Telegram Web Link
በእሁዱ ቅዳሴ መግቢያ ላይ በህብረት የምትዜመዋ የቅዳሴ ዜማ ☝️ እዴት ያለ ምታፅናና ቃል ናት

“ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።” ያዕቆብ 5፥11

አምላከ ቅዱሳን ከሰንበት ረድኤት ይክፈለን🤲

👇ከፅጌሬዳዋም እየቀጠፋችሁ ውሰዱ ለዛሬ😁
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
ሊንኳን ይጫኑ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ኦርቶዶክሳዊ ዕይታ (አዕምሮ) ሚለውን ለመረዳት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ማለት ምን ማለት ነው ሚለውን እንመልከት 👀

ኦርቶዶክስ  :- የግሪክ ቃል ነው በሁለት ተከፍሎ ይነገራል ይህም ''ኦርቶ'':- ማለት ቀጥተኛ ትክክለኛ ማለት ነው ። ''ዶክስ'':- ማለት ዕምነት ፣ ሃይማኖት ፣ አስተምህሮ ማለት ነው።
ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጠሪያነት የዋለው በ 325 ዓ.ም በኒቂያ ጉባኤ በአሁኗ (ቱርክ:-ኢዝኒክ) ከተማ ነው ። የታሪኩ ዋና መነሾ የአሪዮስ የኑፋቄ ትምህርት ቤተክርስትያንን ክፉኛ አውኳት ስለነበረ 318 ቱ ሊቃውንት ቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ  በመሆን አሪዮስን አውግዘው ጥያቄ በተነሳባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ለማስረዳት ቅዱስ አትናቴዎስና ሌሎቹም ቅዱሳን አባቶች የቤተክርስትያንን እምነትና አስተምህሮ የሚገልፅ የሃይማኖት አንቀፅ አዘጋጅተው አፅድቀዋል። በዚህም ትክክለኛ ዕምነት (አስተምህሮ) ያሏት ክርስትያኖች ኦርቶዶክስ ናት በማለት ጠርተዋል ማለት ነው።

ተዋሕዶ:- ከልሣነ ግዕዝ የመነጨ ቃል ነው ። ትርጉሙም 👉'' አንድ መሆን'' ማለት ነው። ምስጢራዊ ፍቹ ግን ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕሪይ አንድ ባሕሪይ የመሆን ምስጢር ነው።
👉ሁለት አካል የተባለው አካለ መለኮት እና አካለ ሥጋ ናቸው
👉 ሁለቱ ባሕሪያት የተባሉት ባሕሪየ መለኮትና ባሕርየ ሥጋ ናቸው።

ታድያ ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕሪይ አንድ ባሕሪይ ተዋሕዶ በተዓቅቦ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው ነው። ተዓቅቦ ማለት :- በመጠባበቅ ማለት ማለትም አንዱ አንዱን ሳያጠፋው ማለት ነው ለምሳሌ ሙሴ በሲና ያያትን እፀ ጳጦስ መውሰድ ይቻላል። ይህም ስያሜ የተሰጠው በ 431ዓ.ም ከካቶሊካውያን 2 ባሕሪ ትምህርት በሃላ እደተሰጠ ሊቃውንት ይናገራሉ
የቀድሞ ኒቂያ ከተማ መገኞዋ ቦታ በአሁኑ☝️☝️☝️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከላይ በተመለከትነው መሰረት ቀለል ያለች ጥያቄ

ኦርቶዶክሳዊ እይታ(አስተምህሮ) ሲባል ምን ማለት ነው? መልሱ🤗
Anonymous Quiz
88%
ክርስቶሳዊ እይታ(አስተምህሮ) ማለት ነው።
0%
ግላዊ እይታ(አስተምህሮ) ማለት ነው።
12%
ኦርቶዶክስ የሚለው ስያሜ ከተሰጠ በሃላ የመጣ አስተምህሮ ነው ።
ተዋሕዶ የሚለው ስያሜ እደመጠሪያነት የዋለው ከመች ጀምሮ ነው
Anonymous Quiz
39%
325 ዓ.ም
18%
431 ዓ.ም
43%
318 ዓ.ም
👉ማታ በሌላ ትምህርት እንመለሳለን እስከዛ በነዚህ ጥያቄዎች ስለሚቀሉ ፈታበሉልኝ🤭

ያላችሁ ሃሳብ ካለ በኮመንቷ ኮምቱልን😁🤜

ተሳትፎዋችሁን በሪያክት እንየው እስቲ😉 👇👇
2024/11/15 10:07:49
Back to Top
HTML Embed Code: