁ.ትጠግቡማላችሁ ከዚህ በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ ተራሮች በተሃ ጠጅ ያንጠበጥባሉ.ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ.በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጎርፋሉ » /ኢዩ.3.18፤ 2.26/፡፡

«ብኪ ተአምረ ዘይቤ ኢዩኤል ነቢየ ኤልዳ፤ያንጸፍጽፍ እምአድባሪሁ ወእምእግሪሁ ለይሁዳ ፀቃውዐ መዓር ወሀሊብ ፀዓዳ»፡፡ ይህም ማለት ነቢዩ ኢዩኤል ከይሁዳ ተራሮችና ኮረብቶች ጣፋጭ ሣርና ፀዓዳ ወተት ይፈሳል ይመነጫል ያለው በአንቺ ተፈጸመ ማለት ነው፡፡ ይህም እመቤታችን ክርስቶስን በወለደች ዕለት መሪሩ ጣፍጦ፣ ይቡሱ ለምልሞ ተገኝቷል፡፡ ይህ ለጊዜው ሲሆን ፍጻሜው ደግሞ ከእርሷ በነሣው ሥጋና ደም ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ፣ ከልጅነት ተራቁቶ፣ በረሀበ ነፍስና በጽምዓ ነፍስ ተይዞ የነበረውን የሰው ልጅ ከጎኑ ውኃን ለጥምቀት፤ ሥጋውንና ደሙን ምግበ ነፍስ አድርጎ የአምስት ሺህ አምስት መቶውን ዘመነ ረሀብ እንዳስወገደልን ያስረዳል፡፡

ድንግል ሆይ፤ ክብር የክብር ክብር ካለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ስርጉት በቅድስና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
እንኳን መላእኩ ለቅዱስ ኡራኤል ወርሀዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ✙ አደረሰን የመላእኩ አማላጅነት አይለየን ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
ይእቲ : ተአቢ : እምአድባራት : ወደብር : ርእሰ : አድባራት : እንጦጦ : መንበረ : ፀሐይ : ቅድስት ማርያም : ቤተ : ክርስትያን : ዘሐነፅዋ : ዳግማዊ ምኒሊክ : ወእቴጌ : ጣይቱ : ብርሃን ዘኢትዮጵያ ::

"፲ ፰ ፻ ፸ : ታነፀች።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
2024/11/18 15:25:39
Back to Top
HTML Embed Code: