Telegram Web Link
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"መሀረኒ ድንግል ወተሰሃለኒ በበዘመኑ"

ድንግል ሆይ ማሪኝ ይቅርም በይኝ በየዘመኑ

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼.

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ

🌼ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
wedase zekidamit
6
በእለተ ቀዳሚት የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና በትርጉም

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

💠 #እንሆ_የሱባዔው_በረከት

ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ፀጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን አዕምሮውን ልቡን በልቦናችን ሳይብን አሳድሪብን፡፡

#ቅድስት_ንጽሕት_ጽንዕት_ክብርት_ልዩ_ሲል_ነው

💠 #ንጽሕት_አለ

🔹ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነፁ ከሐልዮ አይነጹም፤ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ንጽሕት ናትና፡፡

💠 #ጽንዕትም_አለ

🔸ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፤ እርሷ ግን ቅድመ ፀኒስ፣ ጊዜ ፀኒስ፣ ድኅረ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናትና፡፡

💠 #ክብርትም_አለ

🔹ሌሎችን ሴቶች ብናከብራቸው ጸድቃንን ሰማዕታትን ወልደዋል ብለን ነው፤ እርሷን ግን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ብለን ነውና፡፡

💠 #ልዩም_አለ

🔸እናትነት ከድንግልና አስተባብራ የምትገኝ ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡

👌በጾመ ፍልሰታ በሱባዔው ወቅት ያፈስነውን በረከት ያራገፍነውን ኃጢአት ወደኛ እንዳይቀርብ ሁሌ በክርስቶስ ቃል በቃለ ወንጌሉ እየለመለምን እያደግን እያፈራን ጠላታችንን ዲያብሎስ ድል መንሳት አለብን::

የእመቤታችንን ጣዕሟን በአንደበታችን፣ ፍቅሯን በልቡናችን ይሳልብን ያሳድርብን፡፡


🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

🙏 ሼር ማድረግ አይርሱ 🙏

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🔔ነሐሴ 5🔔

በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልእክታት፣ ወንጌልና ምስባክ

👉ዲያቆን
📖2ኛ ቆሮ 12፥10-17

"ስለዚህም ስለ ክርስቶስ መከራ መቀበልን መሰደብን መጨነቅን መሰደድን መቸገርንም ወደድሁ መከራ በተቀበልሁ ጊዜ ወዲያውኑ እበረታለሁና፤.......እኔ አልከበድሁባችሁም ነገር ግን ምክር ዐዋቂ ሆኜ በመጠበብ ወሰድኋችሁ"

👉ንፍቅ ዲያቆን
📖1ኛ ዩሐ 5፥14....

"በእግዚአብሔር ዘንድ ያለችን መወደድ ይህች ናት በስሙ ከእርሱ ዘንድ የምንለምነውን ይሰማናልና፤.......ልጆቼ ሆይ ጣዖታትን ከማምለክ ራሳችሁን ጠብቁ"

👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረ ሐዋርያት 15፥1-13

"ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር፤......ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያደረገላቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲናገሩ ጳውሎስንና በርናባስን
አዳመጡአቸው"

👉ምስባክ
📖መዝ 17፥43-44
ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ
ውስተ ምስማዐ እዝን ተሰጥዉኒ፡፡

👉ትርጉም
የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ
የማላውቀው ሕዝብም ይገዛኛል
በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፡፡

📖ወንጌል
ሉቃስ 15፥1-11

"ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር፤........እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል"

📣ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahed

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo
ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤታችን ምስጋና እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ፣ እንደ ምግብ ተመግቤው፣ እንደ ውሓ ጠጥቼው፣ እንደ ልብስ ተጎናጽፌው ምነው በኖርኩ እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር።

መንፈስቅዱስም የተመኙትን መግለጽ ልማዱ ነውና ገልጾለት ፻፻ ከ፬ ሺህ ድርሰት ደርሷል “አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” እስኪል ድረስ። ከዕለታት በአንዱ ቀን ዕለተ ሠኑይ ጊዜው ነግህ ነው። የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፣ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፣ ከዚያ ላይ ሆና “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርዬ ኤፍሬም” ትለዋለች።እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል። “ወድሰኒ” ትለዋለች “እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ” ፣“ሰማያውያን ወምድራውያን ምድራውያን ጻድቃን ሰማያውያን መላእክት አንችን ማመስገን የማይቻላቸው ለኔ እንደምን ይቻለኛል” አላት “በከመ አለበወከ መንፈስቅዱስ ተናገር” አለችው። በተረቱበት መርታት ልማድ ነውና “እፎኑ ይከውነኒ እንዘ ኢየአምር ብእሴ” ብትለው መልአኩ “መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ” ብሏት ነበር። ከዚህ በኋላ ባርክኒ ይላታል በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ትለዋለች። ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል።

ምንጭ፦ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
Audio
በእለተ እሁድ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና ይህ ነው።

❤️ውዳሴ ማርያም ዘሰንበተ ክርስቲያን አንድምታ ትርጓሜ

🎙በሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

#የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ።" (መዝ 17፥43-44)

የሚነበቡት መልዕክታት
2ኛ ቆሮ 12፥10-17
1ኛ ዮሐ 5፥14-ፍ.ም
የሐዋ ሥራ 15፥1-13።

የሚነበበው ወንጌል
ሉቃ 15፥1-11


< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

"እርሱ ቅሉ እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መልአኩን ወደ አንቺ ላከ መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ይመጣል የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ።

ከአባቱ አጠገብ ሳይለይ ቃል ወደ አንቺ መጣ ሳይወሰን ፀነስሽው በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨምር በማኀፀንሽ ተወሰነ።

መጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በሆድሽ አደራ በምድራዊ እሳት እንመስለው ዘንድ አይገባም ለእሳትስ መጠን አለው አለው መለኮት ግን ይህን ያህላል ይህንም ይመስላል ሊባል አይቻልም።


ለመለኮት እንደ ፀሐይና እንደ ጨረቃ ክበብ አንደ ሰውም መጠን ያለው አይደለም ድንቅ ነው እንጂ የሰው ህሊና የመላዕክት አዕምሮ በማይደርስበት በአርያሙ የሚኖር ነው እንጂ።

(ቅዳሴ ማርያም)

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot
(መጽሐፈ ምሳሌ  31-10-30)
----------
10፤ ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል ? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።

11፤ የባልዋ ልብ ይታመንባታል። ምርኮም አይጐድልበትም።

12፤ ዕድሜዋን ሙሉ መልካም ታደርግለታለች፥ ክፉም አታደርግም።

30፤ ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🔔 ​ነሐሴ 6 🔔

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ

👉ዲያቆን
📖1ኛ ቆሮ 8÷1.....
👉ንፍቅ ዲያቆን
📖1ኛ ጴጥ 4፥1-6
👉ንፍቅ ካህን
📖ግብረ ሐዋርያት 26÷1-24

👉ምስባክ
📖መዝ 86፥5-7

እምነ ጺዮን ይብል ሰብእ
ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ
ወውእቱ ልዑል ሣረራ

👉ትርጉም
ሰው ጽዮንን እናታችን ይላታል
በውስጧም ሰው ተወልደ
እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት

📖ወንጌል
ማቴ 12÷38.......

📣ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedo

#ግሩኙን ለመቀላቀል

@ortodoxtewahedoo

#ለሃሳብ አስተያየት

@Orthodox_tewahedo_Bot.
Audio
በእለተ ሰኑይ የሚነበብ የሚተረጎም የሚጸለይ የእመቤታችን ምስጋና በትርጉም

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

#መልካም ቀን

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም  ትርጓሜ

ክፍል ፪

@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም  ትርጓሜ

ክፍል ፫

@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፬

@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፭

@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፮

@ortodoxtewahedo
@m2vbot
Convert To Voice
ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ክፍል ፩

@ortodoxtewahedo
Audio
ጫማህን ከእግርህ አውልቅ
        
Size:-37.5MB
Length:-1:47:48

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼      

     
      ወይቤሎሙ ሑሩ ወመሐሩ
ለዘየአምን ወንጌለ መንግስተ ሰማያት

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን

💠ጽንሰታ ለማርያም

🔹ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል::

ስለ ምን ነው ቢሉ

🔸ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው::

🔹 #አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::

"ለጽንሰትኪ በከርሥ እንበለ አበሳ ወርኩስ ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ"

"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው"
📖መጽሐፈ ሰዓታት
📖ኢሳ 1፥9

🔸ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል::

የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ

🔹ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ በሕጉ ጸንተው በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር::

🔸ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር፤ ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር::

🔹ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::

🔸እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም፤ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው::

🔹አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች::

"እንስሳትና አራዊትን እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን" ብላ አዘነች::

🔸ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ::

🔹ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ፤ በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ::

🔸#እርሱ ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ በማኅጸኗ ስትደርስ አየ::

🔹#እርሷ የኢያቄም በትር አብቦ አፍርቶ ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች::

🔸ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ::
🔹ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ፤ በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ::

"ዓለም የሚድንባት የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው::

🔸እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

🔹እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::

"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ"

"ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም"

👉(ቅዳሴ ማርያም)👈

#ንፅህ በድንግልና ስርኩ በቅድስና እመቤታችን ፀጋው ክብሩ እንዳይነሳ ለምኝልን አምሮው ልቡን በልቦናች ሳይብን አሳድሪብ አሜን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን

ለመቀላቀል👉 @ortodoxtewahedo

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
2024/09/30 03:30:09
Back to Top
HTML Embed Code: