Telegram Web Link
​​👼 ቅዳሴ ማለት ምንም ማለት ነው?
🤔 በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
🥰 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?

😇 ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
🧎‍♂ እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
👼 አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?


            ይ🀄️🀄️ሉ ይማሩ
                  👇🏾👇🏾👇🏾

https://www.tg-me.com/addlist/AQPOMxHXz_42NDE0
"ሁላችንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምተን ባለመመለሳችን እስካሁን ድረስ መከራችን እንደቀጠለ ነው።" ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ

ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የሊባኖስ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገረ ስብከት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምህላ፣ የዕርቅ እና የጸሎት አዋጅ አውጀዋል።

ብፁዕነታቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ይቀርባል ።

በመላው ዓለም ለምትኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ

"ቅረቡ ኀቤሁ ወያበርኅ ለክሙ" ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ያበራላችሁማል:: መዝ 33፥5

የምሕላ፣ የዕርቅ እና የጸሎት አዋጅ።

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም በየጊዜው ረኀብ፣ መከራ፣ የሰው ልጅ ዕልቂት ማስተናገድ የተለመደ እየሆነ መጥቷል። በሀገርም ሆነ በመላው ዓለም የሚደርሰው መከራ በሰው አለመታዘዝ ምክንያት ከእግዚአብሔር የተላከ የመቅሠፍት በትር መሆኑን አስተዋይ አእምሮ ያለው ሁሉ የሚገነዘበው ሀቅ ነው።

በመሆኑም እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲጎበኘን በቸርነቱ ይቅር እንዲለን ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር በምህላ፣በዕርቅ፣ በጾም እና በጸሎት መቅረብ ይገባናል።

"ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር" ዘካ 1፥3 "ኅሡ ሰላማ ለሀገር ወጸልዩ በእንቲአሃ ኀበ እግዚአብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ" ኤር 29፥7 ስለ ሀገር ሰላም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ በእርሷ ሰላም ሰላማችሁ ይሆናልና በማለት የሀገር ሰላም የሰው ሁሉ ሀሳብ መሆን እንዳለበትና ሁሉም ስለ ሰላም ወደ ፈጣሪው መቅረብ እንዲገባው ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል።

አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በወንጌል "በስሜ ብትሰባሰቡ በመካከላችሁ እሆናለሁ" ማቴ 18፥20 በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት በፍቅር ልንሰባሰብ ያስፈልጋል። ሰላም በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዕርቅ እንጂ በጦርነትና በእንቢተኝነት አይመጣምና ፍጹም ሰላም ለዓለም እንዲሆን በመላው ዓለም ያላችሁ ሰላምን የምትሹ ሁሉ ስለሀገር፣ ሰለዓለም መጸለይ ይገባናል።

ስለሆነም በመላው ዓለም እና በኢትዮጵያ በየጊዜው በሚከሰተው ረኀብ፣ ጦርነት፣ የሰው ልጅ ዕልቂት ምክንያት ሀገረ ስብከታችን በተደጋጋሚ የምህላ፣ የዕርቅ አዋጅ ሲያወጣ የቆየ ቢሆንም ነገርግን ሁላችንም የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምተን ባለመመለሳችን እስካሁን ድረስ መከራችን እንደቀጠለ ነው።

በሀገረ ስብከታችን እና በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ከእግዚአብሔር ቁጣ ለማምለጥ ከመከራውም ለመዳን ዛሬን እንጂ ነገን በሕይወት ለመኖራችን እርግጠኛ ባልሆንበት የሕይወት ዘመናችን ልዩነትን ትተን አንድነትን፣ ኃጢአትን ትተን ጽድቅን፣ ጦርነትን ትተን ሰላምን በመከተል አምላካችን እንዲታረቀን በቤተክርስቲያን ስም እናሳስባለን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#አምላካችን ሆይ
እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን::

@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#አምላካችን ሆይ
እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን::

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇
@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#አምላካችን ሆይ
እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን::

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇
@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#አምላካችን ሆይ
እንደ ቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን::

ለመቀላቀል

👇👇👇👇👇👇👇
@ortodoxtewahedo
#በውስጥ መስመር ለተጠየቀ ጥያቄ መልስ።

#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ_ለምን _እንላለን ?.......

—————“ #ሚስጢሩ ”—————

በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያይፍታቹ ሲሉ

❖ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና
❖ 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ።

ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ።
             ============
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ።
        =============
አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን
12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው።

🌼ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦

☞ 1ኛ በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል•••

• አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

☞2ኛ የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ።

• ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪

—————“እግዚኦ”————-

አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት / በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ።

ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ።

=====================
መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤

• በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።

—————“ብእንተ”————-

በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ
•  ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና

• በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን
የሚያሳይ ምሥጢር ነው ።

• ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው።
         ==============
“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” - የማት ወን23፣12

•  የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀው ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው።

“ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት”- መዝ 132፡8

ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም አታደርግም።

   http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#አመስግነው

አንድ ስጋ የምትጠብስ ሴት ስጋውን መጥበሻው ላይ ትጥድና ታገላብጠዋለች ። ከዛ መብሰል አለመብሰሉን በሹካ ወጋ ወጋ አድርጋ ታየዋለች ። ከበሰለ ታወርድና ለመዓድ ገበታ ላይ ታቀርበዋለች።

ፈጣሪም እኛን እውቀት ይሰጡናል ያበስሉናል ብሎ ባሰባቸው በተለያዩ ነገሮች ላይ ይጥደንና ፍቅረኛ ማጣት ፣ ስራ ማጣት ፣ ገንዘብ ማጣት ... በተባሉ ሹካዎች ወጋ ወጋ አድርጎ መብሰል አለመብሰላችንን ያረጋግጣል።

ችግር ውስጥ ሆነን ካመሰገንን በስለናል ካማረርን ግን ይቀረናልና በተለያዩ ችግር ውስጥ ጥዶ ያገላብጠናል። 1 ካሜራ ማን እኛን ፎቶ ከማንሳቱ በፊት ፈገግ በል ቀና በል ትንሽ ወደ ቀኝ ምናምን እያለ ያስተካክለናል ከዛ ያነሳናል ። ፈጣሪም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን ሚያስተካክለው።

መከራ ፈጣሪ እኛን ወደሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። ዳይመንድን ውድ ካደረጉት ነገሮች መካከል አንዱ አቆራረጡ ነው ። ዳይመንድን የምናውቀውን ቅርፁን ያስያዘውና ከተለያየ አቅጣጫ እንዲያንፀባርቅ ያደረገው አቆራረጡ ነው ።

እኛንም ዛሬ እየቆረጡንና እያማረርንባቸው ያሉ ችግሮች ነገ እኛን ዉድና የሚያበራ ማንነት ባለቤት የሚያደርጉን ናቸው ። ማዕበል ሲነሳና ባህሩን ሲያማስለው ሁሉም እንስሶች ይሸሻሉ። ንስር ግን በመሀሉ ገብቶ አሳ ይዞ ይወጣል ።

ወዳጄ be like Eagle በችግር ውስጥ እራስህን አንፅ። ሸክላ የምትሰራ ሴት እንኳን ሸክላዋን ሰርታ ስትጨርስ እንዲጠነክርላት በእሳት ነው ምትጠብሰው ። ዛሬ የሚጠብሱህ ችግሮች ማንነትህን ነው የሚያጠነክሩልህ ።

ስለዚህ ስለሆነው ስለሚሆነው እየሆነ ስላለው ፣ ስለተደረግልህ ስላልተደረገልህ ፣ ስለ ሰጠህ ስለ ነፈገህ ነገር ሁሉ እሱን አመስገነው ። እንዲ በለው " ደስታንም ሆነ መከራን ብትሰጠው ከኔ ይልቅ ለኔ አንተ ነህ ምትቀርበው "

https://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#ማእበሉን አይታቹ ተሥፋ እንዳትቀርጡ፤
ፈታኝ ቆሞ ፊታቹ መንገድ እንዳታጡ ።
በነብስ ዝላቹ እንዳትታክቱ፤
ወደ ምስራቅ ተመልከቱ።

ለመቀለቀል 👉@Ortodoxtewahedo
#አብርሀምን ላምላክ ወገን ያደረግው

#በሀዋርያት ላይ መንፋሱን የላከው

#ሰለስቱ ደቂቅን ከሳት ያወጣቸው

#ከተራቡ እናብስት ድንኤልን ያዳነው

#ከእደ ረበናት ሶስናን የረዳት

#እንድ እምነት እሱም ተዋህዶ ነው

#ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና ዓለምን የሚያሸንፋው እምነታቹ ነው

1ኛ ዩሐ 5፥4 http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
#መዝሙር_ዘሆሳዕና
"ወእንዘ ሰሙን"

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ መልዕክታት
ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን ዕብ 9÷11- ፍ ም
ን/ዲ 1ጴጥ 4÷1-12
ን/ካ ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 8÷2
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

#ትርጒም
ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ::

#የዕለቱ_ወንጌል
ዮሐ 5÷11-31

ቅዳሴ: ዘጎርጎርዮስ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
" #ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ ..."

#መዝ 8፣2
_

" የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።"

#ማቴ 21፣9

#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም
#ሆሣዕና_በአርያም

#ሆሳህና በአርያም ለወልደ ዳዊት

📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖

#ሰላምሽ_ዛሬ_ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 

ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /

ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው/2/ 


ለመቀላቀል👉
@ortodoxtewahedo
2024/09/28 05:19:50
Back to Top
HTML Embed Code: