የዛሬ 4ኛ ሳምንት ማሕሌተ ጽጌ ቀለማት
ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ/ም
👉 የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ/ም
👉 የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🖤ሰቆቋወ ድንግል 🖤
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ ምስካዮሙ ለግፉዓን፤እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤ ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤ወልደ አብ ፍቁር ዘበኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን።
❤️ የተሰደደው ኢየሱስ ለተሰደዱት ተስፋቸው ነው
የተገፋው ኢየሱስ ለተገፉት መጠጊያቸው ነው
እግዚአብሔር እንደ ምስኪኖች ማደሪያ ሌለው ሆነ
ኢየሱስ ህፃን ሳላ እንግዳና ስደተኛ ነበረ
በሰው ዘንድ የተናቀው ተወዳጁ የአብ ልጅ
የእናቱ ሐዘን የለቅሶ ምስጋና ሆነለኝ ❤️
4ኛ ሳምንት ማሕሌተ ጽጌ

በኮሪደሪ ልማቱ
1- ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
2- መንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን
3- ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን
4- እንጦጦ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
5- እንጦጦ ማርያም ቤተክርስቲያን
6- ደብረ ኤልያስ እና ራጉኤል ቤተክርስቲያን
ከለገሃር እስከ እንጦጦ አዲሱ መናፈሻ ድረስ ለሚሰራውና የኮሪደርልማት በሚባለው ፕሮጀክት የአብያተ ክርስቲያናት ግቢ ከግማሽ በላይ እንደሚፈርስ ነው የተነገረው።
በተለይም ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለምና ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያኖች ካላቸው ጠበባ ቦታ ላይ ተቀንሶና ግቢያቸው ፈርሶ ነው ለአበባ መትከያና ለሳይክል መንጃ ይደረጋል የተባለው። ምስካየ ኅዙናን በመጀመርያም ጊቢው ጠባብ በመሆኑ ከዚሁ ላይ ደግሞ ፈርሶ እንዲቀነስ ተወሰዱ ኖበታል።
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ግቢ አጥሩ ብቻ ሳይሆን ቤተልሄሙና የአስተዳደር ቢሮዎችም ሊነሱ እንደሚችሉ ነው የተነገረው። አብያተክርስቲያናት አባቶቻችን አክብረውና አስከብረው ያቆዩትን ይዞታ በማን አለብኝነት ሲነጠቅ ዝም ብለው የሚያዩ የቤተክርስቲያኒቱ ሰዎች ወደ ፊት ተወቃሽ ናቸው።
በርካታ ምዕመናን ከአካባቢያቸው ተነስተው አብያተክርስቲያናቱ ብቻቸውን እየቀሩ መሆኑም በግልፅ አየታየ ያለ ችግር ቢሆንም የቤተክርስቲያኒቱ ሰዎች በሙስና ተጨማልቀው እርስ በርሳቸው ውዝግብ ላይ በመሆናቸው የምዕመናን መፍለስና የቤተክርስቲያን ይዞታ መዘረፍ አያሳስባቸውም።
ከመተግበሩ በፊት የቤተክርስትያንን ይዞታ ማስከበር ይታሰብበት ።

⭕ ቅዱስ እስጢፋኖስ 🌷
================
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስትያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕት አንዱ ነው ... ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ እየወገሩት "እንደ ሀጢአት አትቁጠርባቸው" እያለ ለክፉ ወጋሪ ደብዳቢዎቹ ምህረትን የለመነ ሰማእት ነው: :
የዲያቆናት አለቃ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሁሌም ለሐዋርያት ይታዘዝና ያገለግላቸው የነበረ ሲሆን ብዙዎችን ወደ ሀይማኖት የመለሰ ወንጌላዊ ሰማእት ነው : :
ዛሬ የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ነው : : የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ረድኤት በረከቱ አይለየን 🙏
ጥቅምት 17
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
================
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከሰባቱ ዲያቆናት መካከል በቅድስና ሕይወቱ ለክርስትያኖች ዓብነት የሆነው ሰማዕት አንዱ ነው ... ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ እየወገሩት "እንደ ሀጢአት አትቁጠርባቸው" እያለ ለክፉ ወጋሪ ደብዳቢዎቹ ምህረትን የለመነ ሰማእት ነው: :
የዲያቆናት አለቃ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሁሌም ለሐዋርያት ይታዘዝና ያገለግላቸው የነበረ ሲሆን ብዙዎችን ወደ ሀይማኖት የመለሰ ወንጌላዊ ሰማእት ነው : :
ዛሬ የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ክብረ በዓል ነው : : የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት ሀገራችን ሰላም ያድርግልን ረድኤት በረከቱ አይለየን 🙏
ጥቅምት 17
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
መልካም መልዕክት ነው አባታችን
"👉 ፈገግ ያልኩት ለሽልማቱ አይደለም። #ቁሰኛ_አይደለሁምና።
የመቅደሱ አባዎራዎች ክፋትና ክዳት ባየለበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቸርነቱ እና የምእመናን የልቡና ንጽሕና ስመለከት ልቡናዬ ሐሴት ተሰማኝ።
ጽኑዕ ድካማችንን እያወቁ ምእመናን አሁንም ይወዱናል።
#እንከሰ_ንትመየጥ_ኀበ_ክርስቶስ ለማለት ነው።
“ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዓይኖቼ በምድር #ምእመናን ላይ ናቸው፤ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል” መዝ 101፥6
ጥቅምት 17/02/2017 ዓ/ም

🕊 † 🕊
[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ ❝ ሕማም ለመለኮት ተነገረለት ! ❞ ]
🕊
❝ የድኅነታችን አለኝታ በዕሩቅ ብእሲ የተደረገ አይደለም ፤ ከአዳም ጀምሮ አምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ሰው ሊያድነን አልቻለም ፤ ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃል አዳነን እንጂ ፤ ማመናችን በዕሩቅ ብእሲ ሆኖ ርጉማን እንዳንሆን ማመናችን በማያልፍ በእግዚአብሔር ነው እንጂ።
ከሰው ወገን የሚሾም ሰው ሁሉ ስለ ሰው ሊቀ ካህናትነት ይሾማል ፤ እንደተጻፈ ስለዚህ ጌታ ከእኛ ሥጋን ተዋሐደ ፤ አምላክ በመሆኑ ድኅነትን ይሰጠን ዘንድ ፥ ሰውም በመሆኑ ስለእኛ እንደ ሰው ሁሉ ተላልፎ ይሞትልን ዘንድ እግዚአብሔር ቃል ሰው ሆነ። [ዕብ.፭፥፩-፯]
በሕማሙ ሕማምን አጠፋ ፤ በሞቱም ሞትን አጠፋው ፤ ሕማም ለመለኮት ተነገረለት ፤ የማይታመም የእግዚአብሔር ቃል ፈቃዱ ታሞ ሞቶ ማዳን ነውና ፥ ደም የተረጨ ልብስን የለበሰ ሰውንም መሰለ ፥ ደም በልብስ እንዲረጭ ደም የለበሰ ሰው መጣ ይባላል እንጂ ያንን ልብስ የለበሰውን የለባሹን አካል እንዳያገኘው ፍጹም ሰው በሆነበት ሥጋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ታመመ ፤ ከሰማይ መጥቶ ሰው በሆነ ጊዜ ለማይታመም ለእግዚአብሔር ቃል ሕማም ገንዘቡ እንደሆነ ተነገረለት ።
ሐዋርያው ጴጥሮስ በመለኮት ሕያው ሲሆን በሥጋ እንደታመመ እንደ ተናገረ ፥ ዳግመኛም ክርስቶስ ስለእኛ በሥጋ መከራ እንደ ተቀበለ ፡ እናንተም እርሱን ምሰሉ እንዳለ። [፩ጴጥ.፫፥፲፰ ና ፲፱ ፣ ፬፥፩]
መለኮት ሕማም ሊነገርለት ወደደ ፥ የዓለም ድኅነት ሕማም በሌለበት በመለኮት ይሆን ዘንድ በሥጋ የመጣ ሕማም ተነገረለት እንጂ መለኮት የታመመ የደከመ አይደለም ፤ የሥጋ ሕማም ተነገረለት እንጂ ቢያውቁስ የክብር ባለቤት እርሱን ባልሰቀሉት ነበር ተብሎ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ። ❞
[ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ]
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።

ይብቃን እንንቃ || በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ @21media27
21 MEDIA ሃያ አንድ ሚዲያ
✝ይብቃን እንንቃ✝
Size:- 53.4MB
Length:-58:08
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Size:- 53.4MB
Length:-58:08
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::
(መልክዐ ገብርኤል)
"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †
(ዳን. ፱፥፳)
#አቤቱ የሆነብንን አስብ
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/
#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!
#ለመቀላቀል
@ortodoxtewahedo
#ለሃሳብ አስተያየት
@ortodoxtewahedoo

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
✞ ጥቅምት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞
† 🕊 ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ንጉሥ 🕊 †
✞ የሰው ልጅ 'ንጉሥ' ተብሎ 'ቅዱስ' መባል ግን ምን ይደንቅ?! ይህ ታላቅ ኢትዮዽያዊ መሪ ንጉሥ ሲሆን: እንደ ደናግል ድንግል: እንደ ባሕታውያን ገዳማዊ: እንደ ቀስውስት ካህን: እንደ ሐዋርያት ሰባኪ ሆኖ መገኘቱ ይደንቃል::
+ የሚያሳዝነው ይህንን እንቁ ንጉሣችን ብዙ ኢትዮዽያውያን መዘንጋታችን ብቻ ነው:: የላስታ አካባቢ እጅግ የታደለችና የተቀደሰች ናት:: እንደ ሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ሁሉ እሷም መካነ ቅዱሳን ናትና::
+ ቅዱስ ይምርሐ የዘር ሐረጉ ከዛግዌ ነገሥታት ሥር ሲሆን አባቱ ግርማ ስዩም ይባላል:: ይኸውም በመጀመሪያው ሺህ ዓመት [Millenium] መጠናቀቂያ ላይ ነግሶ የነበረ ነው:: ዣን ስዩም [የላሊበላ አባት] : ጠጠውድም [ንጉሡ] እና ግርማ ስዩም ወንድማማቾች ናቸው::
+ ቅዱሱ ሲወለድ አባቱ በሕይወት አልነበረም:: እናቱና የወቅቱ አባቶች "ይምርሐነ ክርስቶስ-ክርስቶስ ይምራን" አሉት:: ገና ከሕጻንነቱ መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና ረቡዕና ዓርብ ቀን እስከ ፱ [9] ሰዓት ድረስ የእናቱን ጡት አይቀምስም ነበር:: እናቱ ግን ባለመረዳት ትጨነቅ ነበር::
+ የወቅቱ ንጉሥ ጠጠውድም "ከእኔ ቀጥሎ የሚነግሠውን ባወኩት" እያለ ሲመኝ በሕልሙ "ሕጻኑ ይምርሐ ነው" የሚል በማየቱ ሕጻኑን አስመጣው:: ከደም ግባቱ የተነሳም ቅንዓት አድሮበት አማካሪዎቹን "ምን ላድርገው?" አላቸው::
+ እነርሱም "ብትገድለው እግዚአብሔር በደሙ ይጠይቅሃል:: ግን እንዳይወርስብህ ከፈለክ እረኛ አድርገው" አሉት:: [የዋሃን! ቅዱስ ዳዊት ከእረኝነት መጠራቱን ዘንግተውታል] ከ፯ [7] ቀናት በኋላ ግን መጥተው "ንጉሥ ሆይ! ፈጣሪ ካለ የሚቀር ነገር የለምና በቃ ዝም ብለህ ግደለው" አሉት::
+ በዚያች ሰዓት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ እናቱን "ይምርሐን ስጭኝ" አላት:: እናት ናትና ጨነቃት:: መልአኩ ግን እንደሚጠብቀው ቃል ገብቶላት ከላስታ ነጥቆ ኢየሩሳሌም አደረሰው::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስም ለዓመታት ተምሮ ዲቁናን ተቀበለ:: በኢየሩሳሌም አካባቢም በጾምና በጸሎት ተወስኖ ፈጣሪውን እያገለገለና ወንጌልን እየሰበከ የወጣትነት እድሜውን ገፋ::
+ አንድ ቀን ግን መድኃኒታችን ተገልጦ "ወዳጄ ይምርሐ! ሚስት አግብተሀ: ቅስና ተቀብለህ አገልግለኝ" አለው:: ቅዱሱ ይህንን ሲሰማ አዝኖ "ጌታየ! የእኔስ ፈቃዴ በድንግልና አገለግልህ ዘንድ ነው" አለው:: ጌታችንም "ግዴለህም! ሁሉም አይቀርብህም" ብሎ አንዲት ሕዝባ የምትባል ደግ እሥራኤላዊት ጠቆመው::
+ ቅዱስ ይምርሐም ቅድስት ሕዝባን በተክሊል አግብቶ: ቅስናን ተቀበለ:: ግሩም የሚያሰኘው ግን ፪ [2]ቱ ቅዱሳን ከ፵ [40] ዓመታት በላይ በትዳርም: በድንግልናም መኖራቸው ነው:: "ለሚያምን ሁሉ ይቻላል" ይል የለ ቅዱስ መጽሐፍ!
+ ቅዱሳኑ ወዲያው ለአገልግሎት ወደ ግብጽ ወረዱ:: በዚያ ለጥቂት ዓመታት እንደቆዩ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ወደ ኢትይዽያ መመለስ ፈለገ:: አንድ ቀን ሕዝቡ ተሰብስበው ጸሎተ ኪዳንን ሲመራ "እግዚአብሔር አብ ወሐቤ ብርሃን-ብርሃንን የምትሰጥ እግዚአብሔር አብ" ከሚል ሲደርስ ወደ ሰማይ ጮኸ::
+ ከሰማይም "አቤት ልጄ ሆይ!" የሚል መልስ መጣለት:: ይምርሐም "ምነው ጌታየ በሰው ሃገር ረሳኸኝ?" ቢለው "አልረሳውህም:: ይልቁኑ ሊገድልህ የሚፈልግህ ንጉሥ ሙቷልና ሒደህ ንገሥ" ሲል አዘዘው::
+ ቅዱሱም ሚስቱን ሕዝባን ይዞ ላስታ ሲደርስ ሕዝቡ በዕልልታ ተቀብሎ ወዲያው አነገሠው:: በዚያም ለ፲፭ [15] ዓመታት ቅዱስ ሩፋኤል እየተራዳው: ሕብስትና ጽዋዕ ከሰማይ እየወረደለት ቀድሷል:: ሃገሪቱንም መርቷል::
+ አንድ ቀን ግን ክፉ መካሪዎች "ተጨማሪ ሚስት አግባ" ቢሉት ተቆጣቸው:: በኋላ ደግሞ 'ለምን ተቆጣሁ' ብሎ አዘነ:: ስለዚህም ሃሳቡ ሰማያዊው ስጦታ ቀረበት::
+ እያለቀሰ ጌታን ቢማጸን ጌታችን "ስላሰብከው ክፉ ሃሳብ [ለምን ተቆጣሁ ማለቱ ወደ ምክራቸው ማዘንበሉን ያሳይነበርና] ይቅር ብየሃለሁ:: ነገር ግን እኔ ወደ ማሳይህ ቦታ ካልሔድክ ፪ [2]ኛ አይወርድልህም" አለው::
+ ቅዱሱ ለጊዜው ትንሽ ቢከራከርም "እሺ" ብሎ በቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ዛሬ ወደ ምናውቀው አካባቢው ሔደ:: በዚያም አራዊትን በጸሎቱ አድክሞ: መሠሪዎችን አስተምሮ: ሕዝቡንም አሳምኖ አጠመቃቸው::
+ ጌታም "ከኢየሩሳሌም በደመና እየጫንክ በዚህ ባሕር ላይ ቤቴን ሥራልኝ" አለው:: ቅዱስ ይምርሐም መስከረም ፲፫ [13] ቀን [በበዓለ ባስልዮስ] ጀምሮ ሰኔ ፳ [20] [በበዓለ ሕንጸታ] ፈጸመና ታቦተ ገብርኤልን ሰኔ ፳፩ [21] ቀን ቀደሰው::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ ግን በዚያ ቦታ እየቀደሰ ለ፳፭ [25] ዓመታት ሃገሪቱን አስተዳደረ:: አንድ ጊዜ ቅዱስ ሩፋኤል ለንጉሡ ከሰማይ ሕብስትና ጽዋዕ ሲያወርድለት ፩ [1] ባሕታዊ አይቶ "ለምን?" ብሎ ተቆጣ:: መልአኩ ግን የንጉሡን ክብር ነግሮ "እየዞርክ ስበክ" ብሎታል::
+ በዚያ ባሕታዊ ስብከትም ከመላው ዓለም ብዙ ሺህ ሰወች መጥተው ቅዱስ ይምርሐን "ቀድሰህ አቁርበን?" ብለውለምነውታል:: ቅዱሱም ሲያቆርባቸው በመምሸቱ ጸሐይን አቁሟታል::
+ ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ እንዲህ ባለ ጣዕመ ሕይወት ኑሮ: ለ፵ [40] ዓመታት ሃገራችንን አስተዳድሮ ጥቅምት ፲፱ [19] ቀን ዐርፎ በዚያው ሥፍራ ተቀብሯል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን: ደጅህን የረገጠውን እምርልሃለሁ" ብሎታል::
† 🕊 ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም 🕊 †
✞ በምድረ ግብጽ በዘመነ ጻድቃን የተነሳው ታላቁ አባ ዮሐንስ "ሐዋርያዊ ጻድቅ" ይባላል:: ወላጆቹ ደጋግ: የተወለደው በጾምና ጸሎት: ያደገውም በሥርዓት ነው:: በወጣትነቱ ከቤተሰቦቹ ጠፍቶ: በርሃ ገብቶ የአባ ስምዖን ደቀ መዝሙር ሆኗል::
+ በዚያም በፍጹም ትሕርምት ሲኖር ባልንጀሮቹ ይጠፉበታል:: እነሱን ሊፈልግ ሲሔድ ግን አረማውያን ይዘው አሠሩት: አሰቃዩት:: መንገድ ላይ ውሃ ጠምቷቸው ሲጨነቁ "ውሃ ባጠጣችሁሳ?" አላቸው:: "እንለቅህ ነበር" አሉት::
+ ጸልዮ: ውሃ አፍልቆ ቢያጠጣቸው "አንተማ ታስፈልጋለህና አንለቅህም" አሉት:: ወስደውም ጸይለም በምትባል ሃገር ለባርነት ሸጡት:: በዚያ ሲያሰቃዩት ተአምራትን አድርጐ በክርስቶስ አሳምኗቸዋል::
+ ወደ ጐረቤት ሃገር ሔዶም ዛፍ ሲያመልኩ አገኛቸው:: "ወደ ክርስቶስ ተመለሱ" አላቸው:: "እንቢ" ሲሉት ምሳር [መጥረቢያ] ይዞ: ወደ ዱሩ ውስጥ ገብቶ ጸለየና ምሳሩን አነሳ::
+ "በስመ ሥላሴ እገዝመክሙ" ብሎ ቢቃጣቸው አጋንንት የሠፈሩባቸው ፲ሺህ [10,000] ዛፎች ባንዴ ወደቁ:: በዚህ ምክንያትም ፬ መቶ ሺህ [400,000] ሰዎች አምነው ተጠምቀዋል:: ወደ ሌላ ሃገር ሒዶም ስቃይን ታግሦ: ተአምራትን ሠርቶ ብዙዎችን አሳምኗል:: በቅድስና ኑሮም በዚህች ቀን ዐርፏል::
✞ አምላከ ይምርሐ ደጉን መሪ: አምላከ ዮሐንስ ቸሩን አስተማሪ ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
[ † ጥቅምት ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ [ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ዘጸይለም
፫. አባ ስምኦን ገዳማዊ
፬. ቅዱሳን በርተሎሜዎስና ሚስቱ [ሰማዕታት]
፭. አበው ኤዺስ ቆዾሳት [ሳምሳጢን ያወገዙ]
፮. ጻድቃን እለ መጥራ