Telegram Web Link
መ/ር ዘመድኩን በቀለ ሆነ ከዲያቆን ሄኖክ ሀይሌ ጎን ነን እያልክ አንዱን የምትዘልፊ ክርስትያኖች እናስተውል ሁለቱም ለቤተክርስትያን ብዙ ስራ የሰሩ ዘመዴ ከረጅም ግዜ ጀምሮ ተሃድሶ መናፍቃን በማጋለጥ ለሃገር የገጠር ቤተ ክርስትያን በማሰራት የሚደክም እየደከመ ያለ ነው በማሄኖክም መፅሀፍትን በመፃፍ በኢጃት ጥሩ ስራ እየሰሩ ነው ሰሞኑን በተነሳው ነገር ቤተ ክርስትያንን በቅጡ ያላወቀ የነሱን ያህል ይቅርና ጠጠር የምታክል ነገር ያላረገ ሁሉ ቲክቶክ ከፍቶ ሲተች ማየት ያሳፍራል ላይክ የሚያደርገውም በወንድማማች መሀል ልዩነት ይፈጠራል ማስማማት ሲቻል አንዱን ማወደስ አንዱን ማኮሰስ አለማወቅና አለማስተዋል ነው ። ለቤተ ክርስትያን ከተጨነክ በአደባባይ አትዝለፍ እንዲስማሙ ፀልይ ወይም የሚቀርባቸው ሰዎች መፍትሔ ይፈልጉ ። እሳት ላይ ቤንዚን የምታርከፈክፉ ተጠንቀቁ መፅሃፉ የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው የእግዚአብሔር ልጅ ይባላሉና ነው የሚለው ።


ዘመዴ እንወድሃለን እናከብርሃለን ፈጣሪ ባለህበት ይጠብቅህ።
ዲ/ን ሄኖክ እንወድሃለን እናከብርሃለን ፈጣሪ ባለህበት ይጠብቅህ ።


@ortodoxtewahedo
"እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ..... (ከሕፃናት እና ከሚጠቡ ልጆች ምስጋናን አዘጋጀህ......)" መዝ ፰፡፪-፫

@ortodoxtewahedo
« ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን እናምናለን።»

@ortodoxtewahedo
ኪዳነ ምህረት

🖊 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡

🖊እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችው ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

🖊እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🖊ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

🖊ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል፦
". . . ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ። " ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

🖊በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለ

እንኳን ለ«ኪዳነምህረት» አደረሳችሁ። የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!!

@ortodoxtewahedo
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ጥር 18 ሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ዝርዎተ አጽሙ ለሊቀ ሰማዕታት ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉሥ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ። በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ። ከዚህም በኋላ እንደመጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አወጡት፤ ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ። አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት፤ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች። የሰማዕቱን ሥጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም

ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት። ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው፤ ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ

ንውጽውጽታ ሆነ፤ ምድርም ከመሠረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሉ በብሩህ ደመና ወረደ በተራራው ላይም ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማዕቱን ስጋ እንዲሰበስቡት አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮችም ቁጥር አራት ነው ስማቸዉ ህልቶን አግሎሲስ ሶሪስና አስፎሪስ ነው ይህንንም ታላቅ ተአምራት አይተዉ አምነዋል በኋላም በሰማዕትነ ሞተዋል ይህ የሆነዉ (ጥር ፲፰ በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን ዘርዎተ አጽሙ ስትል ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትዉላለች

ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምዕራፍ ፮ ;፲፭ -፲፰
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆን

@ortodoxtewahedo
ጥር ፲፰ ሰባረ አጽሙ ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ

እንኳን ለሰማዕቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!

የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከቱ ምልጃዉ ጥበቀዉ አይለየን🙏አሜን፫🤲

@ortodoxtewahedo
ይሕ ልጅ ከደሙ ንጹሕ ነዉ🙏
ቢኒ አሜሪካ አገር የተሻለ ገቢ የነበረዉ።የተሻለ ኑሮ የሚኖር ሰዉ ነበር።
ለሐይማኖቱ ባለዉ ፍቅር ኑሮዉን ኢትዮጵያ አደረገ።
በርካታ ቤተክርስቲያናትን ከምእመናን ገንዘብ በማሠባሠብ እንዲረዱ እና እንዲታነጹ አደረገ
ከቤተክርስቲያን መከፈል ጋር በተያያዘ ለእስር ተዳረገ
በርካታ ሰዎችን ከዩቲዩብ እንዴት ገንዘብ እንደሚገኝ አስተማረ ብዙዎችም እራሳቸዉን ለወጡ ይሕ ቅን ሠዉ ነዉ። የዚሕ ሁሉ ጫጫታ እዉነታዉ የሚከተለዉ ነዉ።
አሁን ገንዘቤን አጭበረበረኝ የምትለዉ ግለሠብ በሆነ ወቅት ላይ ፍቅር ዉስጥ እንደሆነችና አበድኩኝ ከነፍኩኝ ስትል የነበረች ናት።እሱም ለሷ መልካም ነገር ስለነበረዉ የፍቅር ጓደኞችም ነበሩ።መሀል ላይ ግን ከሷ ጋር በተያያዘ ችግር ይበቃኛል ከዚሕ በሗላ ከአንቺ ጋር መቀጠል አልችልም የሚል ነገር ሲመጣ በየሚዲያዉ ስሙን ማጥፋት ተያያዘችዉ።
ቢኒ አጠፋ እንኳን ቢባል ያደረጋቸዉ በርካታ መልካም ነገሮች ሚዛን ይደፋሉ።
በቅርቡ ሁሉንም ሊነግረን ወደ ሚዲያ ይመጣል።

@ortodoxtewahedo
አስተርዮ ማርያም ።

@ortodoxtewahedo
ብርብር ማርያምን የማያውቅ ኦርቶዶክስ የአንድ ብሔር ይመስለዋል
***

የኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ባለቤቷ ማን ነው ከተባለ በአንድ ቃል ....ኢየሱስ ከሚል ስም ላይ ይወድቃል።

ባህሪዋም ቅድስት እና ኩላዊት ሲሆን ብዛቷም አንድ ነው።

ጠላት ግን ሲከሳት የነፍጠኛ ሃይማኖት፣የገዢ መደብ ቤት ብሎ ባልዋለችበት ስሟን ይጠራሉ።

ባሻዬ ....

በእርግጠኝነት ብርብር ማርያም የሚባል ገዳምን ብታውቅ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከየትኛውም ብሔር ትከሻ ተንጠልጥላ እንዳልመጣች ትረዳለህ።

ደቡብ በሚባለው ስፍራ ህዝብ እንዲህ ሳይሰፍር ብርብር በምትባል ስፍራ ላይ ንጉስ ቆስጢንጢኖስ አርዮስን በኒቂያ ጉባኤ ይወገዝ ዘንድ ጉባኤ አበው ከዘረጋ ከ3 ዓመት በኃላ በ328 ዓ.ም

ወደእዚህች ስፍራ ታቦተ ገብርኤል እና ታቦተ ማርያምን ይዞ በመምጣት ለ1100 ዓመት በስፍራው ተሰርቶ የነበረውን መሰዋተ ኦሪት ለውጦ ወደ ህገ ወንጌል ቀይሯል።

በእዚህ ስፍራ የነበሩት ቀደምት የጋሞ ህዝቦች ከእግዚአብሔር ጋር የተዋወቁት ክርስቶስ በቤቴልሔም ከመወለዱ ከ800 ዓመታት በፊት በካህኑ ሳዶቅ ልጅ አዛርያስ በኩል እንደሆነ ብነግርህስ?

አንተ ከምትከሳቸው ነገስታት የሥነ ህዝብ ስርዓት በፊት ብርብር በሚባል ማማ ላይ ከህገ ኦሪት እስከ ህገ ወንጌል ተዘርግቶ በአዲስ ኪዳን ዘመን ኦርቶዶክስ የምትባል የእምነት አስተሳሰብ የያዘች መቅደስ በእዚህ ከፍታማ ስፋራ ላይ ነበረች።

የዛሬን አያድርገው እና ይህቺ ስፍራ የእውቀት ፣የምስጋና እና የሊቃውንት መፍለቂያ እንደሆነች አባ ባሕርይ የተባሉ መኖክሴ አማናዊ ምስክር ናቸው።

የቅድስት ቤተክርስትያን የጸሎት እና የታሪክ መጽሐፍ ብርብር ከሚባል ማማ ላይ እንደሚገኝ መዝሙረ ክርስቶስን ብታገላብጥ ታውቅ ነበር።

ስለዚህ ባሻዬ.... ለኦርቶዶክስ ገዢ ፈላጭ እና ፈጣሪ አካል ስትሰጣት "ኢየሱስ" ከሚለው ስም ውጪ ዕጣ አትጣልባት።

ለኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ብሔርም ይመደብ ዘንድ ከተገባ ብሔሯ ሰማያዊት እንደሆነች ከእኛ ከልጆቿ አንደበት ሰምተህ አስተጋባ።

@ጥንታዊት ጽዮን ሰማያዊት ብርብር ማርያም 2015 ዓ.ም

እግዚአብሔር ይመስገን!!!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

@ortodoxtewahedo
2024/09/30 11:33:00
Back to Top
HTML Embed Code: