Telegram Web Link
ከሦስት ወራት በፊት ጥር 2/2016 ዓ.ም. ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ጀምሮ “አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ” የሚሉ ልጥፎች በበርካታ የኢትዮጵያውያን የፌስቡክ አካውንቶች እና ገጾች መሠራጨት ጀመሩ።
በፎቶ እና ጽሁፍ ከተቀናበረ ምስል ጋር የተሠራጩት እነዚህ ልጥፎች ፌስቡክ ላይ የወጡት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ ነበር።
የኒው ዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር የወጡት፤ “ይፋዊ የሆነውን መደበኛ የአሠራር ሥርዓት ተከትለው” እንደሆነ ቢቢሲ ከቤተ ክርስቲያኗ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዕለቱ የተሠራጩት ሦስት ዋነኛ ጽሁፎች “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ”፣ “አሜሪካዊው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል!” እና “ከአሜሪካዊ አቡነ ጴጥሮስ ኩብለላ ጀርባ ያሉ እውነታዎች!” የሚል መግቢያ ያላቸው ናቸው።
ጽሁፎቹ አቡነ ጴጥሮስን፤ “በቤተ ክህነት ውስጥ ህቡዕ የፖለቲካ አደረጃጀት በመምራት” እና “የቤተክህነት ሃብት የሆነ በርካታ ገንዘብ እና ንብረት ይዞ በመጥፋት” ይከስሳሉ።
ከሦስቱ ጽሁፎች ውስጥ በብዛት የተሠራጨው “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ” የሚለው ሲሆን፣ ይህ ጽሁፍ በጥር 2 እና 3/2016 ዓ.ም. ብቻ ቢያንስ 1,004 ጊዜ በተለያዩ የፌስቡክ አካውንት እና ገጾች እንደተለጠፈ ቢቢሲ አረጋግጧል። ከግራፊክስ ምስሎች ጋር የተለጠፈው ይህ ጽሁፍ፤ ጥር ሁለት ቀን ብቻ ይህ ቢያንስ 898 ጊዜ ፌስቡክ ላይ ተጋርቷል።
https://bbc.in/3Q4Mfjh

https://www.facebook.com/100068240109154/posts/736159432002054/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ኒቆዲሞስ ፯ ሣምንት ዐብይ ጾም

ኒቆዲሞስ የትህትና፣ የትጋትና የጽናት አብነት ነው።

ኒቆዲሞስ ማለት:- በግሪክ ቋንቋ “አሸናፊ/ነት” ማለት ነው፡፡

ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ብቻ ሳይሆን የፈሪሳውያን አለቃ፣ የኦሪት መምህር ብቻ ሳይሆን የኦሪት ምሁርም ነበር፡፡

በእርሱ ደረጃ የነበሩ ታላላቅ የአይሁድ ምሁራን መንፈሳዊ ስልጣናቸውና ሹመታቸው የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ረስተው በህዝቡ ላይ የሚመፃደቁ ነበሩ፡፡

በዘመናቸው እውቀትን የሚገልጥ እውነተኛ አምላክ የካህናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛ ለመሆን ወደዚህ ዓለም ሲመጣ አልወደዱም ነበር። እርሱ ግን የትህትና ባለቤት በመሆኑ ሁሉን ችሎ ያስተምር ነበር።

ዮሐ ፫÷፩-፲፪ ፣ ማቴ ፭÷፳
ማቴ ፲፮÷ ፮ ኢየሱስም፦ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ርሾ ተጠንቀቁና ተጠበቁ አላቸው።

እግዚአብሔር አምላክ ትዕግስቱን ሰጥቶ ክፉውን በመጠየፍ ደግ ደጉን ብቻ በመስራት የመንግሥቱ ወራሾች፣ የስሙ ቀዳሾች ያድርገን፣ ወዶና ፈቅዶ ለዚህ ዕለት እንደ አደረሰን ሁሉ እንድ በደላችን ሳይመለከት ቀሪውን ጊዜ ያስፈጽመን አሜን!

" ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ"

@ortodoxtewahedo
". . .አማን መነኑ ሰማዕታት ጣዕማ ለዛ ዓለም
ወከዐው ደሞሙ በእንተ እግዚአብሔር
ወተዐገሡ ሞተ መሪረ በእንተመንግሥተ ሰማያት
ተሣሃለነ በከመ ዕበየ ሣህልከ:: ሰአሊ ለነ ቅድስት "

@ortodoxtewahedo
."ሆዳችሁ ጠግቦ ከምታቀርቡት አንድ መቶ ጸሎትና ተራራ ከሚያርድ ድምጻችሁ ይልቅ በጾም ውስጥ ሆናችሁ የምታቀርቡት አንድ ጸሎት ተሰሚነት አለው።"

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

@ortodoxtewahedo
+ . . . አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም:: እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች:: ስለዚህ እልሃለሁ : እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአቷ ተሰርዮላታል:: ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል:: እርስዋንም:- 'ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል' አላት:: ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው:- 'ኃጢአትን እንኩዋ የሚያስተሰርይ ይህ ማነው' ይሉ ጀመር:: ሴቲቱንም:- 'እምነትሽ አድኖሻል: በሰላም ሒጂ' አላት:: +"

+ (ሉቃ. 7:46)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >.

@ortodoxtewahedo
+ሁለቱ መምህራን+

በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

አንደኛው መምህር የዓለም መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
ሁለተኛው መምህር ከአንደኛው መምህር ለመማር የመጣው ኒቆዲሞስ ነው

ኒቆዲሞስ ብሉይ ኪዳንን ለአይሁድ የሚስተምር
አይሁድን በሶስት ነገር የሚመራ ነበር
በእውቀት
በገንዘብ
በሥልጣን
በእውቀት መምህራቸው ነበር
በገንዘብ ከአይሁድ የተሻለ ሀብት ነበረው
በሥልጣን አለቃቸው ሁኖ ተሹሞ ነበር

ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ሁኖ በሚያስተምርት ወቅት የመምህራን መምህር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን ሊያስተም በምድር ላይ ተገለጠ
ያን ጊዜ ኒቆዲሞስ ሊማር ወደ ጌታችን በሌሊት ሄደ

ኒቆዲሞስ በሌሊት መማር የፈለገው ስለ አምስት ነገሮች ነው
1 አይሁድን ፈርቶ
በቀን ልማር ስሄድ አይሁድ ቢያዩኝ ከሥልጣኔ ይሽሩኛል ሀብቴን ይቀሙኛል ብሎ ፈርቶ ነው
በኢየሱስ ያመነ ከምኩራብ ይሰደድ የሚል ሕግ አይሁድ አውጥተው ነበርና

2 ውዳሴ ከንቱ ፈልጎ
መምህር ነኝ ይላል ለምን ሊማር ይሄዳል ብለው እንዳይነቅፉት ተደብቆ በሌሊት ሂዷል

3 በኦሪት ህግ ውስጥ እንዳለ ለመግለጽ
ኦሪት ሌሊት ወንጌል መዓልት ትባላለች
በኦሪት ሁሉም ሰው ቢሞት ወደ ጨለማዋ ሲኦል ይወርድ ስለ ነበር ኦሪት ጨለማ ትባላለች
ወንጌል የነፍስ ብርሃን ናትና መዓልት ትባላለች

4 ምስጢሩን በደንብ ለመረዳት
የቀን ልቡና ባካና ነው ዓይን በቀን ወጭ ወራጁን ሀላፊ አግዳሚውን ሲአይ
ጆሮ የተለያዩ ድንምጾችን ሲሰማ ልብ ይባክናል
በሌሊት ግን ሁሉ ጸጥ ያለ የሚሰማ ድምጽ የሌለበት የሚንቀሳቀስ የማይታይበት ስለሆነ የሌሊት ልቡና ሀሳቡ የተሰበስበ ነው ስለዚህ ጌታችን የሚነግረውን ምሥጢር ሁሉ ለመረዳት ከቀኑ ይልቅ ሌሊቱን መርጦ ሂዷል

5 የዕረፍት ጊዜውን መርጦ
ቀን አይሁድን ሲያስተምር ሲመክር የተጣላ ሲያስታርቅ የተበደለ ሲያስክስ የተቀማ ሲያስመልስ ወንበር ዘርግቶ ሲፈርድ ይውል ነበር
ሌሊት ግን ሁሉም ወደ የቤቱ ሲሄድ ኒቆዲሞስ ደክሞኛል ልርፍ ሳይል ከስራ እንደዋለ እንቅልፉን ትቶ ለመማር ወደ ጌታችን ሂዷል

ጌታችንም ምሥጢረ ሥላሴን ለአብርሃም በሶስት ሰዎች አምሳል ወደ ቤቱ ሂዶ እንደገለጠ
ምሥጢረ ሥጋዌን ለቶማስ በዝግ ቤት ገብቶ ጎኔን ዳሰኝ ብሎ እንደገለጠ
ምሥጢረ ቁርባንን ለሐዋርያት በዕለተ ሐሙስ በኀብስትና በወይን ነገ የሚቆረሰው ሥጋዬ የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሎ እንደገለጠ
ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታንን ለማርታና ለማርያ ወንድማቸው ዓልአዛርን ከመቃብር አስነስቶ ለኢያኤሮስ ልጁን ከሞት አስነስቶ እንዳስተማራቸው

ለኒቆዲሞስም ምሥጢረ ጥምቀትን ገልጦ አስተምሮታል
ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም ብሎ ስለ ጥምቀት ሲያስተምረው
መወለድን እንጂ መወለጃውን ከምን እንደሚወለድ አልገለፀለትም ነበርና ኒቆዲሞስ ትምህርቱ ሲከብደው ሰው ካረጀ በኋላ ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅጸን ገብቶ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ብሎ ጠየቀ
ጌታችንም ከውሃና ከመንፈስ ካለተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም
ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋል ስላልኩህ አታድንቅ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳል ድምጹን ትሰማለህ ነግር ግን ከየት እንደመጣ ወደየትም እንደሚሄድ አይታወቅም ብሎ ረቂቁን ልደት ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በረቂቁ ነፋስ መስሎ አስተማረው

ዳግም ልደት ረቂቅ ነውና በረቀቀው ነፋስ መስሎታል
ረቂቃን ፍጥረታት ሶስት ናቸው
መላእክት
ነፍሳት
ነፋሳት እነዚህ ሶስቱ ረቂቃን ፍጥረታት ናቸው
ከነዚህ አንዱ ነፋስን ጠቅሶ አስተምሮታል በእርግጥ የነፋስ ድምጽ አለው ወይ?
የሚል ካለ የነፋስ ድምጹ ባህር ሲገስጽ ማእበል ሞገድ ሲያስነሳ ዛፍ ሲያንቀሳቅስ ድምጹ ይሰማል
ኒቆዲሞስ ግን መልሶ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ?አለዉ

ጌታችንም አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ይሄን እንዴት አታውቅም ብሎ ገሰጸው
መምህር ብሎ መምህርነቱን ነገረው
አታውቅም ብሎ አላዋቂነቱ ገለጸበት
የምናውቀውን እንመሰግራለን ያየነውን እንናገራለን ነገር ግን ምስክርነታችን አትቀበሉንም
በምድር ያለውን ብነግራቸው ካላመናችው በሰማይ ያለውን ብነግራችው እንዴት ታምናላችው? ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም እርሱ የሰው ልጅ በሰማይ ይኖራል አለው ከዚህ በሇላ ኒቆዲሞስ አምኗል ሰማያዊ አምላክ መሆኑንም ተረድቷል

ኒቆዲሞስም ተደብቆ በሌሊት ሰው ሳያየው ምስጢረ ጥምቀትን ተምሮ ብቻ አልቀረም በአደባባይ በመጨረሻዋ ሰዓት ሃይማኖቱን ገልጿል
ያስተምራቸው ይመራቸው የነበሩት አይሁድ የኒቆዲሞስ መምህር የሆነውን ክርስቶስን በቅናት ሰቅለው ሲገድሉት የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ሸሽተው የሚቀብረው ባጣ ጊዜ ኒቆዲሞስ በአደባብ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋር የክርስቶስ ተከታይ መሆኑን አሳይቷል
ያኔ በመከራ ሰዓት ሁሉ ሲሸሽ ኒቆዲሞስና ዮሴፍ ተገኝተዋል

መልኩን ለማየት ይከተሉት የነበሩት ሁሉ ሰውነቱ በደም ሲታለል ደምግባቱ ሲጠፋ ከፊቱ ባልተገኙበት ጊዜ

ኀብስት አበርክተው የሚያበሉ እጆቹ ሲቸነከረው ብንራብ አበርክቶ ያበላናል ብለው የሚከተሉት ሁሉ በጠፉበት ጊዜ

ብንሞት ያነሳናል ብንታመም ይፈውሰናል ብለው ሲከተሉት የነበሩት ሁሉ እሱ ታሞ ሲሞት በሸሹበት ጊዜ

የሚያደርገውን ታምራት ለማየት በመደነቅ የሚከተሉት ሁሉ ከፊቱ ባልተገኙበት ጊዜ

ከዋለበት እየዋሉ ካደረበት እያደሩ ወንጌልን ሲማሩ የነበሩት ሁሉ ከእመቤታችንና ከዮሐንስ በቀር ፈርተው ሸሽተው ከመስቀል አውርዶ የሚቀብረው በጠፋበት ጊዜ

ስላሳ ስምንት ዓመት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁረኛ ተይዞ በቃል ፈውሶ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለውማ ይባስ ብሎ ባአደባባይ አንተ ነህ ያዳንከኝ ብሎ በጥፊ በመታው ጊዜ

ሁሉ ፈርቶ የሚቀብረው አጥቶ ከሞተ በሇላ መስቀል ላይ ሁለት ሰዓት እንደተሰቀለ ሲቆይ

ከተወለደበት ጀምሮ ዕውር የነበረው ዓይኑን ያበራለት የት ገብቶ ይሆን?

ሰባት አጋንንት ያወጣላት መግደላዊት ማርያም ከመስቀል አውርዳ ለምን አልቀበረችውም? ከዚያ ሁሉ ስቃይ የፈወሷት ከአጋንንት እስራት ነጻ ያወጣት የሚቀብረው ሲያጣ

12 ዓመት ሙሉ ደም ይፈሳት የነበረቸው ሴት ሰው ሲንቃት ሲጸየፋት ከሰው እኩል ያደረጋት መስቀል ላይ ሲውል የት ሂዳ ይሆን?

በደንጋይ ተቀጥቅጣ ትሙት ብለው ተከሳ ሲያመጧት በሰላም ሂጂ ብሎ ያሰናበታት ከሞት ያዳናት መስቀል ላይ ተሰቅሎ የሚቀብረው ሲያጣ ሆዷ እንዴት ቻለ?

ከሞት ያስነሰው ዓልአዛር የት ገባ ?
ሞት ፈርቶ ይሆን ከመስቀል አውርዶ ያልቀበረው?

የሚገርመው እሱ ተሰቅሎ በመሞቱ የተነሱ ከአምስት መቶ በላይ ሙታን ነበሩ እነሱ እንኳን ከሞት በመነሳታቸው ተደሰቱ እንጂ ከመስቀል አውርደው አልቀበሩት

ያን ጊዜ ነበረ ሰው ባጣበት ጊዜ የሚቀብረው ባጣ ጊዜ
በድብቅ በሌሊት ይማር የነበርው ኒቆዲሞስ ከአርማትያሱ ዮሴፍ ጋራ የመጣው
እሱን ሰቅለው የገደሉ ይገሉናል ሳይሉ ከመስቀል አውርደው አቅፈው እያለቀሱ ስመው በበፍታ ሲገንዙት( ወአንበስበሰ አዕይንቲሁ እግዚእ ኢየሱስ )ጊታችን አምላካችን በባህርየ መለኮቱ ዓይኖቹን ግልጽልጽ አድርጎ እንደሩቅ ብእሲ ዝም ብላችው አትገንዙኝ
ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኀያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት እያላችው ገንዙኝ ብሎ ኪዳኑን አስተምሯቸው ኪዳን እያደረሱ ገንዘው አክብረው ማንም ባልተቀበረበት በአዲስ መቃብር መለኮት ያልተለየው ነፍስ የተለየው ቅዱስ ሥጋውን ሽቱ ቀብተው ሲቀብሩት (ኦ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ በከመ አክበርክሙኒ ወሰአምክሙኒ አነሂ አከብረክሙ በሰማያት ወአነብረክሙ ዲበ ዕንቆ ሰንፔር ሰማያዊ)ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ሆይ እንዳከበራችውኝ እንደሳማችሁኝ እኔም በሰማያት አከብራችዋለው በሰማያዊ እንቆ ሰንፔር ላይ አስቀምጣችዋለው ብሎ ተስፋቸውን ንግሯቸዋል

የቅዱስ ዮሴፍና የቅዱስ ኒቆዲሞስ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን

መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ

@ortodoxtewahedo
"ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" የተሰኘው ዐውደ ርእይ በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ !

በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት አዘጋጅነት የተሰናደው "ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ" የተሰኘው ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ ከሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 9 ቀናት ለዕይታ ቀርቦ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ በትናንትናው ዕለት ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቋል።

ዐውደ ርእዩ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ትውልዳዊ ሀብቶችን በትንናትናዊ ውበታቸው በአሁናዊ ቅኝት የቀረበበት ፣ ትውልዱን የሚመጥን ሥራዎች የታዩበት ነው ተብሏል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከቅዱስነታቸው ጋር ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አባቶች ፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶዶክሳውያን ተገኝተዋል።

@መረጃው የተዋሕዶ ሚዲያ ነው

@ortodoxtewahedo
#እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ወርሃዊ መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ

#እንጦጦ ሀመረ ኖህ ኪዳነ ምህረት ገዳም

በአዲስ አበባ ከተማ በስተሰሜን ምሥራቅ በጉለሌ ክፍለ ከተማ የምትገኝ ስመጥርና ታሪካዊ ገዳም ስትሆን በተራራ፣በሸለቆና በወንዞች የተከበበች በመሆኑዋ በተፈጥሮ አቀማመጧ አረንጓዴ የተላበሰች ናት፡፡ ይህም ለቤተክርስቲያኗ ውበትና ግርማ ሞገስ ከመስጠት አልፎ በሚያስደስት ፀጥታ የአዕዋፍ ዝማሬ ተሞልታ ጸጋን እንድትላበስ አድርጓታል፡፡
ይህች ቦታ የተቆረቆረችው በ484 ዓ/ም ሲሆን በ500 ዓ.ም በአባ ሊባኖስ የአንድነት ገዳም ሆና ተቋቋመች፡፡ አባ ሊባኖስ ወደ ሌላ መንፈሳዊ ተልእኮ ለመሄድ መነኮሳቱን ሲሰናበቱ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግረው ነበር ‹‹ልጆቼ ሆይ በሉ ይህችን ቅድስት ቦታ አደራ ሰጥቻችኋለሁ በኋላ ዘመን ታላቅ ቦታ ትሆናለች' አጋንንት ይወገዱባታል' የብዙ ቅዱሳን አፅም ያርፍባታል' ነገስታት ጳጳሳት ይሰግዱባታል' ብዙ መናንያን መጠጊያ ያደርጋታል ቤተ መቅደሷም በወርቅ በብር ተጊጣ ትታነጻለች የአንድነቱም ገዳም ተሻሽሎ ይቋቋምባታል››፡፡ በ9ኛ መቶ ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት የአክሱም ጽዮንን ቤተ መቅደስ ለማቃጠል ስትነሳ ንጉሡ አንበሣ ውድም ታቦተጽዮንን በምሥጢር በማስያዝ ወደ ሸዋ መጥተው በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ገዳም ታቦተ ጽዮንን አሳድረው ወደ ዝዋይ ደሴት ሲሄዱ ለገዳሟ ንዋየ ቅድሰት ስጦታ አበርክተዋል ጸበሏን ተጠምቀው ቦታውን መርቀው ሄደዋል፡፡
በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከንጉሥ ላሊበላ ጋር ወደ ዝቋላ አምባ ሲመጡ በዚህች ገዳም በእንግድነት አድረው በጸበሏ ተጠምቀው ቦታውን ባርከዋል፡፡ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ለመነኮሳቱ እንዲህ ብለው ነበር ‹‹ይህች ገዳም ታላቅ ስመጥር ገዳም ትሆናለች ከእርሷ በታች የሚታየው ጫካና ዱር መናገሻ ከተማ ይሆናል፡፡››
አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ወደዚህች ገዳም መጥተው አቀማመጧንና የጸበሏን ፈዋሽነት ተመልክተዋል ‹‹ዳሯ እሳት መሐሏ ገነት ይሁን›› ብለው ብዙ ስጦታ አበርክተዋል፡፡ አፄ ልብነ ድንግልም ወደ ገዳሟ መጥተው ተማህጽኖ አድርገው በጸበሏ ተጠምቀው ታቦተ ልደታንና ብዙ ንዋየቅድሳት ሰጥተው ሄደዋል፡፡ በንግስት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት ይህች ገዳም ሐመረ ኖኅ ኪዳነምህረት ገዳም ተብላ ተሰይማለች፡፡
ይህች ቦታ እንደተነገረላት ትንቢት ብዙ ቅዱሳንና ነገሥታት መጥተው የሰገዱባት የባረኳት' ጸበሏ የአጋንንት ድል መንሻ' የብዙ መነኮሳት መጠጊያ 'የህሙማን መፈወሻ' የእመቤታችንን ቃል ኪዳን ለማግኘት ብዙን ጊዜ ለሱባኤ ከሚመረጡ ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ ይህች ደብር በ1957 ዓ/ም የተመሠረተ ሰንበት ት/ቤት ሲኖራት በ1984 ዓ/ም በብፁዓን ጳጳሳት ‹‹መርሶ ሕይወት›› /የሕይወት ወደብ/ የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ የገዳሟ ስያሜ ሐመረ ኖኅ ( የኖኅ መርከብ ) እንደሆነ ሁሉ መርሶ ሕይወት ( የሕይወት ወደብ ) በመባሉ ሁለቱ ተዛማችነት አላቸው ፡፡ ይህ ሰንበት ት/ቤት ለየት የሚያደርገው በግል መኖሪያ ቤት በጋሞኛ ቋንቋ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ከ1986 ጀምሮ በሰ/ት/ቤቱ ስር በማቀፍ የወንጌል ትምህርቱን ከመማር ባሻገር ለጋሞ ሕዝብ መንፈሳዊ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
አዘጋጅ፡- እህተ ማርያም (በሰ/ት/ቤታችን ሰሌዳ መጽሔት ቀርቦ የነበረ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘለአለም ትኑር!!!

ሰው ሁሉ ለመናገር የዘገየ ለመስማት የፈጠነ ይሁን !
(ያዕቆብ 1፥19)

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር

@ortodoxtewahedo
2024/09/28 07:33:39
Back to Top
HTML Embed Code: