Telegram Web Link
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/+DrKpvgD1SyM5OWY0
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

ተወዳጆች የናተው በጎ ኦርቶዶክሳዊ እይታ ፣ ሃሳብ ፣ እርማት የምታሰፍሩበት ግሩፕ በመሆኑ ተቀላቀሉት 🤗🤗🤗

ቻናሉንም ሼር ማድረግ አይረሳ ቁጥራችን እየቀነሰ ነው 🙏🙏🙏
አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀 pinned «⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ https://www.tg-me.com/+DrKpvgD1SyM5OWY0 ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ ተወዳጆች የናተው በጎ ኦርቶዶክሳዊ እይታ ፣ ሃሳብ ፣ እርማት የምታሰፍሩበት ግሩፕ በመሆኑ ተቀላቀሉት 🤗🤗🤗 ቻናሉንም ሼር ማድረግ አይረሳ ቁጥራችን እየቀነሰ ነው 🙏🙏🙏»
#እንኳን_ለግሼን_ደብረ_ከርቤ_ለብዙኃን_ማርያምና_ለቅዱሳኑ_ዓመታዊ_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ_አደረሰን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

#ግሼን_ደብረ_ከርቤ
ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"

ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::

በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::

የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል::

አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል::

አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::

በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው::

#ብዙኃን_ማርያም/#ጉባኤ_ኒቅያ
ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::

የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::

ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::

እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::

#ቅዱሳን_ቆጵርያኖስ_እና_ዮስቴና
ቆጵርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::

በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::

በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::

አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::

ቆጵርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::

ቆጵርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::

አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ጳጳስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::

ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::

#መስከረም_21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
2.ብዙኃን ማርያም
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት
4.ቅዱስ ቆጵርያኖስ ሰማዕት
5.ቅድስት ዮስቴና ድንግል
6.ቅዱስ ጢባርዮስ ሐዋርያ

#ወርኀዊ_በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

"እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል:: እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ:: ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ:: ከእናንተም ይሸሻል:: ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ:: ወደ እናንተም ይቀርባል::" (ያዕ. ፬፥፮)
“ከሁሉም በኋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ።”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥8
እዳለው ቅዱስ ጳውሎስ ከጭንጋፍም በላይ ጭንጋፍ የሆንኩ እኔ ዛሬ ከጉባኤዋ ቃለ ወንጌል  ላይ ከሊቃውንቱ አንደበት ከሰማዋት ምክር እናሰላስላት ዘንድ እነሆ ብያለሁ🤗

ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዓፄ ዳዊት ስናር ላይ በማረፉቸው ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት ነበረበት፡፡ ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዘርዐ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ስናር ሔደው ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅድሳት ጋር አምጥተዋል !

የከበሩ አባት እና ልጅ 🥰 በዚህ ዘመን እውነት የጌታን መስቀል ወደልጁ ልብ ሚያቀብል አባት ይኖር ይሆን ?
ልጅስ ከአባቶቹ የተቀበለውን ርትዕት ሃይማኖት ይፈፅማት ይሆን ?

“ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።”
  — ገላትያ 6፥14

አባቶቼ  ልጆቻችሁን መጫወቻ ብቻ ሳይሆን መስቀሉንም ሰታችሁ አሳድጓቸው ከናተ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ የክርስቶስ ልብ ያላቸው ቤተክርስትያንን የሚጠብቁ ልጆች ይሆናሉ እና

ልጆችዬ የአባቶቻችሁን ርትዕት ሃይማኖት ሳታጓድሉ ተቀበሉዋቸው በዛችም ተጋደሉ መስቀሉን ተሸከሙ ከሰማያዊው አባታችሁ ጋር ለዘለዓለም በምስጋና ትኖሩ ዘንድ🥰🥰🥰

ተወዳጆች ዛሬ የተዘራው ነገ እደሚበቅል ሁሉ የዛሬ ትውልድ ላይ ምናሰርፀው እያንዳንዱ ሃሳብ የነገ ሃገር ህልውና ነው ሃገር ሰላም ትሆን ዘንድ ቤተክርስትያን ትሰፋ ዘንድ እያንዳንዳችን ለልጆቻን ምናስተላልፈውን እያሰብን እና እየተጠነቀቅን ይሁን እላለሁ ቸር ቆዩልኝ🙏🙏🙏🙏
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ለወላጆች☝️
+++

አባት ለልጁ እንዲህ አለው
"ልጄ ስትሄድ ተጠንቀቅ።"
ልጅም መለሰ
"አባቴ አንተ ይበልጥ ተጠንቀቅ፤
እኔ ያንተን እርምጃ ነው የምከተለው።"

+++
ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲያጸና እንዲህ ይላል፦

"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።" ምሳሌ 22፥6

አባቶቼ ለልጆቻችሁ እንዴት አይነት መሪ ሆናቹህላቸው ይሆን ? አንድ አፍታ ራሳችሁን መርምሩ 🤔

“ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና።”
— ኤፌሶን 5፥23

ክርስቶስ ቤተክርስትያንን እደወደዳት አባቶችዬ ልጆቻችሁን እና ሚስቶቻችሁን በዛን ያክል ወዳቹ በቃል ሳይሆን በተግባር እየኖራቹ ይሆን ???

ክርስቶስ በመስቀሉ ጥልን ከመንገድ ጠርቆ አስወግዶ መንግስተ ሰማያት እዳስገባን አባቶችዬ ልጆቻችሁን እና ሚስቶቻችሁን ስንቶቻችሁ ለክርስቶስ መንግስት የተመቸ አድርጋቹሃቸዋል ??
የክርስቶስ ልብ ሊኖረን ይገባል ከፊት የታየ ሁሉ መሪ አይደለም መሪ (የበላይ) የተባለ ሁሉ የበላይ (መሪ ) አይደለም ከታሰበበት ግብ(አላማ) የሚያደርስ አይሆንም የመሪነት ልብ ሊኖረን ይገባል እሱም ክርስቶስን መልበስ ነው🥰🥰🥰
“ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ።” ሮሜ 13፥14
ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን በወደዳት እና በመራት ልክ እናተም አባቶቼ ትንሿን ቤተክርስያናችሁን ቤታችሁን ትዳራችሁን ልጆቻችሁን ልትወዱ እና ልትመሩ ይገባቹሃል

ያኔ ምሳሌ 22÷6 እደተነገረው ልጃቹ በሸመገለም ጊዜ ከመንገዱ ፈቀቅ አይልም

ቸር ዋሉልኝ🙏🙏🙏

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇👇🤗

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ወጥነትና ስምምነት

ሳይንስ እና ሃይማኖት ከሚለው አዲሱ የዲያቆን ያረጋል አበጋዝ መጽሐፍ ከገጽ 348-352 የተወሰደ

መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በ1600 ዓመታት ውስጥ ነው። ይህም ማለት የመጀመሪያው መጽሐፍ ኦሪት ዘፍጥረት ከተጻፈበት ቅ.ል.ክ. 1500 ገደማ አንሥቶ የመጨረሻው መጽሐፍ ራእየ ዮሐንስ እስከ ተጻፈበት 98 ዓ.ም. ድረስ ያለው ዘመን 1600 ዓመት ያህል ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል ለመጻፍ ይህን ያህል ረጂም ዘመን የሚሸፍን ሌላ የሃይማኖትም ሆነ መሰል መጽሐፍ የለም። ጸሐፊዎቹ ደግሞ ከ40 በላይ ናቸው። ጸሐፊዎቹ የኖሩበት ዘመን፣ የሥራቸው ዘርፍ፣ የትምህርትና የእውቀት ደረጃቸው ሁሉ አንድ ዓይነት አልነበረም።
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በጣም የተማሩና ጠቢባን የነበሩ (ሊቀ ነቢያት ሙሴ፣ ጠቢቡ ሰሎሞን፣ ነቢዩ ዳንኤል፣ ቅዱስ ሉቃስ፣ ቅዱስ ጳውሎስ)፤ ከእረኝነትና ከዓሳ አጥማጅነት የተጠሩ (ነቢዩ አሞጽ፣ ንጉሥ ዳዊት፣ ቅዱስ ማቴዎስ፣ ቅዱስ ዮሐንስ . . )የተለያዩ ዓይነት ሰዎች ነበሩ። ሆኖም እነዚህ በዘመን፣ በአኗኗር፣ ወዘተ የተለያዩ የነበሩ ከ40 በላይ ጸሐፊዎች በ1600 ዓመታት ውስጥ የጻፉት መጽሐፍ በይዘቱ ግን ወጥና እርስ በእርሱ የተስማማ ነው። አንዳችም የይዘት ተቃርኖ የለበትም።

ይህን ልብ ብሎ በጥሞና ለሚያስተውል ሰው፣ በእውነተኛው አምላክ ምሪት የተጻፈ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም መንገድ የሚቻል ነገር አይደለም። በአንድ ዘመን ያሉና ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ሰዎች በአንድ ርእሰ ጉዳይ ላይ ተመካክረው የሚጽፉት ነገር እንኳ ወጥ ለመሆን ብዙ ፈተና አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን የያዘ ሲሆን የይዘት ተቃርኖም ሆነ ተፋልሶ የለበትም።

ያውም መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ጥልቅና መሠረታዊ ስለሆኑ ጉዳዮች ነው። ስለ ፍጥረት አገኛኘት፣ ኃጢአት ስላስከተለው ውድቀት፣ ሞት ከየትና እንዴት እንደ መጣ፣ ዐለማችን አሁን ላለችበት ሁኔታ ያበቃት ምን እንደሆነ፣ ከዚህ መውጫው መንገድ ምን እንደሆነ፣ ከኦሪት ዘፍጥረት አንሥቶ እስከ ራእየ ዮሐንስ ድረስ ወጥ በሆነ ሁኔታ ያለ አንዳች ተቃርኖ የሚናገር መጽሐፍ ነው። በ10 እና 20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተጽፈው አለቁ የሚሏቸው፣ ሆኖም ግን ከይዘት ተቃርኖ መትረፍ ያልቻሉ የሃይማኖት መጻሕፍት አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በ1600 ውስጥ ከ40 በላይ በሆኑ ሰዎች ተጽፎ እንደዚህ ያለ ነገር የለበትም።

እዚህ ላይ ማስታወስ የሚያስፈልገው አንድ ነገር ቢኖር ይዘቱን የማይረዱ አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆች “መጽሐፍ ቅዱስ ይጋጫል” እያሉ የሚያወጧቸው ጥቅሶች ምንም የሐሳብ ተቃርኖ ያለባቸው አለመሆናቸው ነው። ተቃርኖዎች ሳይሆኑ አንድን ጉዳይ በተለያየ መንገድ የመግለጽ ወይም የአንድን ጉዳይ የተለያየ ገጽታ የመግለጽ ሁኔታዎች ብቻ ናቸው። ለዚህ ማሳያ ሁለት ምሳሌዎችን ብቻ እንመልከት።

• “ዳዊትም ጋድን፣ እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፣ በሰው እጅ ግን አልውደቅ አለው።” 2 ሳሙኤል 24 ፡ 14

• “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።” ዕብራውያን 10፡31

መጽሐፍ ቅዱስን እንተቻለን የሚሉ ሰዎች ተቃርኖ እያሉ ከሚያቀርቧቸው መካከል አንዱ እነዚህን አገላለጾች ነው። ዳዊት በድሎ በነበረ ጊዜ ከሦስት ዓይነት የቅጣት አማራጮች መካከል አንዱን ምረጥ በተባለ ጊዜ በሰው እጅ ከምወድቅ በእግዚአብሔር እጅ ብወድቅ ይሻለኛል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምሕረቱ ብዙ ነውና ብሏል። ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው” ብሏል። ይህ የዳዊትና የጳውሎስ አገላለጽ የሚቃረን ሳይሆን የአንድን ጉዳይ የተለያየ ገጽታ የሚናገር ነው።

ዳዊት የተናገረው የዚህን ዐለም ሁኔታ ነው። በዚህ ዐለም በእግዚአብሔር እጅ ብንወድቅ ቅጣቱ የአባት ቅጣት ስለሆነ ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም። ስለዚህ “በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ፤ በሰው እጅ ግን አልውደቅ” አለ። ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ደግሞ የዚያኛውን ዐለም ነው። በዚያኛው ዐለም በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ዘለዓለማዊ ስለሆነ እጅግ አስፈሪ ነው።

ከዚህም ጋር ዳዊት በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅን በመምረጥ የእግዚአብሔርን መሐሪነት የሰውን ጨካኝነት አጉልቶ አስረዳ። ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ በዚህ ዘመን ያልፍልኛል ወይም ወደ ሌላ ቦታ ሄጄ አመልጠዋለሁ ሊሉት የማይቻል ከባድ ነገር መሆኑን አስረዳ። ስለዚህ እነዚህ የዳዊትና የቅዱስ ጳውሎስ አገላለጾች የሚቃረኑ ሳይሆኑ የአንድን ጉዳይ የተለያየ ገጽታ የሚያሳዩ ተመጋጋቢ አገላለጾች ናቸው።

•  “ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።” ማቴዎስ 17፡1

• “ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።” ሉቃስ 9፡28

ጌታችን ወደ ደብረ ታቦር ሦስቱን ደቀ መዛሙርቱን ይዞ የወጣበትን ጊዜ ሲጽፍ ማቴዎስ “ከስድስት ቀንም በኋላ” ሲል ሉቃስ ደግሞ “ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ” ብሏል። ቅዱስ ማቴዎስ “ስድስት ቀን” ያለው፣ መጀመሪያ በፊልጶስ ቂሳርያ “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል” ብሎ ደቀ መዛሙርቱን የጠየቀበትን ቀንና ወደ ደብረ ታቦር የወጡበትን ቀን - ሁለቱን ቀኖች - ሳይቆጥር ነው። ቅዱስ ሉቃስ ስምንት ቀን ያለው ደግሞ፣ እነዚህን ሁለቱን ቀኖች (የመጀመሪያውና የኋለኛውን ቀን) ቆጥሮ ነው። ስለዚህ ይህ ተቃርኖ ሳይሆን ወንጌል ነጻ በሆኑ የተለያዩ ሰዎች መጻፉን የሚመሰክር ነው።

ጽሩይ የሆነ አልማዝ ከተለያየ አቅጣጫ ሲያዩት አንዴ ሰማያዊ፣ ሌላ ጊዜ ሐምራዊ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቢጫ መስሎ እንደሚታየው፣ የእግዚአብሔር ቃልም አንድን ነገር ከተለያየ አቅጣጫ ሲያሳየን እንዲህ ባሉ የተለያዩ በሚመስሉ አገላለጾች ይገልጻቸዋል። ስለዚህ ይህን የመሰሉ የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጾች አሉ። ሆኖም እነዚህ ተቃርኖዎች ሳይሆኑ አንድን ነገር በተለያየ መንገድ የሚገልጹ ናቸው። እንዲያውም እነዚህ የተለያዩ የሚመስሉ አገላለጾች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነተኝነት የሚመሰክሩ ናቸው፤ ምክንያቱም ጸሐፊያኑ እነዚህ መኖራቸውን እያወቁ የተዋቸው ችግር ስላልሆኑ ነውና። በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ንባብ የሚፈልጉ ሰዎች በዚህ ዙሪያ የተጻፉ ማብራሪያዎችን መመልከት ይችላሉ🤗


#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
የጽጌ ጾም

በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ንጉሥ ሄሮድስ ሥልጣኔን ይቀማኛል በሚል ቅናት ተነሣሥቶ እርሱን ለማስገደል አሰበ፡፡ ያንጊዜም ጌታችን በተአምራት መዳን ሲቻለው የትዕግሥት፣ የትሕትና አምላክ ነውና በለበሰው ሥጋ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ጀርባ ታዝሎ በመልአኩ ተራዳኢነት፣ በአረጋዊው ዮሴፍ ጠባቂነትና በሰሎሜ ድጋፍ ከገሊላ ወደ ግብፅ ተሰዶ ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ ቆይቷል፡፡ ሄሮድስም ጌታችንን ያገኘው መስሎት በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የሚገኙ ሀለት ዓመት ከዚያ በታች የሆኑ አንድ መቶ ዐርባ አራት ሺሕ ሕፃናትን በግፍ አስፈጅቷል፡፡

በተአምረ ማርያምና በማኅሌተ ጽጌ ተጽፎ እንደሚገኘው ጌታችን በግብጽ ምድር በስደት ሳለ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ከእነዚህ መካከልም ውሃ በጠማቸው ጊዜ ውሃ እያፈለቀ ማጠጣቱና ይህንን ውሃ ክፉዎች እንዳይጠጡት መራራ ማድረጉ፤ ለችግረኞችና ለበሽተኞች ግን ጣፋጭ መጠጥና ፈዋሽ ጠበል ማድረጉ፤ ‹‹የሄሮድስ ጭፍሮች ደርሰው ልጅሽን ሊገድሉብሽ ነው›› ብሎ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ እመቤታችንን በማስደንገጡ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ድንጋይ ሆኖ እንዲቆይ ማድረጉ፤ መንገድ ላይ የተራዳቸው ሽፍታ ሰይፉ በተሰበረች ጊዜ እንደ ቀድሞው ደኅና እንድትሆን ማድረጉ፤ እንደዚሁም የግብጽ ጣዖታትን ቀጥቅጦ ማጥፋቱ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የጌታችንና የእመቤታችን የስደት ወቅት በወርኃ ግንቦት ነው፤ ነገር ግን ዘመነ ጽጌ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የስደቱ ጊዜ በዘመነ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡ ይህ የእመቤታችን አበባነትና የጌታችን ፍሬነትም እንደ ቅዱስ ያሬድ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫና አባ ጽጌ ድንግል ባሉ ሊቃውንት ድርሰቶች በሰፊው ተገልጧል፡፡

የጽጌ ጾም በቤተክርስቲያናችን ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ያሉት አርባ ቀናት ዘመነ ጽጌ (ወርኃ ጽጌ) እንደሚባሉ ይታወቃል። በነዚህም ቀናት በየቤተ ክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩ መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት፣ በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐተ እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋከብት ምድር በጽጊያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው። በወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሳዊ አገልግሎት መነሻው ‹‹መልአኩ ሕፃኑና እናቱን ወደ ግብጽ ይዘሃቸው ሽሽ፤ ሕፃኑን ሊገድሉት ይሻሉና›› ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሰረት ሕፃኑን እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ዮሴፍ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑን ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው። (ራእይ ፲፪፥፲፮)

በዐሥራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባት አባ ጽጌ ብርሃን ‹‹የሮማን ሽቱ የቀናንም አበባ የምትሆኝ ማርያም ሆይ ፥ በረሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪ ጠወልግ ድረስ በስደትና በለቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሶሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህም ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር።›› ብለዋታል፡፡ እንዲሁም አባ አርከ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‹‹ሰቆቃወ ድንግል›› በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፦ ‹‹ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሽ ጊዜ የደረሱብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንዳጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር።››

በዚህ ወቅት በሚገኙ ሰንበታትም ሊቃውንቱ ሌሊቱን ሙሉ ስለ እመቤታችን አበባነትና ስለ ጌታችን ፍሬነት የሚያትት ትምህርት የያዙትን ማኅሌተ ጽጌና፣ ሰቆቃወ ድንግልን ከቅዱስ ያሬድ ዚቅ ጋር በማስማማት ሲዘምሩ፣ ሲያሸበሽቡ ያድራሉ፡፡ ቅዳሴውም በአባ ሕርያቆስ የተደረሰውና ምሥጢረ ሥጋዌን፣ ምሥጢረ ሥላሴንና ነገረ ማርያምን የሚተነትነው ቅዳሴ ማርያም ነው፤ ምንባባቱም ከዚሁ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ናቸው፡፡

የማኅሌተ ጽጌና የጾመ ጽጌ አጀማመር የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው። በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጥዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌተ ጽጌና ከሰቆቃወ ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው። ዝክሩም በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፥ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢው ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው። ዐቅመ ደካሞች ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል። ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን እናቶችና አባቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው።

የጻድቁ አቡነ ዜና ማርቆስ ዜና ገድል የጽጌን ጾም አስመልክቶ የሚከተለውን ይተርካል፦ ‹‹አባ ጽጌ ብርሃን የተባለው አባት እንደ መዝሙረ ዳዊት መቶ ኀምሳ አድርጎ ማኅሌተ ጽጌን ደረሰ። አባ ጽጌ ብርሃን ይህንን በደረሰበት ጊዜ የወረኢሉ ተወላጅና የደብረ ሐንታው አባ ገብረ ማርያም አማካሪው ነበር። ድርሰቱንም ሲደርስ ቤት እየመታና በአምስት ስንኝ እየከፋፈለ ነው። አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም ከመስከረም ፳፮ ቀን እስከ ኅዳር ፭ ቀን ማኅሌተ ጽጌን ለመቆምና የጽጌን ጾም ለመጾም በየዓመቱ በደብረ ብሥራት እየመጡ ይሰነብቱና ቁስቋምን ውለው ወደየ በአታቸው ይመለሱ ነበር።›› ከአባታችን የገድል ክፍል ለመረዳት እንደሚቻለው አባ ጽጌ ብርሃንና አባ ገብረ ማርያም የጽጌን ማኅሌት መቆም ወቅቱንም በፈቃዳቸው መጾም የጀምሩበ ዘመን በዐሥራ አራተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው።

ከዚያ ወዲህ ግን ጥቂት በጥቂት እያለ አብያተ ክርስቲያናት በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ጀመሩ። ጥቂት መነኩሳትና አንዳንድ ምእመናን በፈቃዳቸው ወቅቱን መጾም ጀመሩ። በዘመናችን በወርኃ ጽጌ የጽጌን ማኅሌት መቆም ስለ ተለመደ ከማታው በሦስት ሰዓት ይደወላል። ሴት ወንዱ፥ ትንሹም ትልቁም ይሰባሰባል፤ ማኅሌተ ጽጌው እየተዜመ፤ አስፈላጊ የሆነው በጽናጽል በከበሮ እየተወረበና እየተሸበሸበ እስከ ጥዋቱ ፲፪ ሰዓት ድረስ ተቁሞ ይታደራል። የጽጌ ጾም የውዴታ (የፈቃድ) እንጂ የግዴታ አይደለም። የእመቤታችን ስደት በማሰብ ከትሩፋት ወገን የሚጾም ስለሆነ ምእመናን ሁሉ እንዲጾሙት አይገደዱም፤ የሚጾመው የማይጾመውን ለምን አልጾምክም ብሎ ሊፈርድበት ስለ ራሱም እየጾምኩ ነው ብሎ መናገር አይገባውም። የፈቃድ መሆኑንም የሚያሳየው ይኸው ነው፤ የማይጾመውም በልቡ ያመሰግናል፤ ስደቷን እያሰበ ማኅሌቷን እየዘመረ ያሳልፋል።

አምላካችን እግዚአብሔር የጽድቅ ፍሬን ሳናፈራ በሞት እንዳንወሰድ በቸርነቱ ይጠብቀን፤ አሜን፡፡

#ማኅበረ_ቅዱሳን

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
አንዲት እምነት✟ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮት👀
Photo
ኦርቶዶክሳዊ ልጆችን ማስተማር

በቤተ ክርስቲያን የኦርቶዶክሳውያን ልጆችን ማስተማር የተለመደ ነው። በተለይ በውጭው ዓለም ላሉ ኦርቶዶክሳውያን ልጆችን ስለ ሃይማኖታቸው ስለ ሀገራቸው ለማስተማር የወላጅ ትልቁ ፍላጎትና ስቃይ ነው። ይኹን እንጂ ኹለት ትልልቅ ፈተናዎች እንዳሉ እገነዘባለሁ።

አንደኛው ምእመኑም ካህናቱም ለልጆች የሚሰጡት ቦታ ዝቅተኛ ከመኾኑ ባሻገር ከእቅድና ወሬ ያለፈ አለመሆኑ ነው። እኔም ለመረጃ ስጠይቅ “ከተወራ ይበቃል” አይነት መልስም ሰምቻለሁ። ከልባቸው በትክክል እያስተማሩ ያሉ ጥቂት አጥቢያዎች ይኖራሉ። 

ኹለተኛው ደግሞ የምናስተምርበት መንገድ ነው። በጥቂት አብያተ ክርስቲያናት  ራሱን ችሎ በተመደቡ በብዛት ግን ወላጅ አልያ ፈቃደኛ በኾኑ ምእመናን የሚሰጥ የልጆች ትምህርት ነው። እኔ በጥቂቱ ለመታዘብ በሞከርኩት እንኳን ለማስተማር ቀርቶ የሚናገሩን ምን እንደኾነ እንካ የማያውቁ ብሎም ስህተት መረጃ ለልጆች የሚሰጡ “የልጆች አስተማሪዎች” እንዳሉ ታዝቤያለሁ። 

ሌላው ልጆቹን የሚያስተምሩት ወላጅ እያስቀደሰ ልጆች እንዳይረብሹ አንድ ክፍል ውስጥ ዘግቶ ማንጫጫት ወይም ማስተማር ነው። ፊደል አልያ ዓረፍተ ነገር ማሰራት። ይኽ ትምህርት ሳይሆን  ልጆቹ እንዳይረብሹ ማድረግ ነው ዓላማው። 

በተጨማሪም ኦርቶዶክሳዊ የልጆች ትምህርት ምንድነው የሚለው በደንብ መለየት አለበት። በውጭው ዓለም  እንዳየሁት ልጆች የሚማሩት በቅዳሴ ሰዓት ሲሆን ለቁርባን ተሰልፈው ይመጣሉ። ይኽ በብዙ ምክንያት እንደሆነ ብረዳም በጣም ጎጂ ከመሆኑ በላይ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስ ትምህርት ከክርስቶስ ጋር የምንኖረው የሱታፌ ሕይወት እንጂ እውቀት ብቻ አይደለም። ስለሆነም የምንማረው በተሳትፎ በተግባር ነው። ልጆች ቢረብሹም ከወላጆች ስር ሆነው ማስቀደስ አለባቸው። 

በቅዳሴ ወቅት በር ዘግተን ከምንማረው ትምህርት ይልቅ በቅዳሴ ተሳትፈው ሲያልቅ አንድ ሰዓት በትክክል ልጆችን ማስተማር የበለጠ ትክክለኛ ይሆናል። 

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
@TnshuaBetechrstian
በአንድ ወቅት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ ባሉበት ቤተክርስቲያን ውስጥ ሕጻናት ይጮሁ ነበር። ወላጆችም "ቅዳሴ እንዳይበጠብጡ" ብለው ልጆቹን ወደ አንድ ክፍል ወስደው አስቀመጧቸው። በእነርሱ ቤት ትልልቆቹ ለማስቀደስ ፈልገው ልጆቹ እንዳያስቀድሱ ማድረጋቸው ነው። ምዕመናኑም ወደ ብጹዕ አቡነ ሽኖዳ ቀርበው "አባታችን ሕጻናቱ እየበጠበጡ ስለሆነ ከዚህ በኋላ ቅዳሴ እንዳይመጡ ብለው ይናገሩ" አሏቸው። አቡነ ሽኖዳ ደግሞ እንዲህ ብለው መለሱ "እኔ የሚሰማኝ የብጥበጣቸው ድምጽ ሳይሆን የነገይቱ ቤተክርስቲያን የተስፋ ድምጽ ነው።"
"ሕጻናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው።" ሉቃ 18፡16


ይበልጥ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው የነገዋን ቤተክርስትያን መሰረት ዛሬ እንስራ ቅዳሴ ፀሎት የተለያዩ መንፈሳዊ ተግዳሮቶችን ከልጆቻችን ጋር እናድርግ🥰🥰🤗🤗🤗


⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian
False equivalence "እውነታውን ላለመቀበል እውነትን ከውሸት ጋር አስተካክሎ ሁለቱንም በአንድነት ፈርጆ የሚወቅስ ነው። በብዛት ሚዲያ ላይ ከትንሽ እስከ ትልቅ የዚህ ተጠቂ ሆኖ እያስተዋልኩት ነው። አንድ ሰው ሌቦች በሕግ መጠየቅ አለባቸው ብሎ ሲጠይቅ አንተም ሌባ ነህ ሁላችሁም ዝም በሉ ብሎ የሚፈርጅ ሰው ንግግሩ False equivalence የተባለ fallacy ነው። ክርስቲያን ርቱዕ መሆን አለበት። በእያንዳንዱ ጉዳይ ትክክለኛ ፍርድን መፍረድ አለበት እንጂ የረጅሙን እግሩን ቆርጦ ከአጭሩ ጋር ማስተካከል ስሕተት ነው። ሰይጣን እኔ አምላክ ነኝ ብሎ ዋሸ። መላእክት ደግሞ አይደለህም ብለው ተቃወሙት። False equivalence fallacyን የሚተገብር ሰው አንተም ተው አንተም ተው ያለ መስሎ ትክክለኛውን የመላእክት መልስ በአስታራቂነትና በሚዛናዊነት ሰበብ ከሰይጣን ስሕተት ጋር ያስተካክለዋል። ትክክለኛው መንገድ ግን የሰይጣንን ስሕተት እንደመላእክት መቃወም ነው።
አንዳንዶች ለራሳቸው ዓላማ ሲሉ እውነተኛ ሰዎችን ለማጥቃት ብለው ውሸታም ሰዎችን Promote ያደርጋሉ። እና ይህኮ ተገቢ አይደለም ስትላቸው እነርሱ ያስተዋወቁት ውሸታምንም እውነተኛውንም በአንድነት እንዲጠቁ ይፈልጋሉ። እገሌማ እውነተኛ ነው አይደል ስትላቸው እገሌ እውነተኛ ነው ካልክማ እኛም እገሌን እውነተኛ ነው (ውሸታሙን) ብለን እንኖራለን ይሉሀል። እና የአንተን እውነት ከእነርሱ ውሸት ጋር አስተካክለህ እንድትኖር ወይም በአንድነት እንዲፈረጁላቸው ይፈልጋሉ። የእኔ ምክር በዚህ ጊዜ "ውሸታምን ይዞ መቀጠል ካማራቸው ከነውሸታቸው ይቀጥሉ። አንተ ግን በያዝከው እውነታ ለዘለዓለሙ ጽና የሚል ነው"። ሰው እውነተኛ ሚዛን ከሌለው አንጃ (መንጋ) ይሆናል። የአንጃነት ጸባይ ደግሞ እንደሸንበቆ ነው። ሸንበቆን ወዴት ነህ ቢሉት ነፋስን ጠይቁት አለ እንደሚባለው ነው።

አንጃነትን የሚያብራራልኝ አንድ ምሳሌ ላንሳ። አንድ ሰው በጣም የሚወደውን ሰው ሰላም ሲለው ያ የሚወደው ሰውም ምንም መልስ ሳይመልስለት ሲቀር "አርምሞ ይዞ ይሆናል" ብሎ በቅንነት ለመረዳት ይሞክራል። አንድ በጣም የሚጠላው ሰው ደግሞ ቆርቦ አፉን ሸፍኖ ቁጭ ብሎ ያየውና ለነገር ሄዶ ሰላም ይለዋል። የቆረበው ሰውም ዝም ይለዋል። የቆረበ ሰው ምግብ እስኪቀምስ ዝም ይላል። ይህን ጊዜ "ምን ይለጉመዋል" ብሎ ይወቅሰዋል። አንጃነት እንደዚህ ነው። አንጃ እውነተኛ ሚዛን ስለሌለው ውሸቱን እውነት እውነቱን ውሸት ያደርጋል። ከእውነት መሸሽ አይገባም። እውነትን የያዛችሁ ሰዎች ሆይ መቼም ቢሆን አታፈግፍጉ።

© በትረ ማርያም አበባው

#ለሌሎች_ተደራሽእንዲሆን_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ👇👇
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
ዌል ትንሽ ማብራሪያ ዋቄፈታ ላይ..

ቅዱስ ጳውሎስ የአቴና ሰዎችን እንዲህ አላቸው:

“..የአቴና ሰዎች ሆይ፥ እናንተ በሁሉ ነገር #አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ። የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ፦ #ለማይታወቅ_አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።”
[ሐዋ 17: 22]

እነርሱ የማይታወቅ አምላክ ብለው የሚያመልኩት ጣኦትን ሊሆን ይችላል ግን እውነተኛው እርሱ ሳይሆን ይሄ ነው ብሎ ያሳያቸዋል ማለት ነው..

የዋቄፈታ ሰዎችም ደግሞ አይተውትም ሆኖ ድምጹን ሰምተውት የማያውቁት አምላክ አላቸው.. የሁሉ ፈጣሪ እንደሆነም ያስባሉ.. እንግዲያውስ ይህ ዓይነት ክብር የሚገባው ለእውነተኛው አምላክ የኢየሱስ አባት ነው.. ልጁ ኢየሱስም ከአባቱ እንደመገኘቱ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ ጌታ ነው..

እና በዚህ አምነው አምልኮዋቸውን እንዲያስተካክሉ እና ከፈጣሪያቸው ጋር እንዲገናኙ ጥሪ ማቅረብ ማለት ነው.. ያው በፍቅር እና በትህትና..

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
https://www.tg-me.com/orthodoxzelalemawit
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️
- ማኅሌት ወይም የምስጋና ነገረ መለኮታዊ ትርጓሜ (Theology of Doxa) ምንድን ነው?

- ምስጋና ስንል ምን እያልን ነው? ውስጡ ምን ምን ነገሮች አሉት?

- ዘመን ምንድነው? ዘመነ ጽጌስ?

- ተፈጥሮ በማኅሌት ጽጌ ? አባ ጽጌ ድንግል ተፈጥሮን ለማንሳት ለምን ፈለገ? The conception of Creation as a Sacrament....እና ሌሎችም ሃሳቦች እንደመግቢያ ተዳሰውበታል። ተመልክታችሁ ሃሳብ አስተያየት ትሰጡን ዘንድ ግብዣችን ነው።

https://youtu.be/JUQJQqQdHhE?si=l5PAEAItfVbX5nRC
2024/11/15 16:25:49
Back to Top
HTML Embed Code: