Telegram Web Link
እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡

#የቀጨኔ_ደብረ_ሰላም_መድኀኔዓለም

ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ፤ የ 112 ዓመታት ዕድሜ ያለው ጥንታዊ የኢያሱ ደብር፡፡ ‹‹በወርቅ ወበዕንቊ ሥርጉት ደብረ ሰላም፤ ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ›› ይህችን ደብረ ሰላምን በመጀመሪያ አቤቶ ኢያሱ /አልጋ ወራሽ ልጅ ኢያሱ/ (ክፍለ ያዕቆብ) በሐምሌ 26 ቀን 1903 ዓ.ም. መሠረታት፤ ንግሥት ዘውዲቱ አሁን ያለውን ሕንፃው ቤ.ክ ጥቅምት 27 ቀን 1913 ዓ.ም አስፈጸመች፡፡)

የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፤ የላይ ቤት አቋቋም፣ የተክሌ ዝማሜና የሸዋና የራሱ የደብሩ ቀለም እንደ ወንዝ የሚፈስባት፤ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ቤተ መዘክር (Museum)ና ቤተ መጻሕፍት የሚገኙበት፤ ስዕለት ሰሚ ታቦታት ያሉበት፤ 4ት የሚጠጉ ፈዋሽ ጠበሎች የሚገኙበት፡፡ ጽዶቹ ሳይቀሩ በ72 አርድዕት ቅዱሳን አምሳያ የተተከሉበት፤ በቀድሞ ዘመን መዐዛ ቅዳሴ የተሰኘው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዳሴ በወርኃ ጽጌ የሚቀድስበት፤ 3 ጳጳሳትን ያፈራ፣ ……. ደብር ነው፡፡

✣ ለደብረ ሰላም ይደልዋ ስብሐት፤ እስመ በውስቴታ ኀደረ መድኀኔዓለም (በደብረ ሰላም በውስጧ መድኀኔዓለም ስላደረ ምስጋና ይገባታል፡፡)

ምንጭ 👉 የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት

@ortodoxtewahedo
🔴 መድኃኔአለም 🔴
✍️✍️✍️
መድኃኔአለም ማለት አለምን ያዳነ የአለም መድኃኒት ማለት ነው። ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀድሞ ክብሩ መለሰው። ምን አይነት ፍቅርነው?????
ወንድሜ /እህቴ አስባችሁታል ግን እኛን ለማዳን ብሎእኮ ነው

የተሰቀለው፡ራቁቱን በመስቀል ምን ያህል
አሳፋሪ እንደሆነ እናውቀዋለን
ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ መስቀሉን ናቀው።
በፈጠራቸው ፍጥረት ተተፋበት።
እኛን ትእግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት
እየቻለ እርሱ ግን

💖በፍቅር እያዩ የማያውቁትን አያውቁምና
አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር።
ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድበት
አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም
ሲታበዩበት ሁሉ እርስ ግን በትህትና ያያቸው ነበር።

💖ታዲያ እኛ ደግሞ እራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል።
ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንባላለን።
በ 5 ችንካር ነበር የቸነከሩት።

በመስቀል የተገኙ ድንግል ማርያም ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ። አንተም በመስቀሉ ስር
ለመገኘት ከፈለግህ ትእግስትን ፍቅርን ትሕትናን ገንዘብ አድርግ።

መድኃኔአለም በቸርነቱ ይቅር ይበለን።

@ortodoxtewahedo
"ወዳጄ ሆይ ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው በጌታችን እራስ ላይ እሾህ እዳቀዳጁት ባሰብህ ጊዜ እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር በጌታችን ላይ የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን ወታደሮች ከጎነጎኑት እሾኽ በላይ የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው ደሙን አፍስሶ ያዳነን እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን የምንጎነጉነው የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[ ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}

መድኃኔዓለም ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !

( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@ortodoxtewahedo
‹‹ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ ››

{ ፩ኛ ጴጥሮስ ፪፥፳፬ }

"ወዳጄ ሆይ  ሮማውያን ወታደሮች ጎንጉነው  በጌታችን እራስ ላይ  እሾህ እዳቀዳጁት  ባሰብህ ጊዜ  እጅግ ማዘንህ አይቀርም ። ሆኖም አንተም እሾህ የተባለውን አንድ ኃጢአት በሰራህ ቁጥር  በጌታችን ላይ  የተደፉትን እሾኾች ቁጥር እንደጨመርህ አስብ ።በፈጣሪ የማያምኑት ሮማውያን  ወታደሮች ከጎነጎኑት  እሾኽ በላይ  የጌታችንን እራስ የበለጠ ዘልቆ የሚወጋው  ደሙን አፍስሶ ያዳነን  እኛ ክርስቲያኖች በኃጢአታችን  የምንጎነጉነው  የእሾኽ አክሊል ነው ።{ስለመተላለፋችን የቆሰለው አምላክ በመተላለፋችንም ይቆስላል ።!}

{በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን ከሚለው ርዕስ የተወሰደ )

[  ሕማማት]
{በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ}

መድኃኔዓለም  ሆይ አባት ሆይ ይቅር በላቸው በማለት በታላቅ ቃል በመስቀል ላይ ፥ ለተናገረ ቃልህ ሰላም እላለሁ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህን በጦር በወጉ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ ።
መድኃኔዓለም ሆይ ጻድቃንን ያይደለ ኃጥአንን ለማዳን በራሱ ደም ራሱ ለተጥለቀለቀ ስነ መልክህ ሰላም እላለሁ !

     ( መልክአ - መድኃኔአለም )27

@ortodoxtewahedo
Audio
ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ
ማቴ 26÷39
Size 34.5MB
Length 2:30:38
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Audio
ቀድሞ የገባ ሰው ይፈወሳል
                         
Size 58.7MB
Length 2:48:30

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት

ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።

ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።

በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።

የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩

ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።

ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።

ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
" እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።

እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።

ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "

" እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ "
መዝ.፵፪÷፱

" እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነድዳል፣ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ "

@ortodoxtewahedo
2024/09/28 19:34:34
Back to Top
HTML Embed Code: