Telegram Web Link
በርዕሰ ገዳማት ወአድባራት ጥንታዊት ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም ገዳም በዓለ አስተርዮ እንዲህ ተከብሯል
***

እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን !!!

@ortodoxtewahedo
✞ ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” [መ/ዕዝ. ሱቱ. 2፡1]

✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

በመላእክት ከተማ በራማ ካሉት ሦስት ነገዶች ውስጥ አንዱ ነገድ ሥልጣናት ይባላል፡፡ በሥልጣናት ላይ ከተሾሙ ሊቃነ መላእክት ውስጥ አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ይባላል፡፡ ሱርያል የሚለው ስም በአንዳንድ ድርሳናት ካልሆነ በስተቀር እምብዛም አይታወቅም፡፡ ትርጉሙም ‹‹ዐለቴ እግዚአብሔር ነው›› ማለት ነው፡፡ ሱርያል የቅዱስ ዑራኤል ሌላ ስሙ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያንም በስፋት የሚተወቀው ስም ዑራኤል የሚለው ስም ነው፡፡ /ድርሳነ ዑራኤል 1991 ገጽ 14/

ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ኹለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን” ማለት (እግዚአብሔር ብርሃን ነው) ማለት ነው። "በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን ዐየሁ" [ራዕ. 8፡2] እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቊጥር 7 ናቸው። ቅዱስ ዑራኤልም ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መ.ሄኖክ. 6፥2] ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ኁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። [መ.ሄኖክ 28፥13] “ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤ እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡

የመልአኩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት
• ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣
• መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡
• ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የእውቀት ጽዋ ያጠጣበት ቀን ነው።

በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። የቅዱስ ዑራኤል በረከት በኁላችንም ላይ ይደር!! አሜን።


✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥

@ortodoxtewahedo
ቅዱስ ዑራኤል ቤተ-ክርስቲያን ።

@ortodoxtewahedo
❷❹
'' #ተክለ_ሃይማኖት ሆይ፤ በቁመት ብዛት እግርህ በመሠበሩ በደም ለተነከረ ሰኮናህ ሰላም እላለሁ። ቅዱሱ አባት ሆይ፤ ትዕግስትህ ፍጹም እንደ ኢዮብ ትዕግስት ነው እኮን። አባት ሆይ፤ ኖኅ ልጆቹ ሴምንና ያፌትን እንደባረካቸው አንተም በዓለሙ ሁሉ ያሉ ልጆችህን ደቀ መዛሙርትህን ባርካቸው። ''
#መልክአ_ተክለ_ሃይማኖት

የአባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ረድኤት በረከት ይድረሰን ::

@ortodoxtewahedo
የመርካቶ ደብረ አሚን ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ሕንጻ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ።

ጥር ፳፫ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም አዲስ አበባ።

በትናንትናው ዕለት የእድሳት ሥራው ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተባርኮ መንፈሳዊ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ታለቁ ገዳም በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ታቦተ አቡነ ተክለሃይማኖት ዑደት በማድረግ በዓሉን ለማክበር የተሰበሰቡ ውሉደ ክህነትና ውሉደ ጥምቀትን በመባረክ በዓሉ ተከብሯል።

እንደ ትላንቱ ሁሉ በበዓሉ ላይ የክብር ጥሪ የተደረገላቸው የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።

ከዑደት በኋላም የገዳሙ ሊቃውንት፣ ማኅበረ ዲያቆናትና የምክኀ ደናግል ሰንበት ት/ቤት መዘምራን ወረብ ቀርቧል።
ዕለቱን የተመለከተ ትምህርትም የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህር በሆኑት መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ተሰጥቷል።

በበዓሉ ላይ ለሕንጻ እድሳት ሥራው መከናወን ከፍተኛውን ሥራ ለሠሩ የእድሳት ኮሚቴ አባላትና በተለያዩ መንገዶች ለተራዱ አካላት የተለያዩ የምሥጋናና የማስታወሻ ስጦታዎች በገዳሙ ተበርክተዋል።

@ortodoxtewahedo
“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡(የወንጌል ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል)፨
፨፨፨፨፨፨፨
(ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ፤ እንደ ምድረበዳ
አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ
ትባርከን ዘንድ ና ና በመካከላችንም ቁም)
፨፨፨፨፨፨፨
ኦ! በኅሊናህ ቂም በቀል የሌለብህ!
መዓዛህ እንደ ጣፋጭ ሽቱ የሆነ!
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ (ከሃዲዎች) እንደ ደመና የበተኑህ!
የተጋድሎ ምስክርነትን የፈጸምህ!
ኦ! መርቆሬዎስ ዘሮሜ! (አርኬ)

#እንደልማድህ ፈጥነህ እርዳን!
የቅዱስ መርቆሬዎስ በረከት ይደርብን!

@ortodoxtewahedo
"ወሀሎ አሐዱ አሐዱ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፓዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል
ነገረ ገድሉ መዓርዒር እጹብ በግብር ለተናግሮ በቤክርስቲያን
እንኳን ለታላቁ ሰማእት ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።
ቅዱስ መርቆሬዎስ ሀገሩ ሮም ነው። አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል። የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ፕሉፖዴር” ነው፤ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው። በጥበብ በፈሪሀ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ።
ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል። መምለኬ ጣዖት ነበር። በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ። መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት። ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን “አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ /እኔ ጌታዬን አልክድም/ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ። በመጨረሻም ህዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፤ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን:: ዘኁልቁ ፳፪፡፳፰
የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይድርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፣ የሰማእቱን ገድል እኛም በህይወታችን በመድገም የጽድቅን አክሊል እንድንቀዳጅ አምላከ ቅዱስ መርቆርዮስ ይርዳን: አሜን ፡፡

@ortodoxtewahedo
#ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
2024/11/18 18:20:19
Back to Top
HTML Embed Code: