Telegram Web Link
☝️ተዋሕዶ በተዓቅቦ?

#ነገረ #ክርስቶስ #ትምህርት #ላይ #መዘንጋት #የሌለባቸው #ጉዳዮች
፩. አምላክ ሰው የሆነው ሰውን ለማዳን ነው። ለሰው ልጆች ያለው ጥልቅ ፍቅሩን የገለጠበት ነው ሥጋዌ።

፪. አምላክ እንዴት ሰው ሆነ? የሚለውን አለማወቅ ይጎዳል። እንዴት ሰው ሆነ በሚለው ከብዙ ቤተ እምነቶች ጋር የምንለያይበት ስለሆነ ጠንቅቆ ማወቅ መልካም ነው። እንዴት ሰው ሆነ?
ሀ. እንበለ ውላጤ
ለ. እንበለ ሚጠት
ሐ. እንበለ ኅድረት
መ. እንበለ ምትሐት
ሠ. እንበለ ቱሳሔ
ረ. እንበለ ፍልጠት
ቀ. እንበለ ቡዓዴ
በ. እንበለ ትድምርት
ተ. እንበለ ምንታዌ
ነ. በተዋሕዶ በተዓቅቦ
ነው። እኒህን አለመለየት ከክሕደት አዘቅት ያስገባል። አምላክ ሰው ሲሆን ከአምላክነቱ ተለውጦ ወደሰውነት ተቀይሮ አይደለም። አምላክ ሰው ሲሆን ሰው አምላክ ሆኗል። ሰው አምላክ ሲሆን ከሰውነቱ ተለውጦ ወደ አምላክነቱ ተቀይሮ አይደለም። "ወኢተወለጠ ህላዌ ቃል ኀበ ህላዌ ትስብእት ወኢህላዌ ትስብእት ኀበ ህላዌ ቃል። ዳእሙ ይሄልዉ ክልኤቱ ህላዌያት በበህላዌሆሙ እንበለ ውላጤ" እንዲል (ሃይ.አበ.፵፫፣፭)። በተጨማሪም ሃይ.አበ.36 ላይ "ኢያፍለሰ ፈጣሪ መለኮቶ ለከዊነ ፍጡር። ፈጣሪ ባሕርይውን ፍጡር ወደመሆን አልለወጠውም። ወኢደምሰሰ ትስብእቶ ፍጡረ ለከዊነ ፈጣሪ። የተፈጠረ ሥጋንም ፈጣሪ ወደመሆን አልለወጠውም" ተብሎ ተገልጿል። በተዋሕዶ ሰው ወደ አምላክነት አምላክ ወደ ሰውነት አልተለወጠም። እንበለ ውላጤ መባሉ ለዚህ ነው። ሰውነት ተለውጦ አምላክ ብቻ ሆኗል፣ ክርስቶስን አምላክ ብቻ፣ ረቂቅ ብቻ፣ ምሉእ ብቻ ይባላል ካሉ መለኮት ሥጋን ውጦታል የሚል የአውጣኪ ክሕደት ነው። ክርስቶስን ሰው ብቻ፣ ግዙፍ ብቻ፣ ውስን ብቻ ይባላል ካሉ ይህ የእስልምና ክሕደት ነው። አካልን አዋሕደው ባሕርይን ካላዋሐዱ የካቶሊካውያን፣ የመለካውያን ኦርቶዶክሶች (የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬንና የመሳሰሉት) ክሕደት ነው። አምላክ ሰው ሲሆን ወደሰውነት ተለውጧል ካሉ የሐራ ጥቃ ክሕደት ነው። አምላክ በሥጋ አደረ የሚለውን ይዘው ኅድረት ካሉ የጳውሎስ ሳምሳጢ ክሕደት ነው። አምላክ ሰው መስሎ ታየ እንጂ ሰው አልሆነም ካሉ የማኒ ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስ የሠራውን ሥራ እየለያዩ ይህ የሥጋ ሥራ ነው፣ ይህ የመለኮት ሥራ ነው እያሉ መለያየትም ክሕደት ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለው ሥራ የተዋሕዶ ሥራ ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ አካል የተዋሕዶ አካል ነው። ከተዋሕዶ በኋላ ያለ ባሕርይ የተዋሕዶ ባሕርይ ነው። ኀደረ፣ ደመረ የሚሉት ቃላት እንደ ጊዜ ግብሩ ተዋሐደ ተብለውም ሊተረጎሙ ይችላሉ። ኩሉ መለኮቱ ኀደረ በሥጋ ሰብእ ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል። ነአምን ከመ ተደመረ ኩለንታሁኬ ለቃል ወኩለንታሁ ለትስብእት ሲል ተዋሕዶን ያመለክታል።

የእኛ አስተምህሮ ተዋሕዶ በተዓቅቦ ነው። ፍጹም አንድነት ያለመለወጥ ነው። ተዓቅቦን የዘነጋ ተዋሕዶ ውላጤ ነው። ተዋሕዶን የዘነጋ ተዓቅቦ ምንታዌ ነው። ሥጋ አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የቃልን አካሉን፣ ባሕርዩን፣ ግብረ ባሕርዩን ገንዘብ አደረገ። ቃልም አካሉን፣ ባሕርይውን (ከዊኑን)፣ ግብረ ባሕርይውን ሳይለቅ ባሕርይውን እንደያዘ ሳይለውጥ የሥጋን አካሉን ባሕርይውን፣ ግብረ ባሕርይውን፣ ባሕርይውን ገንዘብ አደረገ። መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል ያለው ይህንን ነው።


በትረ ማርያም አበባው

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሰው የገዛ ሞባይሉ ቢጠፋ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገለባብጦ ነው የሚፈልገው። እግዚአብሔርን ሳናገኝ ግን ውለን እናድራለን። እግዚአብሔርን በማጣታችን ነፍሳችን ደግሞ ጥያቄዋ አያርፍም። ሁልጊዜ ሰው አይረካም፤ ስለማይረካም ነው ይገላል ይቀማል፤ ተሹሞ መሾም ይፈልጋል፤ አግብቶ ማግባት ይፈልጋል፤ ይዞ መያዝ ይፈልጋል። ሰው ለምንድነው ልቡ የማያርፍለት ካላችሁኝ የልብ ማረፊያው እግዚአብሔር ስለሆነ ነው።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🔴አዲስ ስብከት 🔴 "ከእግዚአብሔር ጋር...
ተምሮ ሚዲያ - Temro Media
ትክክለኛው አገልግሎት እዴት ያለው ነው?

ለእግዚአብሔር መስራት ነው ወይስ ከእግዚአብሔር ጋር መስራት 🤔

ራሳችንን እንፈትሽበት ሰሚ ጆሮ አስተዋይ ልቡና ያድለን ወደትምህርቱ 🤗


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድግ_አትዘንጉ👇
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
" ቅጥሩም ወደቀ።”
— ኢያሱ 6፥20

የኢያሪኮን ቅጥር በእግዚአብሔር ታቦት እንዳፈረሱት ሰማሁ እኔም ከኢያሪኮ ግንብ የገዘፈ ኀጢአቴን ያፈርስልኝ ዘንድ በማስተዋል ወደ አዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ወጣሁ።

🫴እንኳን ፍቅር ለሆነው ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓል በሰላም ዓደረሳችሁ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አማኑኤል ማለት:- እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ (እግዚአብሔር ምስሌነ) ማለት ነው።
እግዚአብሔር በአካል ከፍጥረቱ ተለይቶ አያውቅም። እርሱ በአካል የሌለበት ቦታ የለምና።
👉  በረድኤትም በብሉይኪዳን ከቅዱሳን አበው፣ ከቅዱሳን ነቢያትና፣ ከቅዱሳን ነገሥታት ጋር ነበር።

🔰 ይህኛው "ምስሌነ" ግን አነጋገሩ ከረድኤት የተለየ "ምስሌነ" ነው። በረድኤት ከእኛ ጋር መኖርን ብቻ የሚገልጽ አይደለም።

🔰 የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ ከእኛ ጋር መኖሩንም የሚገልጽ አነጋገር ነው። አማኑኤል የሚለው ስም ስመ ሥጋዌውን የሚገልጽ ስም ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን እንደ እኛሰው ሆኖ ክሦ፣ ቤዛ ሆኖ አድኖናል።

እንግዲህ ምንንም፣ ማንንም አንፈራም። የሚያስፈራን ነገር የለም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው።💪

“እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?”
  — መዝሙር 27፥1

አማኑኤል (28)

እንኳን አደረሳችሁ ተወዳጆች🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዮሐንስ 6
⁶⁸ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን?

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
አንድ አንድ ሰው የሃይማኖት መርኆ የሚቀርጸው ከዕቅበተ እምነት እና መናፍቃንን ከማሳፈር ወይም ከመብለጥ አንጻር ብቻ ሲኾን ጥልቅ ለኾነው ኦርቶዶክሳዊ ነገረ መለኮት ዓለምን መፈተሽ ለሚያስችለው ኦርቶዶክሳዊ ንጻሬ ዓለም ደንታ የሌለው ይኾናል። የእንደዚኽ አይነቱ ሰው የኹል ጊዜ ፍላጎት ነገር ኮሽ በማይልበት ቤተ ክርስቲያን መኖርን መናፍቃኑን ማስቀናት ነው። ተባብሮ የውጭ ጠላት እንደማሳፈር እንደ ደላው ሰው በውስጥ ተዋስዖ ማድረግን እንደ ቅብጠት ይቆጥረዋል። ይህ ሰው ቤተ ክርስቲያን በዘመናት እንዴት እውነትን ከሀሰት እየለየች እንደተሻገረች የገባው አይመስልም። በዚህ ምክንያት በውስጥ የሚደረግን ተዋስዖ አጥብቆ ይጸየፋል።

ሌላኛው አይነት ሰው ደግሞ ስለ ትክክለኝነቱ ከመጨነቅ ይልቅ ተያያዥ ጉዳዮች ያሳስቡታል። የግል ጉዳዩ የሚወደው ሰባኬ ወንጌል ዘመዱ የኾነ ጳጳስ ወይም ያስቀጠረው ጳጳስ... ወ.ዘ.ተ ቀስፎ ስለሚይዘው የውስጥ ተዋስዖን ይጸየፋል።

ከዚህ ውጭ የኾነው እምነቱን በመጠየቁ የሚያጣው የሚመስለው የእምነቱን ጉዳይ ለተወሰኑ ሰዎች ሰጥቶ እነሱን እያመነ መኖር የሚፈልግ ሰነፍ ሰው ነው። አብዛኛው ሰው የእምነት ፍርሃት አለበት። ለዚህ ማሳያው የምንዘምራቸው መዝሙራት ሳይቀሩ "አንተ ባታውቅም ኦርቶዶክስ መልስ አላት" የሚል አሳብ ያላቸው ናቸው። ለእንደዚህ ዓይነት ሰው በውስጥ የሚደረግ ተዋስዖ ስጋት ነው።

ውስጣዊ ተዋስዖ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አካል አይደለምን?
እንደ ተለመደው አሳብ አስተያየት ትለመናላችኹ።
ኤማሁሳውያኑ በመንገድ እንዲኽ ተወያዩበት


ኢዮብ ወንድወሠን

https://youtu.be/VYm1SakDhR8?si=lDnLABDv8OcolyqA



https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም በሀይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደል በእደ ህሊና ያዝሁሽ በእደ ስጋ አይደል።
እደ ህሊናዬን ግን የሰው ሀይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና።የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም።

ልትደግፊኝ ያዝኩሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጂኝ ግን አይደለም።

ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለእድሜ ልክ ብቻ አይደለም።እናቴ ሆይ ነብሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለ ቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድሀኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደወደቅሁ እቀር ዘንድ አትርሺኝ።

📖አርጋኖን ዘሠሉስ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለአንዲት ሃገር በተሰጠን ቃልኪዳን መሰረት ሰው ሁሉ ምንም ባይሰራም ይድናል ሃገርም ይጠበቃል የሚል ሃሳብ በቀን ውሎዬ ላይ የሚያንፀባርቁ ሰዎች አጋጥመውኝ ነበረ ታድያ ይህ በጣም ከባድ እሳቤ ነው ካለንበትም ጥፋት ወጥተን ወደንፅህና ከፍ እዳንል የሚጎትተን የቃልኪዳኑ ምንነት ወደሰማያዊ ህይወት የሚያቀናን ሳይሆን ለዚሁ ምድራዊ ህይወት ብቻ እንድናስብ የሚያረገን ማነቆ የሆነ ሃሳብ ነው ይህ ሃሳብ ብዙሃኑ ዘንድ የሚታሰብ ከሆነ ጥቂት ነገሮችን እንበልበት!

በተሰጠን ቃልኪዳን ብቻ መዳን አይቻልም ያንን ቃልኪዳን አሜን ብሎ በመቀበል ውስጥ እንጂ ከሚጠቀሱት ውስጥም ምሳሌ

ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ሃገር ናት አትጠፋም የሚሉ ይኖራሉ ! የቃልኪዳን ሃገር ብትሆንም ቃልኪዳኑን የሚፈፅሙ ህዝቦች ከሌሉ ግን አትጠፋም ብሎ መናገር አይቻልም ቃልኪዳኑ ሚኖረው ተቀብሎ በሚኖረው ምዕመን ዘንድ ስለሆነ ኢትዮጵያ የተባሉትም ህዝቦቿ ናቸው እንጂ ሳር እና ቅጠሉ ስላልሆነ ቃልኪዳኑ ሚኖረው ከሚኖረው ህዝብ ጋር ነው ማለት ነው!


ከአባቶች የተሰጠ ሃሳብ ደሞ እነሆ🤗🤗


ለቅዱሳን የተሰጠ ቃልኪዳን ለመዳናችን ያለው አስተዋጽኦ


#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ

ጥያቄ ካለ ከስር ኮመንት መስጫ ላይ አስፍሩ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
''አንዳንዶች ኢትዮጵያ ምድረ ገነት ናት ይላሉ ኢትዮጵያ ገነት ከሆነችማ መፆሙ መፀለዩ ምን አስፈለገ እየኖርንባትም አይደለ ጎበዝ 😁 ''

ምን ይባላልም ጭራሽ በመጨረሻው ዘመን ከሌሎች ሃገራት ወደኢትዮጵያ ይፈልሳሉ ይከማቻሉ ይሉናል 🤭

ኑሮ ሳይወደድ በፊት ነበረ አሁን ግን እንጃ እዚም ያለው መሮታል እንኳን እነሱ ሊመጡ ሳስበው🤔 😂😂😂😂😂

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
☝️ሃሳቡን በዚች ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ ሃሳብ እንጠቅልለው 🤗

እዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያለው ካለ ኮመንቷ ላይ አስፍሩ👇

በቸር ዋሉልኝ🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
HEALING_and_SALVATION_ፈውስ_እና_ደኀነ_UPDATED.ppsx
2.1 MB
ፈውስ እና ድኅነት

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለጆሮ👂 ቁርስ ትሆነን ዘንድ እነሆ ተጋበዙልኝ 🤗🤗🤗

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡

#ማር_ይስሐቅ

#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ
#ዲያቆን_ሞገስ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
2024/11/15 07:25:40
Back to Top
HTML Embed Code: